በሊቢያ ወገኖቻችን ዙሪያ አስቸኳይ ጥሪ – ግርማ ካሳ

በሊቢያ ቤንጋዚ አካባቢ ያሉ ወገኖቻችንን ወደ ግብድ ለመዉሰድ ታስቧል። እርሱ ላይ ችግር የለም። በትሪፖሊ/ሚስራታ ያሉትን ግን በሱዳን በኩል ለመዉሰድ ነው ኢሕአዴግ እየሰራ ያለው። ይሄ በጣም አደገኛ ነው። እዚህ ላይ ወገኖቻችን በሱዳን በኩል እንዲወጡ ቢደረግ 100% አይሰስ ይይዛቸዋል ማለት አይደለም። ምናልባት በወታደራዊ ኮንቮይ ታጅበው ይሆናል ለማስወጣት የታሰበው። ቢሆንም ትልቅ ሪስክ ነው እየተወሰደ ያለው።

11156316_10206341228440328_1740631521258789980_n
አንደኛ ከዚህ በፊት በአይሰስ የተገደሉት ወገኖቻችን ከሱዳን ወደ ትሪፖሊ ሲጓዙ ነው የተያዙት። ያለዉን ሁኔታ ለመረዳት የተያያዘውን ማኦ ይመለክቱ። አሁን ደጎም ከትሪፖሊ ወደ ሱዳን መጓዝ፣ ያለ ምንም ጥርጥር ወገኖቻችንን አደጋ ላይ የሚጠል መታሰብ ያልነበረበት ነው።
ከትሪፖሊ ሱዳን ያለው ጉዞ በመኪና ቢያንስ አራት፣ አምስት ቀን የሚፈጅ ነው። እጅግ እጣም በረሃማ በሆነ ቦታ የሚያልፍ ነው። ወደ ሁለት ሺህ ኪሎሜትር ይርቃል። የሁለት ሰዓት ተኩል መንገድ የሚፈጅና ከ300 ኪሎሜተር በታች የምትረቀዋ ቱኒዚያ እያለች ወደ ሱዳን መታሰቡ በጣም አሳዛኝ ነው።

ራዲዮ ፋና የሚከተለዉን ነው ያሰፈረው

“ቤንጋዚ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በግብፅ በኩል እና በትሪፖሊ ያሉትን ደግሞ በሱዳን በኩል ወደ አገራቸው ለመመለስ ነው ጥረት እየተደረገ ያለው።በግብፅ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዳስታወቀው 200 የሚሆኑ በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ተመዝግበዋል።”
ዶር ቴድሮስና ጨመሮ ከፍተኛ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት ወንድም ወይም እህት ሊቢያ ቢኖሩ ነው፣ ባለስልጣናቱ በሱዳን ሊያወጧቸው ይሞክሩ ነበር ወይ ? በመሐል አይሰስ ሊኖር በሚችልበት ቦታ በመዉሰድ ለአደጋ እንዲጋለጡ ያደርጉ ነበር ወይ ? በጭራሽ አያደረጉትም ነበር።
እንግዲህ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ያለን ኢትዮጵያዉያን በዚህ ረገድ በጣም ድምጻችንን ማሰማት አለብን። ወገኖቻችን ሲሞቱ ብቻ ማዘን አይደለም። ዳግም ኢትዮጵያዊያን የአይሰስ ሰላባ እንዳይሆኑ መድከም፣ መጣር፣ መጮህ ፣ የድርሻችንን ማድረግ አለብን።
አንዴት ነው ልንረዳ የምንችለው ፡

1) ይሄንን መረጃ ሼር እናደርግ። ኢሕአዴግ ምን እያሰበ እንዳለ፣ ያለዉን አደጋ ለህዝብ እናሳወቅ። ሕዝባዊ ሞቢላይዜሽን ያስፈልጋል። በኢሜል፣ በኤስ.ኤም.ኤስ፣ በቫይበር፣ በስካፕይ፣ ተዊተር …ኢሕአዴግ ወገኖቻችን ለአደጋ አጋልጦ በሱዳን በኩል ሊያስወጣ እንዳሰባ እናሳወቅ።
2) ዶር ቴድሮስ የፌስ ቡክ ገጽ አላቸው። ብዙዉን ጊዜ እዚያ ላይ ሳያጠፉ አይቀርም። ስለዚህ በፌስቡክ ገጻቸው በመሄድ በሺሆች የምንቆጠር «ወገኖቻችን በሱዳን በኩል በመዉሰድ ለአደጋ እንዳታጋልጡ። ከወሰዳቹሃቸው በቱኒዚያ በኩል አስወጧቸው» ብለን አስተያየት እንስጥ።
አንዳንዶች እነርሱ የበለጠ ጉዳዩን ያወቁታል የሚል መከራከሪያ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ማንም ኢትዮጵያዉ ካርታውን አይቶ መፍረድ ይችላላል። ማንም በርግጥ የሚሻለዉና የሚመረጠው በቱኒዚያ በኩል እንዲወጡ ማድረግ እንደሆነ ማየት አያቅተዉም።
አንዳንዶቻችን ላይክ፣ ሼር ለማድረግና አስተያየት ለመስጠት እንኳን የምንፈራ አለን። የድርሻችንን ለመወጣት እንፈልጋለን ግን በፍርሃት ታስረናል። ወያኔዎች አይተው ከሥራ ያባርሩናል፣ ያስሩናል ብለን እንሰጋለን። ዉጭ አገር ያለን ደግሞ፣ ወያኔዎች አገር ቤት ያለንን ቤትም ሆነ ቢዝነስ የሚወስዱብን ይመስለናል። በቃ በአደገኛ ፍርሃት ተተብትበናል።

አንዳንዶቻችን ደግሞ የፍርሃት ችግር የለብንም፣ ግን ምንም ለዉጥ የማናመጣ ይመስለናል። የሚሆነውን አይተን፣ አንብበን፣ ተናደን ፣ ተስፋ ቆርጠን እንተወዋለን። ገና ምንም ለማድረግ ሳንነሳ ራሳችንን በራሳችን እናሸንፈዋለን።
ግን አንድ ነገር ልጠይቅ «እነዚህ ወገኖቻችን የስጋ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ቢሆኑ ኖር ፣ በሱዳን በኩል ኢሕአዴግ ለአደጋ ሊያጋልጣቸው ሲሞክር፣ ፈርተን ወይንም ተስፋ ቆርጠን ዝም እንል ነበር ወይ ? እንግዲህ ከሕሊናችን ጋር እንነጋገር፤፡ ከተሰማን፣ ካዘንን፣ ወገኖቻችን የኛው ናቸው ካልን፣ እንቀሳቀስ። አንድ ተብሎ ነው ወደ ሁለት የሚኬደው። ድምጻችንን ፣ ተቃዉሟችንን እናሰማ።