የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 90 ይከበር!

Image

‪#‎stopbanningofhijab‬

መንግስት በሰኪዩላሪዝም ሽፋን ህዝብን ሀይማኖት አልባ ለማደረግ የጀመረውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ያቁም!

የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 90(2) የሚደነገገው ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተጽእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዳለበት ያስቀምጣል። የዚህን አንቀጽ ቀጥተኛ ትርጓሜ ስንመለከት በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጥ ትምህርት አንድን ሃይማኖት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አቋም ወይም የተወሰነ ማህበረሠብን ባህልና እሴት ማንጸባረቅ አይኖርበትም። በተጨማሪም የአንቀጹን ትርጓሜ በምንመለከትበት ወቅት አንቀጹ ”ትምህርት” እንጂ የትምህርት ተቋማት እንደማይል እንገነዘባለን::

ይህም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገራችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች በእኩልነት ተቻችለውና ተከባብረው የሚኖሩባት ስለሆነች ሁሉም የሃገሪቷ ዜጎች ትምህርት ላይ እኩል ተጠቃሚ እንደሆኑም ጭምር የሚያረጋግጥልን አንቀጽ ነው::

በአሁን ሰዓት የመንግስት አካላት ይህን አንቀጽ በመጥቀስ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት ውስጥ ሃይማኖታዊ ቀኖናዎችንና ማንነታቸውን እንዳተገብሩ እየከለከሉ ይገኛሉ፡፡ ይህን የህገ መንግስቱን አንቀጽ በሚቃረን ሁኔታ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ላይ የራሱን ስልጣን በመጠቀም ትምህርት የሚለውን የትምህርት ተቋም የሚል ትርጓሜ ሰጥቶት የግልም ሆነ የጋራ(ስብስብ) ሀይማኖታዊ ቱፊቶችን(አለባበስ፣ አመጋገብ እና ፀሎት) እንዲከለከል አድርጓል::

የአንቀጹን ትክክለኛ ትርጓሜ ስንወስድ ግን በቡድን የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ስርዓቶችንም ይሁን በግል እሚፈጸሙትን በምንም አይነት መልኩ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ አያሳድር:: ከላይ የተጠቀሱት አንቀጾች ግን በቡድንም ይሁን በግል እሚፈጸሙትን ሃይማኖታዊ ስርዓቶችንም ከዚሁ የህገ መንግስቱ አንቀጽ አያይዘው ትክክለኛ ያልሆነ ትርጓሜ በመስጠት በርካቶችን ከትምህርት ገበታ እያባረሩ ፣ በርካቶችንም እያሰሩ ይገኛሉ፡፡

የሀገራችን Secularism ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ሁለት አበይት ነጥቦች ማካተት ይኖርበታል፡-

1/ Secularism ከአሁን በፊት በኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ በሰፊው የተስተዋለውን ያልተገባ የሃይማኖቶች ግንኙነት በማረም የአንድን ሃይማኖት የተናጥልና ኢ-ፍትሃዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጫና በማስወገድ የሃይማኖቶችን እከኩልነት ማረጋገጥ፣

2/ የSecularism አንፃራዊ ባህርይ በመገንዘብ የመንግስትና የሃይማኖት መነጣጠል የኢትዮጵያን ሃይማኖቶች ባሕርይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም Secularismን ከምዕራቡ Judeo- Christian ባህል አኳያ ብቻ ማየቱ በኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ ሁሉም ሃይማኖቶች አግባብነት ላይኖረው ስለሚችል ነው፡፡

የኢትዮጳያ መንግሰት Secular መሆኑን ለማረጋገጥ የወጡ የህገ-መንግስት ድንጋጌዎችም ከአጠቃላይ የ Secularism ዕይታ፣ ከሕገ-መንግስቱ አጠቃላለይ መንፈስና ዓላማ አንፃር እንዲሁም የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊተረጎሙ ይገባቸዋል፡፡ በጥቅሉ Secularism ማለት ሀይማት አልባ መንግስት መመስረት እንጂ ሀይማኖት አልባ ህዝብ መፍጠር አይደለም፡፡ ስለዚህ መንግስት ሀይማኖት አልባ ህዝብ ለመፍጠር እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም!

በተማሪዎች( በተለይ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ) ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆምልን እንጠይቃለን፡፡ ተማሪዎች የተነፈጉትን መብት እስኪመለስላቸው ድረስ እኛም ፀንተን እንታገላለን!

የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 90 ይከበር!

በሰኪዩላሪዝም ሽፋን የሚፈፀመው የሂጃብ ገፈፋ በአስቸኳይ ይቁም!!!

አላሁ አክበር!!!