አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ

ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል:: የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ ዓላማዎች እንዳሉትም አስረድተዋል:: በውይይቱ የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች አስር ፈጽሞ ያልተገባ መሆኑን ጠቅሰው: ሲፈቱም ሙሉ ነጻነት እንዳልተሰጣቸው ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰላቸው አስረድተዋል::ከዚሁም ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ኤርትራን ስለመምታት የተናገሩትን ዛቻ በተመለከተ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ኢትዮጵያ የኤርትራን ድንበር ጥሳ እንዳትገባና ብትገባ ግን አሜሪካ እንደምታወግዘው ገልጸዋል::