ሞክረው ( ሄኖክ የሺጥላ )
ሞክረው ( ሄኖክ የሺጥላ )
ትናንት ባህርዳር ላይ አማሮች ተገደሉ ፣ ከትናንት በስትያ አምቦ ላይ ኦሮሞዎች ፣ ከዛ በፊት ጋምቤላ ላይ ፣ ከዛ በፊት አርባ ጉጉ ላይ ፣ ከዛ በፊት በደኖ ላይ ፣ እያለ እያለ ይቀጥላል ። በዘር የከፋፈልነው ሬሳ ኢትዮጵያዊ መሆን ያቃተው ለምን እንደሆነ ባላውቅም አንተ አዛኝ ቅቤ አንጉዋች ግን ምን ታመጣለህ ። ግፋ ቢል ሁለት ገጽ የ ፒዲ -ኤፍ ( PDF ) መግለጫ ታወጣለህ ፣ ትንሽ ትዝታለህ ፣ ትንሽ ትሳደባለህ ፣ አይቀርም በቅርብ ምናምን ብለህ ተስፋ ትሰጣለህ ፣ ግድያው ይቀጥላል ።
ውስጥ ውስጡን የሸዋ አማራ ለኢትዮጵያ ጂው ነው ፣ ወይጦው ጅን ነው ፣ ጎጃሜው አድር ባይ ነው ፣ ጎንደሬው ሲፋቅ ትግሬ ነው ፣ መንዜው በጥርሱ እየሳቀ ገዳይ ነው ፣ ወዘተ ወዘተ ትላለህ ። ውጭ ውጩን የአማራ ታጋይ!!!
ኦሮሞውም ጋ እንዲህ ነው ፣ ወለጋ ኮለል ያለ የጠራ ኦሮሞነት መስፈሪያ ነው ፣ የሰላሌ ኦሮሞ አማራነት ያለቀቀው ኦሮሞ ነው ፣ የሸዋ ኦሮሞ ኦሮሞ አይደለም ፣ የባሌ ኦሮሞ ለ አረብነት ይቀርባል እና ወዘተ፣ ውስጥ ውስጡን ልብህን ያደነደነው ነገር ነው ። ዝለዚህ ከዚህ በሽታህ እስካልዳንክ ድረስ ግድያው ይቀጥላል ፣ አንተም መግለጫ እየሰጡ መኖሩን ትቀጥላለህ ።
ስልጤውም ጋ ፣ ሶዶ ጎርደናውም ጋ ፣ ሰባት ቤቱም ጋ ፣ ቅማንቱም ጋ ( ቅማንት የሚባል ነገር ካለ ) ፣ ይሄ በሽታ አለ ። ይሄን በሽታህን ፣ ይሄን የመከፋፈል ነቀርሳህን ሳትድን ፣ ከቁጭት ውጭ ምንም አታመጣም ። አንዳች ለውጥ በሀገርህ ምድር አይፈነጥቅም ።
እስኪ አምላክ ያሳይህ ትናንት በ ሰሜን ጎንደር ቅማንት እራሱዋን በራሱዋ ታስተዳድር ዘንድ አንዳንድ ሽር ጉዶች እየተደረጉ እንደሆነ ሰማን ፣ መቼም መስማት እምቢ አይባልም ፣ ከመሃል ጎንደር እስከ መተማ ጎንደር ልጆቿን ልትበላ ይኸው ሌላ ውርጅብኝ ሊወርድባት ነው ። አንተ ግን ይሄን ሁሉ የሚያረገው ከትግሬ ክፍለ ሀገር የመጣ ከይሲ ስርዓት ነው ማለት ልብህ ይፈራል ።ጠላቶችህን በስማቸው ለመጥራት ልብህ ይራራል ።
ሌላም ታሪክ ልንገርህ
ጅማ ላይ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲያስቀድሱ የተገደሉትን ሰዎች አይተካል ፣ ታዲያ ማን ይመስልሃል ገዳዩ ? ኦሮሞዎች ? አይደለም ! አየህ ያንተ ችግር ይሄ ነው ወያኔ እንድታስብ የሚፈልገውን ነው የምታስበው ፣ ግድያውን የፈጸሙት ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ድርጊቱን ያሴረው ግን አሁንም የትግሬ ወያኔ ነው ፣ ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲነሳ ያደረገው ። ጅማማ እኮ ጂማ! የሰቃ ጨቆርሳ ሀገር! የጌራ ሀገር! የጉማ ሀገር! የጎማ ሀገር! የሊሙ ሂናሪያ ሀገር! አምስቱ የጊቤ መንግሥታት የለመለሙባት ምድር!!
ጅማ! የአባ ሚዛን ሀገር! የአባ ቆሮ ሀገር! የአባ ገንዳ ሀገር! የአባ ዱላ ሀገር! በኦሮሞ ምድር የዘመናዊ ቢሮክራሲ ጥንስስ የተጀመረባት ሰፈር!
ጅማ! የአቦል ሀገር! የበረካ ሀገር! የቃህዋ ጀባ ሀገር! ለስምንት መቶ ዓመታት ተወዳጅነቱ ሳይቀንስ የዘለቀውን “ቡና”ን ለዓለም ያበረከተች የሙሐባ መንበር!! ጅማ! የተሚማ ሀገር! የገሜቲ ሀገር! የአያንቱ ሀገር! የአስሊያ ሀገር! የበድሪያ ሀገር! የፈይሩዝ ሀገር! ውብ ልዕልታትና ወይዛዝርት የወጡባት ምድር!! ነች ይላታል ጸሐፊው ፣ ጅማ ይህንን አታደርግም ፣ ጅማ ላይ አታቂም ፣ አይንህን ወደ ሰሜን ፣ ልብህን ወደ ትግሬ ወያኔ አዙር !
ይገሉሃል አንተ ግን ባጉል ፍቅር ታጥረሃል ፣ ያጠፉሃል አንተ ግን የትግሬ ወያኔ አጥፊህ መሆኑን መናገር ትፈራለህ ፣ መነኩሴ በጥይት ሲመቱ አንተ ዘረኛ እንዳትባል ትፈራላህ ፣ ሀጻናት ሲገሉ አሁንም በስማቸው ለመጥራት ትፈራለህ ፣ ማን እንደሆኑ እያወቅህ " እነ አከሌ " ለማለት በጣም ትፈራለህ ፣ በልብህ ትታበያለህ ፣ በአንደበትህ ትስታለህ ፣ በልቦናህ ግን ከራስህ ጋ ትነጋገራለህ ። ጠላትህን በስሙ እስካልጠራኸው ድረስ አታሸንፍም ፣ ጠላትህን እስካላስገለልከው ድረስ በፍጹም ነጻ አትሆንም ። ገዳዮችህ ሩቅ አይደሉም፣ ብዙዎቹ ያንተ ጎረቤቶች ናቸው ፣ ካንተ ጋ እየበሉ ፣ ካንተው ጋ እየጠጡ የሚውሉት የትግሬ ወያኔዎች ናቸው ይሄን ሁሉ በደል እያደረሱ ያሉት ፣ ይሄንን አንተ አታውቅም ብዬ አላስብም ፣ እርግጥ በደንብ ታውቃለህ ግን እውቀትህ ከውስጥ የማይወጣ የጋን መብራት አይነት ሆነብኝ ፣ ጠላትህ ለመለየት አተኩረህ እየው ( ግንባሩን እየው አላልኩም ) ግንባሩ ፍንጭ ከሰጠህ ማየት መብትህ ነው ፣ ግን አተኩረህ ካየኸው ታውቀዋለህ ። እሱ አንተን ለማጥፋት አንዳች ይሉኝታ የለውም ታዲያ ያንተ የሉኝታ ከወዴት የመጣ ይሆን ። ነገርኩህ እኮ እነሱ ( የትግሬ ወያኔዎች ) ሊገሉህ ኢያሰቡም እንኩዋ ይወልዱልሃል ። ግማሹ ጦርነት ጠላትን ማወቅ ነው ይላሉ አንዳንድ አዋቂዎች ፣ ይህ ትልቅ እውነት ነው ፣ የተቀረው ግማሹ ደሞ ጦርነት መግጠም እንዳይመስልህ ፣ የተቀረው ራስን ማወቅ ነው !
ጠላትህን እስካለየህ ድረስ ጠላትህን አታሸንፈውም ! ይሄ የ ስደት ፖለቲካውን እርሳው ፣ ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል ነው ፣ አንተ ግን ጠላትህን በስሙ ጥራው ። የትግሬ ወያኔ ጠላቴ ነው በል ፣ እሱን ማለት ስትጀምር ማሸነፍ ትጀምራለህ ። ሞክረው! ሞክረው ! ሞክረው !