ሕወሓት መራሹ ኢሕኣዴግ አዲስ የልማታዊ ዲሞክራሲ የእቅድ ሰነድ እያዘጋጀ ነው::
መጭው ምርጫ ያሰጋው ወያኔ ሕዝቡን ለማደናበር እና ለማጭበርበር ሊረዳኝ ይችላል ያለውን አዲስ የልማታዊ ዲሞክራሲ ሰነድ እያዘጋጀ ሲሆን የባለራእዩ የሚሉት የመለስ ዜናዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በዝግታ ለማስቀረት እና ሕዝቡ አኩርፎበታል ያለውን የማንፌስቶ ሰነድ ለማዘጋጀት በአቶ በረከት የሚመራው ቡድን ስራውን መጀመሩ ታውቋል::
ተቃዋሚዎች ከፍተኛውን ድምጽ አግኝተው ከጨዋታ ውጪ ያደርጉኛል የሚል ስጋት ያደረበት ወያኔ በ1997 የተከሰተው አይነት ሽንፈት እንዳይደርስበት ከሰነዱ ዝግጅት ጎን ለጎን ስብሰባዎችን በማካሄድ ተቃዋሚዎች ከምርጫ የሚወጡበትን እና ምርጫውን የሚያጭበረብርበትን አዲስ ስልት እየነደፈ መሆኑንም ምንጮች አክለው ገልጸዋል::የህዝቡ ብሶት እንደበረታ ያወቀው ሕወሃት መራሹ መንግስት በጭንቀት እና በምእራባውያን ጫና ተወጥሮ እንደሚገኝ ይታወቃል::
የመለስ ዜናዊ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በሃገሪቱ የአገልግሎት አቅርቦት ማጣትን:ሙስናን :ድህነትን:የዜጎች ስደትን :ስራ አጥነትን የኑሮ ውድነትን ወዘት ከማስፋፋቱም በተጨማሪ ምንም አይነት ውጠት እንዳልታየበት እና እስካሁን የተተገበረው የተጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ ምንም የፈየደው ነገር እንዳሌለ ኢሕኣዴግ በራሱ ድርጅታዊ ጉባዬ እና ስብሰባዎች መናገር ከጀመረ ሰነባብቷል::ምንሊክ ሳልሳዊ