የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ሊቀመንበር ዛሬ ይመረጣል

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ ባልቻ ሆስፒታል አቅራቢያ በሚገኘው ሶሊሽ ኢንተርናሽናል ሆቴል የምስረታ ጉባኤውን ደርጋል፡፡ ዞኑን በሊቀመንበርነት ለመምራት የጦፈ ፉክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡
አንድነት ፓርቲ በሚመራበት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት ፓርቲውን ይበልጥ ለማጠናከር ሲባል የአዲስ አበባ ዞን ምክር ቤት የአደረጃጀት ለውጥ ሊደርግ ችሏል፡፡ በአደረጃጀት ለውጡ መሰረትም የዞኑ ምክር ቤት 138 አባላት እንዲኖሩት ተደርጓል፤ ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ዞን ምክር ቤት 46 አባላት ብቻ እንደነበሩት ይታወቃል፡፡
በዛሬው የአዲስ አበባ ዞን ምክር ቤት ምስረታ ላየ የአዲስ አበባ ዞንን የሚመሩ ስራ አስፈፃሚዎችም የሚመረጡ ሲሆን ለሊቀመንበርነት የሚደረገው ፉክክር በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡UDJ