ዓለም ሥጋት የሆኑት ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች

ሴቶች በአጥፍቶ መጥፋት ሲሳተፉ ማየት እምብዛም የተለመደ አልነበረም፡፡ ሆኖም በናይጄሪያ መንግሥት አክራሪ ተብሎ የተፈረጀው ቦኮ ሐራም ሴቶችንና ታዳጊ ሕፃናትን በአጥፍቶ መጥፋት እያሳተፈ ይገኛል፡፡ ለድርጊቱ ይረዳው ዘንድም የቦኮ ሐራም የሴቶች ክንፍ ካዋቀረ ሰንብቷል፡፡ የቡድኑ የሴት ክንፍ አብዛኞቹ አባላት ደግሞ በቡድኑ ታጣቂዎች ከየትምህርት ቤቱና ከየመንደሩ የሚጠለፉ ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች በሚስትነትና በሠራተኝነት ከማገልገላቸው ባለፈም፣ በአጥፍቶ መጥፋት መሳተፍ […]