በአንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን የተጠረጠሩት የኤርትራው የጸጥታ ሹም ለወያኔ ሚስጥር አቀብለዋል በሚል ተጠርጥረው ታሰሩ

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስን ከስልጣን ለማውረድ አሲረዋል በሚል አስራ አምስት ባለስልጣናት ወህኒ አስገብተው የነበሩት የኤርትራው የፀጥታ ሹም ወዲ ካሳ ተራቸው ደርሶ ወህኒ ወርደዋል።

ከአስመራ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የጸታው ሹም ለበርካታ ዓመታት የኤርትራን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ ሲያቀብሉ ኖረዋል። በኤርትሪያ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩ ሰዎችን ወያኔ እያደነ ሲገድልና ሲያስር የነበረው በእኚሁ የፀጥታ ሹም መረጃ የተነሳ ነበር። የወያኔን ባለስልጣናት ለመግደል አሲረዋል ተብለው ወህኒ የተጣሉት የአማራ ብሔር ተወላጅ የወያኔ ጄነራሎችን ሚስጥር ለወያኔ የሰጡት እኚሁ ሰው ናቸው።

የአንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ እጅ መውደቅ ሚስጥሩም በእኚህ ሰው እጅ ነው። አጠቃላይ እኚህ ሰው ለወያኔ ወሳኝ ሰው የነበሩ ሲሆን ለኤርትሪያ ደግሞ ራስ ምታት የነበሩ ናቸው። ግለስቡ በወንድማቸው ስም አዲስ አበባ ላይ ባለ አሥር ፎቅ ህንፃም ማስገንባታቸው አስመራ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

በኤርትራው ፕሬዝደንት ክፉኛ ጥርስ የተነከሰባቸው እኚህ ሰው ከትናንት በስቲያ ባልታወቀ ቦታ የታሰሩ ሲሆን በእኚህ ሰው መያዝ የወያኔ የፀጥታ መ/ቤት በመናጥ ላይ ነው ከትናንት ሐምሌ 27/97 ምሽት 5 ሰዓት ጀምሮ የህወሓት ከፍተኛ የጸጥታ ባለስልጣናት ምክር ላይ ናቸው። ከዚህ በኋላ በኤርትራ በኩል ያለው የመረጃ መረባቸው ስለሚበጣጠስ የወያኔው አገዛዞች የአፈ ሙዝ ጨዋታቸውን ይጀመራሉ ተብሎም ተገምቷል።