በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የዘንድሮው ዓመት የሙስና ሠንዘረዥ መሰረት ዴንማርክ እንደ አምናው ከሙስና ነፃ ከሚባሉት ሀገራት ተርታ በቀደምትነት ስትሰለፍ ሶማልያ ደግሞ በሙስና ከተዘፈቁት ሀገራት ከመጨረሻ 1ኛ ሆናለች። ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራትስ?

«ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል» በመባል የሚታወቀው፣ በዓለም ዙሪያ ለነባር ህዝቦች ኅልውና የሚታገለው ድርጅት የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስለኦሞ ሸለቆ ጉዳይ እንዲያነሱ አሳሰበ። ድርጅቱ በኦሞ ሸለቆ «የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተከሰተ ነው፤ ጀርመንም ሆነች ሌሎች የአውሮጳ ሃገራት የመብት ጥሰቱን አይተው እንዳላዩ ሆነዋል» ብሏል።

ህዳር 27 እና 28 2007 ዓ.ም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የሚያደርጉት የአዳር (24 ሰዓት) ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃ ላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ እስካሁን ሰው በሰውና ቲሸርት በመልበስ ቅስቀሳ ሲደረግ እንደቆየና በተለይ ዛሬ ህዳር 24/ 2007 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ በአዲስ ከተማ፣ ጉለሌ፣ አራዳ፣ የካ፣ ንፋስ ስልክ፣ ኮልፌና ሌሎች የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማዎች ወረቀት በመበተን የተሳካ ቅስቀሳ መደረጉን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ለአዳር ሰልፉ ሲቀሰቅሱ ከነበሩት መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ሜሮን አለማየሁ፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ባህረን እሸቱ፣ ማቲያስ መኩሪያ እንዲሁም ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲቀሰቅስ የነበረው ሲሳይ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ተግልጾአል፡፡

ከአሁን ቀደም ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ ሲያደርጉ በርካታ የፓርቲው አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ያስታወሱት አቶ ዮናታን ‹‹ይህ የገዥው ፓርቲ የተለመደ እርምጃ ነው፡፡ በቀጣይነትም ሌሎች አባላትንና አመራሮች መታሰራቸው አይቀረም፡፡ ትግሉ መስዋዕትነት የሚያስከፍል እንደመሆኑ በእስሩ ሳንገታ ትግሉን እንቀጥላለን፡፡›› ሲሉ እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ የዛሬው ቅስቀሳ 12 ሰዓት ላይ የተጠናቀቀ ሲሆን ነገ ጠዋት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Image

Image

ከሰሞኑን በአንዳንድ ድረ ገጾችና በሶሻል ሚዲያው የታቦተ ጽዮን መሰረቅ/መጥፋት አሳዛኝ ዜናን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን መሪ የሆኑት በፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በይፋ መግለጻቸውን እየተቀባበሉ ሲያስነብቡን ሰንብተዋል፡፡ የሶሻል ሚዲያው ተከታታይ በኾኑት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድም ይህ ዜና ምናልባትም መርዶ ብሎ መግለጹ የተሻለ ሣይሆን አይቀርም ለጊዜውም ቢሆን ብዙዎችን ያደናገጠና ያስቆጨ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የዜናውን […]

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለንግዱ ማህበረሰብ ጥሪ ቀረበ ::

ጥሪው እንደሚከተለው ነው::
የንግድ ማህበረሰብ ለአንድ አገር ምሰሶ ነው፡፡ በዴሞክራሲ በበለጸጉ አገራት የንግዱ ማህበረሰብ ለራሱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ያለውን ፈርጣማ የኢኮኖሚያዊ አቅምና ኢኮኖሚያዊ አቅሙ የሚፈጥርለትን የተሻለ ንቃተ ህሊና በመጠቀም ለጭቁኖች መከታ ሲሆን ታይቷል፡፡ ለዚህም ነው የንግዱ ማህበረሰብ ዴሞክራሲን በመገንባት ትልቅ ሚና እንዳለው የሚነገርለት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ባለው ሁኔታ የንግዱ ማህበረሰብ በነጻነት ሰርቶ የሚበለጽግበት፣ ወገኑንና አገሩን በተለያየ መንገድ የሚያግዝበት መንገድ በመዘጋቱ የሚገባውን ያህል አስተዋጽኦ አበርክቷል ለማለት ይከብዳል፡፡

ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት ጊዜ ነጻ ገበያን እንደሚከተል በመግለጹ የንግዱ ማህበረሰብ በነጻ ገበያ መርህ ተወዳድሮ ራሱንም አገሩንም ይጠቅማል የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም ይህ ተስፋ እውን ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ይልቁንም ገዥው ፓርቲ የራሱን የኢኮኖሚ ኢምፓየር በመመስረት የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ስርዓት አበላሽቶታል፡፡ በራሳቸው ነግደው የሚያድሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ግልጽነት በጎደለው መንገድ የአገሪቱን አንጡራ ሀብት እየተጠቀሙ ከሚገኙት የገዥው ፓርቲ ግዙፍ ኩባንያዎች ጋር መወዳደር አቅቷቸው የከሰሩት በርካቶች ናቸው፡፡ በተለያየ መንገድ አሁንም ድረስ የቀጠሉትም ቢሆን ከገዥው ፓርቲ ተቋማት ጋር መወዳደር ተስኗቸው ለራሳቸውም ሆነ ለአገራቸው ማበርከት የነበረባቸውን አስተዋጽኦ እንዳያበረክቱ ተደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ለገዥው ፓርቲ ባለማደራቸው ምክንያት አግባብ ያልሆነ ቀረጥና ሌሎች ጫናዎች እየተጣሉባቸው አንድም ከገበያ ወጥተዋል፡፡ አሊያም የሚገባቸውን ጥቅም ማግኘትና አገራቸውን መጥቀስ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ለገዥው ፓርቲ መዋጮ እንዲከፍሉ ከመጠየቃቸውም በላይ ስርዓቱ ባነገሰው ሙስና ምክንያት እጅ ተወርች ተይዘው ራሳቸውን፣ ህዝባቸውንና ለአገራችን ዴሞክራሲ ግንባታ ያበረክቱትን የነበረው አስተዋጽኦም ተገድቧል፡፡
በሌላ በኩል በገበያው ላይ የሚቆየው ለስርዓቱ ያደረ ብቻ በመሆኑ በርካቶች ለአገር ከመስራት ይልቅ ለገዥው ፓርቲ ማደር መርጠዋል፡፡ በዚህም አንድ የንግድ ማህበረሰብ ለአገሩ ያበረክት የነበረውን አስተዋጽኦ ረስተው የተሳሳተ መንገድ ይዘዋል ብለን እናምናለን፡፡ ራሳቸውን ለገዥው ፓርቲ አሳልፈው በመስጠታቸውም ታሪካዊ ግዴታቸውን ሳይወጡ ቀርተዋል፡፡ ይህን ስንል ግን ከገዥው ፓርቲ ተጠግተው ከሚያገኙት ጥቅም ይልቅ ከህዝብ ጋር ቆመውና ግዴታቸውን እየተወጡ መስዋዕትነት የሚከፍሉ የሉም ማለት አይደለም፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት የንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቅበትን ያህል እየሰራ እንዳልሆነ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

የንግዱ ማህበረሰብ ስርዓቱ በራሱም ሆነ በአገሩ ላይ የሚፈጽመውን ህገወጥነት በየግሉ ከመቃወምም ባሻገር ትግሉን በማገዙ ወደፊት ለራሱም ሆነ ለአገሩ የሚያሰራ ስርዓት መፍጠር ይችላል ብለን እናምናለን፡፡ በመሆኑም ስርዓቱ በራሱና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን በደል በመቃወም ላይ የሚገኙትን ተቃዋሚዎች ትግል በሞራል፣ በገንዘብና በሌሎችም ድጋፎች በማገዝና ትግሉን በመቀላቀል ለንግዱ ማህበረሰብና ለኢትዮጵያ የሚያዋጣትን ስርዓት እንድንመሰርት ጥሪ እናደርጋለን፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለንግዱ ማህበረሰብና በአጠቃላይም ለኢትዮጵያ የሚመች ስርዓት ለመፍጠር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህም መካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋል፡፡ ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያውያን መብታቸው ተከብሮ የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ጮራ የሚፈነጥቅ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በመሆኑም የራሱንም መብት በማስከበርና የአገሩን ዴሞክራሲ በመገንባት ታሪካዊ ሚና ያለው የንግዱ ማህበረሰብ ትግላችን በመቀላቀል፣ በገንዘብና በሞራል በመደገፍ የዚህ ታሪካዊ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

ታሪካዊ ግዴታችን በመወጣት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንገንባ!

ግንቦት ሰባት የተሰኘው ፣ መሰረቱን አስመራ ያደረገው ድርጅት፣ በአገር ቤት ላሉ ተማሪዎች፣ መምህራን ጥሪ አቅርቧል። «የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የትምህርት ኃላፊዎችና ፕሬዚዳንቶች ሆይ! ለገዛ ራሳችሁ ክብር፣ ለአካዳሚ ነፃነት፣ ለትውልድ ስትሉ በዚህ መመሪያ ላይ አምጹ! “እንቢ፣ አሻፈረን፣ በዚህ መመሪያ አንገዛም” በሉ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችሁ ይቆማል» ሲል ነው፣ ግንቦት ሰባት ጥሪ ያስተላለፈው። ይህ የግንቦት ስባት መግለጫ […]

የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ ንግግር ተከትሎ የቆርጦ ቀጥል የፍረጃ ፖለቲካ አራማጆች እና ከሩቅ ሆኖ ድጋይ ለማቀበል የሚፈልጉ ኃይሎች ቁንፅል ነገር ይዘው በየአቅጣጫው በዱምዱም ጥፍራቸው አንድነት ፓርቲንም ደምረው መቧጠጥ ጀምረዋል ፡፡ ሆኖም አቶ ግርማ አሉ የተባሉትንና የመለሱትን ምላሽ እንዲሁም ከተቃወሟቸው ሰዎች መሃል ጥቂቱን ሰምቼአለሁ አንብቤያለሁ ፡፡ አልገባንም ምን ለማለት ተፈልጎ ነው ይብራራልን ማለት የአባት ሆኖ […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደተለመደው በጸረ ሰላም እና በጸረ ሕዝብነት በጥብቅ ይፈረጃሉ::
Minilik Salsawi

የወያኔው ጁንታ ስልጣኑን እንዳያጣ እየተፈረካከሰ ባለበት በዚህ ወቅት መጪው ምርጫ ከመድረሱ በፊት አስፈላጊውን ከለላ ለማግኘት ለመከላከያ ለፖሊስ እና ለደህንነት ክፍሉ ምርጫውን ተገን በማድረግ እና በማሳበብ የስልጠና ሰነድ ይዞ በየክፍሉ ካድሬዎችን በማሰራጨት የፓርቲውን አስተሳሰብ ለመጫን ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል::

ስልጠናው ዋናው ነጥብ በመጭው ምርጫ ህዝባዊ አመጾች የነጻነት እና ይመብት ጥያቄዎች እንዳይይፈነዱ ስጋት ያለብት ወያኔ በሰራዊቱ እና ደህንነቱ ላይ ያለውን ጥርጣሬ ለመቅረፍ እና ለማሳመን ያዘጋጀው ሰነድ እንዲሁን በግሩፕ እየለየ ጠላቱን ለመልቀም ያመቸው ዘንድ ያዘጋጀው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::

ምንጮቹ የስልጠናውን ሰነድ ጠቅሰው እንደተናገሩት በዋናነት በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ የተዘጋጀ ሲሆን እንደተለመደው በጸረ ሰላም እና በጸረ ህዝብነት ይፈረጃሉ::ድርጅቶቹ ለሃገር አደጋ እንደሆኑ እና ሰራዊቱን ሊበትኑ የተዘጋጁ እንደሆነ ታውቋል:: ምንጮቹ አክለው እንደተናገሩ በሃገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ሰራዊቱን ና የደህንነት ክፍሉን በመረጃ በዝርዝር ማስተማር አለባቸው:: ያሉ ሲሆን የሚያጉረመርሙ የሰራዊቱ እና ደህንነቱ ክፍሎች የለውጡ አካል እንዲሆኑ ከፖለቲካ ድርጅቶቹ ትልቅ ስራ ይጠበቃል ብለዋል::ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሰኝ አቀርባለሁ::

በምርጫ አለመሳተፍ መብት ነው !በኢትዮጵያ ያለው ጭላንጭል የፖለቲካ ምኅዳር ሲታይ፣ይህ ውሳኔ የሕግ፣የፖለቲካ እና የሞራል ድጋፍ አለው፡፡ሆኖም ግን በምርጫ ያለመሳተፍ መብት በራሱ-የራሱ የሆነ ተግዳሮቶች አሉትና፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትርፍ-ኪሳራ ሥሌት የግላቸው ነው የሚሆነው፡፡
Yidnekachew Kebede
ይህ ጹሑፍ በምርጫ አለመሳተፍ መብት መሆኑን ከህግ አንፃር ለማየት እንጂ፣ የሚጪው አገረ አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ “ኢሕአዴግ ለመርጫ አልተዘጋጀም !” እና “የ24 ሰዓት ተቃውሞ በአዲስ አበባ !” በሚል ዕርሶች ከዚህ በፌት በፃፍኳቸው ፁሑፍ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ፣ ገዥው መንግስት ለነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ እራሱን አዘጋጅቶ፣ ውጤታማ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል የግል እምነቴን ገልጫለው፡፡
ወደተነሳሁበት ዕርስ ስገባ፡- ማንኛውም ሰው በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ እንዲሳተፉ አይገደድም፣ባለመሳተፉ ግን ተቃውሞን የመግለፅ እና ደግፋ የመስጠት መብት ይነፈጋል ማለት አይደለም ፡፡ይህም በመሆኑ የትኛውም የዲሞክራሲ ሥርዓት የተሟላ ተሳትፎ በህብረተሰብ ካልተደረገበት ውጤታማነቱ ደካማ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡የዲሞክራሲ ሥርዓት ማሳያ መስታዎት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት መንቀሳቀስ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ያለምንም ፍርሃት በፈለገው ወይም በፈለገችው ፓርቲ ውስጥ አባል የመሆን ዕድልና አማራጭ ማግኘት የግለሰብ መብት ነው፡፡ግለሰቦች በፈለጉት የፖለቲካ ፓርቲ የመደራጀት እና የመሳተፍ ነፃነት ሲኖራቸው ለዲሞክራሲ መሠረት ይሆናል፡፡
ይህ አይነቱ የዲሞክራሲ ሥርዓት በአገራችን ምን ያኸል ተፈፃሚ ነው ? ተብሎ ቢጠየቅ ምላሹን ለማወቅ ብዙም አድካሚ አይደለም፡፡ውጤቱ አሉታዊ ነው፡፡እርግጥ ነው በሕገ መንግስት አንቀፅ 31 ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓለማ በህግ “የመደራጀት” መብት እንዳለው በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ይሄን መነሻ በማድረግ በአገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የተቋቋሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው፡፡የእነዚህ ፓርቲዎች መብት እና ግዴታ እንዲሁም ሊከተሏቸው የሚገባ መርህዎች፣ በሕገ መንግስቱ፣በፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ አዋጁች እዲሁም በመተዳደሪያ ደንብቻው ብቻ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ተቋቁመው እየተንቀሳቀሱ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአገራችን ቁጥራቸው በርካታ ቢሆንም፣ ቢሚፈለገው ሁኔታ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ግን በቁጥር አነስተኛ ፓርቲዎች ሲሆን፣ የተቀሩት የምርጫ መጣ ወይም የመግለጫ አሯሯጮች pacemaker መሆናቸው በግልፅ የሚታወቅ ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋንኛ ዓላማ በመርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ የፓለቲካ ሥልጣን በመያዝ የቆሙለት ዓላማ በስልጣን ዘመን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡
ምርጫ በዲሞክራሳዊ አካሄድ ለሚወከል መንግስት የጥንካሬ መለኪያ ነው፡፡ይህን ለማለት የሚያስችለው ተመራጮች መብታቸው እና ግዴታቸውን ሙሉ በሙሉ ከመራጩ ሕዝብ ስለሚያገኙት ነው፡፡እንዲ አይነቱ በሕዝብ ተሳትፎ ሥልጣን የሚቀየርበት ዋናው መንገድ ነፃና ሚዛናዊ የሆነ ምርጫ ሲደረግ ብቻ ነው፡፡ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በኢሕአዲግ/ በህወሐት መንግሰት የ24 ዓመት የስልጣን ዘመን በተደረጉ ምርጫዎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለመሆን አልቻለም፡፡ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በዋነኛነት የሥርዓቱ አስከፊ ድርጊት ቢሆንም፣ በተጨማሪ ጠንካራ የሆኑ በመላው ኢትዮጵያ የሕዝብ ድጋፍ ያለው የተቃዋሚ ፓርቲ አለመኖሩም ጭምር ነው፡፡ እርግጥ ነው በ1997 ዓ.ም በቅንጅት የታየው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መነቃቃት፣ በአገራችን የዲሞክራሲ በዓል አንድ እርምጃ ወደፊት ከነበረበት ያንቀሳቀሰው ቢሆንም፣ በገዥው ሥርዓት ቀጥተኛ ተፅኖ፣ እንዲሁም በቅንጅት ፓርቲ ውስጥ በታየው ድክመት እና የስልጣን ሽኩቻ የለውጥ እንቅስቃሴውን ገትቶታል፡፡
አሁን ላይ በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከበፊቱ “በቆምክበት እርገጥ” አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተላቀው ምን ያህል “ወደፊት” እየሄዱ ነው የሚለውን ምላሽ ይህን ጹሑፍ ለሚያነቡ እና ለጉዳዩ ቅርብ ነኝ ለሚሉ ወገኖች የምተወው ሃሳብ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአገር ውስጥ የሚንቀሣቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከ6 ወር በኋላ አገር አቀፍ ምርጫ ይጠብቃቸዋል፡፡ፓርቲዎች የምርጫ ፓርቲ ቢሆኑም ፣በምርጫ አለመሳተፍ መብታቸው በሕግ የተጠበቀ መሆኑን አውቀው ግራ ቀኛቸውን ቢመለከቱ፣ዝም ብሎ ገዥውን ፓርቲ በምርጫ ከማጀብ ይላቀቃሉ፤አሊያም በእኩል ተሳትፎ ወደ ምርጫው የሚገቡበትን መንገድ ተገዳድረው ማመቻቸት ይቻላል፡፡
የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ቁ .573/2000 አንቀፅ 39 ቁ.2 ሐ.“ የፖለቲካ ፓርቲ ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን የጠቅላላ ወይም የአካባቢ ምርጫ ወድድርን ሳይሳተፍ የቀረ እንደሆነ ” ምርጫ ቦርድ በአዋጁ መሠረት ውሳኔ በማስተላለፍ ከመዝገብ ሊሰርዝ ይችላል፡፡የሚል የህግ ድንጋጌ አለ፣ይህን ድንጋጌ ከተነሳንበት ዓላማ ጋር በማገናኘት ምክንያት እና ውጤቱን መመልከት ተገቢ ነው፡፡
በመሠረቱ የፓርቲ ነፃነት በእንዲ መልኩ መገደብ አጠቃላይ የአዋጁ ችግር ዋንኛ ማሳያ ነው፡፡የትኛውም ፓርቲ በምርጫ የመሳተፍ ወይም ያለመሳተፍ መብት ካለጊዜ ገደብ ለራሱ ለፓርቲ የሚተው ስራ እንጂ ፣በህግ ገደብ የተጣለበት መሆን የለበትም፡፡ይህን ለማለት የሚያስደፍረው የግል እንዲሁም የጋራ መብት የሚጋፋ በመሆኑ ነው፡፡ለዚህም ማሳያ የመምረጥ እና ያለመምረጥ መብት የተጠበቀ ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ በመጪው ምርጫ አልመርጥም ፣አልመረጥም ይህ በህግ ክልከላ ተደርጎብኝ ሳይሆን የእኔ መብት በመሆኑ ነው፡፡ልክ እንደኔ የግል መብት ያላቸው ሰዎች ተሰባበስበን የጋራ መብታችን ለማቋቋም በምንቀሳቀስበት ወቅት በግሌ ማድረግ የምችለውን በጋራ እንደማጣት ይቆጠራል፡፡ከዚህ አንፃር ይህ ድንጋጌ በእኔ እይታ ተገቢ መስሎ አይታየኝም፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሃቅ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሚተዳደሩት በዚህ አዋጅ ነው፡፡በመሆኑም አዋጆን መሠረት በማድገረግ በምርጫ አለመሳተፍ ገደብ ቢኖረውም ለፓርቲዎች የተሰጠ መብት አለ፡፡ ማንኛው ፓርቲ ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን ሳይሳተፍ የቀረ እንደሆነ ይሰረዛል፡-ይህ ማላት፣በ2002 አገር አቀፍ ምርጫ በማንኛውም ምክንያት በምርጫ ያልተሳተፈ “ሀ” የተባለ ፓርቲ በ2007 የማይሳተፍ ከሆነ ይሰረዛል ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይሄ “ሀ” የተባለው ፓርቲ በ1997 ምርጫ አልተሳተፈም ብንል ፣በ2002 ተሳትፏል ካልን በ2007 ምርጫ አለመሳተፍ የ”ሀ”ፓርቲ መብት ነው፡፡ይህም በማድረጉ ከምርጫ ቦርድ ምን አይነት ጥያቄ ለዚህ ፓርቲ አይቀርብም፡፡በዚህ መሠረት ፓርቲዎች ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመን በምርጫ ካተሳተፉ የመሰረዝ እጣቸው በእጃቸው ነው፡፡ሆኖም ግን የምርጫ ዘሙኑ ተከታታይነት ሳይኖረው በምርጫ አለመሳተፍ በአዋጁ መሠረት የሚያስከትለው ውጤት አይኖረውም፡፡
ይህ ከላይ የቀረበው ማሣያ፣ ለአገር አቀፍ እንዲሁም ለአካባቢ ምርጫ የሚያገለግል ነው፡፡በአሁን ወቅት ሁለቱ ምርጫዎች በተመሳሳይ የምርጫ ዘምን ባለመካሄዳቸው እረሳቸውን ችለው የሚቆጠሩ የምርጫ ዘመን ነው፡፡በኢትዮጵያ አሁን ባለው የምርጫ ስርዓት ፣የአንድ የምርጫ ዘመን አምስት ዓመት ነው፡፡ስለዚህም በአገር አቀፍ እና በአካባቢ የምርጫ ዘመን የ2 ዓመት ልዩነት አለ ማለት ነው፡፡በመሆኑም በዘንድሮ የአገር አቀፍ ምርጫ ዘመን ከባለፈው ሁለት ዓመት ከተካሄደው የአካባቢ ምርጫ ዘመን ፈፅሞ የሚገኛኝ አይደለም፡፡
በሕገ መንግሥት አንቀፅ 38 ቁ.1 ሐ.“ በማናቸውም ደረጃ በሚካሄዱ ምርጫ፣የመምረጥ እና የመመረጥ ፣ምርጫው ሁሉ አቀፍ፣በእኩልነት ላይ የተመሰረት እና መራጩ ፈቃዱን በነጻነት የሚገልፅበት ዋስትና የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡”በማለት የህጎች ሁሉ የበላይ ሕግ በሆነው ሕገ መንግሰት በግልፅ ተቀምጧል፡፡
ሆኖም በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ሕገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ ምርጫ ስለመካሄዱ አጠራጣሪለው የሚል ፓርቲ፣እንዲሁም ምርጫው ከመካሄዱ በፌት በምርጫው ሄደት ላይ ቅደመ ሁኔታ እስካልሟላለት ድረስ የታሰበው ምርጫ ነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አይደለም በማለት ከበቂ ምክንያቶች ጋር በማዛመድ ከላይ በተገለፀው የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ መሰረት፣ በምርጫ ያለመሳተፍ መብት በሕግ ድጋፍ ያላው መብት ነው፡፡
ይህ መብት ከሕገ መንግሰቱ እና ከላይ በተገለፀው አዋጅ የመነጨ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ ያሉ ማናቸውም አሰራሮች፣ልማዳች እንዲሁም መመሪያ ይህን መብት የሚጋፉ መሆን እንደሌለባቸው የታወቀ ነው፡፡እናም ፓርቲዎች ሁሌም የፖለቲካ ምኅዳሩ ተዘግቷል፣ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ አልቻልንም፣መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከለከልን……..ወዘተ እያሉ ከሚናገሩ፣ምኅዳሩ እንዲሰፋ ከገዥው ፓርቲ ጋር በመነጋገር ማስተካከል ካልተቻለ፣በጊዜ ከምርጫው ታቅበው ገዥው ፓርቲ እራሱ ደግሶ እራሱ ለብቻው ይስተናገድበት ዘንድ በመተው እውነታውን ለህዝብና ለዓለም ቁልጭ አድርጎ ማሳየት ነው፡፡እስከ መቼ በምርጫ መጭበርበር !
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

መስታወት ራሱን አያይም ! ቀልዶ-አደር ክበበው ገዳና
ሜሮን ጌትነት ፤
አበበ ተካ ፤

ይህን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ በሁሉም ዌብ- ሳይቶች ላይ ማለት ይቻላል ፣ የወጣ አንድ የአድናቆት ፅሁፍ ነው ። ጽሁፉ አንዲት ገጣሚትን ለማድነቅ የተፃፈ ነው ። የፅሁፉ ርእስ “ሐገሬ ፤ ሕዝቤ ፤ ክብሬ ” የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛ እንዲህ ተተርጉሟል ፤ “My Country, My People, My Honor” :: ይህ የአድናቆት ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ፤ ሚሮን ጌትነት በምትባል ኢትዮጵያዊት ዘመናዊ የፊልም ተዋናይ ችሎታና
በግጥሙ ታክኮ ለሃገሯ ያላት ልዩ ፍቅር ላይ ነው ።
ፅሁፉ ገና ሲጀምር ነው “The poet-artist with an “unconquerable soul?” በማለት ተዋናዩዋን ማንቆለጳጰስ የሚጀምረው ። ፀሃፊዋና አድናቂዋ ደግሞ በእንግሊዝኛ መፃፍ የሚቀናቸው አል ማርያም ናቸው ። እናም አል ማርያም ናቸው ከላይ እንደጠቀስኩት በሁሉም ዌብ ሳይቶች ላይ አድናቆታቸውን የናኙት ። የግል አድናቆታቸውን ትክክል ነው አይደለም የሚል ክርክር ወስጥ አልገባም ። ከዚህ በፊትም ይህቺው ሜሮን ጌትነት የተባለች ተዋናይ የተሳተፈችበትን “ድፍረት” የሚል ፊልምን ክሊፕ አይቼ በጣም ተደነቅኩባት ብለው አሞካሽተዋት ነበር ። ካለፈው ሙገሳቸው ላይ እንዲህ ሲሉ በመጨረሻ ባወጡት ፅሁፍ ላይም ቀንጭበው አስቀምጠዋል ፡፤

“… The beautiful young actress Meron Getnet sat stunned and speechless. She is visibly shocked and confused. She looked around in total disbelief trying to get someone to tell her what she has just heard is not true… In her seat, Meron clasps her palms in the traditional praying position as if to implore God’s intervention to save her and her country from such cruel public humiliation. An unidentified interviewer asks her how she feels. (How does one really feel when one’s heart is yanked out before the entire world!?) Meron is visibly brokenhearted. But she puts on a calm and brave face. She is struggling to hide her outrage and fury. She is fighting tears; but she does not breakdown though she is manifestly broken-hearted…”

እንዲህ ይተረጎማል ።

“…..ውቢቱ ወጣት ተዋናይ ሜሮን ጌትነት ፍዝዝ ብላ በዝምታ ተቀምጣለች ፤ እንደሚታየው ደንግጣለች ግራ ተጋብታለችም ። የሰማችውን ነገር ማመን ስላቃታት ዙሪያዋን እየቃኘች እውነት አይደለም የሚላት ሰው ፈለገች…… እንደተቀመጠች ሜሮን የእጆቿን መዳፎች በተለመደው የፀሎት አይነት ገጥማ፤ እግዚአብሄር እሷንና አገሯን ከህዝባዊ ውርደት እንዲያድናቸው ጣልቃ ገብነቱን እንዲያሳያት ተመኘች ። ያልታወቀ ቃለ መጠይቅ አድራጊ ምን እንደሚሰማት ጠየቃት ። (አንድ ሰው በመላው አለም ፊት ልቡ ቡጥርቅ ብሎ ሲወጣ ምን ሊሰማው ይችላል ? ) ሜሮን ልቧ እንደተሰበረ ይታያል ። ሆኖም ግን መረጋጋትና ጀግንነት ይታይባታል ። ብስጭትና ንዴቷን ለመደበቅ ትታገላለች። እንቧዋ ይተናነቃታል ፤ ግን እንባዋ አልወረደም ይሁንና ልቧ የተሰበረ መሆኑ በግልፅ ይታይባታል…….”
የትርጉሙ መጨረሻ ።

አል ማርያም ይህን ከላይ የሰጡትን ሙገሳ ያደረጉት የፊልሙን ቅንጫቢ ብቻ አይተው ነው። ሙሉውን ገና አላዩትም ከፅሁፍዎ እንደተረዳሁት ። እንዴት ነው በቅንጫቢው ብቻ ይህን ያህል ሙገሳ ያፈሰሱላት ። በፊልሙ ውስጥስ ከሷ ሌላ ተዋናዮች አልነበሩም ፤ የነሱስ ሚና ምን ነበር ? ብየ ልጠይቅ እገደዳለሁ ፤ መቼም አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብ ። እንደተመልካችና እንደ ውበቷ አድናቂ ቀደምብየ እንዳልኩት የተዋናይዋ የግል አድናቂዋ ከሆኑ የግል አመለካከትዎ ነውና ነውር የለበትም ። ፍቅር እንደ አፍቃሪው አይን ነው እንደሚባለው ፤ አድናቂም እንደዚያው ነው ። አድናቂና አፍቃሪ አለምንና ህይወትን እንደሚያይበት መነፅርም ይለያያል ።
“ድፍረት” የሚለውን ፊልም ወያኔ/ኢሕዲጎች እንዳይታይ ከለከሉ ። ይህ ዘረኛ አገዛዝ ይህን አደረገ ያን አደረገ ሲሉ የተቹት ግን አልገባኝም ። ፊልሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊታይ ከነበረበት ቦታ በፖሊሶች መከልከሉ እሙን ነው ። የፊልሙ ዳይሬክተር ዘረሰናይ መሃሪ እንደተናገረው በፍርድ ቤት ፊልሙ ክስ አለበት ተብለን ነው እንዳይታይ የተደረገው ሲል በጊዜው ለገባው ታዳሚ ገልጿል ። ዘረሰናይን ለሚያውቀው ደሞ ከማንም በላይ ለወያኔው ስርአት የተሻለ ቀረቤታ አለው ። እኔ እዚህ ላይ አል ማርያም ወያኒያዊውን አገዛዝ አይተቹ አይንቀፉ የሚል ፍላጎት የለኝም ።
“ድፍረት” ፊልም ግን በታገደ ጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲታይ ተፈቅዶ እየተየ ነው ። የፊልሙ ይዘትም ከወያኔ ስርአት ጋር ፖለቲካዊም ሆነ ማህበራዊ ተቃርኖ የለውም ። ወያኔ ለምን ሲል ያግደዋል ? የጠለፋ ጋብቻ ከወያኔያዊው ስርአት በፊትም ነበረ ፤ አሁንም አልፎ አልፎ ይኖራል ብዬ እገምታለሁ ። ይህው ሰሞኑን የሰማነው በታዳጊዋ በሃና ላላንጎ ላይ የተፈፀመ የደቦ አስገድዶ ድፍረት አንዱ ማሳያ ነው ። “ድፍረት” የሚለው ፊልም በራሱ እንዲያውም አገራችን ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ረገድ በጎ አስተወኦ አለው ብዬ አላምንም ። ይህ ራሱን የቻለ ሌላ ርእስ ስለሆነ በሌላ ጊዜ ልመለስበት እችላለሁ ።

አሁን ተመልሰን ወደ ተዋናይቷ ሜሮን ጌትነት እንምጣ ። የተዋናይነት ብቃቷንም ሆነ ገጣሚነቷ ላይ ዛሬ ልተች አልፈልግም ፤ የራሴ አስተያየት ቢኖረኝም ። አል ማርያም ሆይ የሚያደንቋትን የሜሮንን ግጥም እንደገና ያዳምጡና ወደራስዎ እንዲመለከቱ በዚህ አጋጣሚ ጋብዤዎታለሁ ።
“….መቼም የአሳ ዝላይ መልሶ ከውሃው ነው እመጣለሁ ዞሬ ፣ ስሜን ቀያይሬ ፣
ያኔ ይቀበለኛል ፤ ፍቅር ያጠግበኛል ህዝቤ ፤ አገሬ ፤ ክብሬ ፤”.. ….. ይላል አንዱ የገጣሚዋ ስንኝ ። አቶ አለማየሁ ገ/ማርያም የሚለው ስምዎን አል ማርያም ካሉት ጋር አይገጥም ይሆን ይህ ስንኝ ።
በተረፈ ሜሮን ጌትነት በወያኔው ቴሌቪዥን ላይ የወያኒው የልማት ፕሮግራም ውድድር አዘጋጅነቷንና አቅራቢነቷን ነው እኛ የምናውቀው ። “The poet-artist with an “unconquerable soul”? የሚለው ሙገሳዎ አለቦታው የገባ ነው ብየ እከራከርዎታለሁ ፤ የሜሮን ጌትነት ነፍሷ በወያኔ/ኢሓዲጎችconquer ከተደረገ ከረመ። እንዲያውም ሰሞኑን አሶሳ ወስጥ እየተደረገ ባለው የወያኔ ብሄር ብሄረሰቦች በአል ላይ ይመልከቷት፤ የህገ/መንግስቱ አወዳሽና ቀዳሽ አስተዋዋቂ ናት ። ይህ ከልክ ያለፈ ሙገሳዎ፤ ይህን እያወቁ ከሆነ እታዘብዎታለሁ ፤ ካላወቁ ደግሞ ይቅርታ አደርጋለሁ ። ወይም የፅሁፍዎ አቢይ አላማ ሜሮን ጌትነትን የማስተዋወቅ የPR ስራ ከሆነ ደግሞ ከጋራ አገራችን ፍቅርና ደህንነትና ጋር አይለውሱብኝ ። ኢትዮጵያንና ሚሮንን አንድ ላይ ሳይለውሱ ኢትዮጵያን ለቀቅ አድርገው ሜሮንን ጠበቅ ያድርጉ ። እዚህ ላይ እንዲታውቅልኝ የምፈልገው ነገር አለ ። ሜሮን ከወያኔ/ኢሕአዲግ ጋር ሰራች አልሰራች የራሷ ምርጫ ነው ፤ ስሪ ወይም አትስሪ ብዬ ልጫናት መብቱም ሆነ አቅሙ የለኝም ። አል ማርያም ሆይ ፤ እኔ የምመክረዎ ፤ መስታወት ራሱን አያይምና ዘውር ብለው እንደገና ያሞገሱላትን ግጥም “….ህዝቤ ፤ አገሬ ፤ ክብሬ …” የሚለውን ከራስዎ ጋር አያይዘው እንዲመለከቱ ነው ። ለዛሬው በሜሮን ጌትነት ላይ በዚሁ አበቃለሁ ። አስፈላጊ ሆኖ ካገኘሁት ደግሞ በግጥሙም ሆነ በተዋናይነት ብቃቷ ላይ እመለስበታለሁ ። ከዚያው ከሜሮን ጌትነት የግጥም ንባብ ላይ ለወደፊቱ ፅሁፌ ታግዘኝ ዘንድ አንድ ስንኝ ጥዬ ልለፍ ።

“……እድሜህን ቀርጥፈህ ብትሆን ባለ ዲግሪ ፣ ማስትሬት ዶክትሬት ብትደክም ብትለፋ ፤
እውነቱን ልንገርህ በሃገሬ ሂሳብ ፤ ከውጪ የመጣ የሶስት ወር ኮርስ ነው ሚዛን የሚደፋ ፡…….”

…………………………………………………….

ውድ አንባቢዬ ሆይ እንግዲህ ይህን አጋጣሚ አግኝቻለሁና አንዳንድ ተዋንያንና ድምፃውያን ላይ በየዌብ-ሳይቱ ተለጥፈው ካገኘኋቸው ዜናዎችና እኒም ከታዘብኳቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ላጋራችሁ ።
ከጥቂት ወራት በፊት ነው አበበ ተካ የሚባል ነዋሪነቱን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገ ድምፃዊ ላይ “አበበ ተካ ለሴት ሲል አገሩን የከዳ ” በሚል ርእስ አንድ ዜና በተወሰኑ ዌብ-ሳይቶች ላይ ተሰራጭቶ ያየሁት ። ይህ አበበ ተካ የሚባል ድምፃዊ የምን አገር ዜጋ አግብቶ ነው ሙዚቃ ያስተወችው ? የሚል ጥርጣሬ ነው በውስጤ ያደረው ። ምክንያቱም በአበበ ተካና በአገሩ መካከል ያለውን ግንኙነት ፤( በአድናቂዎቹና በሱ መካከል እንዳለ ግንኙነት አድርጌ በመገመት) አበበ ተካም ሆነ ባለቤቱ ትዳራቸውን የሚወዱ ባልና ሚስት አድርጌ ገምቼም ነበር ። ለሚወዳት ባለቤቱ ሲል አንድ ያለችውን ሙያ ትቶ በፍቅር ተሰብስቦ የሚኖር ግለሰብ አድርጌ ገምቼውም ነበር ። ህይ ዜና በወጣ በጥቂት ወራት ውስጥ አበበ ተካን ባለቤቱ አስገድዶ ደፈረኝ ብላ ከሰሰችው የሚል ሌላ ዜና ደግሞ በነዚሁ ዌብ-ሳይቶች ላይ ብቅ አለ ። ምንድነው ነገሩ ! ያቺ ስሙ የጠፋላት ሚስቱ ነች ወይስ ስለሌላ አበበ ተካነው የምሰማው እያልኩ ሳስብ ፡ የአስገድዶ ደፈረኝ ክስ ተነስቶለት ልጆቹን የማየት እድል እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቀ ተባለ ። ከፍርድ ቤት ሲወጣ ፤ በዩ-ቲዩብ ላይ አጥር ያለች ቃለ መጠይቅ ቢጤ ሰጥቶ ስለነበር ያችኑ ሳዳምጥ አበበ ከባለቤቱ ጋር የነበረው አለመግባባት ስር የሰደደ እንደነበር በግልፅ ይታይ ነበር ፤ የወራት ሳይሆን አመታት የተቆጠሩበት አለመግባባትም ነበር ። ስለዚህ ከወራት በፊት አገሩን የከዳ ሲል የተጻፈው ዜና ከንቱና ባዶ ፈጠራ ሆኖ አገኘሁት ። እንግዲህ ጉዳዩ የቤተስብ ቢሆንም አንዴ አደባባይ ወጥቷል ፤ በዚህ ላይ አበበ ተካ Public Figure ታዋቂ ግለ-ሰብ ስለሆነ ነው እንጂ ብዙ አበሻ እሱን ከገጠመው በባሰ ሁኔታ ትዳሩ ተፈቷል ፤ መፋታት አዲስ አይደለም ለማለት ነው ። ይህንና ግን ባለቤቱ እንዲህ አደረገችው እንዲህ በደለችው እየተባለ ነው ወሬው የሚናፈሰው ።ስለዚህ የአንድ ወገን የአበበ ተካን ብሶት ብቻ ከመስማት የባለቤቱን ብሶትም መጠየቅ ተገቢ ነው። አለዚያ ለፍርድ አይመችም ።

……………………………………..

ሌላው ትዝብቴ ደግሞ ቀልዶ-አደሩን ክበበው ገዳን ይመለከታል ። ክበበው ገዳ ከኢትዮጵያ ቀልዶ-አደሮች ውስጥ ቁንጮ ነው ብየ ብናገር ማጋነን አይሆንም ። የቀልድ ስራዎቹ ላይ እንደማንኛው ሰው ችግሮች ሊታዩበት ይችላሉ ።
ተመልካችም በቀልደኛው ንግግር እየሳቀ ሲሰደብ እንኳን መሰደቡ አይገባውም ። ወይም እየገባው ያው የአበሻ ባህሪይ ሆኖበት ዝም ብሎ ያልፈዋል ። የአበሻ ባህሪይ ያልኩት አንድ የምናደንቀው ሰው ላይ ዛሬ የምናየውን ስህተት በይሉኝታ ፤ ወይም ይቅርታ እንድናደርግ ሳንጠየቅ በይቅርታ ፤ እናሳልፈውና ነገ በላያችን ላይ ሲጨፍርብን ፀጉራችንን መነጨት መጀመራችንን ነው ።
ዛሬ በሰለጠነው ዘመን ማንኛውም ሙያ በትምህርት ሲደገፍ ጥቀሜታ አለው ። ሁሉም የቁም ቀልዶ-አደር Stand-Up Comedian በአሜሪካም ቢሆን እንኳ ፤ የመድረክ ላይ ትምህርት አለው ማለት አይደለም ፤ ሆኖም ግን በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎች ያማክሩታል ፤ ቀልዶቹን ይመርጡለታል ፡ቃላቱን ይቀርፁለተል ፤ መድረኩን ይመሩለታል ፤ ሰአቱን ያቅቡለታል ። በኛ ሃገር ግን ከፈረንጆቹ በተለይ ከአሜሪካ ሁሉንም ነገር እየኮረጅን መሟላት ከሚገባቸው ሁነታዎች አንዱን እንኳ ሳናሟላ የምንገባበት ሙያ ላይ ብዙ ስህተቶች ሲፈጠሩ እንመለከታለን ። ከነዚህ ሙያዎች ውስጥ የቁም-ቀልድ Stand-up comedy ሙያ አንዱ ነው ።

ሌላ ሌላውን እንተወውና ከአስኮራጃችን አሜሪካን ሃገር አንድ የቁም ቀልዶ-አደር ፤ ቢያንስ ፕሮግራሙን የሚመራለት ዳይሬክተር ብሎም አማካሪ ይፈልጋል ። እንደፈለገና አፉ እንዳመጣለት ያሻውን አይዘላብድም ። በተለይ ለተመልካቹ ያለው ክብር ከፍተኛ ነው ። ምክንያቱም ኑሮው የተመሰረተው እንጀራው የሚጋገረው በተመልካቹ ላይ ነውና ። ኒውዮርክ ሾው ላይ የነበረውን ተመልካቹን አትላንታ ሄዶ አይቀልድበትም ። በሌሎቹ የአውሮፓ አገሮችም እንደዚሁ ነው ።
ቀልዶ-አደር ክበበው ገዳ የታዳሚውን የልብ ትርታ ማዳመጥና አድናቂዎቹ መኖሪያቸው ኢትዮጵያም ይሁን አሜሪካ ፤ ካናዳም ይሁን ቻይና ማክበር ይገባዋል ። እንደ አለቅላቂ ሴት አንዱ አገር ሲሄድ ቀደም ብሎ የሄደበትን ከተማ ማንቋሸሽ ወይም መዝለፍ አይገባውም ። ይህን እንድል ያነሳሳኝ ክበበው ገዳ ከተወሰኑ አመታት በፊት ወደ ኮሎምበስ ኦሃዮ ብቅ ብሎ ነበር ። ከተመልካቹ መሃል ቀልዱ ያላስደሰተው አንድ ግለ-ሰብ ጋርም መጣላቱን ሰምቻለሁ ። ከዚያ ወደዋሽንግቶን ዲሲ ሲመለስ መድረክ ላይ ወጥቶ “ ኢትዮጵያ እያለሁ አገሬ መራቧን እሰማ ነበር ። አሁን ግን ኦሃዮ ደርሼ ከመጣሁ በኋላ አገሬ ለምን እንደተራበች ገባኝ ፤ ለካ ገበሬው ሁሉ ተሰብስቦ ኦሃዮ ገብቶ ነው ሲል ቀለደ ።” ዋሺንግቶን ዲሲም ኦሃዮ በብዛት የወልቃይት ፀገዴ ተወላጆች እንደሚኖሩበት በማውቅ ለቀልዶ-አደሩ ክበበው ገዳ ሳቀለት አስካካለት ።
የአንተን የቀልዶ-አደሩን ሆድ ለመሙላት ውልቃይት ፀገዴ ማረስ ነበረበት ? ቀልዶ-አደሩ ወንድሜ አገራችን ረሃብተኛ መባሏን ከሰማህና ገበሬው ሁሉ ኦሃዮ መመጣቱን ከተገነዘብክ ለምን ራስህ ገብተህ አታርስም ነበር ። በዚህ አጋጣሚ አገር የምትለማው በአርሶ አደሮች እንጂ በቀልዶ አደሮች እንዳልሆነ ልገልፅልህ እወዳለሁ ። ታዲያ ይህን አባባልህን ሳትወቀስበት በዋሽንግተን ተስቆልህ አለፍክ ።
ውድ አንባቢዬ ፤ አሁን በቅርቡ ደግሞ ይባስ ብሎ አውሮፓ አንድ የፋሽን ትርኢት ላይ እንደሟሟያ ሆኖ ቀርቦ ነበር ክበበው ገዳ ። የአዲስ አበባ ጆክ ነው ብሎ አንድ ቀልድ አወራ ። “ጎስቋላዎቹና ማዲያታሞቹ ሴቶች ሁሉ አሜሪካና ካናዳ ነው ያሉት” ሲል ቀለደ ። ጆኩ እንደጆክ ተወርቶ በዚያ ቢያበቃ መልካም ነበር ። “ለነገሩ እውነት ነው እኔ ዘወር ዘውር ብየ አይቻለሁ” ማንከሽከሻ ብቻ ናቸው ሲል አሾፈ ። ይህን አባባሉን ለመመልከት የሚቀጥለውን ሊንክ ይመልከቱhttps://www.youtube.com/watch?v=t0-qU60ik3E ።ወይም ክበበው ገዳ ብለው ጉግል ያድርጉና “ ቆንጆዋን እንካ ግን አትንካ ” የሚለውን ርዕስ ይጫኑ ።
ቀደም ብየ እንዳልኩት እንደ አለቅላቂ የመንደር ሴት የኦሃዮን ዲሲ የአሜሪካና ካናዳን አውሮፓ እየወሰደ ያለቀልቃል ። ቀልዶ አደሩ ወንድሜ ክበበው! እነዚህ ማንከሽከሻ ፤ ጎስቋላ፤ ያልካቸው የአሜሪካና የካናዳ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ሚስቶቻችንና እናቶቻችን ናቸው ። አዎ ማዲያታም ሊሆኑን ይችላሉ ሊጎሳቆሉም ይችላሉ ። አንተ ኢትዮጵያ ወስጥ ያውም አዲስ አበባ ብቻ እንደምታውቃቸው ፤ ምሽት-አደር ሴቶች ላይቆነጁ ይችላሉ ። ሰርተው ጥረው ግረው በላባቸው በወዛቸው የሚያድሩ ናቸውና ። በዚህ በፈጣኑ አለም ውስጥ ልጆች አሳድገው አስተምረው ትዳራቸውን ጠብቀው ከዚያም አልፈው ኢትዮጵያ ወስጥ ቤተ-ሰብና ዘመድ ረድተው የሚኖሩ ሴቶች ናቸው ፤ ቢጎሳቆሉ ይነሳቸው ፤ ማዲያት ቢወጣባቸው ይብዛባቸው ።
የአንተ የአዲስ አበባ ቆነጃጅት ሴቶች ለፀጉራቸው ሶስት ሰአት ፤ ለጥፍራቸው ሁለት ሰአት ለቅንድባቸው ሌላ ሁለት ሰአት ለማጥፋት በቂ ጊዜ ያላቸው ናቸው ፤ ምነው አይቆነጁ ። ስለዚህ ስትቀልድም የምትናገረውን እወቅ ። በአንድ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ስትቀልድም እዚያው እፊታቸው ላይ ቀልድ ። አንዱን ካንዱ አታምታታ ። አንድ እውነታ ግን ልንገርህ ። ኦሃዮም ካናዳም ሆነ አሜሪካ አንተ መጣህባቸው እንጂ እነሱ አንተን ብለው አልመጡብህም ። ኦሃዮም ካናዳም አሜሪካም ያላንተ ኖረዋል መኖርም ይችላሉ ። አስር አመት ቀልደህ ከአዲስ አበባ ቆነጃጅት ሴቶች የማታገኘውን ገንዘብም በአንድ ትርኢት የምታገኘው ከነዚህ ማንከሽከሻዎች ፤ ማዲያታሞችና ባሎቻቸው ነው ። ዘወር ዘወር ብየ አለምን አይቻለሁ ብለሀናልና እግርህ ተፍታቶ ክንፍ አውጥተህ ዘወር ዘወር ያልከው ከነዚሁ ከማዲታሞቹ በተገኘ ገንዘብ እንደሆነ ልትረዳው ይገባል ። ይህ እውነት አይደለም እንዴ ወንድሜ? መቼም ቀልደኛ ነህና ፤ አይደለም ከአባቴ በወረስኩት ገንዘብ ነው ብለህ እንዳታስቀኝ ።

ውድ አንባቢየ ለዛሬው በዚሁ ላብቃ !

ከአንበሳው ይብራ

እ.ኤ.አ ዲሴምበር 2 2014


ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
እነሆ ከተሚማ ጋር የጂማን ምድር “ሽርርርር” ልንልበት ነው፡፡ ሆኖም “ተሚማ” የትናንትናው ሙገሳ አንሶኛል ብላለች፡፡ “የነየታችሁት ሐጃ ሞልቶላችሁ በደስታ እንድትፍለቀለቁ ካሻችሁ ሙገሳውን ጨመርመር አድርጉልኝ” ትላለች፡፡ ታዲያ እኛም አላንገራገርንም፡፡ “ምን ገዶን! አንቺ ሰኚ ሞቲ! ሙገሳ በየዓይነቱ ይኸውልሽ” ብለን በድጋሚ መወድሳችንን ልንደረድርላት ተዘጋጅተናል፡፡ እንዲያውም ሙገሳችንን የምንጀምረው እሸትነቷን በማወደስ ነው፡፡ ለመወድሳችን የመረጥነውም የሟቹን የዮሴፍ ገመቹን ዜማ ነው፡፡ አዝማቹ እንዲህ ይሄዳል፡፡
Naale naale naalen irgixiidhaa
Maddiin furnoo hidhiin buskutiidha.
በአማርኛ ሲተረጎም እንዲህ ይሆናል (አማርኛው አዛማጅ ትርጉም በመሆኑ የኦሮምኛውን ያህል አስደሳች ላይሆን ይችላል)፡፡
ናሌ ናሌ ናሌ እርግጥ ነው፡፡
ጉንጯ ፉርኖ ከንፈሯም ብስኩት ነው፡፡
ፈገግ ያሰኛል አይደል? (ቂቂቂቂቂ….)፡፡ አዎን! በኦሮምኛ እንዲህ እያሉ መግጠምም ይቻላል፡፡ መወድሱ ከወገብ በታች ያለውን የሰውነት ክፍል አይንካ እንጂ ከወገብ በላይ ያለውን ውበት በሚያውቁት መንገድ ማወደስ ይቻላል፡፡ ከወገብ በታች ካለው የሰውነት ክፍልም ተረከዝን ማሞገስ ይቻላል፡፡ ከዚያ በላይ ያለውን ክፍል ግን መጥቀስ አይፈቀድም፡፡
ዮሴፍ በግጥሙ ውስጥ “ናሌ ናሌ..” የሚል ሐረግ ደጋግሟል አይደል? ቃሉ እንዲህ ሲደጋገም ትርኪ ምርኪ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ያለቦታው የገባ አይምሰላችሁ፡፡ ትናንትና የጠቀስነው “አህለን አህላ” ነው ተቀይሮ እንዲህ የሆነው፡፡ ዘፋኙ ዘፈኑን የሚጀምረው በዚህ ሐረግ ነው፡፡ ከዚያም እርሱ የዘፈኑን ግጥሞች እያከታተለ ሲጠራ ተቀባዮቹ “ናሌ ናሌ…” እያሉ ጨዋታውን ያደምቁለታል፡፡
*****
አሁን ደግሞ የአማርኛ ተናጋሪዎችን በመወከል ተሚማን እናሞግሳታለን፡፡ ለሙገሳችን የመረጥነውም የነዋይ ደበበን “ከጊቤ ባሻገር”ን ነው፡፡
ከጊቤ ባሻገር አለችኧረ አንዲት ሰው
በፍቅር በናፍቆትልቤን የምትወዘውዘው
አቦል ጀባብላኝ ቡናዋን ብቀምሰው፣
እግሬ ወደጅማ ሱስ አመላለሰው
እንግባ አይመሽምወይ
ቤትሽ ጅማ ነውወይ ?
ነዋይ እውነታውን ነው ቁጭ ያደረገው፡፡ “ተሚማ” ቄጤማ ጎዝጉዛ፣ ቡናውን አፍልታ ሐድራውን ሞቅ ሞቅ ስታደርገው ፍቅር የምትፈትል ነው የምትመስለው፡፡ ከሐድራው የሚፈልቀው ሙሐባ የቡና ሱስ ብቻ ሳይሆን የፍቅር ሱስን ያስይዛል፡፡
ደግሞ አንድ ነገር!! በሌሎች አካባቢዎች እንግዳን በእቅፍ አበባ ነው የሚቀበሉት አይደል?… የጅማዋ ተሚማ ደግሞ ለዚያራ የመጣውን ሰው በቡና ቀንበጥ ነው የምትቀበለው፡፡ እንዲህ ያለች ጥበበኛ አርቲስት ናት ተሚማ!
*****
ኧረ ለመሆኑ እኛ እንዲህ ያሞገስናት “ተሚማ” በርግጥ ፍቅርን ታውቀዋለች?… ምንም አትጠራጠሩ!! ተሚማ ፍቅርን ከማወቅም አልፋ ለፍቅር የምትንበረከክ ልበ-ንጹህ ናት፡፡ ከልቧ ለምታፈቅረው ሰው ፍቅሯን የምትገልጸው ደግሞ በጣም ኪነታዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ ይህም “ሂዲ ደርቡ” (Hiddii darbuu) ይባላል:: “ሂዲ ደርቡ” የኦሮሞ ሴቶች ለፍቅር መረታታቸውን የሚገልጹበት ወግ ነው፡፡ ይህም በአማርኛ “ሎሚ መወርወር” ከምንለው ወግ ጋር ይቀራረባል፡፡ ልዩነቱ ግን ተሚማ ፍቅሯን በምትገልጽበት ጊዜ የምትወረውረው ነገር “ሎሚ” ሳይሆን “እምቧይ” ነው፡፡ ሁለተኛው ልዩነት ደግሞ “ሂዲ ደርቡ” እንደ “ሎሚ መወርወር” በጥምቀት ብቻ የሚፈጸም አለመሆኑ ነው፡፡ ሶስተኛው ልዩነት ተሚማ እምቧዩን ሌሎች ሰዎች እያዩዋት የምትወረውር አለመሆኑ ነው፡፡ Safuu የሚባለው የኦሮሞ የስነ-ምግባር ደንብ ይህንን እንዳታደርግ ያግዳታል፡፡ በመሆኑም ተሚማ የወደደችውን ሰው በእምቧይ የምትመታው ሰው በሌለበት ስፍራ ነው (በነገራችን ላይ አንዲት ሴት ወንዱን መውደዷን የምትገልጽበት ይህ የ“ሂዲ ደርቡ” ወግ በሀረርጌና በአርሲም ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በአርሲና በሀረርጌ “ሂዲ ደርቡ” አይባልም፡፡ እዚያ ዘንድ “አሴና” ወይንም “አሼና” እየተባለ ነው የሚጠራው፤ በተጨማሪም የሀረርጌና የአርሲ ኮረዶች ፍቅራቸውን የሚገልጹት በብዙ እምቧዮች ነው፤ ወንድዬው ጠዋት ከቤቱ ሊወጣ ሲል ሴቲቷ በአጥር ላይ ተንጠልጥላ ብዙ እምቧዮችን ከፊቱ ትበትንና ወደ ቤቷ ትነጉዳለች፤ ወንድዬውምም ጉዳዩን ለወላጆቹ ይነግርና ልጅቷን ያገባታል)፡፡

በ“ሂዲ ደርቡ” እና “በሎሚ መወርወር” መካከል ያለው ትልቁ ልዩነት ግን ከላይ ከተገለጹት ውስጥ የለም፡፡ ትልቁ ልዩነት ወዲህ ነው ያለው፡፡ እንደሚታወቀው “ሎሚ መወርወር” በወንድ የሚፈጸም ወግ ነው፡፡ ሴቲቷ ሎሚውን አትወርውርም (ምንም እንኳ ያቺ ጭራ ቀረሽ የሚሏት ዘነበች ታደሰ “ሎሚ ብወረውር” እያለች ብትዘፍንም ሴቶች ሎሚ ሲወረውሩ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም)፡፡ የጅማዋ ተሚማ የምትፈጽመው “ሂዲ ደርቡ” ግን በራሷ የሚፈጸም እንጂ በወንድ የሚፈጸምላት አይደለም፡፡ ወንድዬው ፍቅሩን የሚገልጸው ነጠላ ገዝቶ በማልበስ ነው እንጂ እምቧይ በመወርወር አይደለም፡፡
ታዲያ ተሚማ የምትወደውን ሰው በእምቧይ የመምታቷን ጀብድ ስትገለጸው ሰምታችኋት ታውቃላችሁ?… ካላወቃችሁ “ፌይሩዝ” የተባለች ወጣት ያዜመችውን በትንሹ ቀንጨብ አድርገን እናሳያችሁ (ከፌይሩዝ የተዋስነው አባባል ለተሚማም ይሆናል)፡፡
Akkasumaan hiddii darbannaanii (ለዚያው ነው እምቧይ መወርወሬ)
Sijaaladhe giddiin naqbnaanii (ግድ ብሎኝ ነው አንተን አፍቅሬ)
ተሚማ! ጉብሊቷ ወጣት የጅማ!! ስትወደን እንዲህ ነው የምትለን፡፡ ለፍቅር መረታቷን እንዲህ ነው የምታስረግጠው፡፡ ፍቅሯ ሲባባስባት ደግሞ በጣፋጭ አንደበቷ እየዘማመረች ልባችንን ልታፈርሰው ትችላለች፡፡ እንዲያውም ታዋቂዋ የጅማ ተወላጅ አርቲስት ሲቲና አባዱላ “ቡርቱካኒ” ብላ ያዜመችው ዝነኛ ዘፈን ተሚማ በፍቅር በምትጨነቅበት ጊዜ የምትቀኘውን እንጉርጉሮ ሊወክል ይችላል፡፡ እስቲ ደግሞ የሲቲናን ዘፈን እንዋስና የተሚማን የፍቅር ብሶት እንግለጽ፡፡
Burtukaani mitii hadhaadha miti hadahaadha (ብርቱካን አይደለም ይህስ መራራ ነው)
Kun jaalalaa miti maraachaadha (ፍቅርስ አይደለም ይህስ እብደት ነው)
እጥር ምጥን ቅልብጭ ያለች ግጥም፡፡ የፍቅር ፍላጻ ልቧን ወግቶ ህመሙ በሚያስጨንቃት ጊዜ ነው እንዲህ ብላ የምታዜመው ተሚማ! ያቺ ውብ ቄጤማ! የአባጅፋር ልጅ የጅማ!!
*****
ብራቮ! ብራቮ! ተሚማ ሙገሳችንንና መወድሳችን ከልብ የፈለቀ መሆኑ ስለገባት በጅማ ምድር ልታንሸራሽረን የገባችውን ቃል በድጋሚ አድሳለች፡፡ በመሆኑም ጅማን ልናስሳት ነው፡፡ በአሰሳችን ድብርት ቢገጥመን ተሚማ በጣፋጭ አንደበቷ “Hin mukaayinaa” እያለች  ታባርረዋለች (Hin mukaayinaa ብዬ ስጽፍ ሳቅኩኝ….ቂቂቂቂቂቂ… ቢሆንም በጣም ደስ እያለኝ ነው የምስቀው… እንደ ሐላዋ በሚጣፍጥ አባባል ድብርትን ማባረር ይሏል ይሄ ነው… Hin mukaayinaa)
“Hin mukaayinaa” ምን ዐይነት ትርጉም እንዳለው አውቃችኋልን?…. “እንጨት አትሁኑ” ማለት እኮ ነው፡፡ ከሩቅ ሀገር ሊገበኘን የመጣ ሰው እንግድነት እንዳይሰማው ለማድረግ ከፈለግን “አትቦዝን” እንለዋን አይደል?… አዎን! በፈረንጅኛውም “Just feel at home” ለማለት ይቻላል፡፡ የጅማዋ ተሚማ ግን “Hin mukaayin” ማለትም “እንጨት አትሁን” ነው የምትለው፡፡ ተሚማ የምትጠቀምበት Hin mukaayinaa ውስጠ ወይራ ፍቺን ያዘለ ሐረግ ነው፡፡ “ማዕና”ውም እንዲህ ሊሆን ይችላል፡፡
   እንግድነት የሚሰማው ሰው ዝምታ ያበዛል፡፡ ከሰዎች መሃል የወጣ ይመስለዋል፡፡ ይህም በመንገድ ላይ ለብቻው ከቆመ ዛፍ ወይንም የኤሌክትሪክ እንጨት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ እርሱን የተጫጫነው ስሜትም በኛ ላይ የድብርት መአት ሊጠራብን ይችላል፡፡ እንግዲህ ሰውዬው እንግድነት ተሰምቶት እንደ እንጨት ድርቅ ብሎ ድብርት እንዳይጠራብን ለማድረግ በሚል ነው ተሚማ Hin mukaayin” የምትለው፡፡ ደስ ሲል!!
Hin mukaayinaa” እንዳለችው ተሚማ እኛም “ሂንሙካይና ጋ ማሎ” እንላችኋለን!!
(ይቀጥላል)
—–
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 22/2007
ሀረር… ምስራቅ ኢትዮጵያ
—–
The writer, Afendi Muteki, is a researcher and author of ethnography and history with special focus on Eastern Ethiopia.  You may like his facebook page and stay in touch with his articles and analysis: Just click the following link to go to his page.

ዛሬ ከስዓት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀብታሙ አያሌውን ቂሊንጦ ወደሚገኘው ወህኒ ቤት ሄጄ ለማየት ከባለቤቱ ቤቲ ጋር ቂሊንጡ ተገኝቼ ነበር፡፡ እግረ መንገዴንም ባለፈው ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ ሄጄ የጠፋብኝን ስዓት ካገኘሁት የሚል ተሰፋ ነበር፡፡ የሰዓቱ ነገር … ውሃ የበላው መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ አርድቻችሁ ልለፍ ብዬ ነው፡፡ ነገሩ ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ሳይሆን የተረሳ ንብረትም ሆነ በፖሊስ እጅ ድንገት […]

ምንም እንኳን የፖለቲካ ምህዳሩ የጠበበ ብቻ ሳይሆን የተዘጋ ቢሆንም፣ የአንድነት ፓርቲ በምርጫ 2007 እንደሚወዳደር በይፋ ለሕዝብ ማሳወቁ ይታወቃል። አንዳንድ ወገኖች “አንድነት እንዴት ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ ይገባል ?” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። እነዚህ ወገኖች ይሄን ጥያቄ ለምን እንዳቀረቡ ግልጽ ቢሆንም፣ ወድ ምርጫው አለመግባቱ ደግሞ ሊያስከትል የሚችለው የራሱ ጉዳት እንደሚኖር የመረዳት ችግር ያለ ይመስላል። በተለይም በፖለኢትካው […]

የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) አባል ወጣት ሽሻይ አዘናው ለ24 ቀን መሰወሩ ተያይዞ በ26/02/2007ዓ.ም ከሚሰራበት የስራ ቦታው ታፍኖ በመቐለ ኮሙሽን ፖሊስ ክልል ትግራይ ልዩና ፅኑ እስርቤት ታስሮ ህገ መንግስታዊን መብቱ በመከልከል ጠበቃ እንዳያአማክረው ምግብ እንዳይገባለት ፡ ዘሞዶቹና ጓደኞቹ እንዳያዩት ተነፍጎት 12 ቀን ያህል በህቡእ ታሰሮበት ከነበረበት ተሰውሮ እስከ 18/03/2007ዓ.ም በጠቅላላ ለ24 ቀን በመሰወሩ መጀመርያ ከሰራ ቦታው […]

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል መንግስቱ የ2006 የጸጥታ አጠባበቅ ግምገማ በሚያደርግበት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመቀናጀት የደህንነት ስራ እየሰሩ ነው። አጠቃላይ ውይይቱን በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው ሚስጥራዊ የድምጽ መረጃ እንደሚያስረዳው በአዲስ አበባ በተቋቋመው መዋቅር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ መንግስት መኪና፣ ኮምፒዩተር፣ …

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትብብሩ ህዳር 27 እና 28 በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው የአንድ ቀንና ሌሊት የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ የተጀመረውን የሰው በሰው ቅስቀሳ እንዲደግፍ፣ የገንዘብ የሞራልና ቁሳቁስ ድጋፎችን እንዲያደርግ እንዲሁም ለትግሉ ይጠቅማል ያሉትን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቋል። ህዝቡ በዝግጅቱ ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር በመስቀል አደባባይ በሚኖረው ቆይታ የሚያስልጉት ቁሳቁሶች በተለይም ደረቅ ምግብና ውሃ …

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 ዓ.ም ወዲህ በተከሰተ አደጋ በክልሉ 18ሺ 994 የመኪና አደጋዎች ተከሰተዋል፡፡ በትራፊክ ሳምንት ውይይት ላይ እንደተገለፀው በአጠቃላይ በአምስት አመታት በተከሰተው አደጋ 6ሺ 668 ሰዎች ህይዋታቸውን አጠዋል፡፡ 6ሺህ 581 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ፤ 11 ሺ 781 ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው  994 ሚልዮን 626 ሺህ 866 …

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ አገሪቱ ከግል የገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋን ተከትሎ የኢትዮጵያን ብድር በበላይነት በሚያስተባብረው በጀርመን ትልቁ ባንክ አማካኝነት በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ተብሎአል። ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ ገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋ ብዙ ኢኮኖሚስቶችን እያነጋገረ ነው። ጠ/ሚኒስትሩ ከጀርመን ቻንስለር አንግላ መርክል ጋር እንደሚነጋገሩም ታውቋል። አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ማዳበሪያ ከሚያቀርብ …

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

በጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም የሚመራዉ ቡድን የጀርመንኗን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ የተለያዩ የጀርመን ባለሥልጣናትንና ባለሐብቶችን ለማነጋገር ቀጠሮ አለዉ።ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን፤ የኢትዮጵያ ወዳጆችና የሠብአዊ መብት ተሟጋቾች ባንፃሩ እዚያዉ በርሊን ዉስጥ ተቃዉሞ ሠልፍ ለማድረግ አቅደዋል።

በቱርክ የሶስት ቀናት ጉብኝትን ያደረጉት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ በጉብኝታቸዉ ማጠቃለያ በተደረገዉ የመሰናበቻ ዝግጅት ከኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ በርተለሜዎስ ጋር የሐዋርያዉን ቅዱስ አንድርያስ ዕለተ ሞት በልዩ መንፈሳዊ ሥነ-ስርዓት አስበዋል።

በሶስት የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የተዛመተዉ ኢቦላ 6000 ገደማ ሰው ገልዋል። ወደ 16 ሺህ ህዝብ ደሞ በተውሓሲው ተለክፎአል። የኢቦላ ወረርሺኝ ያደረሰዉ ቀዉስ ከቁጥጥር ዉጭ የሚወጣበት ደረጃ መድረሱ እየተነገረ ነዉ። የኤቦላ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገዉ ጥረትና ትብብር ጀርመን የምታደርገዉ ርዳታ ሳይዘገይ እየተነገረ ነዉ።

የዱሮ ወዳጄ ሰላምታዬ ይድረሽ። እንደምታውቂው ከተያየን ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሆኗል። እኔም ካገሬ ከወጣሁ 21 ዓመት አለፈኝ። በጤናና በምቾት እንደምትኖሪ እሰማለሁ። እግዚአብሄርም መንግስትም ጥሩውን ነገር ሁሉ አብዝቶ እንዲሰጥሽ ምኞቴ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጓደኝነት ከምቀርባቸውና ከማከብራቸው ስዎች ውስጥ አንቺ አንዷ እንደነበርሽ ራስሽም ብዙ ሰዎችም ያውቃሉ። ከጊዜ ብዛትና በስልጣንም ርቀት ምክንያት ጓደኝነቴን ብትረሽውም አልፈርድብሽም። እኔ ግን […]

የሶማልያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የአሸባብ ታጣቂዎች ኬንያ ዉስጥ ሰላሳ ስድስት ድንጋይ አዉጪዎችን ገደሉ። ታጣቂዎቹ በሰሜናዊ ምስራቅ ኬንያ ማንዴራ ከተማ አጠገብ ዛሬ ሲነጋጋ በከፈቱት ጥቃት የገደሏቸዉ አብዛኞቹ ሰዎች የቀን ሰራተኞችን ነበሩ።

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የኮምቦልቻ ከተማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በ07 ቀበሌ ልዩ ስሙ ትዩ አምባ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ላይ በቱርካውያን የባቡር መስመር ዝርጋታ ካምፓኒ የደረሰውን የአዝእርት ጭፍጨፋ በአካል በመሄድ የመስክ ግምገማና ምልከታ እንዲሁም ከአርሶ አደሮች ጋር ውይይት ማካሄዱን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ ፡፡ ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰው መረጃ መሰረት ህዳር 21 ቀን […]

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ ዕለታዊ መግለጫ

ዝግጅታችን ተጠናክሮ ቀጥሏል! እርስዎም ይዘጋጁ!
‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል የአንድ ወር መርሃ ግብር ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ስርዓቱ መርሃግብሮቻችን በማጨናገፍ ለነጻነት የምናደርገውን የትግል ጉዞ ለማደናቀፍ ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል፡፡ ሆኖም የነጻነት ትግሉ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል መሆኑን የተረዳው ትብብሩ ለገዥው ፓርቲ አፈና ሳይንበረከክ ስራውን ቀጥሏል፡፡ በተለይ ከመርሃ ግብሮቻችን መካከል ስርዓቱን ያስፈራውን የ24 ሰዓት የአደር ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅታችን አጠናክረን ቀጥለናል፡፡ ለዚህ የአዳር ሰልፍ የትብብሩ አባል ፓርቲዎች ሰው በሰው በመቀስቀስ፣ ወረቀት በመበተን እንዲሁም በየ ፓርቲዎቻችን ስም የታተሙ ቲሸርቶችን በመልበስ ህዝቡን እያነቃቃን እንገኛለን፡፡ ሰልፉ እስከሚደረግበት ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም ድረስም ዝግጅታችን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ይህን መርሃ ግብር ስንነድፍ ለነጻነት የሚከፈለው መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተንና የቀድሞ አባቶቻችን ካሳዩት ቆራጥነት ተምረን ነው፡፡ በዚህ ለቀጣይ የትግል ጉዞአችን ጭላንጭል ለምናይበት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን፡፡ በውጭም ሆነ አገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለነጻነት ለምናደርገው ጉዞ የጀመርነውን የሰው በሰው ቅስቀሳ በመደገፍ፣ በገንዘብ፣ በሞራልና በሌሎች ለመርሃ ግብሩና ለአጠቃላይ ትግሉ ይጠቅማል ባሉት መንገድ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ መርሃ ግብሩ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በሞራልና በተለያየ መንገድ መልዕክቶቻችን ለህዝብ እንዲደርሱ ድጋፍ ያደረጋችሁልን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ልባዊ ምስጋናችን ማቅረብ እንፈልጋለን፡፡ አሁንም ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ በመቀጠል ታሪካዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡

በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በኩል ለሰላማዊ ሰልፉ የሚያስፈልገው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ህዝቡ በዝግጅቱ ከሚያደርገው ድጋፍ ባሻገር በመስቀል አደባባይ በሚኖረን ቆይታ የሚያስልጉት ቁሳቁሶች በተለይም ደረቅ ምግብና ውሃ ከአሁኑ እንዲያዘጋጅ ማስታወስ እንፈልጋለን፡፡ ህዳር 27/28 2007 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚደረገው የ24 (አዳር) ሰልፍ ኢትዮጵያውያን ላይ የተጫነውን የፍርሃት ድባብ በመስበር ለነጻነት የምናደርገው ወሳኝ ጉዞ ጅማሬ በመሆኑ በሁሉም የማህረሰብ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ራሳቸውንና አገራቸውን ነጻ ለማውጣት የትግሉ አካል እንዲሆኑ ጥሪያችን እያቀርባለን፡፡

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

ህዳር 23/2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ


እኔና ባለቤቴ ልክ እንዳንቺ ሆነን ነበር፡፡ ነገራችን ሁሉ ችኮ ሆኖ፡፡ ያ ድሮ እንደ መልካም ሙዚቃ ጆሮሽን አዘንብለሽ የምትሰሚው የባልሽ ድምጽ ፍሬን እንደያዘ መኪና ድምጽ ሲሆንብሽ ይሰማሻል፡፡ ይናፍቅሽ የነበረው ድምጽ ሲደውል ሐሳብ ውስጥ ይጥልሻል፡፡ ደግሞ ምን ሊል ይሆን? ትያለሽ፡፡ ስልክ ከማንሳት ይልቅ ስልኩን ለመዝጋት ትቸኩያለሽ፡፡ ለመሆኑ ባል ማለት ምንድን ነው? ለእኔ ከባልሽ ጋር ብቻ የምታደርጊያቸው ነገሮች ስላሉ ነው፡፡ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትቀልጃቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምታወሪያቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትሠሪያቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትወስኛቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምትባልጊያቸው፣ ከእርሱ ጋር ብቻ የምታኮርፊያቸው፡፡

ለአንቺ ብቻ የሚቀጸሉ፣ለአንቺ ብቻ የሚውሉ፣ ለአንቺ ብቻ የሚነገሩ፣ ለአንቺ ብቻ የሚገለጡ፣ ለአንቺ ብቻ የሚደረጉ፣ ለአንቺ ብቻ የሚሰሙ የተለዩ ነገሮች ከሌሉ ምኑን ሚስት ሆንሺው፡፡ ባልሽ ደግ፣ ሩኅሩኅ፣ ትዕግሥተኛ፣ የማይሰክር፣ ገንዘብ የማያባክን፣ ታማኝ፣ መልከ ቀና  ቢሆን እጅግ የታደልሽ ትባያለሽ፡፡ ይኼ ሁሉ ግን መልካም ሰውነቱን እንጂ መልካም ባልነቱን አያሳይም፡፡ ደግ ሰው፣ ቆንጆ ሰው፣ ትጉኅ ሰው፣ ፍጹም ሰው ያሰኘዋል እንጂ ብቻውን መልካም ባል አያሰኘውም፡፡
መልካም ባል ለመሆን በመልካም ሰውነት ላይ ሊጨመሩ የሚገባቸው ሌሎች የባልነት ነገሮች አሉ፡፡ በመልካም ባል ውስጥ ሚስትነት፣ በመልካም ሚስት ውስጥ ደግሞ ባልነት መኖር አለባቸው፡፡ መልካም ባል ማለት ሚስት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚረዳ፣ ሚስትነት በውስጡ ያለው ባል ማለት ነው፡፡ መልካም ሚስትም እንዲሁ፡፡ መልካም ባል ማለት የሚስትን ስሜት፣ ልብና ኩላሊት ለማወቅ የሚችል ማለት ሳይሆን ሊረዳውና ሊሰማው የሚችል ማለት ነው፡፡
እንዲህ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቼ ሳስበው ለካ እኛ ቤት ውስጥ የነበሩት ባልና ሚስት ጠፍተው አንድ ወንድና አንዲት ሴት ቀርተዋል፡፡ አብረው የሚኖሩ፣ አብረው የሚሠሩ፣ አብረው የሚያድሩ፣ አብረው የሚበሉ፣ አብረው ልጅ የሚያሳድጉ ሁለት ወንድና ሴት፡፡ ባለ ትዳሮቹ ጠፍተው ትዳሩ ቀርቷል፡፡ አንድ ነገር የሚመሠረተው፣ ለመመሥረቱ በሚኖረው ቀዳሚ ምክንያት ነው፡፡ ያ ምክንያት ነው ለዚያ ነገር የህልውናው ሞተር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ምክንያቱ ይጠፋና ነገሩ ብቻውን ይኖራል፡፡ የምክንያቱ ሳይሆን ምክንያቱ የፈጠረው ተቋም ወይም ቡድን አባል ትሆኛለሽ፡፡
ከዚያ በኋላ የምትኖሪው ወይም የምትንቀሳቀሽው ለምክንያቱ ሳይሆን በምክንያቱ የተነሣ ለተፈጠረው ተቋም ወይም ቡድን ይሆናል፡፡ ያ ተቋም የተመሠረተበትን ምክንያት ለመፈጸም ሲል የፈጠራቸው ሕጎች፣ ሥርዓቶች፣ ደንቦች፣ ባሕሎች፣ ልማዶች፣ ወጎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች በሰው ውስጥ ሰርጸው የመኖር ዐቅም ስላላቸው፤ አንቺም ለእነዚህ እየተገዛሽ መኖር ትቀጥያለሽ፡፡ ያን ጊዜ ሕይወት አዙሪት ይሆንብሻል፡፡ ሥራ ስላለሽ ከቤት ትወጫለሽ፣ ቤት ስላለሽ ብቻ ተመልሰሽ ትመጫለሽ፤ ልጆች ስለወለድሽ ለእነርሱ ስትዪ ትዳርሽን ትቀጥዪዋለሽ፣ ባል ስላለሽ ብቻ አብረሽ ትተኛለሽ፤ የጋራ ጉዳይ ስላለሽ ብቻ ተነጋገሪያለሽ፤ እያለ ይቀጥላል፡፡
እኔ እንዳየሁት አንቺ በትዳር ውስጥ ስትሆኚና ትዳሩ አንቺ ውስጥ ሲሆን ይለያያል፡፡ አንቺ በትዳር ውስጥ ስትሆኚ፣ በውስጥሽ ምንም ስሜት ሳይኖርሽ፣ ነፍስሽ ምንም ሳይሰማት እንዴው ማድረግ ስላለብሽ ብቻ ስታደርጊው ነው፡፡ ምግብን ሆድሽ ብቻ ሲበላውና ኅሊናሽ ጭምር ሲበላው አይለያይም? ለመኖር መብላት ስላለብሽ ብቻ ስትበዪና ደስ ብሎሽ፣ ኅሊናሽ ረክቶ፣ ዘና ብለሽ ስትበዪ ማለቴ ነው፡፡ አንቺ በትዳር ውስጥ ስትሆኚ ለመኖር ብቻ ሲባል ምግብ እንደመብላት ነው፡፡ ትዳር በአንቺ ውስጥ ሲሆን ግን ሌላ ነው፡፡ ስትሄጂ፣ ስትሠሪ፣ ስትተኚ፣ ሲደክምሽና ስትበረቺ እንኳን ትዳርሽን ባሰብሽ ቁጥር አንዳች ልዩ የሆነ የደስታና የእርካታ ስሜት ሲሰማሽ፤ ገብተሸ ስትዋኚበት፣ ያወራችሁትን፣ ያደረጋችሁትን፣ የሆናችሁትን፣ ሌላው፤ ቀርቶ የተኳረፋችሁትን እንኳን እንደ ቤት እንስሳ መልሰሽ ስታመነዥኪው እንደ መልካም ጠጅ በኅሊናሽ ኩልል ብሎ ሲንቆረቆር፤ ከቤትሽ ስትወጭ ለመመለስ ስትቸኩዪ፤ ከባልሽ ስትለዪ ለመገናኘት ስትጣደፊ፤ ባልሽን፣ ልጆችሺን፣ ቤትሽን ይዘሺው ስትሄጂ – ያ ነው – ትዳር በአንቺ ውስጥ ሲኖር ማለት፡፡
ትዳር ስንጀምር ትዳር ውስጣችን ገብቶ ነበር፡፡ ስንቆይ ግን እኛ እንገባና እርሱ ይወጣል፡፡ ያኔ ነው ‹መነጋገር› መነጋገር ብቻ የሚሆነው፡፡ መነጋገር የፍቅር መግለጫ፣ በነፍስ የመዛመድ ምልክት፣ በሐሳብ የመገናዘብ ማሳያ መሆኑ ይቀርና መነጋገር መነጋገር ብቻ ይሆናል፡፡ እኔም እንዲህ ሆኖብኝ ብዙ ጊዜ ተቸገርኩ፡፡ ስነጫነጭ፣ ስብሰከሰክ፣ ስማረርና ስቆርጥ ስቀጥል ኖርኩ፡፡ አንድ ቀን እንደ ድንገት ጋብቻን ስለማደስ የተጻፈ መጽሐፍ አገኘሁ፡፡ በፈረንጆቹ ባሕል ጋብቻን ማደስ (marriage renewal) የተለመደ ባሕል ነው፡፡ ለምን ወደ እኛ አንቀይረውም ብዬ አሰብኩ፡፡
በዚያ መጽሐፍ ላይ አንድ ቁም ነገር አየሁ፡፡ ከትዳር ልምድ ያገኘሺውን ነገር ተጠቅመሽ አዲስ የቃል ኪዳን ሰነድ አዘጋጂ ይላል፡፡ ለባለቤቴ ወሰድኩና አሳየሁት፡፡ ሲያነበው ወደደው፡፡ ያ ነገር ምክንያት ሆነንና ስለትዳር ማደስ አወራን፡፡ እኔም የራሴን እርሱም የራሱን ሰነድ አዘጋጀ፡፡ በቃል ኪዳን ሰነዱ ሞዴል ላይ ያለፈውን የትዳር ዘመን፣ ባለፈው ዘመን በክፉም በደጉም ለቆየንባቸው ዘመናት ለፈጣሪ ምስጋና፣ ለፈጠርናቸው ስሕተቶች ይቅርታ፣ ከዚያ ደግሞ ለወደፊቱ በትዳራችን እንድናደርግ የምንፈልገውን ነገር ይዘረዝራል፡፡ እኔ የርሱን እርሱም የእኔን ልናዘጋጅ ተስማማን፡፡ ባሌ ምን ቢሆንልኝ እንደምፈልግ ለብዙ ጊዜ አሰብኩበት፤ እርሱም አስቦበታል፡፡
ያዘጋጀነው ሰነድ ከትዳራችን ምን እንደምንፈልግና፣ ምን እንደማንፈልግ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር፡፡ ትዳራችንን የፈተሽንብት መልካም አጋጣሚ ሆነልን፡፡ ሁለታችንም በተዘጋጀልን ሰነድ ላይ መጠነኛ ማሻሻያ ከማድረግ ያለፈ አልተጓዝንም፡፡ አሁን በስለናል፤ ከልምድ ብዙ ነገር አግኝተናል፤ በፊት በትዳር ውስጥ እናስባቸው ያልነበሩ ነገሮችን ማሰብ ጀምረናል፤ ተፈታትነናል፤ ተዋውቀናልም፡፡ አንዳችን የሌላችንን በማዘጋጀታችን የተነሣ ነገሮች በዝርዝር ቀርበው ነበር፡፡ አናደርግም የምንለው፣ እናደርጋለን የምንለው ቁልጭ ብሎ ቀርቧል፡፡
በጣም የሚገርምሽ ነገር ችግር የማይመስሉን ነገሮች ሁሉ በሌላችን ተነቅሰው ሲመጡ ችግር መሆናቸውን ለመረዳት አስችሎናል፡፡ ቀላል የሚመስሉ፣ እንደዋዛ የምንዘላቸው፣ ነገር ግን ሌላችንን የሚያናድዱና የሚያሳዝኑ ነገሮች ሁሉ መጡ፡፡  በፈጣሪ ፊት ቆምንና ሁለታችንም እንደገና ቃል ገባን፡፡ እንደገናም ተጋባን፤ ለትዳራችን አዲስ እሴት ጨመርንለት፣ እንደገና የመኖሪያ ምክንያታችንን አደስነው፤ እርሱ ወደ እኔ፣ እኔም ወደ እርሱ ውስጥ ገባን፡፡ ትዳራችንም ወደ እኛ ገባ፡፡ ያንን ሰነድ በየጊዜው እያየሁ ራሴን አረጋግጥ ነበር፡፡ ቃሌን እየጠበቅኩ ነውን? እል ነበር፡፡ እንደ አዲስ ተጋቢ ነበር የሚሰማኝ፡፡
እንዳየሁት ከሆነ ትዳርና አትክልት በየጊዜው ካልተከታተሉት አረም ይበቅልበታል፡፡ ሲብስም አትክልቱ ይጠፋና አረሙ መታየት ይጀምራል፡፡ ያኔ ነው እንጨት እንጨት የሚለው፡፡ ጎበዝ ሰው ቶሎ ብሎ ያርምና አትክልቱ እንዲያብብ ያደርገዋል፡፡ እንደገና መኮትኮት፣ እንደገና ማዳበሪያ ማድረግ፣ እንደገና አፈር መከለስ፣ እንደገና ውኃ ማጠጣት፣ እንደገና አጥር ማጠር ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ድሮ አፈር አድርጌ ነበር፣ ማዳበሪያ ነበረው፣ አጠጥቼው ነበር፣ ኮትኩቼው ነበር አይሠራም ወዳጄ፡፡ አንዳንዴም እርሻው ብቻ ቀርቶ ተክሉ ሊጠፋ ይችላል፡፡
እና እስኪ ቆም ብለሽ ተመልከቺው፤ እንደገና መጋባት፣ ጋብቻውን እንደገና ማደስ፣ ለአዲሱ ሰብእናሽ አዲስ ሐሳብ መፈለግ፣ አሁን ለደረስሽበት ነገር አዲስ ቃል ኪዳን መግባት ያስፈልጋችሁ ይሆናል፡፡ ትዳርሽ አርጅቶ ይሆናል፡፡ ትዳር ይፀነሳል፣ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ያረጃል፣ ዝም ካሉትም ይሞታል፡፡ ጀግኖች ደግሞ እንዳያረጅና እንዳይሞት እንደ አዲስ ያድሱታል፡፡ አንቺም ትዳርሽ እንደ ንሥር አድሽው፤ ያለበለዚያ መጀመሪያ ያረጃል፤ ከዚያም ከባሰ ይሞታል፡፡ እሳትን እንጨት ላይ እያለ መልሶ ማቀጣጠል መልካም ነው፤በእንጨትነቱ ካልተደረሰም እንጨቱ ከሰል ሲሆን ቶሎ መድረስ ነው፤ ከሰሉ አመድ ከሆነ በኋላ ግን እንደገና ማቀጣጠል አስቸጋሪ ነው፡፡ ›› ነበር ያለቺኝ፡፡
አሁን  ሳስበው እርሷ ያለቺኝ ሳይሻል አይቀርም፡፡
‹እውነትሽ ነው› አለቺ ጓደኛዋ ‹‹ሁላችንም ብንሞክረው ሳይሻል አይቀርም››
ዑራኤል የኤሌክትሪክ ሱቆች ጋር ደርሼ ተለየኋቸው፡፡ እነርሱ ግን ቀጠሉ፡፡
ፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎቹ ዋና ኢንስፔክተር ጐይቶም አረጋዊ ኪዳነ ማርያም፣ ረዳት ኢንስፔክተር አንተነህ አስናቀ ተፈራና ኮንስታብል ዘሪሁን ሲሳይ ሲሆኑ፣ ሁሉም በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን የክስ ቻርጁ ያስረዳል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ለሕግ ተቃራኒ በሆነ መንገድ በማስገደድና ከሕግ ውጪ የግል ተበዳይ ናቸው የተባሉትን አቶ አህመድ ኑርን ይይዟቸዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከሶማሌ ክልል ወደ አዲስ አበባ በመምጣት፣ ተበዳዩን የያዟቸው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጐተራ አካባቢ መሆኑን ክሱ ይገልጻል፡፡ የግል ተበዳይ ናቸው የተባሉት አቶ አህመድን ከነበሩበት ተሽከርካሪ ላይ ጐትተው በማውረድ፣ በሽጉጥ በማስፈራራት፣ በቦክስ ፊታቸውንና የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን በመምታት ራሳቸውን ሲስቱ፣ ተጠርጣሪዎቹ በያዙት ተሽከርካሪ ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ መድኃኔዓለም አካባቢ እንደወሰዷቸውም ተገልጿል፡፡

ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በሚገኘውና ‹‹የሶማሌ ክልል ዳያስፖራ ቢሮ›› በመባል በሚታወቀው ጊቢ በሚገኝ ሰርቪስ ቤት ውስጥ በማስገባት፣ ለሦስት ሰዓታት እንዳቆዩአቸውም ክሱ ያብራራል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከሦስት ሰዓታት በኋላ የሰሌዳ ቁጥሩ 0071 በሆነ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ፒክአፕ ተሽከርካሪ ጭነው፣ ወደ ጅግጅጋ ያመራሉ፡፡ አዋሽ፣ ልዩ ቦታው አዋሽ ድልድይ ኬላ ላይ የሚጠብቁ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አባላት በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸውና ሰውን ከሕግ ውጪ ይዞ ማስቀመጥ ወንጀል መከሰሳቸውን የክስ ቻርጁ ያስረዳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና የጠየቁ ቢሆንም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት ኅዳር 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ውድቅ አድርጐ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከራከሩ ብይን ሰጥቷል፡፡
Source: Reporter Amharic


ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
 በለምለሚቷ ምድራችን ላይ እየተሽከረከረ ዚያራ ማድረግ ወጉ የሆነው የኢትኖግራፊ ፈረሳችን ታሪካዊቷን ጅማንና ህዝቧን መጎብኘት አሰኘው፡፡ እኛም “አበጀህ! ጥሩ ሀገር መርጠሃል” በማለት መረቅነው፡፡ ፈረሳችንም የደቡብ ምዕራብ አቅጣጫን ይዞ ገሰገሰ፡፡ ከጊቤ ዉሃ ከተጎነጨ በኋላም ወደ ታሪካዊቷ ቀበሌ ሰተት ብሎ ገባ፡፡
The palace of Abba Jifar, Jimma,
ጅማ! የአባጅፋር ሀገር! የአባ ፎጊ ሀገር! የአባ ቦጊቦ ሀገር! የአባ ጎመል ሀገር! ዝንተ-ዓለም አይረሴ የሆኑ ነገሥታት ታሪክ ሰርተውባት ለታሪክ ያኖሯት ውብ መንደር!!
ጂማ! የሰቃ ጨቆርሳ ሀገር! የጌራ ሀገር! የጉማ ሀገር! የጎማ ሀገር! የሊሙ ሂናሪያ ሀገር! አምስቱ የጊቤ መንግሥታት የለመለሙባት ምድር!!
ጅማ! የአባ ሚዛን ሀገር! የአባ ቆሮ ሀገር! የአባ ገንዳ ሀገር! የአባ ዱላ ሀገር! በኦሮሞ ምድር የዘመናዊ ቢሮክራሲ ጥንስስ የተጀመረባት ሰፈር!
ጅማ! የአቦል ሀገር! የበረካ ሀገር! የቃህዋ ጀባ ሀገር! ለስምንት መቶ ዓመታት ተወዳጅነቱ ሳይቀንስ የዘለቀውን “ቡና”ን ለዓለም ያበረከተች የሙሐባ መንበር!!
ጅማ! የተሚማ ሀገር! የገሜቲ ሀገር! የአያንቱ ሀገር! የአስሊያ ሀገር! የበድሪያ ሀገር! የፈይሩዝ ሀገር! ውብ ልዕልታትና ወይዛዝርት የወጡባት ምድር!!
*****
ተሚማ ነው ያልኩት! ይገርማል!! ገና የፈረሳችን ኮቴ መሬቱን ከመርገጡ ተሚማ በፈገግታ ታጅባ ልትቀበለን መጣች፡፡ ተወዳጅዋ የጅማ ጉብል!
ወይ አፈጣጠር!! “ቁርጥ ባለቤቴን” አለ ሰውዬው፡፡ በእውነት ይህቺ የጅማ ጉብል ናት ወይስ በሀረርጌ የምናውቃት ቀሽቲ?… እንዲያው ሁለመናዋ ከኛዋ ቀሽቲ ጋር አንድ ነው እኮ!!
ይህቺን “ኑረል ዐይን” የምትመስል ጉብል በተራ ሰላምታ ማነጋገር ተገቢ መስሎ አልታየንም፡፡ በመሆኑም ድሮ የ“ሐፈዝናቸውን” ሙገሳዎችና በቅርብ ጊዜያት የሰማናቸውን “ወለሎ”ዎች ተራ በተራ እየደረደርን ዐጃኢብ እስክትል ድረስ እንዘምርላታለን፡፡
*****
እውነቴን ነው!! ለጂማዋ ጉብል ማን ያልዘመረ አለ?… ብዙ ተዘፍኖላታል፡፡ ብዙ ተብሎላታል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ለርሷ የተደረደረው ሙገሳ በጣም ያንሳታል፡፡ እልፍ አዕላፍ “ቀሲዳ”፣ “ሩባኢያት”፣ “ወለሎ”፣ “ቅኔ”፣ “ገዛል”፣ ወዘተ… ይገባታል፡፡ የኛም ዚያራች ያማረ ይሆንልን ዘንድ ወደ ሌሎች ወጎች ከማለፋችን በፊት ለርሷ ክብር የተዜሙትን ዜማዎች አንዴ በጀመዓ ብንከልሳቸው መልካም ይመስለኛል (በአጸፌታው የጂማዋ  ጉብል  ደረጃውን የጠበቀ መስተንግዶ አድርጋልን ዚያራችንን ልታደምቀው ተሰናድታለች)፡፡
ለጅማዋ ጉብል የተዜመው የመጀመሪያው ዜማ የትኛው እንደሆነ በትክክል አናውቅም (አንቺ ተሚማ! ያ ገሜቲ ጂማ!! ያ በሬዱ ነማ!! እኛ “እኛ” መሆናችንን ታውቂዋለሽ አይደል?…. አዎን!  “እኛ” እያልን የምንጽፈው ከሀረርጌ በመሆናችን ነው)፡፡ እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ መሰረት ግን የጥላሁን ገሠሠ “ሰላመካ ያ ገንኔ ሰላመካ” ለጅማዋ ጉብል የተዘፈነ የመጀመሪያው ዜማ ይመስለኛል፡፡ የግጥሙ ደራሲ ተገኑ ባልከው ይባላል (“አሸም ያ ማተቤ”ንም የጻፈው እርሱ ነው)፡፡ ጥላሁን ለጅማዋ ጉብል ሲዘፍን እንዲህ ነበር ያለው፡፡
Salaama kaa yaa gannee salaama kaa
Harka fuune yaa immeetee salaamka.
Dubbiin Tamiima dubbiin mucayyoo magaala
Ija koo qabee gurra koo qabee na raasa
Gandan dhagayee dhiisi naan jenaani
Ittin dhiise yaadden na qabnaani.
ጥላሁን በዘፈኑ ውስጥ የጅማን ስም አልጠቀሰም፡፡ ነገር ግን በግጥሙ ውስጥ የተጠቀማቸውን ቃላት እና የሙዚቃውን ምት (rhythm) በአንክሮ ስናያቸው ዘፈኑ “ለጅማዋ ተሚማ” እንደተዘፈነ በቀላሉ መረዳት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ከበርካታ የኦሮምኛ ዘዬዎች መካከል “ሰላመ-ካ” እያሉ ሰላምታ መስጠት የሚቻለው በጅማው ዘዬ ነው፡፡ “ሰላመት” ከዐረብኛ ወደ ኦሮምኛ የገባ ቃል መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ቃሉ በኦሮምኛ ውስጥ የሚያገለግልበት ስልት እንደየአካባቢው ይለያያል፡፡ በሀረር ኦሮምኛ አንድን ሰው ስንገናኝ “ሰላም ጄኔ” (ሰላም ብለናል) ለማለት እንችላለን፡፡ በጅማው ዘዬ ደግሞ “ሰላመ-ካ” እንላለን (ሌሎች ስልቶችን ከወደታች እንመጣባቸዋለን)፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ጥላሁን ልጅቷን “ተሚማ” እያለ ነበር የጠራት፡፡ ይህም ዘፈኑ ለጅማ ጉብል የተዜመ መሆኑን ያሳብቃል፡፡ የጅማ ሴቶች ከሚጠሩባቸው ስሞች መካከል በጣም ዝነኛ የሆነው እርሱ ነው፡፡ ሌሎች አርቲስቶችም የጅማን ኮረዳ ለመጥራት ሲፈልጉ በዚህ ስም ነው የሚጠቀሙት (ጥላሁን “ፋጡማ” ወይንም “አዒሻ” ቢል ኖሮ ለሀረር ቆንጆ ነው ያዜመው ብለን እንጠረጥር ነበር)፡፡
*****
ከጥቂት ዓመታት በፊት ነው፡፡ “ሃጫሉ ሁንዴሳ” (Haacaaluu Hundeessaa) የሚባል የኦሮምኛ ዘፋኝ መጀመሪያ ካሴቱ በሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቶ ነበር፡፡ በካሴቱ ውስጥ ከተካተቱት ዜማዎች መካከል በጣም ተወዳጅ ሆኖ የወጣው ደግሞ ለጅማዋ ጉብል የተገጠመው ነው፡፡ ሃጫሉ ከጅማ ጉብል የያዘውን ፍቅር ሲገልጽ እንዲህ ነበር ያለው፡፡
Galaanni Gibee guutus daaktuuf bidiruutu nama ceesisaa
Garaan jaalatte hin rafuu halkuu jilbibbii nama deemsisaa
Ani sossodaadhe barana qalbii kootii
Gibee gaman jaaladhe sanyii mootii.
ሃጫሉ የዘፈነውን ወደ አማርኛ ስንተረጎመው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
“የጊቤ ወንዝ የሞላበት ሰው በዋናተኛና በታንኳ ይሻገራል
ያፈቀረ ሆድ ግን አያስተኛም፤ ሌሊቱን በሙሉ በዳዴ ያስኬዳል፡፡
አረ ዘንድሮስ ፈራሁኝ እንዳይታመም ይሄ ቀልቤ
ከጊቤ ወዲያ ያለችውን የንጉሥ ዘር አፍቅሬ ከልቤ፡፡
ሃጫሉ የወደዳት ልጅ “ጉብል” ብቻ ሳትሆን “የንጉሥ ዘር” እንደሆነች ነግሮናል፡፡ የዚህን አባባል “ተፍሲር” ወደፊት ስለምንመጣበት በአዕምሮአችሁ ውስጥ መዝግባችሁት ቆዩ፡፡
*****
ከላይ እንደገለጽኩት ለ“ጅማ ጉብል” የተዜመው የመጀመሪያ ዜማ የጥላሁን ገሠሠ “ሰላመካ” ነው፡፡ ነገር ግን ጥላሁን “ጉብሊቷ”ን በስም አልጠቀሳትም፡፡ ታዲያ “የጅማ ጉብል” የሚለውን ሐረግ በግጥሙ ውስጥ በግልፅ (explicitly) በማሳየት ማዜሙን የጀመረው ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?
  ነፍሱን ይማረውና አሁን በህይወት የለም፡፡ አብደላ መሐመድ ነው፡፡ አብደላ የፖሊስ ኦርኬስትራ አባል ነበረ፡፡ በኦርኬስትራው ውስጥ በነበረው ቆይታ “አሪፍ” ጣዕመ ዜማዎችን አስመዝግቦ አልፏል፡፡ ከነርሱ ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠቃሽ የሆነው ደግሞ “መጋለ ቀሎ ያ በሬዱ ጅማ” የተሰኘው ዘፈን ነው፡፡ አስታወሳችሁት አይደል?… አዎን!! አብደላ ያዜመው ዜማ በጣም ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ በአንድ ሰሞን የህዝብ ዘፈን እስከመሆን ደርሷል፡፡ በተለይም በቀድሞው ጊዜ የኢትዮጵያ ሬድዮ የኦሮምኛ ፕሮግራም የአብደላን ዘፈን እየደጋገመ ያጫውተው የነበረ መሆኑ ኦሮምኛ የማይሰሙ ሰዎችም ጭምር የዘፈኑን ግጥሞች እንዲሸመድዱ አስችሎአቸው ነበር፡፡ እነሆ አዝማቹን ላስታውሳችሁ ነው፡፡
Jenneen ashamaan ashamaa jenneen ashamaa
Magaala qalloo yaa bareedduu Jimmaa
የአብደላ ዘፈን መልዕክቱ እንዲህ ሊሆን ይችላል፡፡
“እንዴት ነሽ… ሰላም ነሽ ወይ” አልናት፡፡
ያቺን ጠይም ጉብል የጅማ ወጣት፡፡
አብደላ በዚህ ዘፈኑ የጅማዋን ጉብል በማወደሱ ብቻ አይደለም የሚለየው፡፡ በዘፈኑ ውስጥ የጅማ ሰዎች መታወቂያ የሆነውን  የኦሮምኛ ቃል በመጠቀም ግጥሙን ያቀናበረ በመሆኑም ጭምር ነው የሚታወሰው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
በርግጥም የጅማ ሰዎች ሰላምታ ሲሰጣጡ ከላይ በጠቀስኩት “ሰላመ-ካ” የተሰኘ ቃል ይገለገላሉ፡፡ ሆኖም ጅማዎች ሰላምታውን በመጠይቃዊ ዘዴ ሲያቀርቡልን ብዙሃኑ የኦሮምኛ ተናጋሪዎች በሚናገሩበት ስልት “አከም” (Akkam) አይሉም፡፡ ከዚህ በተለየ ስልት “አሸም” (Asham) ወይንም “አሸማ” (Ashamaa) ነው የሚሉት፡፡ አንድ ኦሮሞ የትም ሆኖ “አሸም” ብሎ ሰላምታ ካቀረበላችሁ ትውልዱ ከወደ ጅማ እንደሆነ ልብ በሉ፡፡(በነገራችን ላይ ለየት ያለ መጠይቃዊ የሰላምታ ማቅረቢያ ቃል የምናገኝበት ሌላው የኦሮምኛ ዘዬ በኢሉባቦር የሚነገረው ነው፤ የኢሉባቦር ሰዎች “አከም” ለማለት ሲሹ “አተም” ነው የሚሉት፡፡ የወለጋና የምዕራብ ሸዋ ኦሮሞዎችም  “አተም”ን ያውቁታል፡፡ ነገር ግን ወለጋዎችና ሸዋዎች በአብዛኛው “አከም”ን ነው የሚጠቀሙት)፡፡
የጅማ ሰዎች በሚያዜሟቸው ዘፈኖች ላይ በብዛት የሚጠቀሙት ሌላ ቃል አለ፡፡ እንዲያውም ያ ቃል ከቋንቋነትም አልፎ የጅማን ዘፈን የምንለይበት ምልክት (mark) እስከመሆንም ደርሷል፡፡ ለምሳሌ አንድ አርቲስት በዘፈኑ ውስጥ “አራዳ… አራዳ ሆዬ” የሚል ሐረግ ከደጋገመ ዘፋኙ ስለአዲስ አበባ እየዜመ መሆኑን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፡፡ “እሪኩም” እና “መጋሎ” የተሰኙ ቃላትን የሚያበዛ ዘፋኝም ስለወሎ የሚያዜም ነው፡፡ ስለጅማ የሚያዜም ሰው ደግሞ ብዙ ጊዜ “አህላን አህላ” እያለ ነው ዘፈኑን የሚጀምረው፡፡
አዎን! በኦሮምኛ ጨዋታዎች ውስጥ “አህላን አህለ” ከተባለ ዘፈኑ የጅማ መሆኑ ምንም አያከራክርም፡፡ “አህለን” በመሰረቱ የዐረብኛ ቃል ነው፡፡ በዐረብኛ “አህለን ወሳህለን” ከተባለ “ጤና ይስጥልኝ” እንደማለት ነው (አገባቡ ሰፋ ሲል ደግሞ “እንኳን ደህና መጡ” እንደማለትም ይሆናል)፡፡ በሃይማኖታቸው ሙስሊሞች የሆኑት የጅማ ሰዎች “አህለን”ን ከዐረብኛ ወርሰው ነው ቤተኛ ያደረጉት፡፡
*****
ጅማዎች “አህለ”ን የሚሉት ከልብ የመነጨ ስሜታቸውን ለመግለጽ ነው፡፡ እኛ ጅማ ስንገባ የፈረሳችንን ልጓም ይዛ የጅማን መሬት እንድንረግጥ የረዳችን “ተሚማ”ም ከፈገግታ ጋር “አህለን” በማለት ተቀብላናለች፡፡ እንግዲህ በርሷ አስጎብኚነት “አህለን አህለን” አያልን በጅማ መሬት መንሸራሸራችንን ልንጀምር ነው፡፡
አህለን አህላ… ሸጌ አህለን አህላ
አህለን.. አህላ.. ጊፍቲ አህለን አህላ
(ይቀጥላል)
—–
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 22/2007
ሀረር… ምስራቅ ኢትዮጵያ
—–
The writer, Afendi Muteki, is a researcher and author of ethnography and history with special focus on Eastern Ethiopia.  You may like his facebook page and stay in touch with his articles and analysis: Just click the following link to go to his page.

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር  ካካሄደው ውይይት ለመረዳት ተችሎአል፡፡ የትግራይ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰማያዊ ፣አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ጽንፈኞች በመሆናቸው …

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡ “በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት …

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት 111 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል በተከታታይ ተገቢ የሆነ የደሞዝ ማስተካካያ አላደረገም በሚል ጥያቄ ሲቀርብብት ቆይቷል። ሰሞኑን የካቢኔ አባላት ተሰብስበው   የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ከግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እንዲሁም  የኦሮምያ ክልል ጋዜጠኞች ከኦነግ ጋር የሚሰሩትና ለኢሳት መረጃ በማቅረብ በክልሎች …

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንዳለው በዋና ከተማዋ ጁባ አንድ ወንድና አንድ ሴት ሲገደሉ ሁለት ሴቶች ግን በጠና ቆስለው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደዋል። የሁለቱም ሟቾች አስከሬንም በኢትዮጵያውያን እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱ ታውቆል:: ሰዎቹ በምን ሁኔታ እንደተገደሉና እንደቆሰሉ እንዲሁም ጥቃቱን ያደረሱትን ወገኖች ዝርዝር ለማወቅ አልተቻለም። በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ግፍና …

ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!

ከባርነትና ውርደት ለመላቀቅ ነውና በፍጹም አይቀርም፣ አይቀርም!

የ9ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ››በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ዕቅዱን ለህዳር ወር አዘጋጅቶ ወደ እንቅስቃሴ ከገባ ሦስት ሣምንታትን አሳልፏል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተጓዝንበትን መንገድ ለጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤትና ለባለ ድርሻ አካላት ስናሳውቅ የነበረ በመሆኑ ያጋጠሙንን ችግሮች በመደጋገም ማሰልቸት አንሻም፡፡

ስለሆነም የዛሬው መግለጫችን በቀጣይ ለቀሩን ተግባራት የደረስንበትን ድምዳሜና ያወጣነው ዕቅድ በሚመለከት ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በእስከዛሬው እንቅስቃሴያችን ይዘን የተነሳነው ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሚለው መርህ ትክክልና ወቅታዊ፣ ያነሳናቸው ጥያቄዎችም አግባብ መሆናቸውን ያረጋገጥንበትና ገዢው ፓርቲ መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማለት ፍጻሜዬ ነው በሚል ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜትና ሥጋት ለተቃውሞ ጎራው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በሩን ለመዝጋት የተዘጋጀ መሆኑን አገር ለ23 ዓመታት በላይ ካስተዳደረ መንግስታዊ ሥርዓት የማይጠበቅ መረን የለቀቀ የውንብድና ተግባራት ያረጋገጥንበት ነው፡፡ በመሆኑም ጥያቄዎቻችንን በህገ መንግስቱና በአገሪቱ ህጎች መሠረት ለመመለስ ቀርቶ ለመስማትና ለማንበብ ፍቃደኝነቱና የኃላፊነት ስሜቱ እየተሟጠጠ በመሆኑ የአፈናና ማስፈራራት መንገድን ብቸኛ አማራጭ አድርጎታል፡፡ ይህ በመሆኑም የራሱን መንግሥታዊ መዋቅር አሰራር ሥርዓት እንኳ በአደባባይ ለመቀበል እምቢተኛ መሆኑን በአደባባይ አረጋግጧል፡፡ ባለሥልጣናቱ በግንባር ያቀረብነውን ደብዳቤ ካለመቀበል አልፈው በመንግሥታዊው ፖስታ ቤት የተላከ ደብዳቤ ያለመቀበላቸው የሚያመለክተው ይህንና የደረስንበትን የመልካም አስተዳደር አዘቅት ነው፡፡

በተቃራኒው አበረታችና መልካም ዜናም አለ፡፡ ይህም ይህን የአፈናና ማስፈራትት አካሄድ አንቀበልም ያሉ ለነጻነታቸውና ክብራቸው፣የራሳቸው ብቻ ሣይሆን የመንግሥት መዋቅሮችና ባለሥልጣናትም ነጻነት መረጋገጥ አለበት ብለው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል በቁርጠኝነት የተዘጋጁ በትብብሩ የታቀፉ ፓርቲዎች፣ አመራርና አባላት መኖራቸውና በትግሉ ለመቀጠል መወሰናቸው ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ትብብሩ ለመጀመሪያ ዙር ዕቅዱ ማጠቃለያ የህዳር 27/28 የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ አመራሩ በግንባር ቢያቀርቡም አሻፈረኝ አንቀበልም ያሉት አሰራርና ባለሥልጣናት ከፖስታ ቤት እንዲቀበሉ ተደርጓል፡፡ለዚሁ ደብዳቤ መስተዳድሩ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ (ቁጥር 3/1983) ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል በዛሬው ቀን (22/03/07) መልስ አድርሶናል፡፡ በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ በመሆኑም ለተግባራዊነቱ ዝግጅቱን በሙሉ አቅም ጀምሯል፤ ለዚህም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከአገር ውስጥና ከውጪ አጋርነታቸውን ገልጸዋል፤ አበረታተውናል፡፡ ይህም የያዝነው የትብብር የጋራ ዓላማችን ተቀባይነት፤ የኅብረትና አንድነትን ዋጋ አመላካች፣ ለማይቀረው ሠላማዊ ትግላችን ሥንቅ ነውና በታላቅ አክብሮት ተቀብለነዋል፡፡

ስለሆነም ይህ መግለጫ ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28 ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ነጻነታችንና ክብራችን ለማስመለስ ዋጋ ለመክፈል እንዘጋጅ፣ ያለመስዋዕትነት ድል የለምና!!
Image

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን አንድነት ፓትሪያርክ በርጦሎሜዎስ ቀዳማዊ ፣ ክርስቲያኖች ከመካከለኛው ምሥራቅ እንዲጠፉ የመላው ዓለም ፍላጎት አይደለም አሉ።

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ ፈጣን ግስጋሴው ገታ ብሏል፥ የአምናው ባለዋንጫ ማንቸስተር ሲቲ እግር በእግር መከተሉን አላቋረጠም። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ኃያሉ ባየር ሙንሽን እንደልማዱ ሊጋው ከመጠናቀቁ ቀደም ብሎ ዋንጫውን ለመጨበጥ ተቃርቧል፤ የቀድሞው ብርቱ ተፎካካሪ ቦሩስያ ዶርትሙንድ አቅም አንሶት በወራጅ ቃጣናው ጠርዝ ላይ እያጣጣረ ነው።

ኢትዮጵያም -በአብዮትና ፀረ-አብዮት ግብግብ ትናወጥ ነበር።የሶማሊያ ጦርም ገሚስ ኢትዮጵያን ለመያዝ ምሥራቅና ደቡባዊ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ።የአብዮቱ ትርምስ፤ የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት፤ የዩናይትድ ስቴት መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም መያዝ፤ ለቤገን ዕቅድና ቃላቸዉን ገቢር ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ነበር።

የገዳዩን የኤቦላ ተሐዋሲ የመዛመት ዜናን ተከትሎ ሰናይ ዜናን መሰማቱ ያልተለመደ ነበር። በቅርቡ ግን ተሐዋሲዉን ለመከላከል ያስችል ይሆናል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የክትባት መድሃኒት፤ ሰዎች ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጭ ዉጤትን አስገኝቶአል። ። በሌላ በኩል ክትባቱ አሉታዊ ገፆች እንዳሉትም ነዉ የተነገረዉ።

ምንም እንኳን በግብፅ በኩል አድርገው በህገ ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር፣ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ቢቀንስም፣ አሁን ድረስ በእስራኤል 48 000 የአፍሪቃ ስደተኞች እንደሚገኙ ይታመናል።

በአለፈው ዓመት በ­22.11. 2013 የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ፣ በእስራኤል ለሚገኘው የወያኔ ሚዲያ ለ­“IETV” ያመጣው የክስ መዘዝ፣ቀጥሎ ለውሳኔ መቀጠሩ የክሊክ ሃበሻ ዘገባ አመልክቷል::የዛሬ ዓመት ኖቨምበር 22 ቀን 2013 ነበር፤ ቴል አቪቭ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ኢትዮ­ይሁዳያንና ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ዓረቢያ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ፣ ሞተና የሴቶች መደፈር፣ ሰቃይና ሰቆቃ የወያኔ/ኅውሃት ገዥውና እምባገነኑ መንግሥት ችላ ብሎታል ብሎ በመቆርቆርና በመበሳጨት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው እንደነበር የሚታወስ ነው። http://www.clickhabesh.com/?p=105083

Image
ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል አብዛኛዎቹ በልጅነት እድሜ የመጡና ከዚህ የተወለዱ ወጣት የኢተዮጵያ ይሁዳውያን የተሳትፉበት ከመሆኑም ባሻገር፤በዚህ መልኩ በኢምባሲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት ወጣት ኢትዮ ይሁዳውያንን አልገብግቦ እንደዚህ ዓይነት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በእሥራኤል ሲካሄድ በዓይነቱ የመጀምሪያ ነበር ቢባል ማገነን አይሆንም። ምክንያቱም ቴል አቪቭ የሚገኘው አምባሳደር ኽላዊ ዮሴፍ የወጣት ኢትዮ ይሁዳውያን በሰልፉ መሳተፋቸው አስደንግጦት፣ እዚሁ እሥራኤል በሚገኘው የአማረኛ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቀርቦ ከተናገረው፣ በእሥራኤል መንግሥት ሙሉ በሙሉ በሚተዳደረ የአማረኛው ሬዲዮ ጣቢያ የተናገርውን አዳምጡ የሬዲዮውን ቃለ ምልልስ አዳምጡና ንባቡን ቀጥሉ፦

ልብ በሉ፦ በዲሞክራሲና በነጻው ሚዲያ ሃገረ እሥራኤል ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ “የአንድን ወገን ብቻ አቅርቦ” በተደጋጋሚ ማለትም አምባሳደሩንና ደጋፊዎቹን ቃለመጠይቅ ሲያደርግ፣ ቴሌቪዥኑም ሆን ሬዲዮው ከሙያው ህግ ውጭ በመሆን አንድም ቀን የተቃዋሚውን ወገን በጋራም ሆነ በተናጠል ቃለ መጠይቅ አካሂዶ አያውቅም። ህዝቡ በነጻውሚዲያ ሃገር የሁለቱንም ሃሳብ ሳያዳምጥ አንድ ወገን ብቻ ይዞ እንዲጓዝ መደረጉ ያበሳጫቸው ከዚህ ህዝብ አብራክ የወጡ በተናጠል ትግል የጋራ ትግል በማለት ተደራጅተው፣ “መሬት ­

ኢትዮ ­እሥራኤል የሰብዓዊና ነጻነት ድምጽ ምክር ቤት” ብለው ያቋቋሙት የመጅመሪያ ትግላቸው ማተኰር ያለበት በዲሞክራሲና በነጻ ሚዲያ ሃገር የህዝብ ድምጽ የታፈነውን መብተማስጠበቅ መሆኑን እጠቁማለሁ። ይህ የአምባሳደሩ መግለጫ አንዳንድ የዋህ አዛውንቶችን የኢትዮጵያን ህዝብ እያስራበ በሚያስመጣው “ጤፍ” በማታለል ለማሳመን መሞከሩ ነበር። ምክንያቱም የሚያስበው እሥራኤል የሚገኘው ኢትዮ ቤተ እሥራኤላውያን እኛ እንዳዘዝነው ነው ብሎ ያስብ ስለነበር ሳያስበው የደረሰበት የውርደት ካባ የተከናነበበት በመሆኑ ለማስተባበል መሞከሩ ነበር።ስለጤፍ ከአንድ ስብሰባ ላይ የተናገረውን ተመልከቱ፦ይህን ያህል ለመንደርደሪያ ካልኩ ዘንዳ፣ ወደ ዋናው ሃሳብ ልንደርደር።

ምንም እንኳ ዓርብ ቀን ድምጻውያን እንድሚሉት “….ዓርብ ዓርብ ይሸበራል እየሩሳሌም!” ያለ ምክንያት አይደለም። ዓርብ ህዝበ እሥራኤላውያን ለ 26 ስዓታት ሰንበትን የሚቀበሉበት ቀን ስለሆነ፤ ሁሉም ነገር ከመዘጋጋቱ በፊት ማልደው በመገዛዛት ሲያበስሉና ቤታቸውን ሁሉ ሲያጸዱ ከዋሉ በኋላ ሁሉም ቤተሰብ ሰውነቱን ታጥቦ ጽዓዳ በመልበስ ወደ ጸሎት ቤት ሄደው ሲመለሱ፣ ሰንበት ከመግባቱ በፊት ያበሳስሥሰሉትን፣ መላው ቤተሰብ በአንድ የጠረጴ ዙሪያ በመቀመጥ እየበሉና ወይናቸውን እየተጡ አምላካቸውን የሚያመሰግኑብት ቀን ሲሆን፤ የህዝብ ማመላለሻዎች፤ ሱቆች፤ መ/ቤቶች፤ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ማንኛውም በሙሉ ዓርብ ከስዓት በኋላ ከቀኑ 14፡00 ማለት 02፡00ስዓት (በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር ከቀኑ 08፡00 መሆኑ ነው) ይዘጋል።

ሆኖም ግን በዚህ ቀን የቤተሰብ ኃላፊነት ያላቸው ሌሎች በእድሜ ትንሽ ከፍ ያሉ ቢኖሩም፤ አንዲት ወጣት ቤተ እሥራኤል ከገጠሪቱ ኢትዮጵያወደ እሥራኤል በ­8 ዓመት ዕድሜዋ፤ ኅውሃት አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ ከሁለት ቀን በፊት “ዘመቻ ሰሎሞን” (Operation Solomon) በተባለውየመጣች፤ አሁን የ 31 ዓመት ወጣት፤ በፌስ ቡክ ያተላለፈውን በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን መከራና ሥቃይ ችግርና ስቆቃ ተመልክታ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው!” ብላ፤ ልጆቿን ዛሬ የ­7 እና የ­የ­5 ዓመት ዕድሜ፡(ባለፈው ዓመት የ­6 እና የ­4 ዓመት) ከወላጆቿ አስጠግታ፤ ከምትኖርበት ከተማከተወሰኑ ጓደኞቿ ጋር በባቡር ተሳፍራ በስዓቱ ከተባለው ቦታ ቴል አቪቭ በመድረስ ከሌሎች ከሰላማዊ ሰልፈኛው ጋር በመሆን፤ በሳዑዲ ዓረብያ ጭካኔ የተጐዱትንና የሞቱትን ኢትዮጵያኖች ፎቶ በማንገብ፤ የኢትዮጵያው መንግሥት ለዜጐቹ ግድ ሳይሰጠው ዝም ማለቱ በጣም ስለአንገበገባት፣ የዲሞክራሲ መብቷን በመጠቀም በጉዳት ላይ ላሉት ወገኖቿ ስትጮህላቸውና ድምጿን ስታሰማ ዋለች፡፡

ታዲያ ከሰላማዊ ሰልፉ አንድ ሳምንት በኋላ (በሳምንቱ ዓርብ) “IETV” በተባለው ቴሌቪዥን ይህችን ወጣት ያልተናገረችወን በኤዲቲንግ የተቀነባበረ ፕሮግራም ቀረበ። (የኢዲቲንግ ዕውቀቱ ወይም ሙያው ያለው አቆራረጡንና አቀጣጠሉን ይረዳል)ይህን ፓርት/ክፍል ተመልከቱ፤ፊልሙ ተጀምሮ እስኪያልቅ “ሰባት” (7 ጊዜ)ይህ ቃል በፕሮግራሙ ተደጋግሟል። ለምን? ተደጋገመ የሚለውን የፍርዱ ሁኔታ ሲያበቃ ከህግ ጠበቃዋና ከወጣቷ ጋር ፈቃደኛ ከሆኑ በቃለ መጠየቅ ከአንደበታቸው እንሰማለን የሚል እምነት አለኝ። እንደ ባለመያ እስኪ የራሴን አስተያየት ጠቆም አድርጌ ልለፍ፤

1ኛ) እንደዚህ ዓይነት ነገር ልጅቱ ከተናገረች፣ መሆን ያለበት ሙሉ ንግግሯን ከነመልኳ ማቅረብግዴታ ነው፤ ከዚያ በኋላ ቋንቋ ልማይረዱ ትክክለኛ ትርጉሙን ማቅረብ የሙያ ግዴታ ነው፣

2ኛ) በጋዜጠኛ ህግናደንብ መሰረት “Sling” ወይም “የመንገድ ቋንቋ” ብሎ ነገር የለም። ለህዝብ መቅረብ ያለበት “እውነተኛና ሃቅ ብቻ እና ሃቁ ብቻ ነው”፤ ምክንያቱምሚዲያ የአንድ ሃገር ህዝብ ጠበቃ ማለት ነው፣ወደ ታሪኩ ልመልሳቸሁ፣ ይህን የተላለፈ ፕሮግራም ያዩ ዘመድ አዝማድና ቤተሰቦቿ ”እንዴት ፋሲል ይገደል ትያለሽ?” “ለምን ልጆችሽን ዝም ብለሽ አታሳድጊም?” እያሉ
ሲያዋክቧት በመደናገጥ በጣም ተረብሻ ወዲያውኑ የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊ የነበሩትን ስታማክር፤ በመጀመሪያ እንድትረጋጋ ከመከሯት በኋላ፡
ፕሮግራሙን በኢንተርኔት በማየት በፍጹም ቃላት የተለቃቀመበት የተቀጣጠለ ስለሆነ፤ ቴሌቪዥኑንና አቅራቢውን “በስም ማጥፋት” የሚያስወነጅል እንደሆነ ገለጹላት። ይህች የ­31 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባትና ልጆችዋን ብቻዋን እንደምታሳድግ ስታማክር፤ የተወሰኑ ከተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ የተሳተፉ በመመካከር ወደ­5 የሚሆኑ ገንዘብ በማዋጣት ከፍለውላት“ፒኒ ጌልዓድ” የተባለ የሀግ ጠበቃ እንድትይዝ ሆነ።

በተላለፈው ፕሮግራም ላይ እንዳያችሁት፦የሀግ ጠበቃዋ በህጉ መሰረት ክሱን ጀመረ፣ “IETV” ወዲያውኑ ከኢንተርኔትና ከፌስ ቡክ ላይ ሙሉ ፕሮግራሙን አወረደው፤ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ፕሮግራሞችን እያወረደ የሚያስቀምጥ የተጠናከረ የወጣቶች ቡድን ቀድሞ ቀድቶ አስቀምጦታል።ክሱ ተጀመረ ብያለሁ፤ እናስ ማለታችሁ አይቀርም፤ እናማ የቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ የከሳሽና ተከሳሽን የህግ ጠበቆችን ቃል ከሰማ በኋላ፤ እንደ እሥራኤል ህግና ደንብ መሰረት የሚቻል ከሆነ ሁለቱ የከሳሽ የህግ ጠበቃና የተከሳሽ የሀግ ጠበቃ በጋራ ተስማምተው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ ለሆነ የሀግ ጠበቃ ሁኔታውን በመካከላቸው ሁና ከህግ አንጻር እንድታሸማግል “Court Mediators” ዘንድ ተላኩ። እዚያ መስማማት ባለመቻላቸውም በአለፈው ኦጐስት/ነሃሴ 2014 ወረዳው ፍ/ቤት ቀርብው ነበር።

ታዲያማ የተከሳሽ ጠበቃ ለዳኛው በ”ይፋ” ከሳሾችና ተከሳሾች በተገኙበት(በ”ይፋ” የሚለው ይሰመርበት) በመከራከሪያነት የተጠቀመው (የ“IETV” የህግ ጠበቃ በሂብሪው የተናገረውን ቃል በሂብሪውና በእንግሊዝኛ ላስቀምጠው) በሂብሩ የተጠቀመው ቃል “להבהיר” (Apologize) ከማለቱም በተጨማሪ፤ ከሳሿ ፈቃደኛ ከሆነች በዚያው ቃለ መጠይቅ ልናደርግላት እንችላለን ሲል የመከላከያ መልሱን አቅርቧል። የወጣቷ የህግ ጠበቃ ግን በወጣቷ ማህበራዊ ህይዎትም ሆነ የሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ መረበሽና አለመረጋጋትን ስላስከተለባት፤ ሆን ተብሎ በወጣቷ ላይ የተክናወነ የስም ማጥፋት ዘመቻ ስለተካሄደ፤ ለድርጊቱ “IETV” ይቅርታ ከመጠየቅም ባሻገር የሥነ ልቦና ጉዳት ካሳና የህግ ጠበቃዋን ወጭ ሊከፍል ይገባዋል ሲል መልስ ሰጥቷል።

ዳኛውም ወጣቷን ተከሳሾቹ በሚሉት ትስማማ አትስማማ እንደሆን ተጠይቃ፤ በ­“IETV” ምን ዓይነት ቃለ ምልልስ እንደማትሰጥና፣ ይህ ቴሌዥን በህይወቴ ላይ ከፍተኛ የሆነ መጥፎ አሻራ ያጣለባት መሆኑንና፤ የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ከተለያዩ ክፍሎች የደረሳት መሆኑንም ለፍ/ቤቱ አስረድታለች። ፍ/ቤቱም ለ­19.01.2015 ቀጥሯል። ችሎቱ ክፍት ስለሆነ ማንም ሰው የዲሞክራሲ መብቱን ተጠቅሞ መገኘት ይችላል። ቦታው ቴል አቪቭ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፤ “ቫይጽማን ጎዳና 1 ­ ቴል አቪቭ“ ትክክለኛውን ስዓትና ቀን ቀኑ ሲቃረብ እናሳውቃለን። ለወገን ደራሽ ወገን ነው ብላ ድምጿን ለማሰማት ወጥታ ሥነ ልቦናዊ ድቀት ለደረሰባት ወጣት እህታችን፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ያለበት ሃገር ያለሽ በመሆንሽ ሁላችንም መልካሙን ሁሉ እንመኝልሻለን!!
ሐና መከተ – ጋዜጠኛ እሥራኤል