The Secret ሚስጢሩ ወለላዬ ከስዊድን
ስለተከሰተው ሚስጥርና የሚስጥሩን ቀላል መደረግ አሁን የሚጠይቁኝ አይመስለኝም። ይልቁንም አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ይሉኝ ይሆናል። ለዚህ በክፍል ሦስት ጽሁፌ መልስ ይዣለሁ። ከዛ በፊት ግን ታላቁ መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላል? የሚስጥሩ ተጠቃሚዎችስ ምን ይነግሩናል? ይሄን አንብበው ወደ ሚስጥሩ አጠቃቀም ይሻገሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

Ethiopia Zare (ሰኞ ነኀሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. September 2, 2013)፦ እሁድ ነኀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ነኀሴ 25 ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች መሪነት በፖሊሶች ጽሕፈት ቤቱን ጥሰው በመግባት አመራሮቹ መታሰራቸውንና ንብረቶች መወረሳቸውን ፓርቲው ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሠይፉ ማሩ
ሰሞኑን ከፀረ-አሸባሪነት ሕግ በማስቀጠል የአዲስ አበባን ከተማ ነዋሪን በተለይ ሲያምስ ከርሞ አሁንም በማመስ ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ነው። በአዲስ አባባ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳለ አሌ የሚባል አይደለም። ይህ ችግር እዚህ እንዲደርስ ደግሞ ዋናው ተዋናይ መንግሥት እንደሆነ መዘንጋት የለበትም። ምክንያቱም ለቤት መስሪያ የሚሆነውን ቦታ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ለዜጎች እንዳይደርስ በማድረጉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

“ከአድባይነት እርግማን ይሰውረን!”

ታክሎ ተሾመ

የኃይማኖት መሪው ቡድሐ የሚሰጠን አንድ እንቆቅልሽ የሚከተለውን ይመስላል። አንድ ነጋዴ ሩቅ ሄዶ ሲመለስ፤ ቤቱ በሽፍቶች ተዘርፎና ተቃጥሎ ይደርሳል። ከቤቱ ከተረፈው ረመጥ – መካከል አንድ ተቃጥሎ የከሰለ የሰው ገላ ያያል። “ይሄ ትንሹ ልጄ መሆን አለበት” አለ። በዚህ ምክንያት ምርር ብሎ አለቀሰ። ደረቱን መታ። ፀጉሩንም ነጨ። ገላውን እንደገና የማቃጠል፤ የሐዘን ሥነ-ስርዓት እንዲካሄድም አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክር ቤት፤ የትላንት እሁድ ሰልፍ
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከተመሠረቱት አዲሶቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ወገን የሚመደበው የሰማያዊ ፓርቲ አሁንም የተቃውሞ ድምጹን የሚያሰማበት ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርግ መሆኑን ገለጠ።

Marthe Van der Wolf ከአዲስ አበባ ለአሜሪካ ድምጽ ባጠናቀረችው ዘገባ እንደጠቆመችው፤ ሰማያዊ ፓርቲ ከመቶ በላይ አባሎቹ ከታሰሩበት በኋላ ለትላንት እሁድ ጠርቶት የነበረውን ሕዝባዊ ትዕይንት መሠረዙን አስታውቋል።

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክር ቤት፤ የትላንት እሁድ ሰልፍ
 የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት ከአክራሪነት ጋር ተባብረዋል የተባሉ የፖለቲካ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ፤ ወጣቶችም “ሥልጣን ፈላጊ” ላሏቸው መሣሪያ እንዳይሆኑ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

ማሳሰቢያው የተሰማው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ነው፡፡

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ከየክልሉ የተውጣጡ የአስተዳደር አባላት እና የሃይማኖት ተጠሪዎች ባለፈው ሳምንት ከማክሰኞ እስከ ኀሙስ በአፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ተገኝተው ሀገር አቀፍ ጉባኤ ማካሄዳቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳት ኦባማ የሚተማመኑበትን እቅዳቸዉ ለማስፈፀም-የሚተማመኑበትን ዘመናይ ጦር ከምርጥ መሳሪያዎቹ ጋር አዝምተዋል።የሶሪያ የቅርብ ወዳጆች ሩሲያ፥ ቻይና እና ኢራን የድብደባዉን ዕቅድና ዘመቻ አጥብቀዉ ይቃወማሉ።የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን ከዚሕም አልፈዉ አሜሪካና የተባባሪዎችዋን አቅድ አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።

ለረጅም ጊዜ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ ሆኖ ያገለገለዉና የጋዜጣዉ ህትመት ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ የኢቦኒ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ሆኖ በመስራት ላይ የሚገኘዉ ጋዜጠኛና ብሎገር ብስራት ወልደ ሚካኤል ሰሞኑን በ4 የደህንነት ኃይሎች ታግቶ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እንደተፈፀመበት ተናገረ ፡፡ ድርጊቱ የተፈፀመዉ ባሳለፍነዉ ሰኞ (ነሐሴ 20 – 2005ዓ.ም) ከምሽቱ 2፡35 ላይ ከስራ ወደ ቤቱ በጉዞ ላይ እያለ ነበር፡፡ […]

አመራሩ በታገደበት ቆይቶ የኑፋቄ ውዝግቡ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቋል አመራሩ ኑፋቄው በአግባቡ እንዳይጣራ የተለያዩ ተጽዕኖዎችን ሲፈጥር ቆይቷል ብዙኀኑ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በውሳኔው ቃለ ጉባኤ ላይ አልፈረሙም ‹‹ከዚህ በኋላ ለሚፈጠረው ችግር ሓላፊነቱን የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ይወስዳል፡፡›› /ሰበካ ጉባኤው/   በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ሕዋስ በመጠለፉና በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሠረት ለሰበካ ጉባኤው መመሪያ ባለመገዛቱ የመዘጋት ርምጃ የተወሰደበት የድሬዳዋ ደብረ …

የኢትዮጵያን ነጻነት ስናስብ ልንዘክራቸው የሚገቡ፣ ለሀገሪቱ ደማቸውን ያፈሰሱ፣ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የታገሉ፤ ለነጻነቷ ሲሉ ከገዛ መንግሥታቸው ጋር የተሟገቱ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን የከሰከሱ አያሌ የሌላ ሀገር ሰዎች አሉ፡፡ በተለይ ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ቆሻሻ እንደ ነካው ልብስ በሚገፋበት ጊዜ ለኢትዮጵያዊነታችን ዋጋ የከፈሉትን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ሰዎች ማስታወስ ግድ ይለናል፡፡

እዚህ አውስትራልያ መጥቼ ካገኘኋቸው መጻሕፍት አንዱ ‹ተልዕኮ 101 – Mission 101› የተባለ ዱንካን ማክናብ(Duncan Mcnab) በተባለ ሰው የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ማክናብ መርማሪ(detective) ፖሊስ፣ የግል የምርመራ ሥራ (Investigator) ባለሞያ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ የነበረ አውስትራልያዊ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በእንግሊዝ ወታደራዊ ተልዕኮ ውስጥ በመሰለፍ ለኢትዮጵያ ነጻነት የታገሉ አራት አውስትራልያውያን ወታደሮች ታሪክ ቀርቧል፡፡ ከአራቱ አንዱ የዱንካን ማክናብ አጎት ነበረ፡፡

በዚህ መጽሐፍ ላይ ከአራቱ ወታደሮች ጋር ታሪኩ ተያይዞ የቀረበ አንድ ሌላ ሰው አለ፡፡ ይህ ሰው የተወለደው እኤአ ኖቬምበር 25 ቀን 1877 ዓም በደቡብ ብሪዝበን(አውስትራልያ) ነው፡፡ አያት ቅድመ አያቶቹ ትንግርታዊ ጉዞ የሚወዱ(adventurers) ነበሩ፡፡ አያቱ ከእንግሊዟ ዌልስ በ1800ዎቹ ነበር ወደ አውስትራልያ የገባው፡፡ በምሥራቅ አውስትራልያ ከ117ሺ ሄክታር በላይ መሬት የነበረው ሀብታም አሳራሽ ነበረ፡፡ በኋላ ግን ወደ እንግሊዝ ተመልሶ በሄርፎርድ ሻየር ኑሮውን ቀጠለ፡፡ ልጁን አርኖልድንም በአዳሪ ትምህርት ቤት አስተማረው፡፡

በ1896 አርኖልድ እንግሊዝን ተወና ወደ አውስትራልያ መጥቶ በቤተሰቡ እርሻ ላይ መሥራት ጀመረ፡፡ በከተማ በሚገኘው ዘመናዊ ቤት ከመኖር ይልቅ በገጠር በነበረው የገበሬዎች ቤት ውስጥ በመኖርና አኗኗሩን ሁሉ እንደ ገበሬዎቹ በማድረግ የተለየ ሕይወት የመኖርን ዘይቤ እንደ አያቶቹ ተካነበት፡፡ ‹ቋረኛው› አርኖልድ ዊንሆልት እንግዲህ የዚህ ሰው ልጅ ነበር፡፡

ዊንሆልት ሲፈጥረው የትግል ሰው ነው፡፡ መከራ ባለበት ቦታ ገብቶ መታገል የሚወድ፡፡ በ1899 እኤአ በደቡብ አፍሪካ የቦር ጦርነት ሲፈነዳ የቤተሰቡን ሀብት ትቶ እንዲያውም ለፈረስ መግዣ እንዲሆነው የተወሰነውን ሽጦ በኩይንስ ላንድ ጦር ወስጥ በመመዝገብ በ1900 ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄደና ለለስምንት ዓመት በውጊያ ላይ ቆየ፡፡ ጦርነቱ ሲፈጸምም ወደ አውስትራልያ ተመልሶ የቤተሰቡን ሀብት ማስተዳደር ጀመረ፡፡ ከሀብቱ ጎን ለጎን በኩዊንስ ላንድ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ለግዛቲቱ ሕግ አውጭ ምክር ቤት በ1909 ተመርጦ ነበር፡፡ ከዚያም በኋላ በ1913 እኤአ ወደ አፍሪካ ተመልሶ በደቡብና በደቡብ ምእራብ አፍሪካ ውጊያዎች ላይ በፈቃደኛነት ተሳትፏል፡፡ እንዲያውም በናሚቢያ በረሃ እያለ በአንበሳ እስከ መነከስ ደርሶ ነበር፡፡

በዚህ መካከል በ1928 ዓም ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን ወረረ፡፡ ዊንሆልት ይህ ነገር በጣም ነበር ያሳሰበው፡፡ በአንድ በኩል የኢትዮጵያ መወረር፤ በሌላ በኩል ሞሶሎኒ በአፍሪካ ለነበሩ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች አደጋ መሆኑ ልቡን ገዝቶታል፡፡ ጦርነቱን በቅርብ ለመረዳት እንዲችል የብሪዝበኑ ኮርየር ሜይል ጋዜጣ የጦርነት ሪፖርተር አድርጎ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ እንዲልከው አደረገ፡፡ በኖቬምበር 22 ቀን 1935 እኤአ ከአውስትራልያ ወደ አፍሪካ በመርከብ አመራ፡፡ በኤደን በኩል አድርጎ ጅቡቲ፣ በጅቡቲ በኩልም በባቡር ተሣፍሮ አዲስ አበባ ገባ፡፡ ኢምፔሪያል ሆቴልም ዐረፈ፡፡

አርኖልድ ዊንሆልት

ዊንሆልት በኢትዮጵያ አርበኞች የአልበገር ባይነት ውጊያ መንፈሱ ተማርኮ ነበር፡፡ እርሱ በደቡብ አፍሪካ፣ በናሚቢያና በአንጎላ የተዋጋው የደፈጣ ውጊያ ስልት በኢትዮጵያ አርበኞች ሲተገበር ማየቱ እንዲቀላቀላቸው ይገፋፋው ነበር፡፡ ዊንሆልት ስለ ደፈጣ ውጊያ አንብቧል፣ ሠልጥኗል፤ በተግባርም ሠርቶበታል፡፡ የደፈጣ ውጊያም ይማርከዋል፡፡ ይህንን የአርበኞች ውጊያ ለመረዳትና ለመዘገብ ግን አልቻለም፡፡ ጣልያኖች ጋዜጠኞች ከአዲስ አበባ እንዲወጡ አይፈቅዱም ነበር፡፡
ዊንሆልት ይህ ነገር መንፈሱን አላረካው ሲል የቀይ መስቀል ሾፌር ሆኖ በመቀጠር ወደ ገጠሮች ለመሄድ ወሰነ፡፡ በ1936 እኤአ የፈለገውን ሥራ አገኘው፡፡ በዚህ ሥራው አማካኝነት በአዲስ አበባ ለነበረው የእንግሊዝ ሌጋሲዮን መረጃ ከማቀበሉም በላይ ጦርነቱን በቅርብ ለመረዳትም ቻለ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ጦርነቱ ዜና መሆኑ አበቃ፡፡ ዊን ሆልትም ወደ አውስትራልያ ተመለሰ፡፡

ዊንሆልት በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ጠባይ ባይደሰትም የኢጣልያ ወረራ ግን ትክክል አልነበረም ብሎ ያስብ ነበር፡፡ በወቅቱ የነበሩት ኃያላን ሀገሮች ለኢትዮጵያ ጥያቄ ተገቢ መልስ አለመስጠታቸውም አሳዝኖታል፡፡ ይህንን ስሜቱን ኮርየር ሜይል ለተሰኘው ጋዜጣ እየጻፈ ቢልክም ዋና አዘጋጁ ግን ለማተም ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ዊንሆልት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሞሶሎኒንና የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ቻምበርላይንን ያወግዝ ነበር፡፡ ጋዜጦች የነፈጉትን ዕድል የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት ይወጣ ነበር፡፡ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ ይናገራል፡፡

በ1937 እኤአ ዊንሆልት አውስትራልያን ለቅቆ እንደገና ወደ የመን አመራ፡፡ በየመን ዋና ከተማ ኤደን ያገኛቸውን የእንግሊዝ ታላላቅ ወታደራዊ ባለ ሥልጣናትንም ኢትዮጵያን ለማገዝ እንግሊዝ ጦር ማዝመት እንዳለባት መወትወት ጀመረ፡፡ በተለይም የአርበኞችን የደፈጣ ውጊያ በመጠቀም ጣልያንን ሰላም መንሣትና በመጨረሻም ማስወጣት አለብን የሚለውን ሃሳቡን በተደጋጋሚ ለማሳመን ይጥር ነበር፡፡ የየመን ቆይታው አልሳካ ሲለውም ወደ ለንደን አምርቶ ከእንግሊዝ የዲፕሎማሲና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር በሃሳቡ ተነጋገረ፡፡ ማንም ግን ትኩረት ሊሰጠው አልወደደም፡፡ ዊንሆልት በዚያ እያለ ታዋቂዋ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሲልቭያ ፓንክረስት ለምታሳትመው New Times – Ethiopian News ዋና የጽሑፍ አበርካች ሆኖ ነበር፡፡

 በተለይም በአፕሪል 16 ቀን 1938 እንግሊዝና ጣልያን ‹የአንግሎ ጣልያን› ስምምነትን ሲፈራረሙ ዊንሆልት በጣም አዘነ፡፡ ለንደንንም ለቅቆ ወደ የመን ተመለሰ፡፡ ከየመንም አገሩ አውስትራልያ ገባ፡፡ በየሄደበት ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ መናገርና መቀስቀስም ዋና ተግባሩ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይም የመተዳደርያ ሥራውን እስከ ማስረሳት አደረሰው፡፡

በዚህ መካከል እንግሊዝና ጀርመን እየተቃቃሩና ወደ ጦርነት እያመሩ ሄዱ፡፡ የአውስትራልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ሜንዝየስም በጀርመን ላይ ጦርነት ዐወጀ፡፡ ዊንሆልት ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ ወሰደው፡፡ ፊቱንም ወደ አፍሪካ ለመመለስ እንዲችል አበቃው፡፡ ሴፕቴምበር 27 ቀን በ1935 እኤአ በ62 ዓመቱ ከአውስትራልያ ለቅቆ ወደ ሲንጋፖር፣ ከዚያም ወደ ኤደን አመራ፡፡ በዚያም አንድ አፓርትመንት ተከራይቶ ዐረብኛና አማርኛ የሚችል ተርጓሚ ቀጠረ፡፡ ለሲልቭያ ፓንክረስት የሚልከውን ጽሑፍ ሳያቋርጥ ያገኛቸውን አካላት ሁሉ የኢትዮጵያ አርበኞችን ስለመርዳትና በእነርሱም አማካኝነት ጣልያንን ድል ስለማድረግ ያማክር ነበር፡፡

ይህ ጥረቱ ውጤት በማምጣቱ የተነሣም በሜይ 1940 ሃሳቡን ተግባራዊ ለማደረግ የሚያስችል ደብዳቤ ከእንግሊዝ ወታደራዊ ባለ ሥልጣናት ደረሰው፡፡ ዊንሆልትም እየፈነደቀ በ62 ዓመት እድሜው እንደገና ወደ ውትድርና ተመለሰ፡፡ በጁን 17 ቀን 1940 እኤአ ከየመን ወደ ሱዳን ካርቱም በረረ፡፡

ምንም እንኳን ለንደን ለሚገኙት ለቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የተገለጠ ነገር ባይኖርም እንግሊዞች ግን እያሠጋቸው የመጣውን የጣልያኖችን ኃይል ከምሥራቅ አፍሪካ ለማስወጣት ምሥጢራዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያን አርበኞች በማገዝ ጣልያኖችን ሰላም መንሣትና በመጨረሻም እንዲወጡ ማደረግ በብዙዎቹ ባለሞያዎቻቸው የታመነበት ዕቅድ ሆነ፡፡ ይህ ዕቅድ ዊንሆልት በተደጋጋሚ ሲወተውተው የነበረ ዕቅድ ነበረ፡፡ እንግሊዞች ይህንን ዕቅድ የተሳካ ለማድረግ በሕንድና በመካከለኛው ምሥራቅ ያገለገለውን በተለይም ደግሞ በምድረ ፍልስጤም እሥራኤልን በመርዳት የተሳከለት ሥራ የሠራውን፣ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላም ወደ ኢትዮጵያ ክርስቲን ከምትባለው ባለቤቱ ጋር መጥቶ ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን ኑሮ የጀመረውን ዳን ሳንፎርድን ነበር የመረጡት፡፡ ሳንፎርድ ስለ ኢትዮጵያ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ ይቆረቆር የነበረ፤ ከብዙዎቹ የዘመኑ መሳፍንትና መኳንንት ጋርም መልካም ግንኙነት የነበረው፤ በንጉሠ ነገሥቱ ዘንድም መታወቅንና መከበርን ያተረፈ ሰው ነበር፡፡

ሳንፎርድና(ግራ) ዐፄ ኃይለ ሥላሴ በደምበጫ ግንባር(ጎጃም)
ዳን ሳንፎርድ አዲስ አበባን ለቅቆ ወደ እንግሊዝ የተመለሰው ጣልያኖች ኢትዮጵያን ሲወርሩ ነበር፡፡ አሁን ከጡረታ ተጠርቶ የዚህ የኢትዮጵያ ተልዕኮ መሐንዲስ እንዲሆን ተደረገ፡፡ መጀመሪያ ወደ ካይሮ ከዚያም ወደ ካርቱም በመምጣት ከሌሎች የውትድርና ባለሞያዎች ጋር ዕቅዱን ነደፈ፡፡ ዊንሆልት ካርቱም የደረሰው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ ዳን ሳንፎርድ በጎጃም በኩል ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ከአርበኞች ጋር ሆኖ ጣልያንን ለመውጋት ሲያስብ በደቡብ አፍሪካው የደፈጣ ውጊያ ጊዜ አንድ እጁ ጉዳት የደረሰበት ዊንሆልት እዚያው ሆኖ እርሱም ከአርበኞች ጋር ተቀላቅሎ የደፈጣ ውጊያ ለመቀጠል እየተሟሟቀ ነበር፡፡

ሳን ፎርድ በገለባት በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ የነበረው ዕቅድ ጣልያኖች ገለባትን በመያዛቸው ምክንያት ከመተማ 19 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ሌሞና ተዛወረ፡፡ ጣልያኖችና ባንዳዎች ከቋራ እስከ መተማ ያለውን ቦታ መሽገውበት ነበር፡፡ ከእንግሊዝ የምሥራቅ አፍሪካ እዝ የመጨረሻውን መመሪያ ሲጠባበቅ የነበረው ኮሎኔል ሳንፎርድ በኦገስት 6 ቀን ዶቃ ከሚገኘው ካምፕ 54 በቅሎ፣ 36 አህዮች፣ ስድስት ገመድ አልባ መገናኛዎች፣ 13303 ጠመንጃዎች፣ 3 ሪቮልቨሮች፣ 30 አሮጌ ጠመንጃዎች፣ ከአራት የእንግሊዝ ወታደሮች፣ ከአንድ ሐኪምና ከአንድ የራዲዮ ሠራተኛ ጋር ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ተነቃነቀ፡፡ ሳንፎርድ ዊንሆልትን በዶቃ ካምፕ ትቶት ነበር የመጣው፡፡

በአንድ በኩል ይህ የተደረገው እነ ሳን ፎርድ መንገዱን ከጠረጉ በኋላ ዊንሆልት እንዲከተላቸው በማሰብ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ያን ጊዜ ዊንሆልት ገና የመጓጓዣ አጋሰሶችን አላዘጋጀም ነበርና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዊንሆልት በዶቃ ካምፕ መገኘት ከሌላኛው መኮንን ከሮኒ ክሊችሌይ ጋር አለመጣጣም አስከትሎ ነበር፡፡ የመረጃ ሰው የሆነው ክሊችሌይ ዊንሆልት አርጅቷል ብሎ አስቧል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ለመዝለቅ ያለውን ጉጉትና ከሲልቭያ ፓንክረስት ጋር ስለሠራው ሥራ ደጋግሞ ማውራቱን አልወደደውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እርሱ ራሱ በዚያ ጊዜ ጥቂት በእድሜ ገፍቶ የነበረው ሳን ፎርድ ዊንሆልትን ‹አርጅቷል› ብሎ በማሰብ በተልዕኮው ውስጥ ማካተት አልፈለገም ነበር፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ዊንሆልት አንድ እጁ በሚገባ አይሠራም፡፡

ዊንሆልት ግን ሁሉንም ትቶ 11 አህዮችን፣ ስድስት የታጠቁ የኢትዮጵያ ወታደሮችንና አንድ ሱዳናዊ  ምግብ አብሳይ አዘጋጀ፡፡ በ1940 እኤአ፣ ኦገስት 31 ቀን ሳን ፎርድ የሄደበትን መንገድ በመተው ዊንሆት ከመተማ በስተደቡብ ወደ ቋራ አቅጣጫ የሱዳንን ድንበር ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ጀመረ፡፡ በመንገድ ላይ የተወሰኑትን ኢትዮጵያውያን ወታደሮችና ሱዳናዊውን አብሳይ ቀነሳቸው፡፡ ሁለት አገልጋዮችንና ሦስት አህዮችን ብቻ በመያዝ ጠመንጃውን እንደ አገሬው ሰዎች በትከሻው ወደ ታች አጋድሞ ጉዞ ቀጠለ፡፡ ከመነሣቱ በፊት ሊሄድ ያሰበበት መንገድ ለጣልያን ያደሩ ባንዳዎች የሚገኙበት አደገኛ መንገድ መሆኑን ተነግሮት ነበር፡፡ እርሱ ግን አልተቀበለውም፡፡ እንዲያውም መጣቢያ በምትባል ጣቢያ 50 የጣልያን ወታደሮችና 300 የአካባቢው ተወላጅ ባንዶች ካምፕ መሥርተው አካባቢውን እየቃኙ ነበር፡፡
ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ
ዊንሆልት ኦገስት 31 ከሌሎቹ የእንግሊዝ መኮንኖች ተለያይቶ በቋራ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ከዘለቀ በኋላ ድምፁ ጠፋ፡፡ ሳንፎርድም ዊንሆልት ወደ እርሱ ዘንድ አለመድረሱን ገለጠ፡፡ በገለባትና በካርቱም የሚገኙ የእንግሊዝ ሚሲዮኖች ዊንሆልት የት እንደገባ ለማወቅ አልቻሉም፡፡ የዊንሆልት ዜና ከተሰማ 15 ቀናት አለፉ፡፡ ሴፕቴምበር 15 ቀን 1940 ከዊንሆልት ጋር አብረው ሄደው የነበሩ ሁለት ሰዎች  በዶቃ ካምፕ ተገኙ፡፡ በካምፑ የነበሩት ቴሲገርና ላውሬ የተባሉ ሁለት የእንግሊዝ መኮንኖች የዊንሆልትን ዜና ጠየቋቸው፡፡ ኢሳ አቡ ጂያር እንደተናገረው ከሆነ ይመራቸው የነበረው ሰው የጉሙዝን አካባቢ እያቋረጡ እያሉ ጠፋባቸው፡፡ በዚህም ምክያት በመጣቢያ አካባቢ ካምፕ ሠርተው ተቀመጡ፡፡ በዚህ መካከልም አንድ ቀን በድንገት ከአራቱም አቅጣጫ ተኩስ ተከፈተባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ዊንሆልት ጠመንጃውን ለአስተርጓሚው አሸክሞት ነበር፡፡

ሁለቱ አገልጋዮቹ ተኩሱን ሲሰሙ እየሮጡ በየአቅጣጫው ጠፉ፡፡ መሣሪያ ያልያዘው ዊንሆልት ብቻውን ቀረ፡፡ ከዚህ በኋላ ያለውን ኢሳ አቡ ጂያር የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ እርሱ አምልጦ ወደ ዶቃ ገብቷል፡፡ ሁለቱ የእንግሊዝ መኮንኖች ይህንን ሪፖርት ሲያስተላልፉ ሌላ ዘገባ ከገለባት መጣላቸው፡፡ ‹‹ሌፍትናንት ዊንሆልት በብዙ ችግር ወደ ሰራቆ ደርሷል፡፡ ፊታውራሪ ወርቁ ስንቄም አስፈላጊውን ነገር ረድተውት ወደ ጎጃም አምርቷል›› ይላል፡፡ ነገር ግን ዊንሆልት ወደ ጎጃም ዘልቆ ሊታይ አልቻለም፡፡ በኋላ እንደተረጋገጠውም የገለባቱ ዘገባ ትክክል አልነበረም፡፡

ከወራት በኋላ እንግሊዞች በአካባቢው ባደረጉት አሰሳ ዊንሆልት ይጠቀምበት የነበረውን  ሄልሜት፣ የተበጫጨቁ ልብሶቹንና ይዞት የነበረውን ቦርሳ(ኪት) አገኙት፡፡ አሳሽ ጓዱም ዊንሆልት መጀመሪያ ተመትቶ ወደ ጫካ በመግባት በዚያው ሳይሞት እንዳልቀረ ገመተ፡፡

ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የዊንሆልት ባለቤት በካርቱም ያለውን የእንግሊዝን ሚሲዮን የባሏን መጨረሻ እንዲያሳውቃት ጠይቃ ነበር፡፡ በጁላይ 8 ቀን 1941 እኤአ ከጋላባት የተነሡ እንግሊዝ ወታደራዊ አሳሾች ዊንሆልት የሄደበትን መንገድ ተከትለው እነዚያ ሁለት አብረውት የተጓዙ ሰዎች ካምፕ ሠራንበት ወዳሉት ቦታ ተንቀሳቅሰው ነበር፡፡ በአካባቢው የተገኙ መረጃዎች እንደጠቆሙት ጣልያኖች የዊንሆልትን መምጣት በማወቃቸው በመንገዱ ተከትለውታል፡፡ በመጨረሻም ካምፑን በመውረር ተኩስ ሲከፍቱባቸው ዊንሆልትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ካምፑን ጥለው ጠፉ፡፡ ጣልያኖችና ባንዶችም ወደ ካምፑ ገቡ፡፡

ከዓይን እማኞችና በጊዜው ከነበሩ የአካባቢው ሰዎች ያገኘውን መረጃ ይዞ አሳሹ ጓድ ከመጣብያ የአራት ወይም የአምስት ሰዓት መንገድ ወደሚርቀውና ከሺንፋ ወንዝ አጠገብ ወደነበረው የዊንሆልት ካምፕ ቦታ ደረሰ፡፡ በአካባቢው በተደረገው ምርመራ የአህዮች አጥንት፣ የተተኮሱ ጥይቶች ቀለሃዎችና የጫማ ቅሬቶች ተለቀሙ፡፡ በአቅራቢያውም የጥርስ መፋቂያና ቦት ጫማ ተገኘ፡፡ ካምፑ ነበረበት ከተባለው 300 ያርድ ርቀት ላይም በመበስበስ ላይ የነበሩ የሰው አጥንቶች ታዩ፡፡ ምናልባትም የቆሰለው ዊንሆልት እዚህ ድረስ ተጉዞ ይሆናል ለሞት እጁን የሰጠው፡፡

ካርቱም የሚገኘው የዊንሆልት የመታሰቢያ ሐውልት 
ይህ ሪፖርት ሲድኒ ሲደርስ የኩዊንስ ላንድ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ኦክቶበር 10 ቀን 1941 እኤአ የዊንሆልትን መሞት በይፋ ዐወጀ፡፡ ቋረኛው የአውስትራልያ ሰውም የኢትዮጵያን ነጻነት ሳያይ ቋራ ላይ ቀረ፡፡ አንደኛው ቋረኛ(ዐፄ ቴዎድሮስ) ለእንግሊዝ እጄን አልሰጥም ብሎ በጀግንነት ሞተ፡፡ ሌላኛው ቋረኛም ኢትዮጵያን ነጻ አወጣለሁ ብሎ በሀገሬው ባንዶች ተገደለ፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር እንዲህ ነጭ ከጥቁር ዋጋ ከፍሎባታል፡፡ ኢትዮጵያ እንግሊዞች፣ ኩባዎች፣ አውስትራልያዎች፣ ዐረቦች፣ አይሁድ፣ ሱዳኖች፣ ሩሲያዎች፣ አሜሪካኖች፣ ግሪኮችና ሌሎች ዋጋ ከፍለው ሀገር ያደረጓት ሀገር ናት፡፡ እንኳን የተወለዱባትን ያወቋትን ሰዎች ሕይወት የምታስገብር ሀገር፡፡

 ከፐርዝ ወደ ሜልበርን፣ ኳንታስ አውሮፕላን ላይ

ለወራት በአ/አ የተቀመጡት ሊቀ ጳጳሱ ትላንት ምሽት ወደ ደ/አፍሪካ ተጉዘዋል በሊቀ ጳጳሱ አስተዳደር የተማረሩና አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ አቤቱታዎች ለውጭ ግንኙነት መምሪያውና ለፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እየጎረፉ ነው ከዚህ በታች የምናቀርበውና ‹‹የአቡነ ያዕቆብ ሲሞናዊነት[ስምዖናዊነት] ሲገለጥ›› በሚል ርእስ የተጠናቀረው መልእክት የደረሰን በኬንያ – ናይሮቢ ከሚገኙ ምእመናን ነው፡፡ መልእክቱ÷ የመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከትን የተመለከተ ዘገባ በጡመራ መድረኩ ለንባብ ከበቃበት […]

1-ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው። የአንድነት ምሽት በቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል። የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስም መከሰስም የለበትም። ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ […]

የኢትዮጵያ ጀግኖች ታሪክ ሲነሳ፤ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱት መካከል ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ በዋናነት ይጠቀሳሉ። – በአባታቸው ኦሮሞ፣ በናታቸው የጉራጌ ተወላጅ የሆኑት ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባ ነፍሶ) በተለይ በ1888 ዓ.ም. በአድዋ ጦርነት ወቅት በአጼ ምኒልክ ስር ሆነው በመድፍ አስተኳሽነት በሰሩት ጀግንነት ይታወሳሉ። እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያ ለአገራቸው እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ያደረጉት ታላቅ ጀብዱ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ይኖራል። […]

በአንድ ወቅት በደቡብ አፍሪካዊቷ ከተማ በኬፕታውን የሚኖር አንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደር ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ አንድ አሳዛኝ ገጠመኙን እንዲህ አጫውቶኝ ነበር፡፡ ይህን ታሪኩን ያካፈለኝ ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ የሥራ ቦታው ላይ ከአንድ ከኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጋር በተነሳ ጠብ በተፈጠረ ግጭት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን አንድ የፊቱን ጥርሱን በቦክስ ያወልቀዋል፡፡ የጥርሱን መውለቅ የሰሙ የዚህ ሰው ጓደኞችም ተሰባስበው ይህን ሰው […]

በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” […]

ተክለሚካኤል አበበ – ቶሮንቶ (ካናዳ)

በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ

 

1-      ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው።የአንድነት ምሽትበቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል።የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስምመከሰስም የለበትም።ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስትወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ …

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋና እንደዘገበው ፤ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነበራቸውን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል  ተጠርጥረው ነው ። ፋና ይህም ቢልም አቶ ወልደስላሴ ከደህንነት ዋና ሹሙ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር ጠብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸው በስፋት ሲነገር ቆይቷል። በተለይ መቀሌ በተካሄደው የህወሀት ጉባኤ ላይ በአቶ ጌታቸው …

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከኪራይ ቤቶች ድርጅት ባገኘው መረጃ በአዲስ አበባ የተገነቡ 2345 ቤቶች ለሚኒስትሮች እና ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ባለስልጣናት ተሰጥተዋል። የቤቶች ልማት ባካሄደው ጥናት ፣ አብዛኞቹ ባለስልጣናት የግል ቤቶቻቻውን በማከራየት በመንግስት ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ።  ኪራይ ቤቶች ቤቶቹን እንዲለቁ ሲጠይቃቸው በግል የገነቡዋቸው ቤቶች ለደህንነታቸው ዋስትና እንደማይሰጡ በመከራከር ቤቶቹን ለማስረከብ ፈቃደኞች …

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዩ -ኤርትራ ግጭት እና ኢትዮጵያ ከሶማሊያው አልሸባብ ጋር ካደረገችው ጦርነት ጋር በተያያዘ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች በስነልቦና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን የጦር ሃይሎች ሆስፒታል የስነ ልቦና ህክምና ቡድን መረጃ አመለከተ ከመዝገብ ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ፤ በጦርነቱ ስዓት በተከሰተ ምንነቱ ባልታወቀ የሞራል እና የስነ ልቦና ችግር ከ3 ሺ 500 በላይ …

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬው እለት 3ኛው የአማራ ክልል ትምህርት ፊስትቫል ምክትል ጠቅላይ ሚነስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ፤የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሺጉጤ ፤ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ በተገኙበት ሲከፈት፣ ዶክተር ጸሐይ ጀምበሬ ባቀረቡት ጽሁፍ፣ የመንግስት ትምህርት ቤት አሰተዳደራዊ ችግር ለትምህርት ጥራት እንቅፋት እየሆነ መጥቱዋል ብለዋል።  ከአመቱ ውስጥ  260 ቀናት ይባክናሉ ያሉት …

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞያሌ ከተማ  በገሪና በቦረና ጎሳዎች መካከል ከሳምንታት በፊት የተነሳው ግጭት እንደገና አገርሽቶ የአካባቢው ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው። የኬንያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ወደ አካባቢው በመላክ ግጭቱን ለመከላከል እየሞከረ መሆኑን ቢናገርም ችግሩ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የኬንያ ጋዜጦች አየዘገቡ ነው። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ20 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። በአካባቢው የሚገኙ …

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ሶሪያ ውስጥ መርዘኛ ጋዝ በመጠቀም ባለፈው ሣምንት ተካሂዶ በነበረ ጥቃት ከሶሥት መቶ የሚበልጡ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉ ወዲህ የዳማስቆስን መንግሥት ተጠያቂ በማድረግ የአየር ድብደባ ለማካሄድ በዩ ኤስ አሜሪካና በአጋሮቿ የተያዘው ዝግጅት ውጣ-ውረድ እየበዛው ነው።

ለአንድ ህዝብ ሃገር ማለት የመኖር ዋስትናው ተጠብቆ ሳይሸማቀቅ፣ ሳይበደል፣ ፍትህ ሳዩጓደል፣ የዜግነት መብቱ ተጠብቆ የህግ ከለላ አግኝቶ በነፃነት የሚኖርብት ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን ሃገር መሆን ከተሳናት እንሆ ሃያ ሁለት አመት ተቆጠረ፡፡ የደርግ ስርዓትን ተክቶ በትጥቅ ትግል መንበሩን የተቆናጠጠው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ የፖለቲካ ስልጣኑንም ሆነ የኤኮኖሚ አውታሩን በአንድ ብሄር ብቻ አደራጅቶ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ እንደ […]

  ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen

ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ በተነሳ የእሳት አደጋ ቃጠሎ በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ፡፡ ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በ18 ሚሊዮን …

ሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እየተካሄደ ያለውን የሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ የማፈን ተግባርን በመቃወም ነገ በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ የሰልፉ አስተባባሪ አካላት ለኢሳት ገለጹ፡፡ የአርብ የፀሎትና የስግደት ስነ ስርዓትን ተከትሎ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በሀገር ቤት እየተካሄደ ያለውን የመንግስት እርምጃ ለማውገዝ ያለመ እንደሆነ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሰይድ …

ነሃሴ ፳፫(ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ …

የሶሪያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ፈፅሟል የተባለው የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቃት በተባበሩት መንግስታት ፈታሾች በመጣራት ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ምዕራባውያን መንግሥታት በሶሪያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር የተዘጋጁ ይመስላል ከህግ አንፃር ሲታይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ዓለም ዓቀፉን ህግ የሚጥስ እርምጃ ነው ።

በአዲሱ የትምሕርት ዘመን ላይቤሪያ ዩኒቨርስቲ ያመለከቱ 25 ሺህ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናውን መውደቃቸው የላይቤሪያ የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑን እንደሚያመለክት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ሳይቀሩ አምነዋል ።

ቀሬ ቤተእስራኤላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ የትናንቱ ጉዞ የመጨረሻው እንዳይደለ ቤተ እስራኤላዊ የፓርላማ አባል ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ትንናት እስራኤል የገቡት ኢትዮጵያውያን አይሁዶች እጎአ በ2010 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የሚገኙ ቀሪ የቤተ እስራኤል ወገኖች በ 3 ዓመት ውስጥ ተጠቃለው እስራኤል እንዲገቡ በታቀደው መሠረት የተከናወነ ነው።

ይኽው መፀሀፍ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ ለቀሪው ትውልድ የሚያቆይ ታላቅ ቅርስ መሆኑን በመፀሃፉ ምረቃ ላይ ተገልጿል ። መፀሃፉ ለህትመት የበቃው ደራሲው ተስፋዮ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ በኋላ ነው ።

ፎቶ አንሽው ሚካኤል ፀጋዬ በተለያዩ አገሮች አውደ ርዕይ አሳይቷል። ከዚህ ባሻገር ፎቶዎቹ በታዋቂው ሳምንታዊ የጀርመን መፅሄት «ዴር ሽፒግል» ታትመው ወጥተዋል። ሮይተርስን እና ብሉምቤርግን የመሳሰሉ የመገናኛ ብዙኋንም በፎቶዎቹ ተጠቅመዋል።