የደቡብ ሱዳን አማጺያንና መንግሥት በጠብ ያለመፈላለጉን ስምምነት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ እንዲፈራረሙ ዩናይትድ ስቴትስ ጠይቃለች፡፡

ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪርም ታሣሪዎቹን የሱዳን ሕዝብ አርነት ንቅናቄ – ኤስፒኤልኤም አመራር አባላት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርባለች።

ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ወገኖች ዛሬም ለሦስተኛ ቀን ፊት ለፊት አልተወያዩም።

የተያያዘው የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ያዳምጡት

በሕዋ ሣይንስ ዘርፍ የሚሠራው የሥነ ፈለክ ኅብረት አሥራ አራት አገሮችን የሚያስተባብር ፅሕፈት ቤት አዲስ አበባ ላይ ለመክፈት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

የፅሕፈት ቤቱ አዲስ አበባ ላይ መከፈት ኢትዮጵያን ይበልጥ ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል የኢትዮጵያ የጠፈር ሣይንስ ማኅበረሰብ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተፈራ ዋልዋ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ወሎ፥ ቦረና ውስጥ ካሁን ቀደም የማይታወቁ ጥንታዊ የድንጋይ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን ማግኘታቸውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች አስታወቁ።

አብያተ ክርስቲያናቱ ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውንም ባለሞያዎቹ አክለው አስረድተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መብቶች መከበር የሚሟገተው ዓለምአቀፍ ጥምረት የ30 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት – አይኦኤም ዛሬ አበረከተ፡፡

ደቡብ ሱዳን ውስጥ የተቀሰቀሰው ግጭት መላውን ዓለም አሳስቧል ማለት ይቻላል።

ደም አፋሳሽ የሆኑትን ግጭቶች ለማስቆም የታቀደውና በምሥራቅ አፍሪካው የጋራ ልማት ተቋም – ኢጋድ የተዘጋጀው የሰላም ንግግር የመጀመሪያው ዙር ውይይት በሸራተን አዲስ ነገ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

የደቡብ ሱዳንን ሁኔታ እንዲገመግሙ ዶክተር ሰሎሞን መብሪን ጋብዘናል፡፡

ዶ/ር ሰሎሞን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስና ዓለምአቀፍ ትምህርት ክፍል መምህር ናቸው። እስክንድር ፍሬው ነው ያነጋገራቸው።

ለሙሉው ውይይት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡