የኢትዮጵያ መንግሥት ቦንድ ምን ያህል አስተማማኝ ነው?
(ሳ. ግርማ) የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች የሰሞኑ አሰልቺ ሙዚቃ “ቦንድ፣ ቦንድ፣ ቦንድ” ሆኗል:: የገንዘብ እና የንግድ አስተምሮት እምብዛም ባልጠናበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ ማኅበረሰብ ውስጥ መደናገር ቢበዛ አይደንቅም:: ስለዚህም ጊዜው የመረጃ እንደመሆኑ ለራሴ ግንዛቤ ለመጨበጥ ይረዳኝ ዘንድ አስተማማኝ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን …