የአሥር ድርጅቶች ስብስበ የሆነው ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አመራር አባላት ከመኢአድ እና አንድነት ጋር በመሆን በባህር ዳር ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመልክታል። የትብብሩ መስራች ድርጅቶች ዉስጥ የሐዲያ ብሔር አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ፣የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፣ የሶዶ ጎርደና ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የከምባታ ሕዝቦች ኮንግሬስ ፣ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣የመላው ዐማራ […]

አንድነት – የባህር ዳር ሰልፍን በተመለከተ የዛሬ የካቲት 15 ዉሎ – የባህር ዳር፣\ ሰልፍ ተሟሙቆ ዋለ – የአመራር አባላትን በሆቴል ቤታቸዉ እንገድላቹሃለን እየተባሉ ነው – ከባህር ዳር አካባቢ ያሉ እንቅስቃሴውን እዬትቀላቀሉ ነው – 10 ድርጅቶች ስብስብ የሆነው የትብብር አመራሮች መኢአድ እና አንድነት ተቀላቅለው እየቀሰቀሱ ነው የባህር ዳር ሰልፍ ነገ የካቲኡት 16 ቀን ከጠዋቱ 3 ሰዓት […]

“አንድነትን በመግፋት መድረክን ወደ አክራሪ ብሔረተኛ ስብስብነት ለመግፋት የተደረገ ስልታዊ ውሳኔ ነው” የአንድነት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተክሌ በቀለ መድረክ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውጤት ያመጣ ስራ እየሰራ የሚገኘውን አንድነት ፓርቲን ማገዱ ትዝብት ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው፡፡” የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ አባል ፓርቲዎች አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ማገዳቸውን ዛሬ […]

አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣ ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል። ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር። ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ። ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ። በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር። ለሰይጣን፣ ለዚያውም […]

የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን በግልፅ እመራዋለሁ የሚለውን ህዝብ በመሳደቡ ያለምንም ማንገራገርና ማምታታት ይቅርታ ጠይቆ እራሱን ለፍርድ ማቅረብ አለበት፣ ማስተዋሉ ካለው፡፡ በርግጥ የኢህአዴግ መሪዎች የህዝብና የሀገር ክብር እንደሌላቸው ግልፅ ነው፡፡ ያው በትዕቢትና በጠመንጃ እንጂ አንዳቸውም ህዝባዊ ፈቃድና ይሁንታ አግኝተው እንደማይመሩ እራሳቸውም ያውቁታል፡፡ ነገር ግን እንደ አቶ አለምነው መኮንን በቆሸሸ […]

በዛሬው እለት 14/06/2006 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአንድነትና የመኢአድ አባላት በሞንታርቦ በመቀስቀስ ላይ ሲሆኑ በራሪ ወረቀት የሚያድሉ አባላት በፍፁም ቁርጠኝነት የብአዴኑ ባለስልጣን የተናገሩትን በመቃወም በባዶ እግራቸው በከተማዋ በመዘዋወር ለህዝቡ ግንዛቤ እየፈጠሩና በራሪ ወረቀቶችን እያደሉ ሲሆን የከተማው ነዋሪ በቁጭት አጋርነቱን እየገለፀ ይገኛል። በረዳት አንስፔክተር ክንፈ ሀይሌ ጉልላት የሚመራ የፖሊስ ሀይል በተለምዶ ከአባይ ማዶ በሚባለው አካባቢ የመኪና ላይ […]

ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች […]

«በባህር ዳር ከተማ፣ ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣ ሁሉም ድጋፉን ይስጥ» ሲል የበርካታ አንጋፍ ደርጅቶች እና ሲቪክ ማህበራት ስብስብ የሆነው ሸንጎ ለመኢአድ እና አንድነት አጋርነቱን ፣ የካቲት 10 ቀን ባወጣዉ መግለጫ ገለጸ። «የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ ከመኢአድ ጋር በመሆን በባህር ዳር ከተማ የካቲት 16 ቀን፣ ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣ ያለውን ድጋፍ ይገልጻል» ሲል […]

አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤ እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ […]

ኢሕአዴግ ሕዝብን የሰደቡና ያዋረዱ የብአዴን አመራር አባል አቶ አለምነህ መኮንንን ተጠያቂ በማድረግና ከሃላፊነታቸው ከማንሳት ይቅል፣ ከጎናቸው መቆሙን አረጋገጠ። መኢአድ እና አንድነት ፣ በአማራዉ ክልል የሚኖረው ሕዝብ ላይ ከአንድ መሪ የማይጠበቅ አሳዛኝ፣ ንቀት አዘል አስተያየት የሰጡት አቶ አልምነዉ መኮንን ከሃላፊነታቸው እንዲነሱና ለፍርድ እንዲቀርቡ መጠየቁ ይታወቃል። ኢሕአዴግ ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን ጥያቄ አናንቆ፣ ምንም ምልሽ ባለመስጠቱ፣ አንድነት እና መኢአድ […]

አቶ አልምነው መኮንን በ«አማራዉ» ላይ በተናገሩት የንቀት አባባሎች ምክንያት፣ ባለስልጣኑ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱና ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ አንድነት እና መኢአድ በመጠየቅ የክልሉ መስተዳደር በሚገኝበት በባህር ዳር ከተማ እሁድ የካቲት 16 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱ ይታወቃል። በባህር ዳር ቅስቀሳው እየተፋፋመ ባለበት ወቅት፣ አቶ አልምነዉ መኮንን ማስተባበያ በኢቲቪ እየተላለፈ መሆኑ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡክ የሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስ ቡክ ፔጅ […]

አንድነት እና መኢአድ በባህር ዳር ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል። ሕገ መንግስቱን በመጻረር ፣ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታቸውን በመገፋት የብአዴን ካድሬዎች የተለያዩ ምክንያቶ እያቀረቡ የሰልፉ አስተባባሪዎች የማገት፣ የማስፈራራት ሥራ እየሰሩ እንደነበረ የደረሰን ዜና ይጠቁማል። አንድነት እና መኢአድ በባህር ዳር ቅስቀሳቸውን ቀጥለዋል። ሕገ መንግስቱን በመጻረር ፣ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታቸውን በመገፋት የብአዴን ካድሬዎች የተለያዩ ምክንያቶ እያቀረቡ የሰልፉ […]

የካቲት 16 በሚደረገዉ የባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት በጋራ የጠሩት ነዉ። ድርጅቶች እንዲህ ሲተባበሩ ያስደስታል። የተናጥል የብቻ ጉዞ የትም አይደርስምና። ይህ ሰልፍ ምንም እንኳን የብሃአዴን አንድ አመራር አባል ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጉዳዩ ከአንድ ግለሰብ ያለፈ መሆኑን መረዳት አለብን። ባለስልጣኑ ጸያፍና ነውረኛ አስተያየት ሰጡ የሚል ክስ ሲቀርበባቸው ፣ ገዚው ፓርቲ ፣ ግድ የለም፣ አሁኑኑ […]

ግብጾች ሱዳን ኢትዮጵያ እና ግብጽ እያደረጉት ከነበረው የሶስትዮች ድርድር እራሷን ማግለሏ ይታወሳል። የግብጽ ሜዲያዎች በዚህ ጉድያ ጉዳይ ላይ በስፋት እየዘገቡ ሲሆን ጸረ-ኢትዮጵያ ዘመቻና ፖሮፖጋንዳዉን በስፋት ተያይዘዉታል። የቻይናዉ CCTV በዚህ ጉዳይ ያቀናበረዉን ለማየት እዚህ ይጫኑ።

(በፋክት መጽሔት ቅጽ 2 ቁጥር 33 የካቲት 2006 ታትሞ የወጣ) ሕፃን እዮሲያስ የጓደኛዬ ልጅ ነው። በሰባት ዓመቱ ሁለተኛ ክፍል ገብቷል። ፈጣንና መጠየቅ የሚወድ ታዳጊ ነው። ባገኘኝ ቁጥር በጥያቄ ልቤን ጥፍት ያደርገዋል። አብዛኛው ጥያቄዎቹ ትምሕርት ቤት ከጓደኞቹ ጋራ ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚመነጩ ናቸው። ባለፈው ሰሞን እንዲህ ብሎ በእንቆቅልሽ መልክ ጠየቀኝ። ለእኔም አጠያየቁ ልጅነቴን ስላስታወሰኝ በትዝታ ፈገግታ ታጅቤ […]

«መንግስት የነዳጅ ዋጋን ማረጋጋት አለበት» (ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ብሩህ ተስፋ) «ባለፉት 8 ዓመታት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአራት እጥፍ በላይ አድጓል» «የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መንግስት ለዜጎቹ ግድ ማጣቱን አመላካች ነው፡፡» (የከተማዋ ነዋሪ) የስምንት ዓመት የዋጋ ንረት 1998 2006 ቤንዚን 6.57 20.47 ነጭ ጋዝ 3.45 15.75 ታክሲ (አጭር ርቀት) 0.60ሳ 1.50 ታክሲ (ረዥም ርቀት) 1.25 3.00 አንበሳ አውቶብስ […]

ልማታዊ ጋዜጠኛ፣ ልማታዊ ነጋዴ፣ ልማታዊ መመህር፣ ልማታዊ ሃኪም፣ ልማታዊ ቄስ፣ ልማታዊ ሼክ—- ልማታዊ የሚል መዳልያ ከኢህኣዴግ የሚገኝ ትልቅ የክብር ሽልማት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ኣይነት ሽልማት የሚሰጣቸው የተወሰኑ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህም ኢህኣዴግ በህዝብ ላይ የፈለገውን አፈና ሲፈፅም ፣ የሃገር ኢኮኖሚ በሙስና ሲበዘብዝ ለምን ያማይሉ፣ ለሂሊናቸው ሶይሆን ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩና ለታሪክ ደንታ ቢስ የሆኑ ሁሉ በኢህኣዴግ […]

አገሬን ለቅቄ ስደት የጀመርኩት በ1984 ነዉ። ኢሕአዴግ ስልጣን በጨበጠ በአንድ አመቱ። ከአስራ አራት አመታት በኋላ ለአንድ ወር ጉብኘት ቦሌን ረገጥኩ። እሑድ ቀን ፣ ግንብት ሰባት 1997 ነበር። ከዚያ በፊት ብዙም የፖለቲካን ነገር አልከታተለም ነበር። ምርጫ እንደሚደረግ፣ ቅንጅት ሕብረት እየተባለ የምርጫዉ ዘምቻ እንደተጧጧፈ ያወኩት ትኬት ከቆረጥኩ በኋላ፣ ከምርጫዉ 15 ቀናት በፊት ነበር። በአጭሩ አባባል፣ በአገሬ ዉስጥ […]

አንድነት በዚህ ጉዳይ ላይ ለየካቲት 16 ሰልፍ የጠራ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን በኦንላይን ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ፔተሽን ይፋ አደርጓል። ወደ ፔትሽኑ ለመሄድና ለመፈረም እዚህ ይጫኑ

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፣ በባህር ዳር ከተማ የካቲት 16 ቀን ፣ ከመኢአድ ጋር በመሆን በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ፣ የባህር ዳር እና የአካባቢዉ ሕዝብ፣ በነቂስ እንዲወጣ፣ ከፍተኛ የቅስቀሳ ዘመቻ እንደተጀመረ የሚገልጹ ዘገባዎች እየደረሱን ነዉ። «አንድነታችን ከልዩነቻትን በላይ ነው» ፣ «የአማራዉን ሕዝብ ያዋረዱ የብአዴን/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ» «ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በባህር ዳር ከተማ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም፣ […]

በመጀመሪያ በአቅርቡ በተከታታይ ለአንባቢያን ያቀረብኩዋቸውን ሁለት ጽሁፎች አንብበህና ጊዜህንም ወስደህ በዝርዝር ላቀረብከው የሙግት ሃሳብ ምስጋናዮ የላቀ ነው። ለነገሩ የጽሑፌም ዋና አላማ ጉዳዩን ሕዝብ እንዲያውቀው ብቻ ሳይሆን በተነሱት ነጥቦችም ዙሪያ በአንባቢዎች ዘንድ የውይይት ሃሳብንም በማጫር ጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝም ጭምር ስለሆነ ያንተ ምላሽ እኔንም በዚሁ ጉዳይ ላይ በድጋሚ እንድመለስበት አድርጎኛል። ምንም እንኳን ባነሳሃቸው በርካታ ሃሳቦች ፍጹም […]

“ለወደቀ ዛፍ ምሣር ይበዛብታል” እንደሚሉ ሆኖ ነው መሰል አገራችንን እትዮጵያንና ሕዝቧን ከያቅጣጫው የገጠማቸው ችግር ከመቼውም የበለጠ የሚያስደነግጥና፤ ሊታመንም በማቻልበት ሁኔታ በጆሮ ለመስማት እንኳ የሚቀፍና የሚዘገንን ነው። በአባቶቻቸን፤ በአያቶቻችንና በቅድመ አያቶቻቸን ደም ፍሳሽና አጥንት ክስካሽ ተፈርቶና ተከብሮ የነበረው ዳር ድንበሯ ዛሬ “የምትፈግ ገብተህ እግርህን ዘርግተህ ተዝናንተህ ፈንጪበት፤ ሁሉም በጅህ ሁሉም በደጅህ ይሁንል” የተባለ ይመስላል። የቤልጅየምን የቆዳ […]

የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ሁለተኛውን የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚው ተግባራዊ እንዲደርግ ወሰነ፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2006 ባደረገው አስቸኳ ስብሰባ በሶስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ከነዚህ ውሳኔዎች መካከል ሁለተኛው ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” ህዝባዊ ንቅናቄ ይገኝበታል፡፡ የፓርቲው ፕሬዝደንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሁለተኛው ዙር የ“ሚሊዮኖች ድምፅ” […]

አዎ! የኢህአዴግ መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በMonopoly መቆጣጠሩ ይታወቃል። ለዚህም ምክንያት አለው። በህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ፍልስፍና መሰረት ስልጣን የሁሉም ነገር መሳርያ ነው። ስለዚህ ስልጣንን መቆጣጠር ግድ ነው። ስልጣን ለመቆጣጠር ደግሞ ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ያስፈልጋል። ለዚህም ነው ስልጣን ለመቆጣጠር ሲሉ ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠሩት። ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር ትርፋማ የሆኑ ሴክተሮችና የኢኮኖሚን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩ ተቋማት በmonopoly መያዝ ያስፈለገው። ትርፋማ ከሆኑ ሴክተሮች ኢትዮቴለኮምና […]

የአዲስ አበባ ዞን ሊቀመንበርና ስራአስፈፃሚዎችን ለመምረጥ የ3 አስመራጭ ኮሚቴ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተደርጓል፤ በመቀጠልም ለሊቀመንበርነት 3 አባላት ተጠቁመዋል፡፡ በዚሁ መሰረት አቶ ዳዊት ሰለሞን አቶ ትግስቱ አወሉ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን ለዕጩ ሊቀመንበርነት ተጠቁመዋል፡፡ 3ቱም ዕጩዎች እያንዳንዳቸው የ7 ደቂቃ የምረጡኝ ቅስቀሳ አድርገዋል፤ ለሊቀመንበርነት ጠንካራ ውድድር ከተደረገ በኋላ እና የድምፅ አሰጣጡ በምስጢር ከተካሄደ በኋላ በቆራጥ አመራራቸው በአንድነት […]

በትላንትናው ዕለት በሁለት አመት ገደብ የአምስት ወር እስራት ተፈርዶባቸው እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም የቂሊንጦ ወህኒ ቤት አቶ አስራትን እስከ ሰኞ እንዳይለቅ መመሪያ እንደደረሰው ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት ሃላፊ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ በዛሬው እለት የአቶ አስራት ጣሴን ከእስር መውጫ ወረቀት ይዘው ቂሊንጦ የተገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ከወህኒ ቤቱ ቀና ምላሽ አላገኙም፡፡ የወህኒ ቤቱ […]

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ባልቻ ሆስፒታል አቅራቢያ በሚገኘው ሶሊሽ ኢንተርናሽናል ሆቴል የምስረታ ጉባኤውን ደርጋል፡፡ ዞኑን በሊቀመንበርነት ለመምራት የጦፈ ፉክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ አንድነት ፓርቲ በሚመራበት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት ፓርቲውን ይበልጥ ለማጠናከር ሲባል የአዲስ አበባ ዞን ምክር ቤት የአደረጃጀት ለውጥ ሊደርግ ችሏል፡፡ በአደረጃጀት […]

ዶር ያእቆብ ኃይለማሪያም፣ የአሰብ ወደብን በተመለከተ የጻፉት መጽሃፍ ሰባት ጊዜ እንደታተመ ከሲ.ቢ.ኤስ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገለጹ። «ይህ የሚያመለክተዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል የአሰብ ጉዳይ እንደሚያንገበግበው ነዉ» ያሉት ዶር ያእቆብ፣ በአሰብ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች በስላም መፍታት እንደሚቻልም ለማሳየት ሞክረዋል። የኤርትራ ሕዝብና የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድማማች ህዝብ እንደሆኑ የተናገሩት ዶር ያእቆብ፣ ጠቡና መለያየቱ የመጣዉ በመሪዎች […]

አቶ ብርሃኑ በርሄ ይባላሉ። እስከ 1994 ድረስ የሕወሃት አባል ነበሩ። የሕግ ባለሞያ ናቸው። በትግራይ ክልል የፍትህ ቢሮ ሃላፊ ነበሩ። « የፍህት ቢሮ አደረጃጀት እና አቃቢ ሕግ ከፖለቲክ ገለልተኛ መሆን አለባቸዉ » በሚል አማራጮችን አቀረቡ። « አቃቤ ሕግ ተጠሪነቱ ወይም ለካቢኔ ወይንም ለምክር ቤት መሆን አለበት» የሚል የጥናት ወረቀት አቀረቡ። ያቀረቡት ሃሳብ በሕወሃት አመራሮች ዉድቅ ተደረገ። […]

ኢሕአዴግ የዘረጋቸው ትላልቅ ፕሮጅክቶች የሕዝቡ ተሳትፎ እንደሚጠይቁ የተገነዘቡት በርካታ የኢሕአዴግ ደጋፉዎችና አባላት፣ ኢሕአዴግ መሰረታዊ ማሻሻያዎችን እንድያደርግ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲያሰፋ፣ እስረኞችን እንዲፈታ ዉስጥ ዉስጡን ጫና እያደረጉ እንደሆነ ከኢሕአዴግ አካባቢ ያሉ ምንጮቻችን ይገልጻሉ። ትግራይን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በኢሕአደግ ዘንድ ባሉ የመልካም አስተዳደር፣ የኢፍትሃዊነት ችግር ላይ፣ እንዲሁም አልቻል በተባለው የኑሮ ዉድነት የተነሳ፣ የሚነሱ ተቃዉሞዎች እየተበራከቱ መሆኑ ያዩ […]

የሱዳን መንግት ኢትዮጵያዉያን ከዘመናት ከኖሩበት ቦታ እንዲለቁ የሳምነት ማስጠንቀቂያ እይሰጠ እንደሆነ የአራን አመራር አባል አቶ አብርሃ ደሳት ገለጹ። «የሱዳን መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አከባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሳምንት ዉስጥ ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ መስጠቱ የሑመራና አከባቢው ኗሪዎች ለዓረና ትግራይ ፅሕፈትቤት አስታውቀዋል። የሱዳን መንግስት ትእዛዝ ያስተላለፈው መሬቱ የሱዳን ግዛት ሁኗል በሚል በምክንያት እንደሆነ አክለዋል።”” ሲሉ ነገር አቶ አብርሃ […]

አቶ ዳንኤል ተፈራ በዋስ መለቀቃቸው፣ አቶ አሥራት ጣሴም መፈታታቸውን አነበብኩ። መጀመሪያዉኑ እነዚህ የአመራር አባላት መከሰስ ብሎም መታሰር አልነበረባቸውም። ሆኖም ግን ኢሕአዴግ ነገሮችን በማርገብ እንዲፈቱ ማድረጉ በአዎንታዊነት ተቀብዬዋለሁ። አዎ «የኢሕአዴግ አመራር አባላትን ጥሩ አድርጋቹሃል » እላለሁ። ይህ አይነቱን፣ መቀራረብን የሚያመጣ፣ ፖለቲካዉ የበለጠ እንዳይከር የሚያደርግ ተግብራትን እንዲፈጸሙ ነበር የሁላችንም ፍላጎት። ኢሕአዴግ በአገራችን እያደረጋቸው ያለው የልማት እንቅስቃሴዎች ሰፋፊና […]

የትግራይ ህዝብና ታጋዮቹ የህ.ወ.ሃ.ት ትጥቅ ትግል የተጀመረበት ቀን ከ1967 ዓ/ም የካቲት ወር ጀምሮ እስከ 1983 ዓ/ም በየአመቱ ለምትመጣዉ የካቲት 11 ለማክበር በናፍቆት የሚጠብቁት ነበር። በአሉን ለማክበርም የሚበላ፣ የሚጠጣ፣ የሚለበስ ያላቸውን ሃብት በማሟጠጥ አስቀድመዉ ይዘጋጁበት ነበር የትግራይ ህዝብ ይቅርና በነፃ መሬት በጠላት ውስጥ በስደት በተለይ ደግሞ በ1977 ዓ/ም በድርቅ፣ በደርግና በሻዕቢያ ወረራ ወደ ሱዳን ተሰዶ በለጋሾች […]

ወደ ዉቅሮ ከተማ ጎራ ብዬ ነበር። የትግራይ ክልል ዕጩ ዳኞችና ዓቃብያን ሕግ የሚሰለጥኑት በዉቅሮ ከተማ ነው። ዳኞቹ ከዩኒቨርስቲዎች በሕግ የተመረቁ ወጣቶች ናቸው። ዳኞችና ዓቃብያን ሕግ ሁነው ለማገልገል ስልጠና ይሰጣቸዋል። ስልጠናው ግን ስለ ዳኝነት ሳይሆን ስለ ህወሓታዊ ፖለቲካና ፕሮፓንጋንዳ ሁኖ ተገኝቷል። የሚሰለጥኑት ስለ ወያናይ ዴሞክራሲ (አብዮታዊ ዴሞክራሲ) ነው፤ ስለ ልማታዊ መንግስት ነው (ልማታዊ መንግስት በኢህአዴጋዊ ቋንቋ […]

እንደመግቢያ፤ ያሬድና ጽሁፉ አቶ ያሬድ ሀይለማሪም (ያሬዶ) ለሰብአዊ መብት መሟገት አመል ሆኖበት (አመሉ፤ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ማለቴ ነው)፤ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ ጽሁፍ አውጥቶ ነበር፡፡ ያንን ጽሁፍ ተከትሎ አንዳንድ በብእር ስም ጀርባ የተደበቁ ተቺዎች አበሳጩት መሰለኝ ሌላ ተከታይ ሁለተኛ ጽሁፉም ጽፎዋል፡፡ የኔ አስተያየት በመጀመሪያው ጽሁፍ ላይ ነው፡፡ ከሞላ ጎድል ጽሁፉ፤ ግንቦት ሰባት፤ ለኢትዮጵያ እንታገላለን ብለው […]

የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ መምታታቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንደጠቆሙት የተቃውሞው መነሻ ምክንያት ሶስት ተከታታ ቅታት የተጣለበት ሹፌር ለስድርት ወር እንዳያሽከረክር የሚከለክል ደንብ በመውጣቱ ነው፡፡ የታክሲ ባለንብረቶችም የታሪፍ ማስተካከያ አለመደረጉን በመቃወም የታክሲ ሹፌሮቹን ተቀላቅለዋል፡፡ የከተማው አስተዳደር ባለስልጣናት ሾፌሮቹና ባለንብረቶቹ ወኪል ልከው እንዲነጋገሩ ጠይቀዋል፤ ሆኖም […]

ዳኛ –የማረሚያ ቤቱ ፖሊስን ‹‹እዚሁ ልትለቃቸው ትችላለህ›› የማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ‹‹አለቃቸውም›› አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና ሬዲዩ ድርጅት ባቀረበው “አኬልዳማ” በተሰነ ዶክመንተሪ ፊልም ስሜን አጥፍቷል በማለት ያቀረበው የፍትሀ ብሄር ክስ በአስር ቀናት ውስጥ ውሳኔ ማግኘት እንደሚገባው አዋጅ እንደሚደነግግ የተረዱት አቶ አስራት ጣሴ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የፍትህ መጓተት ከፍርድ ቤቱ ፍትህ ማግኘት እንደማይቻል ማሳያ ነው […]

በአዲስ አበባ የሚገኙ የዓረና ፓርቲ አባል ወጣቶች የአሰብ የባህር በርን በተመለከተ በየካቲት 2/2006 ዓ.ም ፓርቲው በከፈተው አዲስ ጽ/ቤት ጥልቀት ያለው ፖለቲካዊ ውይይት አድርጓል፡፡ በእለቱ ሰፊ ትንተና ያቀረበው ደራሲ እና ፖለቲከኛ ወጣት አስራት አብረሃም ሲሆን በውይይቱ ጊዜም ወጣቶቹ የጦፈ ክርክር አካሄደዋል፡፡ ወጣት ፖለቲከኛው ስለ አሰብ ጉዳይ ሲያብራራ ንጉስ ሐይለሥላሴ በአንድ ወቅት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ወይይት […]

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የሥልጣን ዘመናቸውን ከጨረሱ በኋላ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታትን ማስታረቅ እንደሚፈልጉ የመንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያ በሆነው ኢቴቪ በይፋ ገልጸው መስመር የያዘላቸው መሆኑንም አሳውቀው ነበር፡፡ በቅርቡ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግን ምንም ዓይነት የዕርቅ ፍላጐት እንደሌላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በፕሮፓጋንዳ ብልጫ እየተጠቀመበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ […]

አቶ ወልደስላሴ በሕወሃት ተመድበው የጉምሩክ ምክትል ሃላፊ ነበሩ። ስራ ሲጀምሩ ደሞዛቸው 1600 ብር ነበር። በእድገት ደሞዛቸው ወደ 6000 ብር ይወጣል። እንዴት እንደሆነ በማይታወቅበት ሁኔታ ባለ 4 ፎቅ ህንጻ ባለቤት ሆነዋል። ወንድማቸው አቶ ዘርዓይ ወልደስላሴ፣ ደሞዛቸው 532 ብር ነበር። ነገር ግን በግል የባንክ አካዉንታቸው ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል። በአፋር ክልል ከ 1 ሚሊዮን አራት መቶ […]

የአንድነት አባል በመሆኑ በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት አስተዳደር የተለያዩ ዛቻዎችና ማስጠንቀቂያዎች እየደረሱበት እንደሆነ የሚናገረው መምህር አማኑኤል መንግስቱ “ከዚህ በፊትም ያለምንም ምክንያት ከማስተምርበት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንስተው ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አውርደውኛል፡፡” በማለት በመንግስት ኃላፊዎች የደረሰበትን በደል ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ተደጋጋሚ ዛቻ እየደረሰበት መሆኑንና በቅርቡም ከስራው ሊያፈናቅሉት እንዳቀዱ ጨምሮ አስረድቷል፡፡ መምህር አማኑኤል ላይ እየደረሰ ስላለው […]

ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሰጠ መግለጫ !!!! ብአዴን ኢህአዴግ የአማራን ህዝብ የመምራት የሞራል ልዕልና የለውም፤ ህዝብ ያዋረዱ አመራሮቹም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚገነዘበው በዚህች ታሪካዊት እና የጥቁር ህዝብ ድል ማዕከል፤ የነፃነት ተምሳሌትና የአፍሪካ ህዝብ ኩራት በሆነች ሀገር የኋላ ዘመን ውጣ ውረድ ውስጥ ሰፊው የአማራ ህዝብ ከመላው […]

እንደ መግቢያ ቅጥፈት የስብዕና መሽርሽር ምልክት ነው፡፡ የግለሰቦች ስብሰብ በሚፈጠረው ማህበረሰብ ውስጥ የስብዕና መሸርሸር ሲበራከት ማህረሰበባዊ አደጋ ሰላማዊ አኗኗሩን ማነዋወጥ ይጀምራል ፡፡ ማህበራዊ ቀውስ በሰፈነበት ደግሞ ከግለሰቦቹ ውድቀት የሚነሳው ገፊ ምክንያት እንደ ማህበረሰብ የተገነቡ የጋራ እሴቶችን ይንዳል፡፡ ባህል ፤ ሃይማኖት ፣ታሪክ ፣ወግ እና ልማዶች ሁሉ መሰረታዊ ይዘታቸውን የላቁና የሰው ልጅ እንደ እንስሳ በቀላሉ ከእንቱ ነገሮች […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ብአዴንን በመቃወም በባህርዳር ከተማ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ፡፡ ፓርቲዎቹ ነገ በ4 ሰዓት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ለተቃውሞ ሰልፉ አስፈላጊው የማሳወቅ ተግባር መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ አንድነትና መኢአድ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ምክንያት እንዲያስረዱ በፍኖተ ነፃነት የተጠየቁት የአንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች […]

በቅርቡ ለንባብ ካበቃው መጽሐፍ ጋር በተያያዘ የስም ማጥፋት ክስ የተመሰረተበት የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ዛሬ በድጋሚ ማዕከላዊ እንዲቀርብና በድጋሚ የተከሳሽነት ቃሉን ከሰጠ በኋላ በመኪና ሊብሬ ዋስ ከእስር ተፈቷል፡፡ ኢህአዴግ በመንግስት እና በተለጣፊ ፓርቲዎች አማካኝነት በአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ የእስር ዘመቻ መክፈቱ ይታወቃል፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንጠቆሙት ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 1 እና የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም(ቅዳሜና እሁድ) ለሊት በተደጋጋሚ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በድንጋይ መደብደቡን ተከትሎ ቤታቸው ቀንና ለሊት በፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ አቶ አለምነው መኮንን የአማራን […]

“ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነት አለኝ” ብዬ ስል የራሴ (የግሌ) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የአከባቢ ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የክልል (የብሄር) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። ወይም እነዚህ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ማንነቶቼ መጥፋት አለባቸው ማለት አይደለም። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል የራሴን ማንነት አልቀበልም ማለት አይደለም። የራሴ ማንነት ስላለኝ ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ሊኖረኝ የቻለው። እኔ የግል ማንነት ባይኖረኝ […]

አስገራሚው የሳውዲው “ኮራጅ ” አባት ምክር ነገሩ እንዲህ ነው …ከ20 ዓመት በፊት ሳውዲው ወጣት ራሱን ለሁለተኛ ደረጃ ፈተና ከማዘጋጀት ይልቅ በረቀቀ መንገድ ለፈተናው መልስ የሚሆነውን ማጭበርበሪያ የመልስ ወረቀት አዘጋጅቶ ለፈተና ይቀርባል። ፈተናውን በረቀቀ መንገድ አጭበረብሮ ሰርቶታልና ፈተናውን በተገቢ ውጤት አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለማለፍ በቃ ! ከዚያም በታዋቂው ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ተከታትሎ ይመረቃል። ይህ ሁሉ አልፎ […]