ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አለም የሚኖሩ ሙስሊሞች 1 ሺ 436ኛውን የኢድ አልፈጥር በአል አክበረዋል። በአሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተከበረ ሲሆን፣ ካለፉት 3 ዓመታት ጀምሮ ሲታይ እንደነበረው በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ ታይቷል። በተለያዩ አለም ክፍሎች በአሉ በአንጻራዊ መልኩ በሰላም ሲጠናቀቅ፣ በናይጀሪያ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ከ10 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን …

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ችግሩ የተፈጠረው በጋሞና በጎፋ ተወላጅ ባለስልጣኖች መካካል ነው። የዞኑን፣ የክልሉንና የፌደራል ስልጣኑን የተቆጣጠሩት የጎፋ ተወላጅ ባለስልጣኖች፣ ጋሞዎችን ሰድበዋል ፣ የጋሞ ተወላጅ ባለስልጣናትን በንቀት ያያሉ በሚል እርስ በርስ በጀመሩት ቁርሾ፣ የመንግስት ስራ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ የእርስ በርስ ሽኩቻውን ወደ ህዝብ በመውሰድ የጋሞ ባለስልጣናት የጋሞ …

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ኤንድ ኢንተርናሽናል ስተዲስ የተባለው ተቋም ” ከአሜሪካ ጉዞ በፊት የአሜሪካ ፖሊሲ በኬንያና በኢትዮጵያ” በሚል ርእስ ባዘጋጀው ፓናል ውይይት ላይ የተገኙት በጆርጅ ማሶን ዩኒቨርስቲ የግጭት አስወጋጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ቴሬንስ ሊዮንስ እንደተናገሩት ኢህአዴግ በቅርቡ በኤርትራ ላይ ጦርነት ለማወጅ የሰጠውን መግለጫ አሜሪካ እንደማትደግፈውና እንደማትተባበር በግልጽ …

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በበሳውዲ አረቢያ ለረዢም ጊዜ በስደት ቆይተው ወደ ትውልድ ቀያቸው የተመለሱ በአማራ ክልል የሚገኙ ከስደት ተመላሾች ፤በራሳቸው ካፒታል እና ጥረት ለመንቀሳስ ቢሞክሩም “ልዩ ልዩ መሰናክል በመፍጠር የገዢው መንግስት ሊያሰራን አልቻልንም “በማለት ተናግረዋል፡፡‹‹ ከስደት ከተመለስን በኋላ በማህበር ተደራጁ በማለት ቢያደራጁንም የምንሰራበት የእርሻ መሬት ለማግኘት ለአምስት ወራት አሰቃይተውናል፡፡ ›› …

ሐምሌ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ 2007ትን መቶ በመቶ በሆነ ድምጽ አሸንፊያለሁ ብሎ ያወጀው ኢህአዴግ፣ ከምርጫው በሁዋላ ያሰባሰበው የህዝብ አስተያየት ለፓርቲውም ሆነ ለአገሪቱ ህልውና አስፈሪ መልእክት የያዘ ነው ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ሪፖርቱ በመጪው ነሃሴ በሚካሄደው የግንባሩ ጉባኤ ላይ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ህዝቡ በአስተዳዳር፣ በፍትህ፣ በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች፣ በውሃና በመብራት እጦት …

ወንድሜ ሆይ ይህን ለኢትዮጵያ ህዝብ አድርስልኝ።ነገሩ እንዲህ ነው። ምንአልባት አጋዚ ስለሚባል ልዬ ሃይል ሰምተህ ይሆናል። አጋዚ ማለት ከትግራይ ገጠር ቦታወች የሚመለመሉ ወጣቶች ስብስብ ነው። እኒህ ወጣቶች ገና የስምንት አመት እድሜ እያሉ ነው የሚመለመሉት። ከትግረኛ ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቋንቋ አይናገሩም። …

የአጋዚ ጦርና የወያኔ ሴራ በውስጥ አወቅ ሲጋለጥ! (የውስጥ መልዕክት) Read more »

**የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ ** “የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰ እናውቃለን:: መጀመርያውኑ መታሰር እልነበረባቸውም:: ሲፈቱም አፈታታቸው ሙሉ አይደለም” ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል:: የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ […]

የአእምሮ ህመምተኛ የሆኑ ወላጅ እናት አሉት፡፡ወጥቶ እስኪገባ በስስት የሚጠብቁት ሁለት ልጆቹን በተመለከተ ቁጥር የሚወርሷት አገር ብዙ የችግር ቋጠሮዎችን እንደተሸከመች ያስተውልና ነገን ስለ ልጆቹ ‹‹ብሩህ ››ለማድረግ ስጋውን፣አእምሮውንና መንፈሱን ያድሳል፡፡በትግሉ ውስጥ የሚያደክሙ ‹‹ምን አገባኝን የሚያስመኙ››ብዙ መሰናክሎች ቢደቀኑበትም ስንታየሁ ለበቃኝ ‹‹ግንባሩን ››አያጥፍም፡፡ በአንድ ወቅት ኢመደበኛ በሆነ ጭውውት መሐል የእነ ናትናኤል መኮንን ጉዳይ ተነስቶ ‹‹እቤቴ ገብቼ ልጆቼን በናፍቆት ስስማቸው […]

ሕግ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ መብታቸዉን ለማስከበር ፣ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ፣ ወንጀል ሳይፈጽሙ በዉሸት ክስ በወህኒ በግፍና በጭካኔ እየሰቃዩ ያሉ የአንድነት አባለት ብዙ ናቸው። ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ቢያንስ ፣ ለማረጋገጥ የቻልነው ከአምስት በላይ አንድነቶች ታስረዋል፡ 1. አንድዋለም አራጌ ( ም/ፕሬዘዳነት) 2. ሃብታሙ አያሌው (የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ድምጽ ሰብሳቢ) 3. አለነ […]

ሁለት ሕጻናት አሉት። የመጀመሪያ ወንድ ልጁ ሩህ ይባላል። ከአራት አመታት በፊት፣ ልጁን ከትምህርት ቤት ሊያወጣ ወደዚያ ሲያመራ ታጣቂዎች ከበቡት። እየሰደቡ፣ እየደበደቡ ወደ ወህኒ ወሰዱት። አንድ ፖሊስ ይበቃ ነበር። ግን የለየለት ነፈሰ ገዳይ የሚይዙ ይመስል፣ ይሄን አንድ ሰላማዊ የልጅ አባት ለመያዝ ተረባረቡ። አይ ጭካኔ ! ይህ ሰው አንዱዋለም አራጌ ነው። የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳነት የነበረ፣ አንጋፋ […]

አስቴር ስዩም ትባላለች ። በጎንደር ምእራብ አርማጭሆ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል ነች። የማስተርስ ዲግሪዋን ከዩኒቨርሲቲ በማእረግ ተቀብላለች፡ ላመነችበት ነገር ወደኋላ የማትል የጣይቱ ልጅ መሆኗን ለመረዳት ብዙ ጊዜ አላስፈለግም። ስትናገር ቁጥብ ናት ። ከመናገር ማዳመጥን ታስቀድማለች ።ታዲያ ይህች ባለትዳርና አንድ ልጅ እናት የሆነች የነፃነት ታጋይ፣ ከገዢው መደብ ካድሬዎች፣ የተለያዩ ማባበያዎች ቢቀርብላትም ሳይማር ያስተማረኝን እና ገዢዎቻችን […]

ወያኔ ሃብታሙ አያሌው ላይ ላቀረበው ክስ፣ ምንም አይነት መረጃ የለዉም ። ክሱ በአብዛኛው “በኢሳት ፣ በዚህ ራዲዮ፣ በዚያ ፓል ቶክ ክፍል … ቃለ መጠይቅ አደረገ ..” ወዘተረፈ የሚል ነው። ኢሳት ላይ እጅግ በጣም በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና የዉጭ አገር ዜጎች ቀርበዋል። ቪኪ ሃደልሰንን፣ ዶር መራራ ጉዲናን፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ አርቲስቶችን መጥቀስ ይቻላል። አንድ ንግግር […]

ያልተዘመረላት፣ ያልተነገረላት ጀግና ኢትዮጵያዊት ሴት ናት። እንዴሌሎች “እኔ ምን አገባኝ ? አርፌ ልቀመጥ” ብላ፣ ባርነትንና ዉርደትን አሜን ብላ ተቀብላ፣ ሕሊናዋን ሸጣ፣ የገዢው ፓርቲ አዉደልዳይ ሆዳም ካድሬና አገልጋይ ሆና ፣ በዘረኘንትና በጠባብነት በሽታ ተለክፋ መኖር ትችል ነበር። ግን አላደረገችውም። ከደቡብ ክልል ከወላይታ ሶዶ ናት። ሃይለማሪያም ደሳለኝ መጣሁበት ካለው። እንደ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሌሎች አሽከር አልሆነችም። እንደ ኃይለማሪያም […]

የአንዲት ትሁት ኢትዮጵያዊት ባላቤትና የልጅ አባት ነዉ። የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ወጣት አመራር አባል ነበር። በፓርቲዉ ዉስጥ፣ በዉጤት ላይ የተመሰረተ፣ የሰለጠነ ሰላማዊ ፖለቲካ ያራምድ የነበረውን በወያኔ ሕጋዊነትን በጉልበት የተነጠቀ የአንድነት ፓርቲ አደራጅ ነበር። በሐሰት የሽብርተኝነት ክስ ይከሰሳል። ምንም እንኳን በአገራችን የሕግ ስርዓት እንደሌለ ቢታወቅም፣ የአገዛዙን ሕገ-አራዊነትን ለማጋለጥ ሲል፣ ራሱን ለመከላከል ሞከረ። ሕግን […]

ጀግናችንን ፍቱልን!! ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት የነፃነት ታጋይ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ መስራች አባል፣ የወረዳ 2/14 ሰብሳቢ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባል ነው:: ለሰው ልጆች ያለውን አክብሮት እና ፍቅር የትግል አጋሮቹ እንዲሁም የስራ ባልደረቦቹ እና እውቀቱን ሳይሰስት የሚለግሳቸው ተማሪዎቹ ምስክርነት የሚሰጡለት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ::ናትናኤል መኮንን ይባላል:: በቅርብ የምናውቀው ጓደኞቹ ሆድዬ በሚል ቅፅል ስም እንጠራዋለን። ለሰው […]

አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ በነአንዱዋለም አራጌ ላይ ክስ ያቀረበ አቃቤ ሕግ ነው። ይህ የሕግ ሰው ነኝ ባይ ካድሬ፣ በወያኔ ኢቲቪ ቀርቦ «አንዱዋለም አራጌን በተመለከተ፣ የግንቦት ሰባትን ተእልኮ ለማስፈጸም አገር ዉስጥ በሕቡእ (ስዉር) ይንቀሳቀሳል። በሰላማዊ ትግል እንታገላለን የሚሉ የፓርቲዎችን ሽፋን አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረ በመሆኑ በቂ ማስረጃ አቅርበናል» ሲል ነበር የተናገረው። አንዱዋለም ያደረጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ሲያደርግ የነበረው […]

ለሃያ ስምንት ዓመታት ካገለገሉበት ተቋም ያለአግባብ መባረራቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ እና የዓለምአቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር መረራ ጉዲና ተናገሩ።

የታሰሩትን ማሰብ፣ ለታሰሩት መቆም ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነት ነው። ዜጎች በዉሸት ሲታሰሩ፣ ፍትህ አጥተው ሲጉላሉ፣ ሐሳባቸውን በነጻነት በመናገራቸው ብቻ ወንጀለኛ ወይንም ሽብርተኛ ተብለው ስታሰሩ፣ በእስር ቤት ራቁታቸውን ሆነው ሲደበደቡ፣ ወንዶች ብልታቸው ሲቀጠቀጥ ፣ ሴቶች በወንድ መርማሪዎቻቸው ፊት ጅምናስቲክ እንዲሰሩ ተደረጎ ክብራቸዉን የሚነካ ነገር ሲፈጸምባቸው፣ በፍርድ ቤት ፍትህ ማግኘት ሳይቻል ሲቀር፣ ዳኞች ከደህንነቶች “ይሄን ፍረዱ፣ ይሄን […]

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 9 2007) ግጭት ወደአለበት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ አሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትናንት ረቡእ ገለጸ ። በየመን ያለው የጸጥታ ሁኔታ አደገኛ ቢሆንም በብዙ ሺ  የሚቆጠሩት ስደተኞች አሁንም ድረስ ወደ ሀገሪቱ እየገቡ መሆናቸውን ረቡእ ከጄኔቫ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ የሰጡ የደርጅቱ ሀላፊዎች አስታውቀዋል። ከኢትዮጵያኑ በተጨማሪ የሶማሊያ ተወላጆች ወደየመን እየተሰደዱ እንደሆነ የገለጸው የተባበሩት መንግስታት …

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በገዢው መንግስት ከፍተኛ አፈና የሚደርስበት የኢሳት የቴሌቪዝን ስርጭት ከሳምንታት ሙከራ በሁዋላ ዛሬ ሙሉ ስርችቱን በ ኤም 44 ሳተላይት ጀምሯል። አዲሱ ሳተላይት ጠንካራ ሲግናል ያለው ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በሙከራው ወቅት ስርጭቱን ለማፈን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን የኩባንያው ኢንጂነሮች ገልጸዋል። ተመልካቾች አልፎ አልፎ የድምጽ ወይም የምስል መዛባት ቢያጋጥማቸው …

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲያችሁ አባሎች የትጥቅ ትግልን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በመርህ ደረጃ ኢህአዴግን ብሶት ከወለደው ሰው ጠመንጃ የማያነሳው ለምን ድነው ሲሉ ጠይቀዋል። ሰው መኖር ካልቻለ ምን አማራጭ አለ ሲሉ የጠየቁት ኢ/ር ይልቃል ሰው መቀመጫ መሄጃ ሲያጣ ቢሀድ ምን ይገርማል፣ አትሂድስ …

ሐምሌ ፺፻ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ቀደም ብሎ እንደተዘገበው በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እስረኞች ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችሁዋል ከተባልን፣ አቶ አንዳርጋቸው ቀርበው ይጠየቁልን የሚል መከላከያ መልስ ሰጥተው ነበር። ፍርድ ቤቱ አቶ …

የሜክሲኮው አደጋኛ የእጽ አዘዋዋሪ ከጥብቁ እስር ቤት እንዴት አመለጠ? በዚህ ቪዲዮ ይመልከቱት አደገኛው የእጽ ነጋዴ ጆአኪም ጉዝማን (ኤልቻፖ) ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግበት ከሜክሲኮ እስር ቤት ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ማምለጡ አይዘነጋም፡፡ ይህ ሲናሎአ የተባለውን የእጽ ዝውውር ወንጀል መረብን የሚመራና በመላው አለም ግዙፍ መረብና የዘረጋ ወንጀለኛ በእስር ክፍሉ ሻወር ቤት አካባቢ በተከፈተ አነስተኛ ጉድጓድ በመጠቀም መሬት ለመሬት ተሸሎክሉኮ […]

የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር በአካል ተገናኝታችኋል›› የሚል ክስ የመሰረተባቸው ተከሳሾቹ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ …

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ወሰነ – ነገረ ኢትዮጵያ Read more »

*በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መከፋፈል ተፈጠረ፡፡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የሚከተለው ከቅኝ ገዥዎች የተወረሰ ህዝብን በመከፋፈል ለረዥም ጊዜ የመግዛት ፀረ ኢትዮጵያዊ አንድነት የሆነ የበሰበሰ አውዳሚ ፖለቲካዊ ቀመር ከጎሳዎች አልፎ በመንደርና ቤተሰብ ውስጥ ገብቶ ስር በመስደድ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በደቡብ ክልል ጋሙ ጎፋ ዞን አስተዳደር የህወሓት አሻንጉሊት ባለስልጣናት መካከል መንደርንና […]

‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡›› አበበ ካሴ እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ […]

የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረውና አገዛዙ ጥርስ ውስጥ በመግባቱ ‹‹ሽብርተኛ›› በመባል የእድሜ ልክ እስራት የተበየነበት ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ሁለተኛ የሆነውን የፖለቲካ መፅሐፍ ቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ አበርክቷል፡፡ ቁርጠኛና የፅናት ተምሳሌት እንደሆነ የሚነገርለት አንዷለም ከዚህ በፊት ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› የሚል መፅሐፍ ከታጨቁባት እንድ ክፍል ውስጥ ሆኖ በማይመች ሁኔታ እስረኞች ሲተኙና በብርድ ልብስ ተሸፍኖ በመፃፍ ለሕትመት […]

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ሰርግና ምላሽ በኢትዮጵያ ከወዲሁ የተወሰኑ እስረኞችና በመፍታትና ብዛት ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን በማሰር ወደ ቀኑ እየገሰገሰ ይገኛል፡፡የሰማያዊና የቀድሞው አንደነት አመራሮችና አባላት ኦባማ ወደ አገራችን ሲመጡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እያሴራችሁ እንደሆነ ደርሰንበታል በማለት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ባሳለፍነው ሐሙስ የሞያ አጋሮቹ መፈተታት የፈጠረበትን ደስታ አጣጥሞ ሳይጨርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ምናለ ከአምስት […]

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምፕዩተሬ ላይ “የስለላ ማልዌር ልኮብኝ ሲሰልለኝ ቆይቷል” ሲሉ ኪዳኔ ተብለው የተጠሩ አሜሪካዊ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ወረዳ ፍርድ ቤት ክሥ መሥርተው ጉዳዩ ትናንት ዳኛ ፊት ቀርቧል፡፡ ያዳምጡ↓↓↓

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፣ የቀዳሚ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅና የሚሊዮኖች ድምጽ ጋዜጣ ሪፖርተር የነበረው ሃብታሙ ምናለ ” የአልሸባብ የሽብር ወንጀል ቡድን ሴል ነህ” በሚል ተጠርጥሮ መገናኛ አካባቢ በሚገኘው አምቼ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ገልጿል። ሃብታሙ፣ “የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሚገኙበት ስብሰባ ላይ …

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሰሜናዊ ምዕራብ 302 ኪሎ ሜርት ‘ርቀት ላይ በሚገኘው በዋጅድ አውራጃ ልዩ ስሙ ቦቆል ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ማክሰኞ ዕለት የጦር መሳሪያ ያነገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በከተማዎች ውስጥ ሲርመሰመሱ መታየታቸውን የዘገበው ሆርስድ ሚዲያ፣ በወታደሮቹ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሞከሩ 7 ወታደሮች መገደላቸውን የሰድሩ አውራጃ …

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የሁለተኛው ዙር የትራንስፎርሜሽን እቅዱን እያስታወቀ ባለበት ቢዘህ ወቅት ከህዝቡ በርካታ አቤቱታዎችን እያስተናገደ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እና አቶ በረከት ስምኦን በመሩት ፤ የእንጅባራ ፤ ወልድያ እና ቻግኒ ከተሞች ስብሰባ ፣ ህዝቡ “ኢህአዴግ ለወጣቱ መልካም አማራጮችን አለማቅረቡን እንዲሁም በውሃ ና በመብራት ችግር እየተሰቃየ መሆኑን” …

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ የአፍሪካና የዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾች ኅብረት ማክሰኞ ዕለት ባወጡት የአቋም መግለጫ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በያዝነው ወር በሚያደርጉት የአፍሪካ ጉብኝታቸው ወቅት ከዴሞክራሲ መብት ተሟጓቾች ጋር ፊትለፊት መገናኘት እንዳለባቸው አሳሰቡ። የሰብዓዊመብት ኅብረት ለሁዋይት ሃውስ በላኩት ደብዳቤ ላይ ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያና በኬንያ ያለውን የመብት ጥሰቶች ሊመለከቱዋቸው …

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኢትዮጰያውያኑ በምራባዊ የሀገሪቱ ግዛት በኢምቡ ክፍለ -ከተማ በኪቲሙ ገበያ አቅራቢያ በሚገኝ እርሻ ውስጥ ሊደበቁ ሲሞክሩ ነው የተያዙት። ሁሉም ወንዶችና ከ30 ዓመት በታች የሆኑት ኢትዮጰያውያን ባካባቢው ነዋሪዎች ጥቆማ በበቆሎ ማሳ ውስጥ እንዳሉ መያዛቸውን የገለጹት የኢምቡ ኮሚሽነር፤ ሁሉም የኪስዋሀሊ ቋንቋን እንደማያውቁ አመልክተዋል። በ አካባቢው ህገወጥ …

ሐምሌ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ በመለስተኛ የግል የአውሮፕላን የበረራ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ባቀረቡት አቤቱታ፣ የስራ ዘርፉ ከቢሮክራሲ ጋር በተያያዘ ለኪሳራ እየዳረጋቸው መሆኑን ሳያንስ፣ ከበረራው 24 ሰአታት በፊት ለመከላከያ ሚኒስቴር ሪፖርት እንዲያደርጉ መታዘዛቸው ስራቸውን አስቸጋሪ አድርጎታል። አንዳንድ ባለሀብቶች በተለይ ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚደረገው በረራ ፈታኝ እንደሆነባቸው ገልጸዋል። አስቸኳይና …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ከተከናወነው አምስተኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ በኋላ፣ በአባላት፣ በአመራሮችና በምርጫ አስፈጻሚ ግለሰቦች ላይ በተጠናከረ ሁኔታ እየደረሰ ያለውን ወከባ፣ እስራትና ግድያን በተመለከተ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት፣ በጉዳቱ ላይ ቁርጠኛ ውሳኔ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ …

መድረክ የአባላቱ እስራትና ሞት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ Read more »

በተለያዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመተወን የምትታወቀው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን እና ግብረ አበሯ በእስራት ተቀጡ። በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሾቹ በእስራት የተቀጡት ከታዘዘላቸው ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ከባንክ ቤት በማውጣት ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ነው። የ22 አመቷ ተዋናይት ከግብረ አበሯ ጋር በመሆን በተሰጣቸው የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት ለፊቱ ሁለት ቁጥርን በመጨመር ያልተፈቀደላቸውን […]

የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል አራማጆች፤ ከሌሎች ሰላማዊ ትግል አራማጆች የምንማረው በክፍል አንድ፤ የሰላማዊ ትግሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምን እንደሆነ ገልጫለሁ። በክፍል ሁለት ደግሞ፤ ስለሰላማዊ ትግሉ ያለንን ግንዛቤ አሳይቻለሁ። በዚሁ በሶስተኛው ክፍል ላይ፤ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሰላማዊ ትግል፤ ከሌሎች ከዚህ ቀደም የሰላማዊ ትግል ካካሄያዱ ሀገሮች የምንማረውን ተመክሮ እዘረዝራለሁ። ሰላማዊ ትግሉ፤ ዕለት በዕለት በገዥው ወገንተኛ አምባገነን ገዥ መንግሥት ፊት […]

በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከደላሎች ጋር እንደሚሰራ ብዙዎች በምሬት ይገልጻሉ ‹‹ወተትና ማር ታፈልቃለች››ወደሚሏት ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር በተለይ ከደቡብ ኢትዮጵያ በመነሳት በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በመግባት ረዥሙን ጉዞ ለመያያዝ ራሳቸውን በሚያዘጋጁበት ቅጽበት እየተያዙ ወህኒ የሚወርዱ ወጣቶች ቁጥር በኬንያ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በኬንያ ለመቆየት፣ስራ ለመስራት አልያም የሽብር ተግባር ለመፈጸም የመጡ እንዳልሆኑ ቢታወቁም በአገሪቱ ፖሊሶች […]

ቄራዎች ድርጅት በልኳንዳ ነጋዴዎች ምክንያት አገልግሎቱ መስተጓጎሉን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ጠየቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቄራዎች ድርጅት የዘንድሮው ሰኔ ፆም ሲፈታ አንድ ቀን ሲቀረው በልኳንዳ ነጋዴዎች ምክንያት አገልግሎቱ እንደተስተጓጎለበት አስታወቀ፡፡

ለ2,800 እንስሳት የዕርድ አገልግሎት ለመስጠት አቅዶ እንደነበር፣ ለእርድ አገልግሎት የቀረቡት ግን 900 እንስሳት ብቻ እንደሆኑ፣ ይህም ለሕገወጦች በር መክፈቱንና መንግሥትም ከአገልግሎቱ ማግኘት የሚገባውን ገቢ ማጣቱን  የድርጅቱ ዋና ሥራ አቶ ኤፍሬም ደሳለኝ አስኪያጅ አስታውቀዋል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በቁም እንስሳት ንግድ አዋጅ በከተማው ክልል ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ባዘጋጀው የተግባር ምዕራፍ ላይ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት ሐምሌ 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ ይህ ዓይነቱ ድርጊት ገቢ በማሳጣት ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ኅብረተሰቡ ጤንነቱ ያልተመረመረ ሥጋ በመብላት ለተለያዩ በሽታዎች እንዲጋለጥ ማድረጉ መታወቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ 

ድርጅቱ ዕቅዱን ያላሳካው የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ ችግር ሳቢያ እንስሳቱን ከመግዛት በመቆጠባቸው፣ በዚህም የተነሳ የንግድ ቤቶቻቸውን ዘግተው ለኅብረተሰቡ የሽያጭ አገልግሎት መስጠቱን እርግፍ አድርገው በመተዋቸውና በዚህም ምክንያት የሥጋ እጥረት በማስከተሉ ነው፡፡

 ከዚም በተጨማሪ ቄራዎች ድርጅት ለዕርድ አገልግሎት የ2,000 ብር ዋጋ ጭማሪ እንዳደረገ የተነዛው አሉባልታ፣ ለልኳንዳ ንግድ ቤቶች መዘጋትና ነጋዴዎቹም እንስሳቱን ላለመግዛት ለማንገራገራቸው ተጨማሪ ምክንያት እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቄራዎች ድርጅት ለዕርድ አገልግሎት የሚያስከፍለው በአንድ እንስሳ 230 ብር ብቻ እንደሆነ፣ ይህም የተመረተውን ሥጋ በተሽከርካሪ እስከ ልኳንዷ ቤቶች ድረስ የማጓጓዙንም ሥራ እንደሚያካትት፣ ከዚህ ውጪ ግን ምንም ዓይነት ጭማሪ እንዳላደረገ በመገናኛ ብዙኃን ጭምር ማስታወቃቸውን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

‹‹ድርጅቱ አገልግሎቱን የሚሰጠው የንግድ ፈቃድ ላላቸው ብቻ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተቋቋመው ጤናማነቱ የተረጋገጠ የዕርድ አገልግሎት ለከተማው ነዋሪዎች መስጠት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ለተለያዩ ጉዳዮች ማለትም ሠርግ፣ ተዝካር፣ ወዘተ ላላቸው ወገኖች አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይህ ዓይነቱ አሠራር እንዲቀጥል እናበረታታለን፡፡ ከክፍያ አንፃር ግን ከነጋዴው የተለየ ጭማሪ ሳይደረግ ነው የዕርድ አገልግሎቱን የሚያገኙት፤›› ብለዋል፡፡

በተረፈ ለድርጅቱም ደረሰኝ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው፣ በተለይ እንስሳት ከገበያ ወደ ቄራ በሚጓጓዙበት ጊዜ ሲሞት ካሳ የሚከፈልበት አሠራር እንዳለ፣ በዚህም የተነሳ ደረሰኝ ላይ የሚታወቅ ሁኔታ ካለ በዚያው ልክ እንደሚከፈል፣ ይህ ባለመሆኑ የተነሳ ግን አንዳንድ ጊዜ ከዋጋው በላይ እየተጠየቀ ድርጅቱን ላላስፈላጊ ወጪ እንደተዳረገ አልሸሸጉም፡፡

የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ ከደረሰኝ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ሁኔታ አስመልክተው እንዳብራሩት፣ የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ባለፈው ሳምንት ማዘጋጃ ቤት አካባቢ ስብሰባ አድርገው ልኳንዳ ነጋዴዎች ለገዙት በሬ ደረሰኝ እንደማይፈልጉ፣ ምክንያቱ ደግሞ ያለደረሰኝ መሸጥ ስለሚፈልጉ ነው የሚል መረጃ በተባራሪ ልኳንዳ ነጋዴዎች ጆሮ ይደርሳል፡፡ 

ይህ ጉዳይ ተጋግሎ እየመጣ ረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ደረሰኝ ካላገኙ ከብት እንደማይገዙ በልኳንዳ ነጋዴዎች ዘንድ ጎልቶ ታየ፡፡ በዚህም ብቻ ሳይወሰኑ የማኅበሩ ቢሮ ድረስ እየመጡ ‹የሠራችሁልን ነገር የለም፣ በመብታችን ትደራደራላችሁ፡፡ እንዲያውም ማኅበሩን እናፈርሳለን› የሚል አቋም እንደያዙ ነው ምክትል ሥራ አስኪያጁ የተናገሩት፡፡

በዚህም ምክንያት ልኳንዳ ነጋዴዎች ደረሰኝ ወይም ለሕጋዊነታቸው ማረጋገጫ ካላገኙ እንስሳት መግዛት አንችልም በማለት በራሳቸው መንገድ ንግድ ቤታቸውን እንደዘጉ፣ ማኅበሩም እስከ ፆም ፍቺው ዕለት ድረስ የማረጋጋት ሥራ ቢያከናውንም ሊሳካለት እንዳልቻለ አቶ አየለ ጠቅሰው፣ ‹‹በዚህም ምክንያት የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ለተፈጠረው ችግር የከተማይቱን ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቃል፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ንጉሴ ‹‹በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀ ጉባዔ 5,000 የሚሆኑ እንግዶች እየተስተናገዱ ባሉበት፣ የሰኔ ፆመኞች ፆማቸውን ሲፈቱ የልኳንዳ ንግድ ቤቶችን መዝጋት በማንኛውም ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ሕገወጥ ተግባር ነው፡፡ ምንም ዓይነት ችግር ቢኖርም መዝጋቱ መፍትሔ አይሆንም፡፡ የታወቅንበት መቻቻል፣ ሰላምና ፍቅር ደፍርሶ ሌላ ነገር እንዲከስት ያደርጋል፤›› ብለዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረ ሥላሴ የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማኅበር ስብሰባ ስለማድረጋቸው ለቢሮው የደረሰ ምንም መረጃ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ በተረፈ በቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት ውስጥ በጉልበት የታጀበ ጣልቃ ገብነትንና ሕገወጥነትን እንዲቀር ለማድረግ እንታገላለን፡፡ ለዚህም ዕውን መሆን ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መተጋገዝ ያስፈልጋል ብለን እናምናለን፤›› ብለዋል፡፡ 

 

በዚህ ወር መጨረሻ የአባታቸውን ሀገር ለሁለት ቀናት ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት ባራክ ኦባማ ወደ ኬኒያ ምድር ሲመጡ በግብረ ሰዶማውያን ጉዳይ ላይ አንዳችም ነገር እንዳይናገሩ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስጠነቅቁ ሰንብተዋል። የተለያዩ እምነት መሪዎችና የፓርላማ አባላት ጭምር ደብዳቤዎችን ለዋይት ሀውስ አስገብተዋል። የኬኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው “ይህ የአፍሪካውያን ባህል ካለመሆኑም በላይ ድርጊቱ የሀይማኖታችንን ህግ የሚጥስ ነው።” በማለት ተችተዋል። አንድ የቤተክርስትያን […]