የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን ያለውን ፍርድ ቤት ለመለየት የሚያስችለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሣኔ ዛሬም እንዳልደረሰው አስታውቋል፡፡

ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን የችሎት ውሎ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

በደቡብ ሱዳን ውጥረቱ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት ይፋ የሆኑ ዘገባዎች እንዳመለከቱት የምክትል ፕሬዚደንቱ ሪያክ ማቻር ታማኝ ወታደሮች የጆንግሌይ ስቴት ዋና ከተማ ቦርን ለመቆጣጠር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተሰምቷል።

ውጥረቱ በነዋሪው ሕዝብ ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተፅዕኖም ቀላል አይሆንም እየተባለ ነው።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማውጣት መንግሥት ምን እያደረገ ነው?

ዘጋቢያችን እእስክንድ ፍሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲን አነጋግሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በፅናትና በብልህነት፣ በይቅርባይነትና በትህትና ኑሮ መርተው ከጥቂት ቀናት በፊት ከዚህ ዓለም የተለዩት ኔልስን ማንዴላ በዘረኛው ሥርዓት ወኅኒ ተወርውረው ለረዥም ዓመታት ሲማቅቁ፣ ጥቁሩ ወገናቸው፤ ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት፣ ሽማግሌ ሳይባል ሲገደልና ሲታሠር፣ ሥርዓቱ ወንጀሉን እንዲያቆም ለመናገር የደፈሩ የዓለም አገሮች ከኢትዮጵያና ሌሎችም የአፍሪቃ አገሮች በስተቀር እንደ ኩባና ሶቪዬት ሕብረት ያሉ ጥቂት ሶሻሊስት አገሮች ነበሩ።

በዩናይትድ ስቴትስ ግን ማንዴላ ከእሥር ቤት እንዲፈቱ፣ በደቡብ አፍሪቃ እኩልነት እንዲሠፍን፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የጮኹና የነፃነቱን ትግል በዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ውስጥ ያቀጣጠሉ፣ የአፓርታይድ ሥርዓት የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተጥሎበት እንዲንበረከክ ያስቻሉ፣ ጥቁር አሜሪካዊያን የሲቪል መብቶች መሪዎች ናቸው፡፡

ትዝታ በላቸው…

ዋሽንግተን ዲ.ሲ ወደሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ትናንት ሐሙስ፣ ታኅሣስ 3/2006 ዓ.ም የሄዱ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ የዛሬ ሃምሣ ዓመት ለኔልሰን ማንዴላ የሰጠቻችውን ፓስፖርት የኮምፕዩተር ቅጂ አበርክተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የደቡብ አፍሪካው የጸረ-ዓፓርታይድ እንቅስቃሴ መሪና የነጻነት አባት ኔልሰን ማንዴላ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በዛሬው እለት በተካሄደ የጸሎት ስነ ስርዓት ታስበዋል።

በብሄራዊ ካቴድራል በተካሄደው በዚህ ሥነ ሥርዓት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፥ የኮንግረስ አባላትና ዲፕሎማቶች፤ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።