የሰማያዊ ፓርቲ ታጋዮች ኢየሩሳሌም ተስፋው እና እመቤት ግርማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

“የታዛቢዎችን ምርጫ ለማወክ ተንቀሳቅሳችኋል::” – ፖሊስ ===== Minilik Salsawi
ዛሬ በየቀበሌው የሚካሄደውን የታዛቢዎች ምርጫ ተከትሎ ወደ ሚኖሩበት ጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ 3 ያመሩት የሰማያዊ አባላቶቹ ኢየሩሳሌም ተስፋው እና እመቤት ግርማ የታዛቢዎችን ምርጫ ለማወክ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የምርጫ ታዛቢ መሆን የሚችሉት ገለልተኛየሆኑ እንጂ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ አይደሉም በሚል ባነሱት ክርክር ምክንያት ለማወክ እየሞከራችሁ ነው በሚል ፖሊስ ሊይዛቸው ችሏል፡፡

Image