ወደ አሥራ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን እስከአሁን ከሣዑዲ አረቢያ አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ተመላሾቹን ለማቋቋም በፌደራል መንግሥቱና በክልል አስተዳደሮች የትብብር ሥራ እንደሚከናወንም መሥሪያ ቤቱ አመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ተፈፅሟል የሚል ዜና ከወጣ ጀምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፡፡

ዛሬ፣ ሐሙስ፣ ኀዳር 12 / 2006 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጅና ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ውስጥ ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡

ባለፉ ጥቂት ቀናት ውስጥም በእንግሊዝ፣ በጣልያን፣ በአውስትራሊያ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ደግሞ በዳላስ፣…

ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመሠረተባቸው ክስ ሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ያሉት የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ አዘጋጆች ጉዳያቸው አዲስ አበባ ላይ እንዲታይ ያቀረቡት ጥያቄ ዛሬም ተቀባይነት አላገኘም።

አዘጋጆቹ ወደፍሬ ነገሩ ገብተው እንዲከራከሩ ብይን የሰጠው የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለኅዳር ሃያ አምስት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የሳውዲ አረብያ መንግስት በቅርቡ “የመኖርያ ፈቃድ የላቸውም፤” ያላቸውን በዚያች አገር የሚኖሩ የውጭ አገር ሠራተኞች ለማስወጣት በያዘው ዘመቻ ከፍተኛ ግፍና በደል የደረሰባቸው ወገኖቻቸው ጉዳይ ነው በቁጣ ግልብጥ ያሉት ሠልፈኞች በዛሬው ዕለት ለቅዋሜ አደባባይ የወጡት።

በብዙ መቶዎች የተቆጠሩት ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ከዋሽንግተን ዲሲው የሳውዲ ኤምባሲ ደጃፍ ባካሄዱት በዚህ ሠልፍ፥ የሳውዲ መንግስት ‘ከአገሬ ውጡ!’ ያላቸውን የተለያዩ አገር ዜጎች የሰብዓዊ መብት እንዲያከብር፥ የኃይል እርምጃውን እንዲያስቆምና ተጠያቂ ይሆን ዘንድ ከልዩ-ልዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡትን ጨምሮ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎችና የማኅበራት ተጠሪዎች ባሰሙት ጥሪ ጠይቀዋል።

የዘገባውን ዝርዝር ለመስማት የሚቀጥለውን ይጫኑ።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ትናንት ዕሁድ ፤ ኅብር 8 / 2006 ዓ.ም ሊያደርግ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ኅዳር 29 / 2006 ዓ.ም ለማዛወር መወሰኑን አስታውቋል፡፡

መድረክ ሰላማዊ ሰልፉን ትናንት የሠረዘው የከተማዋ የሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባዎች ዕውቅና ሰጭ አካል ለመድረክ በፃፈው ደብዳቤ በዕለቱ በከተማይቱ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ስብሰባዎች እንደሚካሄዱ ገልፆ ለጥበቃ ይሠማሩ የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች ዕጥረት ስላለ የግንባሩን ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይችል በማስታወቁ መሆኑን የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

በመጭ ቀናትም በከተማይቱ ውስጥ ተመሣሣይ ክንውኖች ስለሚደረጉ በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎችን ማስናገድ እንደማይቻልም አስተዳደሩ መግለፁን ሊቀመንበሩ አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ…

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥራ አምስተኛ የወንጀል ችሎት በአቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ እንዲሁም አንዳንድ ተዋቂ ባለሃብቶች ላይ አቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክሥ በመደበኛው የሕግ ሥነ-ሥርዓት መሠረት እንደሚመለከተው ወሰነ።

የአንደኛውን ተከሣሽ የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ መመልከት ይችል እንደሆነ ለመወሰን ግን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ለዝርዝሩ የመለስካቸው አምሃን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ ሣዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ “ተፈፅሟል፣ እየተፈፀመም ነው” ያለውን ግፍ በመቃወም ዕሁድ፤ ኅዳር 8/2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡

የሰልፍ ዕውቅና የሚሰጠው ክፍል ግን በቃል አሉታዊ መልስ እንደሰጠው አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር በመቃወም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ፡፡

አዲስ አበባ በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አቅራቢያ በተሰባሰቡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ “ከፍተኛ ድብደባ፣ እንግልትና እሥር ተፈፅሟል” ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ድርጊቱን አውግዟል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር በበኩሉ ለቪኦኤ በሰጠው ቃል ሰልፉ “ሕገወጥ ነው” ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አዘጋጆቹ “ከሚመለከተው ክፍል ፍቃድ…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍበኛ መሻሻል ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ፈባጠን አካሄድ አፍሪካን አልፎ በቀሪውም ዓለም መድረክ ሊያሣትፈው የተቃረበ ይመስላል፡፡

ነገ፣ ቅዳሜ ኅዳር 7/2006 ዓ.ም ከናይጀሪያ አቻው ጋር በሚያደርገው የመልስ ግጥሚያ አስፈላጊውን ሁሉ አሟልቶ ካሸነፈ በመጭው ሰኔ ብራዚል በምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ አህጉሪቱን ከሚወክሉ አምስት የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች አንዱ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ለዚህ ወሣኝ ፍልሚያ ቡድኑ “ብቃት ያለው ዝግጅት አድርጌአለሁ” ይላል፡፡

ሰሎሞን ክፍሌ የነገው የመልስ ጨዋታ ወደሚካሄድባት የናይጀሪያ ከተማ ካላባ ደውሎ የቡድኑን ዋና አሠልሐኝ ሰውነት ቢሻውንና ሌሎችም የቡድኑን አባላት አነጋግሯል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ፌደራል አቃቢ ሕግ “የግንቦት ሰባት አባል በመሆን” ና “የሽብር ወንጀል ፈፅመዋል” ሲል በሃያ ሰዎች ላይ ክሥ መሥርቷል፡፡

ሰዎቹ መቼ እንደታሠሩ ግን አልገለፀም፡፡

ጉዳዩ እየታየ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን ተከላካይ ጠበቃ ያቀረበው የክሥ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ሆኗል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የአንዳንድ ተከሣሾች ጉዳይ በሌሉበት መታየት ጀምሯል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቹ ወደሀገራቸው እየተመለሱ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱም ከሳዑዲ አቻዎቻቸው ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሣደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ሪያድ መጓዙ ተገልጿል፡፡

ሰሞኑን መግለጫ እያወጡ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን መንግሥት ለእርምጃው ዘግይቷል፥ የበለጠ ሥራም ይጠብቀዋል ይላሉ።

በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ለነገ ጥሪ የበተነው መኢአድ የሌሎች አንዳንድ ሃገሮች ዜጎች መብቶች ከኢትዮጵያዊያኑ በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠበቅና በኢትዮጵያዊያን ላይ ግፍ ሲደርስ ግን የአሁኑ የመጀመሪያ አለመሆኑን የድርጅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ አመልክተዋል፡፡

ዛሬ መግለጫ ያወጣው ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ነገ ዐርብ፣…

“የወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል መሪ ቃል የተጠራ የኢትዮጵያዊያን ሰልፍ ዛሬ፣ ኅዳር 5 / 2006 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የሣዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ደጃፍ ላይ ተካሂዷል፡፡

በሰልፉ ላይ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ሣዑዲ አረቢያ ለሚገኙ ወገኖቻቸው ጥበቃ እንዲደረግ፣ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ፣ በአፋጣኝ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቀዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በቁጫ ወረዳ፥ ከ 20 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ከ 100 በላይ ተማሪዎች፥ መምህራንና አርሶ አደሮች መታሠራቸውም ይነገራል።

ከወረዳው ባለሥልጣናት ጉዳዩን ለማጣራት ባባለፉት ሁለት ቀናት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

መለስካቻው አምሃ ተከታዩን ከአዲስ አበባ ልኳል።