ከላይቤሪያ የተመለሰው አሜሪካዊው የኢቦላ ሕመምተኛ ቶማስ ኤሪክ ዳንከን ትናንት በዳላስ ቴክስስ ካረፈ ወዲህ ይህን አደጋና በሽታ ለመታገልና ለመግታት ጠንካራ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚያሻ በመነገር ላይ ነው።

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“የመከላከያ ሰራዊቱ ያዛዥነት ቦታዎች በአንድ ብሄር ቁጥጥር ስር ነው” በሚል ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት ኢህአዴግ፣ ሰራዊቱን ህብረብሄራዊ ማድረጉን ገለጸ። የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች  እንዲወያዩበት ተብሎ በኢህአዴግ የተዘጋጀው ሰነድ የትምክት ሃይሎች ”  በአገራችን የአንድ ብሄር የበላይነት ያለ ለማስመሰል የማያደርጉት ሙከራ የለም” ካለ በሁዋላ፣ ሰራዊታችን በህገ መንግስቱ መሰረት የተዋቀረ ህብረብሄራዊ ሰራዊት …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በአዲስአበባ ባለፈው ዓመት 22ሺ ያህል የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል የሚል ሪፖርት ማቅረባቸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት 22ሺ ያህል ቤቶች ቀደም ሲል ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠረው ማኅበር ጽንፈኛና አሸባሪ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው››ሲሉ የኢትዮፐያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተናሩ። ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ይህን ያሉት ፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልፀግ›› በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ጉባዔ በከፈቱበት …

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጥቃቅን እና አነሰተኛ ተደራጅተው ፤በየቀኑ ላባቸውን እያፈሰሱ የሚደክሙ የድሃ ድሃ እናቶች እለቅሶ ርቆ እየተሰማ መሆኑን የክልሉ ዘጋቢያችን ነጋዴዎችን አነጋግራ የሰራቸው ዘገባ ያመለክታል 33 በእድሜ የገፉ እናቶች ” በመንግስት ሌቦች ተዘርፈናል ሲሉ ” እያለቀሱ ብሶታቸውን ገልጸዋል። በአማራ ክልል በስራ አጥ እና የድሃ ድሃ ከተደራጁ 31 ሺ 549 ማህበራት …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው ዕለት ዘ ሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ «አይ ሲ ሲ» ቀረቡ። «አይ ሲ ሲ» ከሰባት ዓመት በፊት በኬንያ ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ የተካሄደውን የጎሳ ግጭት አቀነባብረዋል በሚል በጠረጠራቸው ኬንያታ ላይ ክስ መመሥረቱ የሚታወስ ነው።

ሰብል በመስክ ላይ እያለ ወይም በሚደርቅበት፣ በሚከማችበት ወይም በሚጓጓዝበት ጊዜ በሚፈጠር ሻጋታ ውስጥ የሚገኘው አፍላቶክሲን የሚባለውን መርዛማ ንጥረ ነገር በአፍሪቃ በቆሎን እና ለውዝን የመሳሰሉ የግብርና

የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው ዕለት ዘ ሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት፣ «አይ ሲ ሲ» ቀረቡ። «አይ ሲ ሲ» ከሰባት ዓመት በፊት በኬንያ ከተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ የተካሄደውን የጎሳ ግጭት አቀነባብረዋል በሚል በጠረጠራቸው ኬንያታ ላይ ክስ መመሥረቱ የሚታወስ ነው።

ከሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ወደ ደቡብ እስከ ምድር ሰቅ የሚዘልቁና ወደመጡበት ሳይደናገሩ የሚመለሱ አእዋፍ ምንቃራቸው አጠገብ በቀኝ በኩል አቅጣጫ አመላካች የተፈጥሮ «ኮምፓስ» አላቸው። የሌሊት አእዋፍ ፣ ዓይን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ አቅጣጫ ጠቋሚ አላቸው።

በምዕራብ አፍሪቃ ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ በተከሰተው እና በዓለም እስከዛሬ አስከፊ መሆኑ በተነገረለት የኤቦላ ወረርሽኝ የ3,431 ሰዎችን ሕይወት ማጥፋቱን፣እንዲሁም፣ በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴየራ ልዮን ወደ 7,470 ሰዎች ደግሞ በኤቦላ አስተላላፊ ተሀዋሲ መያዛቸውን የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት አስታውቋል።

የሶማልያ ብሄራዊ ጦርና የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ኃይል ‘አሚሶም’ከአሸባብ አክራሪ ኃይል ጠንካራ ይዞታዎች መካከል አንዷ ነች የተባለችውን የባራዌ የወደብ ከተማ ከቀናት በፊት ነፃ አዉጥተዋል። ለበርካታ ዓመታት ከሶማልያ ማዕከላዊ መንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆና የቆየችው የባራዌ ከተማ ለአሸባብ ዋንኛ የገቢ ምንጭም ነበረች።

ዐጽሟ ያረፈበት አርመን የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን

ቅድስት አርሴማ በ290 ዓም በአርመን በሰማዕትነት ያረፈች ወጣት ክርስቲያን ሰማዕት ናት፡፡ ትውልዷ ሮም ሲሆን ሰማዕትነት የተቀበለችው አርመን ነው፡፡ እኛ አርሴማ ስንላት እነርሱ Saint Hripsime ይሏታል፡፡ ታሪኳን የፈለገ ሰው በዚህ ስሟ ጎጉል ላይ ቢፈልግ በቀላሉ ያገኘዋል፡፡ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መስከረም 29 ቀን ወይም ኦክቶበር 9 ሰማዕትነት የተቀበለችበትን ቀን ያከብራሉ፡፡ የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን በስሟ የተሠራውም አርመን ኤችሚዚን ውስጥ በ395 ዓም ነው፡፡ ይህ የአርሴማ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ሳይፈርሱ ከኖሩት እጅግ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ነው፡፡

የዚህች ወጣት ሰማዕት ታሪክ በስንክሳር በመስከረም 29 ቀን ተጽፏል፡፡ በሀገራችን ገድላቸው ከተተረጎመላቸው የውጭ ቅዱሳን አንዷ አርሴማ ናት፡፡ የዚህ ምክንያቱ የታወቀ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ አርመን ከአርመንም ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱና የሚመጡ ቅዱሳን ነበሩ፡፡ በ10ኛው መክዘ አካባቢ በአርመን የደረሰውን የፋርሶችን ወረራ በመሸሽ አያሌ አርመናውያን ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውንና ዛሬ ሐይቅ እስጢፋኖስ በተባለው ቦታ መሥፈራቸውን የአርመን ታሪክ ይነግረናል፡፡ በአርመንኛ ‹ሐይቅ› ማለትም ገዳም ማለት ነው ይላሉ፡፡
                        በአርመን ቤተ ክርስቲያንዋ የሚታወቀው ሥዕል ይህ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በ13ኛው መክዘ ኢትዮጵያዊው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ መጀመሪያ ወደ ግብጽ (1330-32 ዓም)፣ ከዚያም ወደ እሥራኤል በመጨረሻም ወደ አርመን ተጉዘው በዚያ ለአሥራ አራት ዓመታት ከቆዩ በኋላ በ1352 ዓም ዐርፈዋል፡፡ ከእርሳቸው ዕረፍት በኋላም ደቀ መዝሙሮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ እነዚህ የተመለሱ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ደቀ መዛሙርት ብዙ የውጭ ሀገር ቅዱሳት መጻሕፍትን ይዘው በመምጣትና ወደ ግእዝ በመበተርጎም ታላቅ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡ (ዝርዝር ታሪኩን የፈለገ ‹አራቱ ኃያላንን› መመልከት ነው)፡፡ በጎንደር መንግሥት ጊዜም አቡነ ዮሐንስ የተባሉ ቆሞስ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስን ተረፈ ዐጽም ይዘው በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን መጥተው ነበር፡፡ እነዚህ ከወዲህና ከወዲያ የነበሩ ግንኙነቶች ቅድስት አርሴማን በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንድትታወቅ አድርጓታል፡፡ ገድሏም ወደ ግእዝ ሊተረጎም ችሏል፡፡

በአሁኑ ዘመን አርሴማ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዘንድ ይበልጥ እየታወቀችና እየተከበረች መጥታለች፡፡ ወጣቱ የወጣቷን ሰማዕት አርአያ ማንሣቱ የሚያስመሰግን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስለ ክርስቶስ ስትል የከፈለችውን ሰማዕትነት፣ ድንግልናን በብጽዐት ለመጠበቅ ስትል የተቀበለችውን መከራ፣ ወጣትነቷ ሳያጓጓት ለእምነት የከፈለችውን ዋጋ፣ በሕይወቷ ሳለች ከሠራችውም በላይ በሰማዕትነቷ ያፈራችውን ፍሬ በማሰብና ከእርሱም በመማር ዘመኑን ከመዋጀት ይልቅ የሰማዕቷን ዝክር ከትዳርና ከፍቅረኞች፣ ከጥራጥሬና ከታሪኳ ጋር ከማይሄዱ ነገሮች ጋር ማገናኘቱ መልካም አይደለም፡፡

                                                    ቅድስት ባርባር
ሌላው ቀርቶ በአሁኑ ጊዜ የቅድስት አርሴማ ሥዕል ነው ተብሎ በስፋት የሚታወቀው ሥዕል በኦርቶዶክስ ሥነ ሥዕል (አይኮኖግራፊ) የቅድስት ባርባራ ሥዕል ነው፡፡ አርመን ኤችሚዚን በሚገኘው መቃብሯ ላይ የሚገኘው ሥዕሏ ከታች የተገለጠው ነው፡፡ ጣና ደሴት ውስጥ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያንዋም ኢትዮጵያዊውን ሥዕል ማግኘት ይቻላል፡፡

                በመቃብሯ ላይ የሚገኘው ሥዕል

በአጠቃላይ ቅድስት አርሴማ ታሪኳ በመላው ዓለም ክርስቲያኖች ዘንድ የታወቀ፣ ከንጽሕናና ቅድስና ጋር በእጅጉ የተገናኘ፣ ለወጣት ሰማዕታት ታላቅ አርአያ የሚሆን፣ ንጽሕናን ለመጠበቅ ፈታኝ በሆነበት በዚህ ዘመን ምሳሌ የሚሆን፣ ቀደምት እናቶቻችንና እኅቶቻችን ስለ ክርስቶስ ሲሉ የከፈሉትን ዋጋ የሚያሳይ በመሆኑ በዓሏም በዚህ መንፈስ መከበር ይኖርበታል፡፡ 
ሜልበርን፣ አውስትራልያ

ብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ” ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ […]

ጥቂት የሕወሓት የዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲ ሠራተኞች እና አንዳንድ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ተነጥቆ በሚሰጣቸው የስኮላርሺፕ ገንዘብ የደለቡ የስርዓቱ ደጋፊዎች በሰለሞን ተካልኝ መሪነት በስቴት ዲፓርትመንት ደጃፍ ዛሬ ሰልፍ ወጡ። በተመሳሳይም የአሜሪካ መንግስት በዋሽንግተን ዲሲ የሕወሓት ኢምባሲ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰውን የስርዓቱን ተላላኪ ከሃገሩ በማባረሩ ለዚህም ምስጋና ለማቅረብ ኢትዮጵያውያን በስቴት ዲፓርትመንት ተመሳሳይ ሰልፍ አድርገዋል። ሃገር ወዳዱ ኢትዮጵያውያን […]

አቶ ፈቃዱ ደሪሎ ከአባቱ ከአቶ ደሪሎ ተክለማሪያምና ከናቱ ከወ/ሮ ጥሩነሽ ደረሳ መስከረም 6 ቀን 1948 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ።

አቶ ፈቃዱ በበረራ መሐንዲስነት ከ20 ዓመታት በላይ እጅግ የላቀ የሥራ ልምድ ነበረዉ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በ1964-65 ዓ/ም የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተግባረዕድ ት/ቤት ገባ። የሙያ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በሰኔ 15 ቀን 1965 ዓ/ም ዝነኛ በነበረዉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀጠረ። የበረራ ፈቃድ በመያዝ በቦዪንግ 707/720 እና 727/737/767 ((Boeing 707/720 b/727/737/767) ላይ አገለገለ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዉስጥ በመሥራቱ ወደ ተለያዩ የአዉሮፓ፤ ኢስያ፤ ኩባና አፍሪቃ አገሮች የመዘዋወርና የመሥራት ዕድል አገኘ። ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እድሜ ልኩን እጅግ የሚወዳቸዉን ጓደኞች አተረፈለት።

በ1985 ዓ/ም ሂትሮ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ለቦዪንግ 76 ጥገና በመመደብ በሎንዶን ከተማ እስከ 1990 ዓ/ም ድረስ ሠራ። በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በርክሼር ዉስጥ ላነግሌይ በሚባል ቦታ ከኖረ በኋላ በ1989 ዓ/ም ወደ ሎንዶን ከተማ ከቤተሰቡ ጋር በመዞር በምሥራቅ አክቶን ተቀመጠ። በነዚህ ዘመናት ከርሱ ጋር ያሳለፉትን ደስታ ቤተሰቦቹና ኋደኞቹ እስካሁን ያስታዉሳሉ።

ለተለያዩ ኩባኒያዎች የሠራ ሲሆን በመጨረሻ የሠራዉ ለኤየርክራፍት ሴርቪስ ኢንተርናሺናል ግሩፕ (Aircraft Service International Group) ነበር።

አቶ ፈቃዱ ከወ/ሮ አይናለም በሻህ ጋር በኢትዮጵያ ዉስጥ የተጋባዉ በ1974 ዓ/ም ነበር። በ1985 ዓ/ም ወደ ሎንዶን ከመላኩ በፊት ኑሮዉም ሥራዉም በኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ቤተሰቦቹ መጥተዉ ተቀላቀሉት።

አቶ ፈቃዱ ተወልዶ ያደገዉ ጠንካራ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሆኑት ቤተሰቦች መሃል ነዉ፤ ይሄም ለመልካም የዕድገት ደረጃና ጠንካራ አምልኮት አድርሶታል። በየዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ በሄደ ቁጥር ቤተሰቦቹንና ኋደኞቹን ከማየቱ በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፀሎት ያደርስ ነበር። ጊዜዉን በደስታ የሚያሳልፈዉ ከቤተሰቦቹ ጋር እቤት ዉስጥ በመሆን ነዉ፤ ሰፖርት ፕሮግራሞችን ይመለከታል፤ የተሌቪዥን ጥያቄዎች ይከታተላል፤ የበረራ መጻሕፍትን ያነባል፤ መኪናዉን ያጥባል፤ ይጠግናል።

መልካም ባል፤ ጥሩ አባትና ቆራጥ አያት ነበረ። ቅርቡ የሆኑት የሥራ ባልደረቦቹና ቤተሰቦቹ ዝምተኛነቱንና ተቖርቋሪነቱን ይመሰክራሉ።

የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ አቶ ፈቃዱ በሰላም በተኛበት ቦታ በ65 ዓመቱ ማክሰኞ መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ/ም ከዚህ ዐለም በሞት ተለየ፤ ሞቱም በተፈጥሮ ምክንያት መሆኑ በአጣሪዎቹ ኮሮኔሮች ተረጋግጧል።

ቤተሰቦቹም የሚከተሉት ናቸዉ፤ ባለቤቱ ወ/ሮ ዓይናለም፤ ሁለት ልጆቹ ዮናስና እዮብ፤ የልጅ ልጆቹ፤ ረዲኤት፤ አቤልና ሲሳይ ሲሆኑ 6 ወንድሞቹና እህቱ ግርማ፤ ሙሉ፤ ታምሩ፤ ታደለ፤ ብርሃኑና አክሊሉ ናቸዉ።

ቸሩ አምላካችን ነፍሱን በመንግሥተ ሰማያት ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቹና ወገኖቹ በሙሉ ጽናቱን ይስጥልን አሜን።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በሦስት አሳታሚ ድርጅቶች መሪዎች ላይ የእስራት ፍርድ በየነ።

የፌዴራል አቃቤ ሕግ ዩፋ ኢንተርቴይንመንትና የፕሬስ ሥራዎች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ ዳዲሞስ ኢንተርቴይንመንትና ሮዝ አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በተሰኙ ድርጅቶችና በዋና ስራ አስኪያጆቻቸው ፋጡማ ኑርዬ፣ አቶ ግዛዉ ታዬ ኦርዶፋና አቶ እንዳልካቸዉ አድጉ ላይ ባቀረበዉ ክስ መሰረት፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት “ጥፋተኛ” ናቸው ሲል ወስኖባቸዋል። ሶስቱም ተከሳሾች ቀደም ብሎ አገር ጥለው የኮበለሉ ሲሆን፤ የእስራት ቅጣቱ የተፈረደባቸው በሌሉበት ነው።

ዛሬ በዋለዉ ችሎት ፍርድ ቤቱ በእያንዳንዳንዱ ተከሳሽ ላይ ከ3 አመት ከ3 ወራት እስከ 3 ዓመት ከ11 ወራት የሚደርስ እስራት ፈርዷል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የዳዲሞስ…

 

 

 

የቦስተን ማራቶኑ የቦምብ ጥቃት አድራሾች ጓደኛ ትውልደ ኢትዮጵያ ሮቤል ፊሊጶስ አደጋው በተጣለ ሰሞን ስለነበረው ሁኔታ አንዱን ቅዳሜ ሙሉ ዕፀ-ፋሪስ ሲያጤስ ስለዋለ አደንዛዡ ዕፅ ባደረሰበት የማስታወስ ችሎታ መታወክ ምክንያት በዕለቱ ምን እንደተፈፀመ ማስታወስ አልቻለም እንጂ የዋሸው አንዳች ነገር የለም ሲሉ ጠበቆቹ ለፍርድ ቤት መከራከሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የሮቤልን ጉዳይ የተመለከተው የቦስተን ችሎት የተሰየመው – ሰኞ ትናንት ነበር፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተቃውሞ ለማሰማት በሄዱ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰው ሰለሞን ገብረስላሴ፣  በ48 ሰአታት ውስጥ ከአሜሪካ እንዲወጣ ከተደረገ በሁዋላ የመንግስት ደጋፊዎች የአሜሪካን እርምጃ ለመቃወም የጠሩትን ተቃውሞ ለማክሸፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ተመሳሳይ ተቃውሞ አዘጋጅተዋል። የመንግስት ደጋፊዎች አሜሪካ ለኢምባሲው በቂ ጥበቃ አላደረገችም በሚል ሲቃወሙ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው አገሪቱ ለሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለመንግስት ሰራተኞች እና ለኢህአዴግ አባላት የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና የዩኒቨርስቲ መምህራንም እንዲወስዱ በመገደዳቸው፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን በቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር እና በአሁኑ የጠ/ሚ የፖሊሲ አማካሪ በአቶ በረከት ስምኦን እንዲሰለጥኑ እየተደረገ ነው። ስልጠናውን የሚወስዱት በታሪክ፣ በፖለቲካል ሳይንስ፣  በሶሺኦሎጂ፣ በጆግራፊ፣ በፊዚክስ እና በመሳሰሉት የትምህርት ዘርፎች …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሩ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ስልጠና በመውሰድ ላይ ላሉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ነው። አቶ በረከት በምእራባውያን እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ገንዘብ በሃይማኖት ስም የፖለቲካ አላማ ለማራመድ በሚል ወጪ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ በረከት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ትርምስ እንዲፈጠር ይፈልጋሉ ያሉዋቸውን …

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው እስከ 200 የሚደርሱ የመጨረሻ ዓመት የህክምና  ተማሪዎች በመመረቂያ አመታቸው ላይ እንዳሉ ሲመረቁ የሚከፈላቸውን የደመወዝ ግማሽ የሚከፈላቸው ሲሆን የውዝግቡ ዋነኛ ምክንያት የሚከፈላቸው ግማሽ ክፍያ በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪ መሰረት አለመሆኑ ነው፡፡ የህክምና ተማሪዎቹ ለአካባቢው  አመራሮች  ቅሬታቸውን አቅርበው የፓለቲካ አመራሮቹ “ቅሬታችሁ ተገቢ ነው” የሚል መልስ ቢሰጡዋቸውም የዩኒቨርስቲው ዲን  ተማሪዎቹን …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች በየሳምንቱ በሊቢያ በኩል አድርገው ወደ አውሮጳ ለመግባት ይሞክራሉ። የአንዳንዶቹ እጣ ፋንታ በሜዲትሪያን ባህር ሰምጦ መሞት ሲሆን በህይወት የተረፉት ደግሞ በስፓኝ፣ በማልታ፣ በግሪክ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በኢጣሊያ አድርገው ወደሰሜን አውሮፓ ለመግባት ይሞክራሉ።

ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በዋለባቸው ያለፉት ሁለት ዐሠርተ- ዓመታት ውስጥ በዓለም ሕዝብ ፤ መንግሥታትና ተቋማት የርስ በርስ ግንኙነት ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን በማበረታታት ሃገራት ዓመታዊ የምርት መጠናቸውን (GDP) እንዲያሳድጉ በር ከፍቷል።

አፍሪቃ ዉስጥ በስተምዕራብ በሚገኙ አራት እና አምስት ሃገራት ቀስ በቀስ የተስፋፋዉ ኤቦላ ወደአዉሮጳም እንዳይዛመት ስጋቱ አሁንም አለ። ዓለም ከገዳዩ የኤቦላ ተሐዋሲ ጋ የተያያዘዉን ፍልሚያ ገና በድል ሳያጠናቅቅ እሱን መሰል ማርቡርግ የተሰኘ አደገኛ ተሐዋሲ ዩጋንዳ ዉስጥ መታየቱ ተሰምቷል።

አቤ ቶክቻው

ትላንት ለንደን ነበርኩ። እኔ ካለሁበት ማንችስተር ከተማ ለንደን ለመሄድ ወደ ስምንት መቶ ሰው ጭኖ በሰዓት እስከ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ድረስ በሚወነጨፈው ቨርጂን ባቡር የፈጀውን ይፍጅ ብዬ ከተሳፈርኩ ሁለት ሰአት ከ ሃያ ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስድብኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አቤ ቶክቻው

ትላንት ለንደን ነበርኩ። እኔ ካለሁበት ማንችስተር ከተማ ለንደን ለመሄድ ወደ ስምንት መቶ ሰው ጭኖ በሰዓት እስከ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ድረስ በሚወነጨፈው ቨርጂን ባቡር የፈጀውን ይፍጅ ብዬ ከተሳፈርኩ ሁለት ሰአት ከ ሃያ ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስድብኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በአሜሪካን የቢልቦርድ ሰንጠረዥ ላይ የበላይነቱን የያዙትን ዜማዎች እና Laddy Gaga እና Tony Benett በጋራ ያወጡትን Cheek to Cheek የተሰኘውን አልበማቸውን ያካትታል።

ከይማም አባተ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አካባቢ በተለያዩ ኢትዮጵያዊያንን የተመለከቱ ጉባዔዎች፣ ስብሰባዎች፣ ሰልፎችና ሌሎችም ዝግጅቶች ላይ እንደ እርጎ ዝምብ ጥልቅ ማለት ልምድ ያደረገው እራን እንደ ጋዜጠኛና የመገናኛብዙሃን ባለቤት በማቅረብ ለወያኔ አሳፋሪና ወራዳ ተግባር በመፈጸም ላይ የሚገኘው መስፍን በዙ የተባለው ግለሰብ ስቴት …

“አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” መስፍን በዙ በስቴት ዲፓርትመንት Read more »

የትግራይ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት “ሉአላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ሰፋፊ ነጥቦችን የዳሰሰና ስህተቶች ነበሩ ያልዋቸውንም ያካተተ አዲስ መጽህፍ መጻፋቸው ይታወቃል። መጽሀፉን መሰረት በማደርግ አቶ ገብሩን አነጋግረናል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመጨረሻ የስራ ዘመናቸውን ዛሬ ለጀመሩት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት የመክፈቻ  ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መንግስት አምና እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮም ከኤርትራ መንግስት ለሚሰነዘር ማንኛውም ትንኮሳ ተመጣጣኝ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል። የኤርትራ መንግስት አስታጥቆ የላካቸውን የ ግንቦት7 ፣ ኦብነግና ኦነግ ጥቃቶችን መከላከላቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በዚህ አመትም …

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአሁን ቀደም  ከትርፍ አምራች የአማራ ክልል ወረዳዎች ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉ ቦታዎች አሁም ድረስ በሁለቱ ክልሎች መካከል የውዝግብ ምክንያት ሆኖ በቀጠለበት በዚህ ወቅት የአብደራፊ ከተማን ወደ ትግራይ ክልል ለመጠቅለል የሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ስጋት አሳድሮብናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልጸዋል። የክልሉ መሪዎች  ለአጎራባች ክልል ኢንቨስተሮችና …

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ  ማክሰኞ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ/ም በመተማ ወረዳ  ገንዳ-ውሃ ከተማ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ  በወሰደው እርምጃ የወረዳው ፖሊስ ኢንስፔክተር ዮሃንስ ይግዛው ሲገደል፣ ኮንስታብል ሻንበል አበበ በጥይት ተመቶ ክፉኛ ቆስሏል ብሎአል። ህዝብን እየበደሉ ባሉ የስርዓቱ ታጣቂዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ግንባሩ አስጠንቅቋል። ኢሳት የመተማ …

መስከረም ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ የዕንቁላል ምርቶች እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በአስደንጋጭ ፍጥነት እያሻቀበ መሆኑን ተጠቃሚዎች ገለጸዋል፡፡አንዳንድ አምራቾች በበኩላቸው እጥረቱ ያጋጠመው ከመኖ እጥረት ጋር በተያያዘ ነው ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተዘዋወርንባቸው ሳሪስ፣ ሾላ እና ካዛንቺስ አካባቢዎች በበርካታ መደብሮች የዕንቁላል ምርቶች ሰሞኑን ጨርሶ የሌለ ሲሆን አቅርቦቱ ባለባቸው መደብሮች የአንድ አበሻ …