ክፍል አንድ በቀናት አቆጣጠር ሰባተኛው እረድፍ በምትይዘው በዕለተ ቅዳሜ ከዚህ ቀደም በጸረ ሽብር አዋጁ ዙሪያ ካደረግነው የተሟሟቀ ክርክር በኋላ ከገዥ ፓርቲ ጋር በሃሳብ ክርክር ለ11 ሰዓታት የተሟገትነው ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ይህ መድረክ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት እና ኮሚዩኒኬሽን የድህረ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ ጋር በመተባበር እንደነበረ ከደረሰን […]

አንድ ዘመን ሥርዓተ መንግስቱ በመቆየትም ሆነ አባላቱ የአሥራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የተረት ዓለም ሰዎች ስለ መሰሉን- ሁሉም ነገር ስለገለማን አዲስ ሥርዓት፣ አዲስ መሪ፣ አዲስ ዘመን መናፈቅ ይዘን ነበር። ሰዓሊ ሁሉ፣ ደራሲ ሁሉ፣ ጸሐፌ -ተውኔት ሁሉ እጁን የሚያሟሸው በቴዎድሮስ ሥዕል፣ ተውኔትና ታሪክ ሆነ። ብርሃኑ ዘሪሁን- የቴዎድሮስ እንባ -(መጽሐፍ) ከዚያ በፊት ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያት- ቴዎድሮስ (ተውኔት) አቤ […]

ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ አቶ ዳንኤል ተፈራ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቀርብ መጠየቁ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል። አቶ ዳንኤል መጀመሪያ ላይ እንዲቀርብ የተጠየቀዉ በስልክ፣ ሲሆን፣ ሕጋዊ መጥሪያ ወረቀት ካልመጣለት በቀር ለመቅረብ ፈቅደኛ ሳይሆን እንዳልቀረ ለማወቅ ተችሏል። ከአቶ ዳንኤል ተፈራ በተጨማሪ፣ የአንድነት ብሄራዊ ምክር አባል የሆኑትና በርካታ መጽሃፍት በመጻፍ የሚታወቁት አዛዉንቱ አቶ አንዳርጌ መስፍንን፣ ፖሊስ ለመከሰስ እንደተዘጋጀ፣ እንዲቀርቡም እንዳዘዘ ለማረጋገጥ […]

«ከንቲባ ድሪባ ኩማና ኮሚሽነሩ መከራከሪያቸውን ለፍ/ቤት ያቀርባሉ » «አንድነት፣ የመንግስት አካላትን በተከታታይ እከሳለሁ ብሏል» አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)፣ የአዲስ አበባ ከንቲባና የፖሊስ ኮሚሽነራቸው ላይ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሰረተ ሲሆን ተከሳሾች መልሳቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለየካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ አንድነት ፓርቲ፤ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የተሰኘ አገር አቀፍ የ3 ወር […]

ሌላኛው ሰሞነኛ ጉራማይሌ የፖለቲካችን ገፅ አንጋፋውን የኦሮሞ ልሂቅ ሌንጮ ለታን የተመለከተው ርዕሰ-ጉዳይ ነው፡፡ ኦነግን በመመስረትም ሆነ ፖለቲካዊ ቁመና ይዞ ህልው እንዲሆን ከዮሀንስ ለታ በላይ ማንም የለፋ እንደሌለ ይነገራል፤ ዮሀንስ ከጓዶቹ ጋር ተባብሮ ድርጅቱን ሲመሰርት ካነገበው አጀንዳ አኳያ ያለውን ተዛምዶ ገልፆ ባይነግረንም፣ ከልጅነት እስከ ጎልማሳነት ይታወቅበት የነበረውን መጠሪያ ስሙን ‹ሌንጮ› በሚል ቀይሮታል፡፡ ኦነግ እስከ 1983 ዓ.ም […]

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊዉ ወጣት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ድርጅታቸው «ውህደት ፈጽሞ አያስፈልግም ብሎ የማያምን እንደሆነ የገለሱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን ዉህደት እንደማይታሰብ አሳወቁ። ፓርቲዉ ከሌሎች ድርጅቶ ጋር አብሮ ለመስራት እና ለመዋሃድ ፈጽሞ የተዘጋ በር እንደሌለው የገለጹት አቶ ብርሃኑ ከዉህደት በፊት ግን መቅደም ያላባቸው ጉዳዮች (የቤት ስራዎች) እንዳሉ ይናገራሉ። መሰራት ያላባቸውን የቤት […]

በዘመነ ኢህአዴግ ከታሪክ ተጠያቂነት በፍፁም ሊያመልጡ ከማይችሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ብአዴን እና ኦህዴድ በግንባር ቀደምትነት ይሰለፋሉ፡፡ ሁለቱም ‹እንወክለዋለን› በሚሉት ሕዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደት ለመፈፀማቸው፣ ደርዘን ያለፉ ድርሳናትን ማዘጋጀት እንደሚቻል እናውቃለን፡፡ አልፎ ተርፎም ህወሓትን ከመሰለ የማፍያ ቡድን ጋር ግንባር ፈጥረው ‹‹ወከልነው›› የሚሉትን የማህብረሰብ ክፍል ህልውና ማድቀቃቸው እውነት ነው፡፡ በርግጥ ምንም እንኳ የሀገር አንድነትን አደጋ ላይ የጣለ […]

ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ዋናው ምንጩ በሆነው፤ እ.አ.አ በ2013 (2006 ዓ/ም) ታትሞ ለንባብ በደረሰው፤ ካርልሔንዝ ዴሽነር (Karlheinz Deschner) “እግዚአብሔርና ፋሺሽቶቹ – የቫቲካን ሕብረት ከሙሶሊኒ፤ ፍራንኮ፤ ሒትለርና ከፓቬሊች ጋር” “God and The Fascists – The Vatican Alliance with Mussolini, Franco, Hitler, and Pavelic” በተሰኘው መጽሐፍ በተካተተው ማስረጃ ላይ ነው። የጽሑፌ ዓላማም በፋሺሽቶች ኢትዮጵያ ላይ ስለ ተፈጸመው እጅግ […]

ፓርቲያችን አንድነት በተደጋጋሚ ከገዥው ፓርቲ ህግን ከለላ በማድረግ እና የመንግስትን ሥልጣን በመጠቀም የሚደርስበትን ከፍተኛ አፈና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን የበላይነት ለማረጋገጥ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በተለይም ፓርቲያችን በመላው የሀገራችን ክፍል የዘረጋውን መዋቅር በህዝባዊ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ በማሸጋገር በአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅዱ መሰረት እያከናወነ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ እና በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባዔ […]

የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ፡፡ ፍኖተ ነፃነት ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ በአራት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ክስ ለመመስረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መዘገቧ ይታወሳል፡፡ በቅርቡ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ […]

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎቻቸው እንዲወዳደሩ ወይም ስልጣን እንዲይዙ ለማድረግ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡የውክልና ዴሞክራሲ እንዲጠነክርና እንዲጎለብት ፓርቲዎች የሚጫወቱት ሚናም ቁልፍ ነው፡፡ በሰለጠነው አለም የፖለቲካው ልቀት የሚለካው በፓርቲዎች ብዛት ነው፡፡የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት የሚፎካከሩ ፓርቲዎች ቁጥር ሁለት ቢበዛ ሶስት ነው፡፡ለምሳሌ በአሜሪካ ኋይት ሃውስ ለመግባት የሚፎካከሩት ፓርቲዎች ሁለት ናቸው፡፡ዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች፡፡ በእንግሊዝ ዋነኞቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሶስት ናቸው፡፡ወግ አጥባቂዎቹ (ኮንሰርቫቲቭ)የሰራተኛው(ሌበር ፓርቲ)እና ሊበራሎች፡፡ […]

አረና በሁመራ ለማድረግ ያቀደው ህዝባዊ ስብስበ በአዲግራት እንደተደረገው ሁሉ በሕወሃት አምባገነንነት ሳይሳካ ቀርቷል። የአረና አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ በፌስቡክ ብሎጋቸው : «ዓረና መድረክ በሑመራ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ለዓርብ ጥር ሰለሳ ቀጠሮ ይዞ፣ አስተዳዳሪዎችን አሳውቆ፣ የማዘጋጃቤት አዳራሽ ተፈቅዶለት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር የተሳካ ቅስቀሳ ቢያደርግም የሑመራ (እንዲሁም የወልቃይት) ህዝብ ጥሩ አቀባበል ያስደነገጣቸው የከተማው አስተዳዳሪዎች […]

በዶር መራራ ጉዱና የሚመራዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፣ የወጣቶችን ሊግ ማቋቋሙ የዶር መራራ እና አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ፌስቡክ ዘገበ። ሊጉ የኦሮሞዎች መብት በኢትዮጵያ እንዲከበር ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ በኦሮሚያ ዞኖች ይንቀሳቀሳል ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ አበባን ጨምሮ ሃያ አንድ የኦሮሞያ ዞኖች ሲኖሩ፣ አዲስ ለተቋቋመዉ የወጣቶች ሊግ፣ ተወካዮች ከአሥራ ሁለት ዞኖች እንደመጡም ለማወቅ ተችሏል። ወጣት ተወካዮች የመጡት፣ […]

ከማንነት ጋራ የተያያዙ ጥያቄዎች፣ ሙግቶች፣ በተቃራኒውም አስቀያሚ ሐሳብ አልባ ስድድቦች ሰሞኑን በርከትከት ብለዋል። ጥያቄዎቹና ሙግቶቹ መኖራቸውን አጥብቄ እደግፈዋለሁ። በእኔ እይታ አብዛኞቹ ምልልሶች ወይም ሙግቶች በመሠረቱ አዲስ ጭብጥም ሆነ መከራከሪያ አላቀረቡም። ቢሆንም የነበረውንም ቢሆን በአግባቡ በተደጋጋሚ እያነሱ ሐሳብ መለዋወጡ ጠቃሚ ነው፤ ሙከራው ቢያንስ እርስ በርስ መተዋወቅን ይጨምራል፤ አልፎም አዲስ ሐሳቦችን ለማፍለቅ እድል ይሰጣል። የማነ ናግሽ ኢትዮጵያዊ […]

አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸዉ ሽፈራዉ፣ ለገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የሰላምና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። «ኢሕአዴግ እኛን እንደ ጠላት እና ሽብርተኛ ማየቱን ማቆም አለበት። እኛም ደግሞ ኢሕአዴግን እንደ አዉሬ ማየት ማቆም አለብን። ከጥላቻ ፖለቲካ በመዉጣት ችግሮቻችንን በሰላም መፍታት መማር አለብን» ሲሉ ነበር፣ ለአገር በሚጠቅሙ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢሕአዴግ ጋር ለመስራት፣ ያሉትን ልዩነቶችን በዉይይት ለመፍታት አንድነት […]

ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ የአገራችንን ፖለቲካ የተጠናወተው የ“…. ወይም ሞት” አስተሳሰብ ከአስርት አመታት በኋላም አለቅ ብሎን ዛሬም እኔ ከምደግፈው ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ቡድን ወይም አስተሳሰብ ውጭ ያለው መንገድ ወይም አማራጭ ሁሉ ገደልና ሞት ነው ብለው የሚያስቡ ፖለቲከኞችና ዓጃቢዎችን ቁጥር በብዙ እጥፍ አባዝቶ ቀጥሏል። በ‘ደርግ ወይም ሞት’ የጀመረው የኼው የተወላገደ እና ጸረ-ዲሞክራቲክ የሆነው አስተሳሰብ ሳንወጣ ዛሬም […]

የአንድነት ልሳ የሆነዉ ፍኖት ነጻነት፣ ሰበር ዜና ብሎ እንደዘገበዉ፣ ኢሕአዴግ አቶ ዳን ኤል ተፈራን ጨምሮ በርካታ የአመራር አባላትን ለማሰር እየትዘጋጀ እንደሆነ፣ በፍትህ ሚኒስቴር ያሉትን ምንጮች በመግለጽ ዘግቧል። « አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ አራት የአንድነት አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱን የፍትህ ሚ/ር ምንጮች አጋለጡ፡፡ ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት በኢህአዴግ ጽ/ቤት ትዕዛዝ ክስ እንዲከፈትባቸውና እንዲታሰሩ የተወሰኑት የአንድነት አባላት በርካታ […]

ሕገ-መንግሥቱ የሚፈቅድልኝን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳላካሂድ ከልክለውኛል፤ አባላቶቼን ያለአግባብ በማንገላታት አስረውብኛል፤ ቅስቀሳ እንዳላካሂድ አግደውኛልና ድምፅ ማጉያዎቼን ቀምተውኛል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህና ፓርቲ (አንድነት) በሶስት የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ መሰረተ። ፓርቲው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሔር ችሎት ላይ ክስ የመሰረተባቸው ተቋማት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ […]

የአንድነት ፓርቲ ለበርካታ አመታት በዋና ጸሃፊነት ያገለገሉት አቶ አስራት ጣሴ መታሰራቸዉን የአንድነት ፓርቲ ሚሊየም ድምጽ፡ለነጻነት ፌስቡ ገጽ ዘገበ። «የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበረው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ከፃፉት አስተያየት ጋር በተያያዘ “ዘለፋ አዘል ጽሑፍ” ጽፈዋል በሚል ፍርድ […]

የኢትዮጵያ ፈዴራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 46 «ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ የማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነዉ» ይላል። አንቀጽ 47 ደግሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሩፑብሊክ አባላት የሆኑቱን ክልሎች ይዘረዝራቸዋል። እነርሱም የትግራይ፣ የአፋር ፣ የአማራ፣ የሱማሌ፣ የቤኔሻንጉል/ጉሙዝ፣ የደቡብ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች እና የሃረሪ ሕዝብ ክልሎች ናቸው። የዚህን የፌደራል ክልልን በተመለከተ በክልሎች እየታዩ ያሉትን አንዳንድ […]

ሥርጉተ ሥላሴ የተባሉ ጸሐፊ በተለያዩ ጊዜያት የሚጽፏቸውን በአብዛኛው ታሪካዊ የሆኑ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርስ አዘል፣ በኃይለኛው አገራዊ/ኢትዮጵያዊ ዘዬ፣ ትውፊትና ባህል የተጫነው የሚመስለውንና፤ (ይህን ለማረጋገጥ የሚወድ ጸሐፊዋ ‹‹ኢትዮጵያዊነት የሚነበብ መንፈስ ነው›› በሚል ርእስ ያስነበቡትንና ‹‹የኢትዮጵያዊነትህን መንፈስ በቅጡ ካልተረዳኸውና ካልተቀበልከው ‘ጉግ ማንጉግ’ የኾነ አንካሳ መንፈስ ይጨፍርብኻል፡፡›› እስከ ማለት የደረሱበትን፣ በኢትዮጵያዊነት ወኔ፣ ስሜትና ረቂቅ መንፈስ ፈጽሞ የሰከረውን መጣጥፋቸውን ማየቱ […]

አቶ አያሌው ጎበዜ ድርጅቱን የተቀላቀለው አስተማሪ ሆኖ እየሰራ በነበረበት አዲስ ዘመን ከተማ በ1984 ዓ.ም ቢሆንም በተፋጠነ ሂደት የሽግግር መንግስቱ የስራ አስፈፃሚ አባል መሆን ችሎ ነበር፤ ከ1987-1992 ዓ.ም የክልሉ አስተዳዳሪ አዲሱ ለገሰ ምክትል ሆኖ ተሹሟል፤ በዮሴፍ ረታ የአስተዳደር ዘመን (ከ1992-97 ዓ.ም) ደግሞ መጀመሪያ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ኃላፊ፣ ቀጥሎ አፈ-ጉባኤ ሆኖ ሰርቷል፡፡ ይሁንና በምርጫ 97 ዮሴፍ በተወዳደረበት […]

ከእነዚህ ክስተቶች በተጨማሪ በአካባቢው የተመለከትኩት ከባድ ውጥረት አለ፤ ይኸውም ‹ለሱዳን ሊሰጥ ነው› እየተባለ የሚነገርለት የመሬት ጉዳይ ካመጣው ጣጣ ጋር የሚጋመድ ነው፤ በርግጥ በአንዳንዶች ዘንድ መሬቱ ወደ ውስጥ ስልሳ (60)፣ ወደ ጎን ደግሞ አንድ ሺህ (1000) ኪሎ ሜትር ድረስ እንደተሰጠ ይታመናል፡፡ ይሁንና በግሌ ይህ ክስ ማረጋገጫ የሚቀርብበት ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ በጉዳዩ ላይ ምክንያታዊ ለመሆንም በዚህ በተጠቀሰው የመሬት […]

በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን፡፡ የሁሉም መነሻና መድረሻ ዓላማ መንፈሳዊ ይሁን እንጂ እንደ መስቀል፣ ጥምቀትና ሬቻ… ያሉ አንዳንድ በዓላት ከመንፈሳዊነታቸው በተጨማሪ የባሕል መገለጫ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም በዓላቶቹ በሚከበሩባቸው […]

የአንድነት ፓርቲ፣ በሶስት ከተሞች ታላላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለማድረግ መወሰኑን ከሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡ ገጽ አነበብኩ። እንቅስቃሴዎቹ የሚደረጉባቸው ከተሞች፣ አድዋ፣ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ናቸው። በአድዋ እና በአዲስ አበባ ከሌሎች ደርጅቶ ጋር በጋራ በመሆን (ሚአድ፣ አረና፣ ትብርር፣ መድረክ..) ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቡ ሁሉ ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል በማሰብ ትልቅ አከባባር ለማድረግ ነው የታቀደው። […]

በሳዉዲ መንግስት በግፍና ጭካኔ ተባረው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ፣ በዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ፣ «መንግስት ትኩረት አልሰጠንም» በሚል ድምጻቸውን ለማሰማት የተሰባሰቡ ወደ 400 መቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን በፖሊሲ እንዲበተኑ መደረጉን የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው የፍኖት ጋዜጣ ዘገበ። «ቦሌ አካባቢ ከሚገኘው ጊዜያዊ ማረፊያቸው፣ ከ400 በላይ ሆነው ቅሬታቸውን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለማሰማት ያቀዱትን […]

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ትላንት ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት መከበር ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት በቅርቡ 93ኛ ዓመታቸውን ላከበሩት ሌተናል ጀነራል ጃገማ ኬሎ የክብር መግለጫ ምስክር ወረቀት እንዳበረከተላቸው የማህበሩ ምክትል ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ም/ጸሀፊ ወጣት ጥላዬ ታረቀኝ ለፍኖተ ነፃነት የሚከተለውን ብሏል “ሌተናል ጄነራል ጃገማ ኬሎ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ታላቅ […]

ባለፈው ቅዳሜ (ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም) በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን የድህረምረቃ ተማሪዎች የኢትዮጵያን የፕሬስ ሁኔታ በልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት ውስጥ የሚኖረውን ሚና በተመለከተ የአንድ ቀን የውይይት መድረክ አዘጋጅተው ነበር። መድረኩ ዘግየት ብሎ ቢጀመርም የተጠናቀቀውን ግን ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ነው። የውይይቱ ሙቀትና ግለት በፈጠረው ስሜት የሻይና ቡና እረፍትን ያስፈለገው አልነበረም። በውይይቱ […]

‹ጉድ ሳይሰማ…›› እንደሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስርዓቱ እየተፈፀመበት ካለው ጭቆናና በደል፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋ፤ አፈናና ስደት፤ ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት በተጨማሪም በአምባገነን ገዥዎች እየተዋረደ፣ በአደባባይ እየተሰደበና ሰብዓዊ ክብሩ እየተጣሰ ይገኛል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖም ሀገራችን ላይ ያለው ስርዓት ህዝቡን የሚያዋርድ፣ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ስልጣኑን የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ የሌለው ነው፡፡ ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ […]

ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።” ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። “ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ […]

የሀገራችንን የፖለቲካ አካሄድ ለአርባ ዓመታት ተከታትያለሁ። ሀገሪቱን የሚመሩት ሆኑ ተቃዋሚዎች በውል የሕዝቡን ችግር የተረዱት አይመስሉም። የሕዝብን ይውንታ ያላገኙ በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ላይ የወጡትም ቢሆኑ፣ እሽ አትበሉን የንጉሥ ዶ ሮ ነን ባዮች ናቸው። ሕዝቡም የቅኝ ገዥዎችን እየተከላከለ ነፃነቱን አስከብሮ የኖረ ነወ። በዚህም ይኩራራል፣ ግን የራሱን ነፃነት እርሱን ከሆነ ሰው ይጠብቃል። በለስ ቀንቷቸው ስልጣን ላይ የወጡትም በመሣሪያ […]

በዕርግጥ የአንድን የሀገራችን ክፍል ነዋሪዎች ጉዳይ አንስቶ በአንድ መንገድ ወይንም በሌላ መንገድ መነጋገር፤ ወደድንም ጠላንም፤ ያለንበት ዘመን ግዴታ ሆኗል። ትናንት አኝዋኮች ተረሸኑ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን ተከበው ተሰቃዩ፣ ኦሮሞዎች በእስር ቤት ታጎሩ እያልን እንደጮህን ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ በአማራዎች ላይ የሚደርሰውን በደል አንስተን መነጋገር ግዴታችን ሆኗል። የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲህ ሆኑ፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲያ ሆኑ ስንል ብዙ […]

በከፍተኛ ወከባ ዉስጥ ቢኮንም፣ የሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር መስቀል አደበባይ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ዘገባዎች ገለጹ። የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ የተጠራው ሰልፍ ፣ ከበላይ በተሰጠ ትእዛዝ መሰረት፣ ፖሊሶች መንገዶችን እየዘጉ ሕዝብ እንዳይቀላቀል ቢያደርጉም፣ በርካታ ሕዝብ፣ የነበሩ መሰናክሎችን ሁሉ እያለፈ፣ በሰልፉ ተገኝቷል። «ተከበርሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም ፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይወደም» እያሉ ሰልፈኞች በመዘፈን በአገር ዳር […]

ዓረና ትግራይ ራኢዩን የትግራይ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ በማድረግ ወደፊት ይገሰግሳል እንጂ በህወሓት የሽብር ተግባር አይታጠፍም !!! (ከዓረና ትግራይ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ) የዓረና ትግራይ 3ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ በትግራይ ከተሞች ተከታታይ የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች በማካሄድ በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር ምንጩና መፍትሄው፣ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የፖለቲካ ራኢና ኣማራጭ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የማስቀረት ብቃት […]

በጀርመን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን አቆጠጠር 1971 ጀምሮ የዓመቱ ምርጥ ቃል ይመረጣል። ይህ በየዓመቱ የሚደረገው ምርጫ አዲስ የተፈጠሩ አባባሎች ወይም ቃላቶች አሮጌም ቢሆኑ በአለፈው ዓመት ውስጥ የአጠቃቀማቸው ሁኔታ ታይቶ የሚካሄድ ብሂል ነው። ለአሸናፊነት የሚበቃው ቃል በሕብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው ይሆናል። ምርጫው በኮሚቴ ዳኝነት ተሳታፊዎቹን ቃላቶች አወዳድሮ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘውን አሸናፊ ያደርጋል። በዚህ ውድድር ማንም ሰው ሊያሸንፍ […]

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን መልካ ሶዳ ወረዳ ኩሮ ነጌሌ ቀበሌ በቦረና እና በጉጂ ኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት ከ8 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማጣታቸውን የፍኖት ነፃነት ምንጮች አስታወቁ፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱ ምንም አይነት የማረጋጋት እርምጃ አለመውሰዱ ጉዳቱን እንዳባባሰውም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳስታወቁት ለጊዜው መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም በተነሳ የሁለቱ […]

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ፤ ፓርቲያችን አንድነት በአፅንኦት እንደሚያምነው የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የዴሞክራሲ ዕጦት ሰለባ ነው፡፡ ስርዓቱ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል እንደሚያደርገው በትግራይም ሰብዓዊ መብት ይረግጣል፣ ፍትህ ይደፈጥጣል፣ በካድሬዎች ይደበደባል፣ ይንገላታል፣ እንዲሰደድ ይደረጋል፡፡ ስርዓቱና በስርዓቱ ውስጥ የደላቸው ሹማምንት በስሙ ከመነገድ በዘለለ ዋጋ የተከፈለበትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዘርግቶ ተጠቃሚ ማድረግ አልቻለም፡፡ ህወሓት/ኢህአደግ ክልሉን እንደዋና […]

ለውድቀት ስኬት “የምሥራች!” ወይም “እንኳን ደስ ያለን!” የማይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ የደስታ ማብሠሪያ አባባሎች በአንደኛው ጽሑፌን መጀመር ቃጥቶኝ ነበር፡፡ ለማንኛውም ሀገራችን በማንኛውም ዘርፍ በገባችበት ውድቀትና ኪሣራ ምክንያት ልባችሁ ያዘነና ቅስማችሁ የተሰበረ ወገኖቼን “እግዚአብሔር ያጽናችሁ፤ የሀገራችሁን ትንሣኤም ፈጣሪ በአፋጣኝ እውን እንዲያደርግላችሁ የእግዚአብሔርን ልብ ያራራላችሁ” በሚለው የልመና ቃል ፈጣሪን እየተማጸንኩ ወሬየን ልቀጥል፡፡ ትንሽ በንዴት እንድትንጨረጨሩ ፈቃዳችሁ […]

ትንሽ ወደኁዋላ፤ እንደ መግቢያ 1.ግንቦት፤ 2003/2011፤ በቶሮንቶ ከተማ፤ ጃዋርና ኦባንግ፤ አሎ አይደሂስና (ሸጋ የአፋር ሰው ነው) አበበ በለው በእንግድነት የተገኙበትን ሕዝባዊ ስብሰባ ተንተርሼ፤ አንድ ወርቅ የሆነ ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ ጽሁፉን ያላነበባችሁ ብታነቡት፤ ያነበባችሁትም ብትደግሙት አይቆጫችሁም፡፡ ጽሁፉ ይቀጥላል ብዬ ጊዜ ጠፋና ቀጣዩን ክፍል ሳላቀርብ ቀጠልኩ፡፡ ስለኦባንግ ገጠመኝ ተርኬ፤ ስለጃዋር ጀምሬ ነበር ያቆምኩት፡፡ አሁን መቀጠሉ ወቅታዊ መስሎ […]