በሲጃራ ሙስና የተጠረጠሩት የትንባሆ ሞኖፖል ኃላፊ ነፃ መባላቸውን የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ተቃወመ።
ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፀረ-ሙስና ኮሚሽን- የብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል ድርጅት የሥራ ኃላፊ በተጠረጠሩበት የእምነት ማጉደል ወንጀል በፍርድ ቤት በነፃ መሰናበታቸውን በመቃወም- ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታወቀ። ሪፖርተር እንደዘገበው ፤የብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል ድርጅት ያለቀላቸው ምርቶች ግምጃ ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ በሻና 787,531.50 ሳንቲም በሚያወጣ 210 ካርቶን ኒያላ ሲጋራ በመሰወር ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ጉዳዩን …