ሰልጣኝ ተማሪዎች በፌደራል መደብደባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ወስደው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው የመጀመሪያ አመትና ነባር ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ‹‹የውሎ አበላችን ይሰጠን›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው በትናንትናው ዕለት

በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ስልጠናው አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱት ተማሪዎች  መጀመሪያ ላይ እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸው የነበረው የውሎ አበል አይከፈላችሁም በመባላቸው በትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ተማሪዎቹ አበሉ አይከፈላችሁም ቢባሉም አሰልጣኞቻቸው

‹‹ገንዘቡ መጥቷል፡፡ አንከፍልም የሚሉት ዝም ብለው ነው›› ማለታቸው ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ገፋፍቷቸዋል ተብሏል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ሴት ተማሪዎች ከግቢው እንዳይወጡ የከለከለ ሲሆን ወንድ ተማሪዎች ከግቢው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ መደብደባቸውንና

መታሰራቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የአዋሳ ፖሊስ አዛዦችን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

1 Comment on “ሰልጣኝ ተማሪዎች በፌደራል መደብደባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ”

  1. why in the first place agree to go to the meeting it is just for the sake of per dime? you shouldn’t have to go in the first place if you did with out receiving the money. that what you deserve you dealing with weyanes remember?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*