በሸፍጥ ሀገር ሲናጥ ታደለ በመኩሪያ
እንደወትሮው ከኢትዮጵያ የሚመጡ ዜናዎች አያስደስቱም፤ ሀገራችን ከጥፋት ማማ ላይ መድረሷን ያሳያሉ። ለአራት ጊዜ በሸፍጥ ተመርጫለሁ ብሎ ሥልጣን ላይ ቂጥ ያለው ወያኔ ለአምስት ጊዜ ሊያወናብድ እየተዘጋጀ ነው። በየጊዜው ጥቂቶች ብቻ በገሃድ የምርጫውን ሸፍጥነት ሲያጋልጡ ምዕላተ ሕዝቡ ግን ከሹሹክታ ያለፈ እንደ ቡርዲና ቡርኪነፋሶ ዳር እስከዳር በአደባባይ ወጥቶ ሲቃወም አይታይም፤ ዘንድሮ ግን ሌላ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ሣይጠብቅ እርሰ በእርሱ በጎበዝ አለቃ ተቧድኖ ምርጫውን ማክሸፍ አለበት። ወያኔ ለአምስተኛ ጊዜ ለመመረጥ የተዘጋጀ ይመስላል፣ ይህ ከተሣካ ደግሞ ሕዝባችን ሸፍጥን እንደሥረዐት የተቀብሎታል ማለት ይቻላል። የወጪ አገር ታዛቢዎችም ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ የምትመራ ሀገር ናት እሰከማለት የደረሱት ይህን በመታዘብ ይመስላል። ‘ወደሸ ከተደፋሽ ቢረግጡሺ አይክፋሽ’ እንደማለት፣ የአሜሪካኗ ዲፕሎማት ወይዘሮ ዊዲ ሸርማንም በተዘዋዋሪ የነገሩን ያንን ነበር። ወያኔ የሽፍጥ መንግሥት መሆኑን ከአሜሪካ በላይ የሚያውቅ የለም ፤ የአሜሪካን ሰቴት ዲፓርትሚት ሪፖርት ያንን ያሣያል፡፡ ሸፍጥና ነፍጥ ርዕዮተ ዓለሙ የሆኑት ወያኔ እንደሥረዐት እንድንቀበል ካደረን ዓመታት ተቆጥረዋል ፤ ከጫቃች ላይ አሽቀጠሩ መጣሉ የእኛ ሕዝቦች ሃላፊነት መሆን አለበት። የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባርን ሸፍጥ በዓለም የመገናኛ ብዙሃን ሺፋን ሲያገኝ እኛም ለድርጊቱ አዲስ ሆነን አብርን እናጫፍራለን፤ በሊቢያው በአይሲሲ አረመናዊ ቡድን በወገኖቻችን ላይ ለተፈጻመው ግድያ ያደረግነው ያንኑ ነው። ለምሳሌ በሚያዚያ 11፣ 2007 ዓ ም [Islam Society of Iraq and Syria] ISIS ሃያ ስምንት ወገኖቻችን በዚህ አረመኔ ቡድን በሊቢያ በካራ አነገታቸወን መግዝር፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በሚነድ የጎማ ነበልባል መቃጠል፣ በሜዴቴሬያን ሐይቅ፡ በሕንድ ዊቂያኖስ መስመጥ፣ በየመን ከሚያለቅሱ ሕጻናት እናቶች ተነጥለው ወደ መታጎሪያ ሲነዱ፣ ሕጻናት በረሃብ ሲያለቅሱ ዓለም አጀብ ፣አጀብ፣ ሲል ከዚህ የከፋ ግፍ ወያኔ በሕዝባችን ላይ እንዳልፊጸመ እኛም አብረን አጀብ አጀብ ብለናል። በሻማ ማብቱ ሥነስረዓት ላይ ተካፍለናል፣ ያ ባልከፍ ነበር፣ ግን ክፋቱ ግን ይህ ድርጊት መደጋገሙን አምነን ለመጨረሻ ጊዜ የዚህ ሁሉ ግፍ መሐዲሱ ወያኔ መሆኑን ተቀብለን ለማስወገድ በተግባሩ ሥራ ላይ ለመተባበር ቁርጠኛነት ያለመኖሩ ፣ በእግር ኳስ ሕግ ኳሷን እንዴት እንደምትመታት ከማሰብህ በፊት ወደኳሷ ተጠጋ ይላል፤ ሰለመተባበር ሰንደሰኩር በተግባር መሬት ላይ እየሰራን ቢሆን ይመረጣል። ይህን ቡድን ለማስወገድ ቆርጠን መነሣትን ይጠይቃል፤ ለዚህ ውርደት በተዘዋዋሪ የዜጎች አስተዋጾ አለበት፤ ዋነኛውን ተዋናኝ ወያኔን በገሃድ ለማውገዝ እንኳን አልደፈርንም፤’ በሰዎች ሰቆቃ ፖለቲካ አንሥራ የሚሉም አልታጡም፣ የአዛኝ ቅቤ አንጓቾች አይነቶች፣ የሀገር ቤቱ ወጣት ይሻላል፣ ‘የሀገር ውስጥ አንበሣ የውጭ ሬሣ ሲል ተሳልቈል ። በውጪ ሀገር የአንድ ፖለቲካ ድርጅት መሪ ብቻ ናቸው፣ በገሃድ ወያኔ ሌለኛው አይሲሲ ነው ሲሉ የተደመጡት፤ በየአቅጣጫው በተሰደድንበት አገሮች ም ሆነ በሀገራችን ለመሞትን አልፈራንም፣ ሆኖም ግን በአንድነት ወያኔ ይወገድ ለማለት በአደባባይ ምን አሰፈራን? ይህንን ለሃይማኖት አባቶች ልተወው፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሲኖደስ ተወካይ አባት፣ የእስልማና ሃይማኖት አባት የወንጌላዊ ቤተክርስትያ ተወካዮች 1997 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 200 ሰዎች በአጋዚ ታጣቂ ተገለው እነዚህ እላይ የተጠቀሱት የሃይማኖት አባቶች አይናችንን ግንባር ያድርገው ነበር ያሉት፤ ዛሬም አሲሲን አውግዘው ወያኔ ሲዘሉ አስተምህሮታቸው ሰሚ ይኖረው ይሆን? የካቶሊኩን መሪን አይጨምርም። ፍርዱን ለዓምላካች ልተወውና ሰለአይሲሲ ትንሸ ልበል፤
እነዚያ አይሲሲዎች በእስልምና ሰም ሃያ ስምንቱን ወገኖቻችንን ሲግዝሯቸው የሚሳየው ቪዲዮ በጉታናሞ ቤዬ በአልካይዳ ስም ተጠርጥረው የታሰሩት እስረኞች ለብሰውት የነበረውን ዩኒፎርም ይመስል። ይህን ቡረቱካናዊ መልክ ቱታ አሰለብሰው በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስም አይግዝሯቸው እንጂ በአማራ ሰም ሊቢያ ከተፈጸመው ግፍ በላይ በክርስትያኑኖ ሕብረተሰብ ላይ በወያኔ ታጣቂዎች ተፈጽሟል። በቪዲዮ ባለመቀረጹ ምንም ዓይነት ግድያ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩ ክርስትያኖች ላይ እንዳልተፈጸም ገምተን የሊቢያውን አጋነን ካራገብን ተሣስተናል። ሳሞራ ዩኑስና ሳራ መኮንን፣ በጋራ ሙለታ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በአርባ ጉጉ ከነሕይወታቸው ገደል ያስጣሏቸው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ዓምላክ ነፍሳቸውን ከገነት ያኑርልነና ፕሮፌሰር አሰራት ወልደየስ የአማር ድረጅት ብለው ሲያቈቁሙ በአማራ ስም ወያኔዎች ያስገድሉት የነበረውን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩን ለመታደግ ነበር። እንደሳቸው ድሬ ደዋ ተወልዶ ላደገ አማራ ማለት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መሆኑን ጠንቅቶ ያውቃል። አንዳንድ የወያኔ ሸፍጥ ያልገባቸው ወይም እንዲገባቸው ያልፈለጉ እኛን ታላቅ ሰው ለዘር ፖለቲካ የቆሙ አሰመስለው ያቀርቧቸዋል። ከአድራጊዎቹ ግን በድፍረት ሐቁን ይነግሩናል፣ ለምሳሌ አቶ ሰብሃት ነጋና አቶ ተፈራ ዋልዋል ተራ በተራ እንዲህ ይነግሩናል፣ በገሃድ’ ‘አማራውነና የኦርቶዶክ እምነት ተከታዮን አከረካሪውን ሰበረነዋል፣ የኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን የአማራው ምሽግ ናት’ እስከማለት ደርሰዋል፤ ይህ አሉ አሉ ሣይሆን በማስረጃ የተያዘ ነው። በመኝታ ክፍላችን የተኛውን ትልቁን ዘንዶ ረስተን በዱሩ ባለው እባብ ላይ እንጮሃለን፣ ይህ ስሜት ይሰጣችኋል? ለእኔ አይሰጠኝም፤ የክርስቲያኑና የእስልምና ተከታዩ መሳ በመሳ በሚኖርባትት ኢትዮጵያ ላይ ‘ጀሃድ’ የሚያውጅ የእስልምና ተከታይ ካለ እርሱ እስላም አይደለም፣ በክርስታኑም በኩል ያንን የሚያስብ ካለ ሸፍጠኛ ነው። ሸፍጠኛው ወያኔ ‘ጀሃድ’ ታወጀብኝ ብሎ ሱማሌን 1997 ዓ ም የወረረው በምርጫ የደረሰበትን ሸነፈት አቅጣጫ ለማስለወጥ መሆኑን ተግባሩ ገላጭ ነው፤ ራሱ ወያኔ አሸባሪ ሆኖ የሃይማኖት ጽፈኞችን ሊዋጋ አይችልም፣ በሦልጣን የሚያቆየው ከሆነ ከእነረሱ ማበሩን ይመርጣል፣ በዱር በነበረበት ዘመን ያደረገው ያንን ነበር፣ የነርሱን መንገድ ይከተላል፣ በተግባር ሲያደርገው ያየነው ያንኑ ነው፣ በጋንቤላ በአንድ ሌት አራተ መቶ ሰው፣ በቤንሻጉል፣ በጉራ ፈርዳ፣ በኦጋዴን፣ ሬሣ ተጋድሞ ሲቆጠር፣ ወንድሙ የወንድሙን አሰከሬን መሬት ለመሬት እንዲጎትት በውያኔ ታጣቂዎች ትዕዛዝ ሲሰጠው ያየነው ነው፤ እንደዜጋ ከዕንቅልፋች መንቃት አለብን። በየመን የከተመው አልካይዳ በሱማሌ የሚቀሳቀሰው አልሸባብ የሃይማኖት አሰተህምሮታቸው ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ያልገባው በወያኔ ሠራዊት ጥንካሬ አይደለም፤ በሕዝቡ ውስጥ በቅርበት የሚሰሩ የሁለቱ ሃይማኖት አባቶች አርቆ አሰተዋይነት ነው። በወያኔ የተመለመሉትን የክርስትያኑንም ሆነ የእስልምናው ተከታይ አባቶችን አይመለከትም። ወያኔ በሦልጣን ከቀጠለ ግን ሁኔታዎች መቀጠላቸው አሰተማማኝ አይሆንም፤ የዚህ ቡድን ያለፉ ድርጊቶቹ የሚያሳዩን ሕዝብን በሃይማኖትና በዘር እያለያየ ሲያጋድል፣ቦንቦችን በሕዝብ ማመላሻ መኪናዎች ወስጥ እያጠመደ በተቃዋሚዎቹ ላይ ሲያላክክ ነው። ይህ የሸፍጠኛ ቡድን በጎሣ ፖለቲካ ሽፋን፣ የሃይማኖት ልዩነት ያራምድ እንደነበረ አሁንም እያደረገ እንዳለ አንድ ማስረጃ ልጥቀስ፣ ጃራ የሚባለው በምሥራቅ ሐርረጌ ኢስላሚያ ኦሮሚያ በማለት ቆቱውን ወይም አርሶ አደሩን በግብርና መሣሪያው፣ በጌጅራና በሜጫ ክርስትያኑን አሣርዷል፣ ሳሞራ ዩኑስና ሳራ መኮንን አማራውን ለማስገደል መልክተኛቸው እርሱ ነበር። በአሜሪካ ከአንድ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ የጎሳ አቀንቃኝ በጥቅሉ በሜጫና በግጅራ ተዋጓቸው በማለት የጃራን መፈክር ሲያስተጋባ ስሰማ ጆሮዬን አላመንኩም፣ ወያኔም የሚፈልገው ይህን መሰል ካድሬ ነው።
ኢትዮጵያ ሀገራችን በነፃነት ለሦሰት ሺ ዓመት ኖራለች የሚል ታሪክ አለን፤ በሃያ አንደኛው መቶ ዓመት ነፃነታችንን አሳልፈን ሰጥተን በዓለም ሕበረተሰብ ፊት ተዋርደናል፤ ለመሞት የማንፈራ ኢትዮጵያውያን እንዴት ነው በግልም ሆነ በጋራ ወያኔን በቃህ የማንለው? ይህን ማድረግ የማንቸለው ለምንድነው? በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ሽፋን ይህ ቡድን ሸፍጥ ሲሰራ የትገራይ ሕዝብስ ምን ያስባል? ከተናገርን እናልቃለን፣ አልሰማንም አላየንም ማለቱ ለልጅ ልጆቻችን አይጠቅምም፣ እውነት ኮስሶ ሽፍጥ ሥረዓት በሆነባት ሀገር፣ እንዴት ትውልድ መተካት ይቻላል? ለሸፍጥና ለነፍጥ ሣንበረከክ የዜግነት ግዴታችንን የምንወጣበት ወቅቱ አሁን ነው፣ ከዚህ ከምነያውና ከምንኖረው ሐቅ በላይ ምን ማየት እንሻለን? ታሪክ የጣለብንን ተግዳራት መጋፈጥ ግድ ይለናል። ‘አሣ ግማቱ ከአናቱ’ እንደሚባለው ወያኔ በሸፍጥ የገማ ብድን ሰለሆነ በሕዝብ የተባበረ ከንድ መወገድ አለበት። የሚመጣው ምርጫ የወያኔ ሳይሆን የእኛ እናድርገው፣ ትንሽ አገር ብትሆንም ትልቅ ልብ ካለው የ ቡርኪነፋሶ ሕዝብ እንማር! በሊቢያ አይሲሲ አረመኔው ቡድን ካራውን በአንገታቸው ላይ ሲያርፍባቸወ የሚሰማችው የሞት ጽልመት ፣ዛሬ ያ እንዳይሆን ለወገን ክበር ለሀገር ነጻነት በመቆማችው በወያኔ እስር ቤት የሞት ጽልመት ሰለ አጃበበባችው ወኖች እናስብ፤ ለእዚህም ነው ወያኔና አይሲሲ አንድ ናቸው የምንለው።
ኢትዮጵያ ሀገራችንን እንታደጋት፣ ሕዝባችን ማደሪያ እንደሌላት ወፍ አይከራተት።