ዋ!!! ዋ!!! ዋ!!! አደጋ አለ !!! በምእራብ ኢትዮጵያ ያልተሳካውን በምስራቅ ኢትዮጵያ ለመድገም አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል::ይህ መንግስታዊ ሽብር አደጋ አለው:: የመንግስታዊ አካላት ስውር እጆች ግፊት እየበዛ ነው፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ:- ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ ስለሆነ ሕወሓት መራሹ ገዥው ፓርቲና አማካሪዎቹ ባለስልጣኖቹ ችግሩን ዓይተው መፍትሔ ካላስቀመጡ፣ አገርንና ሕዝብን በማስቀደምና በማሳተፍ ካልተንቀሳቀሱ አደጋ አለ፡፡ ያልታሰበና ያልተጠበቀ ግጭትና ችግር በአገራችን ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለ ነው::ኢትዮጵያ ደሃ አገር ናት ተብላ ትጠቀሳለች እንጂ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ተከፋፈሉ ተጣሉ፣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተከፋፈሉ ተጋጩ፣ የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ተባሉ፣ ወዘተ የሚል አንሰማም ነበር፡፡
አሁን በዘመን ወያኔ በመስጊድም በቤተክርስቲያንም አካባቢ ይህን እየሰማን ነው፡፡ የህዝብን አንድነት ለመናድ የሚፈልገው ገዢው ኢህኣዴግ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት እና መተራመስን ለመፍጠር ፕሮፓጋንዳውን በስፋት እየነዛ ይገኛል::በምእራብ ኢትዮጵያ ያልተሳካውን በምስራቅ ኢትዮጵያ ለመድገም አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል::ይህ መንግስታዊ ሽብር አደጋ አለው::ድሮ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር ለማስታረቅ ሩጫ ነበር፡፡ አሁን ለማባባስ የሚሯሯጥ ወያኔያዊ ኃይል እንዳለም በግልጽ እየታየ ነው፡፡ መፍትሔ ከማስገኘት ይልቅ የበለጠ ብጥብጥ እንዲከሰት የመንግስታዊ አካላት ስውር እጆች ግፊት እየበዛ ነው፡፡
የኑሮ ውድነት በህዝቡ ላይ ተደራርቦ ከጭነት ልክ በላይ እየሆነ ነው፡፡ ብር እየመነመነችና እየከሳች በመሞት በየቀኑ የቀብሯ ጥሩንባ እንደተነፋ ነው፡፡ የሃገራሽን ገንዝብ ብር በራሷ ግሽበቱ ተሽኖባት አትክልትና ፍራፍሬን ፣ ስንዴና ጤፍን፣ ትራንስፖርትና ልብስን፣ የላስኪት ቤትን እና የቤት ኪራይን፣ የተማሪውን ደብተርና ስክሪፕቶን መጋፈጥ ተስኗታል፡፡ የኑሮ ውድነት የሚያስከትለው የወንጀል ድርጊት አለ፡፡ ኑሮ ውድነቱ ወንጀልን ወልዷል::ሴቶች እህቶቻችን እድሜ እና የስራ ሁኔታ ሳይለይ ስጋቸው በመሸጥ ስራ ላይ ሲሰማሪ ከተማሪ እስከ ባለትዳር ከሕጻናት እስከ አዛውንት የሚያቀርቡ የወሲብ ደላሎች በሃገሪቱ ከትመዋል::ይህም ዋነኛ አደጋ ነው::
ለፖለቲካው እና ለስልጣኑ አትኩሮት የሚሰጠው ኢህኣዴግ ተቋማትን በሚገባ አለመገንባቱና ሥርዓቱን በሁሉም ዘርፍና መስክ አለመሞከሩን ብዙ ቀዳዳዎችን እንዲፈጠሩ ከማድረጉም በላይ፣ ለችግርና ለአደጋ የሚዳርግ ሁኔታ መኖሩ በገሃድ እየተስተዋለ ነው፡፡ የሃገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት በስራ ላይ ሊውል ነው ከሚለው ዘገባ ጀምሮ እስከ ማዕድን በመገኘቱ ሀብት ተፈጠረ ብለን በሰማን ማግስት ፖታሽና ወርቅ ፍለጋው ዩራኒየም ፍተሻው ተቋረጠ:ነዳጅ የሚፈልግ ኩባንያ ሥራ እንዲያቆም ተደረገ መባሉን ስንሰማ ያሳስበናል፡፡ ሃገሪቱ ወደ አደጋ ውስጥ ሰተት ብላ መግባቷን እና እንደማትወጣውም ይጠቁመናል::
ወያኔ በፖለቲካ ታማኝነት ያደራጃቸው እውቀት እና ልምድ የሌላቸው በሙስና እና በዝምድና የተሳሰሩ አትኮሮታቸው በሰው አገር ንብረት እና ገንዘብ ማከማቸት በሆኑ ባለስልታናት የተዋቀሩ መሥርያ ቤቶች ሲልፈሰፍሱና ውሳኔ መስጠት ሲያቅታቸው ማየቱም ወዴት እየሄድን ነው የሚያሰኝ ሆኗል፡፡ ይህም ከባድ እና እስካሁን ሊፈታ ያልቻለ አደጋ ነው::
በዳያስፖራው ያለው ዘረኝነት፣ ጐሰኝነት፣ መከፋፈል፣ መራራቅ፣ ሃይማኖትን መጠቀሚያ ማድረግ፣ ከጠላት ጋር ወግኖ መሟገት፣ አገርንና የአገርን ክብር አሳልፎ መስጠትና ፖለቲካን ቢዝነስ በማድረግ ለአትራፊነት መወራጨት፣ አስፈሪ የሆነ አቋምና እንቅስቃሴ ማድረግ አሳሳቢ ነው፡፡ይህም እንዲፈጠር ከባድ ሚና የሚጫወተው ከሃገር ቤት የሚራመደው አሳዛኝ የፖለቲካ ፖሊሲ ሲሆን እንዲሁም ወያኔ እያሰለጠነ የሚያሰማራቸው የበግ ለምድ የለበሱ ቀበሮዎች የሚረጩት መርዝ ነው ይህም ሌላኛው በሃገር ላይ የተደቀና አደጋ ነው::
አንድነታችንን የሚፈታተኑ የጠባብ ጐሰኝነትና አካባቢያዊ ስሜት የተላበሱ አስተሳሰቦች እዚህም እዚያም ሲሰሙና በቦታው መሟሟቂያ ሲሆኑ ማስተዋልም የተለመደ ሆኗል፡፡ የረዥም ዘመናት አንድነት ያለውን በፍር የተሞላውን በማህበርዊ እሴቱ እና ጉዞው አለም ያደነቀውን ኢትዮጵያዊነት የሚሸረሽሩ መንግስታዊ የማፊያ እጆች ሕዝብን በማፈናቀል እና ጎሰኝነትን እና ስልጣንን የማስረዘሚያ ስልት በማድረግ ከህዝብ አናት ላይ የሚሸኑ ትናንሽ የመንደር መንግስታት እንዲፈጠሩ በማድረግ የአብሮነት ፍቅርን እና አንድነትን በማደፍረስ በስፋት እየሰሩ ነው::ይህ ደግሞ እያየነው ያለነውን ከባድ አደጋ በሃገሪቱ ላይ እንዲሰራፋ አድርጓል::
እደግመዋለሁ::ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢና አስጊ ስለሆነ ሕወሓት መራሹ ገዥው ፓርቲና አማካሪዎቹ እና ባለስልታኖቹ ችግሩን ዓይተው መፍትሔ ካላስቀመጡ፣ አገርንና ሕዝብን በማስቀደምና በማሳተፍ ካልተንቀሳቀሱ አደጋ አለ፡፡ ሃገራችን እና ህዝቧ ሊወጡበት የማይችሉት ከባድ አደጋ ከፊታችን መደቀኑን ልብ ብለን በአንድነት እና በጋራ ከላይ የተቀመጡትን አደገኛ ሽብሮች የፈጠረውን በስልታን ላይ ያለውን መንግስት በአንድነት በመታገል ወደ ከርሰ መቃብሩ ከተን ዳግም እንዳያንሰራራ ማድረግ የኢያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታ ነው::