ማክሰኞ፣ ታኅሣስ 1/2006 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ በብዙ አሥር ሺሆች የተቆጠረ ህዝብ ዕኩልነትን ዕውን ለማድረግ አስቸጋሪ የሆነ የረጅም ጊዜ ትግል ያካሄዱትን የፀረ-አፓርታይድ ትግል መሪውን ኔልሰን ማንዴላን ተሰናብቷል።

በጆሐንስበርግ ሶከር ሲቲ ስታዲየም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማንና የቀደሙ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ በርካታ ታላላቅ ዕንግዶች፣ ታዋቂ ሰዎች እና ደቡብ አፍሪካዊያን መጥፎ የአየር ሁኔታ ሳይበግራቸው እኒህን ሁሉ ሰው ”ታታ” እያለ በፍቅር የሚጠራቸውን ሰው በአክብሮት ለመሰናበት ተገኝተዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1962 ዓ.ም ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ሥልጠና ስትፈቅድ የማሠልጠኑን ኃላፊነት የተወጡት ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ ትውስታቸውን ለቪኦኤ አካፍለዋል።

ሥልጠናው “እጅግ ምሥጢራዊ ነበር” ይላሉ የ77 ዓመቱ ጡረተኛ ኮሎኔል።

ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔን በአዲስ አበባ መኖርያ ቤታቸው ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ያዘጋጀው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ያዳምጡት፡፡

የአዲስ አባብን ገጽታ ለመቀየር በወጣው ትልቅ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ውጥኖች መሰረት ሰፊ የግንባታ ስራ እየተካሄደ ነው። አንድን የሀገር መዲናን በአጭር ጊዜ ለመቀየር የሚደረግ ጥረት አንደምታም ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል።

ላሳለፈነው ሰኞ ተቀጥሮ የነበረው በእሥር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ ኅብረተሰብ ጥያቄ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የእነ አቡበከር አሕመድ ጉዳይ ለፊታችን ታኅሣስ 3/2006 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

የሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኛ ሠራተኞች ላይ እንደደረሱ በስደተኞቹ የሚገለፁ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችን የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት እንዲያጣራ የመብቶች ተሟጋች ቡድኑ ሂዩማን ራይትስ ዋች ጠየቀ።

ቡድኑ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች በሳዑዲ ደረሱብን ያሏቸውን የመብቶች ረገጣዎች በዝርዝር አስቀምጦ፤ ጉዳዩ ተጣርቶ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር – ዩኤንኤችሲአር ከሳኡዲ አረቢያ እየተመለሱ ላሉ ኢትዮጵያዊያን የፍልሰት ሠራተኞች ሰብአዊ እርዳታ ማድረግ መጀመሩን ገልጿል።

እርዳታው ከኮሚሽኑ ግዴታ ውጭ ቢሆንም ሰብአዊ ቀውስ ሲከሰት በዝምታ ማለፍ እንደማይቻልም አመልክቷል።

ይህ እርምጃ በቅርቡ አንዲት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣን ሰጡ…

ገቢዬን ከሌቦች ጋር እየተጋራሁ ነው ሲል ያማረረው ኢትዮ-ቴሌኮም በተለይ ከውጭ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ የሚደወሉት ስልኮች በሕገ ወጦች በኩል የሚያልፉበት ሁኔታ መኖሩን አስታውቋል።

ከውጭ ሀገር በሚደወሉ ስልኮች ላይ የጥራት ችግር የሚያጋጥመውም በዚሁ የተነሣ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽንስ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አብራርተዋል።

አቶ አብዱራሂምን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ያጠናቀረውን ዘገባ የያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኤችአይቪ ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር ፓትሪሽያ ሃስላክ ገለፁ፡፡

ምናልባትም ሃገሪቱ ከኤድስ ነፃ ትውልድ በመፍጠር ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለኤድስ አጣዳፊ ድጋፍ መርኃግብር – ፔፕፋር አሥረኛ ዓመትም አዲስ አበባ ላይ በአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከብሯል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያን መንግሥት ወክለው የተገኙት የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ፈይሣ የተገኘው ውጤት ሊቀለበስ እንደማይችል ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

እስካሁን ባሉት አመልካች ሁኔታዎች ከተሄደ ኢትዮጵያ በመጪው አስር ዓመታት ጊዜ ዉስጥ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመሆን ግባቸው እንደሚሳካ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በተከፈተዉ የአፍሪቃ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቶች ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈኛ ንግግር ነው አገራቸው በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ነዳጅ አምራች ያልሆኑ አገሮች አንዷ መሆኗን የተናገሩት።

“ፖሊሲዎቻችንና ስታራቴጂዎቻችን ብቃትና ጥራታቸዉን አረጋግጠዋል። እናም አሁን ያሉትን አመልካቾች ከተከተልን፥ ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አስር ዓመታት ጊዜ ዉስጥ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመሆን ግባችንን እናሳካለን፤” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ እምነታቸውን ገልጠዋል። የዛሬውን ጉባኤ ያዘጋጀዉ ከአርባ በላይ አገሮች ብሔራዊ ምክር ቤቶች አባል የሆኑበት የፓን…