ፒያሳ አካባቢ ያየነው ትንሽ ለየት ይላል፡፡ መርካቶን አሊያም ከዛም አለፍ ያሉትን የአዲስ አበባ ክፍሎች በቁጥጥር ስራቸው አውለው ወደ አራት ኪሎ እየገሰገሱ የሚመስሉ ፈርጣማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፒያሳ ላይ ገዥ መሬት ይዘዋል፡፡ መኪና አይቀርባቸውም እንጅ መኪና መንገዱን ግማሹን እነሱ እየተንፈላሰሱበት ነው፡፡ ተቆጣጥረውታል! ደግሞ ኮዳና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሳቸውን ግጥም አድርገው ታጥቀዋል፡፡ አንድ ሁለት እርምጃ እንዳለፉ የሚተኩሱ በሚመስል ሁኔታ መሳሪያቸውን ዘቅዝቀው ይዘውታል፡፡ በተጠንቀቅ! በቃ ፒያሳን የጦር ቀጠና አስመስለዋታል፡፡

ከሶስቱ መካከል አንዱ የሁለቱን ደህንነት ለመጠበቅ በሚመስል መልኩ ወደኋላ ይቀራል፡፡ ሰውንም፣ ወርቅ ቤቶቹንም፣ መኪናዎችንም ዘወር ዘወር ብሎ ያያል፡፡ እንደገና ፈጠን ፈጠን ብሎ ይቀላቀላቸውና በአንድ ላይ ወደቀኝና ግራ እያማተሩ መሳሪያቸውን ዘቅዝቀው ይነጉዳሉ፡፡

ሌላ ሶስት አባላት ያሉት ‹‹ጋንታ›› ይከተላል፡፡ እነዚህም በተመሳሳይ ሶማሊያ አሊያም ኤርትራ ድንበር ያሉ ነው የሚመስሉት፡፡ ቀኝና ግራ፣ ወደኋና ወደፊት ይቅበዘበዛሉ፡፡ የቆሙ መኪናዎችን ጠጋ ብለው ያያሉ፡፡ አላፊ አግዳሚው ላይ ያፈጣሉ፡፡ ከእነሱ በኋላ ደግሞ ጯፉ እሳት የተቆሰቀሰበት የሚመስለውን ዱላ ከአጋማሹ ላይ የያዙ አራት ‹‹ተራ አስከባሪዎች›› (ካልሲ አባራሪዎች) ይከተሏቸዋል፡፡ ደጀን ጦር መሆናቸውን ነው፡፡
በዛሬው እለት Getachew Shiferaw አዲስ አበባን እንዲህ ቃኛት::
ማሳሰቢያ፡- አብረውኝ ከነበሩት ሁለት ጓደኞቼ ጋር ፎቶ የማንሳት ፅኑ ፍላጎት የነበረን ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ፎቶ ማንሳት ሳይቻለን ቀርቷል!
Image

በእስራኤል ፓርላማ ሲገቡ የመጀመሪዋ ሴት ትውልደ ኢትዮጵዊት አይሁድ የሆኑት የሽአዲስ ታመኑ ሽታ ዘረኝነትን እንደሚዋጉ ተናገሩ፡፡ ሴትየዋ ባገባደድነው ወር በእስራኤል ተካሂዶ በነበረው የፓርላማ ምርጫ በጥቂት ድምጾች ተሸንፈው ከፓርላማ እንደራሴነት ውጪ ቢሆኑም እንኳን ዘረኝነትን በየትም ቦታ ሆነው ለመዋጋት ነው ቃል የገቡት፡፡ የምሰራው ብዙ ስራ አለኝ ያሉት ወይዘሮዋ “የኔና የወገኖቼ የፊት ገጽ በዘረኝነት ወላፈን በሚገረፍበት ሀገር ውስጥ መኖር […]

The post ኢትዮጵያዊቷ አይሁድ በእስራኤል የሰፈነውን ዘረኝነት እዋጋለሁ አሉ appeared first on ሳተናው .

ኅዳሴ ግድብን የቴክኒክ ጥናት ሂደት እንዲመራ የተሰየመው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ዛሬና ነገን (ረቡዕና ሐሙስ) ለሚዘልቅ ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ተቀምጧል፡፡ ኮሚቴው በዚህ አምስተኛ ስብሰባው ወቅት የቴክኒክ ጥናቱን የሚያካሂድ ዓለምአቀፍ ድርጅት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በስብሰባው ላይ የሦስቱ ሃገሮች የውኃ፣ ኢነርጂና መስኖ ጉዳዮች ሚኒስትሮች፣ ኤክስፐርቶች፣ የዲፕሎማሲ ባለሙያዎችና ሌሎችም እየተሣተፉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የድርጅቱ ምርጫ የሚካሄደው ቀደም ሲል […]

The post ለኅዳሴ ግድብ ዓለምአቀፍ የቴክኒክ አማካሪ ድርጅት ለመምረጥ ሃገሮቹ ስብሰባ ተቀምጠዋል – VOA appeared first on ሳተናው .

 

የኅዳሴ ግድብን የቴክኒክ ጥናት ሂደት እንዲመራ የተሰየመው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የጋራ ኮሚቴ ዛሬና ነገን (ረቡዕና ሐሙስ) ለሚዘልቅ ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ተቀምጧል፡፡

ኮሚቴው በዚህ አምስተኛ ስብሰባው ወቅት የቴክኒክ ጥናቱን የሚያካሂድ ዓለምአቀፍ ድርጅት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በስብሰባው ላይ የሦስቱ ሃገሮች የውኃ፣ ኢነርጂና መስኖ ጉዳዮች ሚኒስትሮች፣ ኤክስፐርቶች፣ የዲፕሎማሲ ባለሙያዎችና ሌሎችም እየተሣተፉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የድርጅቱ ምርጫ የሚካሄደው ቀደም ሲል በመጣ አጭር ዝርዝር ላይ ከቀሩ አራት አማካሪ ኩባንያዎች መካከል መሆኑንና መራጮቹ የሚመለከቱት የቴክኒክና የበጀት ሰነዶችን እንደሚሆን የምሥራቅ ናይል ተፋሰስ ዞን ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ከአቶ…

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከጎንዬሽ ጉዳዬች ውጪ ለ25ተኛ ጊዜ (በአጠቃላይ ለ27ተኛ ጊዜ) የተሰየመው ችሎት ዛሬም የደረጃ ምስክሮችን ሲያሰማ ውሏል፡። ከሳምነትት በፌት የተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ 41 ምስክሮች አሉኝ ነገር ግን ላገኛቸው ስላልቻልኩ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ቆይተው ተጨማሪ ማፈላለጊያ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም ዛሬም “የሽብር ተግባሩ “ ዋና ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍተሻ ላይ ተገኝተናል […]

The post ” ምስክር ፈላጊው ችሎት ” – 27ተኛ የፍርድ ቤት ውሎ -የዞን9 ማስታወሻ appeared first on ሳተናው .

ፍቅር ለይኩን

ጎልጎታ Golgota by Geberekirstos Desta
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሳምንቱ ሰሙነ ሕማማት በሚል ሲጠራ የዛሬዋ ዕለት አርብ ደግሞ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው፣ ሕማሙና ስቅለቱ በፍቅርና በትሕትና የሚታሰብበትና በተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች የሚዘከርበት ታላቅ ዕለት ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቃውንቶች ዘንድ “ደረቅ ሐዲስን ተናጋሪ” ተብሎ የሚጠራው ነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ በትንቢቱ፡-

ሙሉውን አስነብበኝ …

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከጎንዬሽ ጉዳዬች ውጪ ለ25ተኛ ጊዜ (በአጠቃላይ ለ27ተኛ ጊዜ) የተሰየመው ችሎት ዛሬም የደረጃ ምስክሮችን ሲያሰማ ውሏል፡። ከሳምነትት በፌት የተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ 41 ምስክሮች አሉኝ ነገር ግን ላገኛቸው ስላልቻልኩ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ቆይተው ተጨማሪ ማፈላለጊያ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም ዛሬም “የሽብር ተግባሩ “ ዋና ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍተሻ ላይ ተገኝተናል […]

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ “ግድቡን መገንባት ወይም ደግሞ እርግፍ አድርጎ መተው” የሚለው የመለስ ጥያቄ ነበር፡፡ ከዛሬ አራት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2/2011 አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው ቤንሻንጉል ጉሙዝ እየተባለ በሚጠራው “ክልል” ልዩ ስሙ ጉባ በሚባለው ቦታ በመገኘት በዚያን ወቅት የሚሊኒየሙ ግድብ/Millennium Dam እያለ ይጠራው የነበረውን እና እንደገና በኋላ ደግሞ በደቀ መዛሙርቶቹ አማካይነት […]

The post የመለስ ግድብ ሕዳሴ ከንቱ ዉዳሴ? – ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም appeared first on ሳተናው .

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሰው ለምን በአይሮፕላን መብረርን ይፈራል? በእንግሊዝኛ «አቪፎቢያ» ወይም «ኤይሮፎቢያ» የሚባለው ለምን ያድርበታል? ከሚነቀሳቀስበት የብስ ራቅ ባለና አንዳች ሊቆጣጠረው ፣ ሊይዘው- ሊጨብጠው በማይችልበት ሁኔታ ስለሚገኝ? ሰው በሠራው የሥነ ቴክኒክ

(በቴክኖሎጅስት ዳንኤል አማረ)
ምግብ ከተመገቡ በኃላ በፍጽም ሊያደርጓቸው የማይገቡ ተግባሮች

1. ትኩስ ሻይ መውሰድ

ሻይ የበላነውን ምግብ እንዳይዋሀድ ያደርጋል። ሻይ በውስጡ ያለው ቁስ ነገር ብረት(iron) የተሰኝውን ንጥረ ነገር ከሰውነታችን ውስጥ በማስወገድ ለብረት እጥረት እና ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል። በተጨማሪም ሻይ (Tannin) የ

በምዕራብ አፍሪቃ ባለፈው ዓመት የተከሰተውን የኤቦላ ወረርሽኝ ለመታገል ዓ/አቀፉ ማህበረሰብ የወሰደው ርምጃ ንዑስና አዝጋሚ ነበር ሲሉ የርዳታ ድርጅቶች ወቀሳ ሰንዝረዋል። ተላላፊ በሽታ በሚከሰትበት ጊዜ ተመሳሳይ ዝግመት እንዳይታይም፣ የጀርመን መንግሥት አስቸኳይ የህክምና ርዳታ የሚሰጥ ሁሌ ዝግጁ የሚሆን የጦር ግብረ ኃይል ለማቋቋም አቅዷል።

ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም በነዚህ እጩዎች ላይ የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ከእጩነት ቢያገላቸውም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ እንዲወዳደሩ እንደተበየነለት ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል ።

የማምነው ነገር፣ የሀገሪቷ ችግር ሲፈታ፤ እስክንድርም አብሮ እንደሚፈታ ነው”

የስደት ህይወት ሁሉንም ነገር ከዜሮ ያስጀምርሃል

የእስክንድር ፅናት እና ብርታት ከፈጣሪ የተሰጠው ፀጋ አድርጌ እመለከተዋለሁ

በሀገራችን ጉዳይ ላይ ለመሳተፍ የግድ ፖለቲከኛ መሆን አይጠበቅብንም” ሰርካለም ፋሲል (ጋዜጠኛ)

Eskinder Nega, Serkalem Fasil and Nafkot Eskinder
በአንባቢያን ዘንድ ታዋቂ የነበሩት “አስኳል”፣ “ሚኒሊክ”ና “ሳተናው” ጋዜጦች አንዷ አሳታሚ ነበረች። የ97 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር ለእስር ከተዳረጉት ጋዜጠኞች እና አሳታሚዎች መካከልም አንዷ ነች – ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል። በሀገራችን የግል ፕሬስን በመጀመር ፈር ቀዳጅ የሆነው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ሰርካለም ልጃቸው ናፍቆትን የወለደችው በቃሊቲ እስር ቤት መሆኑ ይታወቃል። 

ሙሉውን አስነብበኝ …

‹‹የማምነው ነገር፣ የሀገሪቷ ችግር ሲፈታ፤ እስክንድርም አብሮ እንደሚፈታ ነው›

‹‹የስደት ህይወት ሁሉንም ነገር ከዜሮ ያስጀምርሃል››

‹‹የእስክንድር ፅናት እና ብርታት ከፈጣሪ የተሰጠው ፀጋ አድርጌ እመለከተዋለሁ››

‹‹በሀገራችን ጉዳይ ላይ ለመሳተፍ የግድ ፖለቲከኛ መሆን አይጠበቅብንም››
ሰርካለም ፋሲል (ጋዜጠኛ)
—————–
በአንባቢያን ዘንድ ታዋቂ የነበሩት ‹‹አስኳል››፣ ‹‹ሚኒሊክ‹‹ና ‹‹ሳተናው›› ጋዜጦች አንዷ አሳታሚ ነበረች፡፡ የ97 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር ለእስር ከተዳረጉት ጋዜጠኞች እና አሳታሚዎች መካከልም አንዷ ነች – ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል፡፡ በሀገራችን የግል ፕሬስን በመጀመር ፈር ቀዳጅ የሆነው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ሰርካለም ልጃቸው ናፍቆትን የወለደችው በቃሊቲ እስር ቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡ index.jpg
ከእስር ከተለቀቁም በኋላ እስክንድር የጋዜጣ ፍቃድ ቢከለከልም ሀገሬን ጥዬ አልመሄድም በሚል አቋሙ በመጽናቱ ጽሑፎቹን በተለያዩ በውጭ ሀገር ባሉ ድረ-ገጾች ላይ ማቅረብ ቀጠለ፡፡ በሀገር ውስጥ የግል ጋዜጦች ላይም ቃለ-ምልልስ በማድረግ የግል ሀሳቡን በድፍረት በማቅረብ ላይ ሳለ ነበር በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥሮ መስከረም 03 ቀን 2004 ዓ.ም ለእስር የተዳረገው፡፡ በፍርድ ሂደትም 18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ባለቤቱ ሰርካለም ከጎኑ ነበረች፡፡
ሰርካለም በአሁኑ ወቅት በስደት አሜሪካ ሀገር ትገኛለች፡፡ የዚህ ሳምንት የ‹‹ፍቱን›› እንግዳ የሆነችው እ.አ.አ በ2007 ዓ.ም ከዓለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን “Courage in Journalism Award” የሚል ሽልማት ካገኘች በኋላ የሽልማት ገንዘቡን ለአምነስቲ ኢንተርሽናል ተቋም ድጋፍ እንዲውል ያደረገችው ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ነች፡፡ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የተወሰኑ ጥያቄዎችን (ስደትን፣ እስክንድርን፣ ልጃቸው ናፍቆትን በተመለከተ) በማንሳት እንዲህ አነጋግሯታል፡፡

በቅድሚያ ለቃለ-መልልሱ ፈቃደኛ በመሆንሽ በ‹‹ፍቱን›› መጽሔት ስም እናመሰግናለን፡፡
——

እኔም ለቃለ-ምልልሱ ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ በአንባቢዎቻችሁ እና በራሴ ሥም አመሰግናለሁ።

ሰርካለም፣ ከሀገር ከወጣሽ ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ? ለምን እንደወጣሽም በአጭሩ ንገሪን?
—————

ከሀገር ከወጣሁ አንድ ዓመት ከስድስት ወር አካባቢ ሆኖኛል። ከሀገር የወጣሁትም በግሌ ወስኜ ሳይሆን፣ ከእስክንድር ጋር ለረጅም ጊዜ ተነጋግረንበት፣ በጋራ በደረስነው ውሳኔ መሰረት ከሀገር ልወጣ ችያለሁ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ፣ ማንም እንደሚያውቀው ልጃችን ናፍቆት የተወለደው እኔ እስር ውስጥ ሆኜ ነው። በ1998 ዓ.ም የአንድ ወር ተኩል ነብሰ ጡር ሆኜ ነበር የታሰርኩት። የወለድኩትን ልጅ ማቀፍም ሆነ ማጥባት ሳልችል ነው ከልጄ ጋር የተለያየሁት። ከእስር ስንፈታ፣ ልጃችን አንድ ዓመት ሊሆነው የአንድ ወር ዕድሜ ሲቀረው ነበር ዳግም የተገናኘነው። በአጠቃላይ የልጃችን ታሪክ ከእስር እና ከመከራ ጋር የተያያዘ ነው። በአሁኑ ሰዓት ካለአንዳች ወንጀል፣ በሀሰት ክስ እስክንድር በግፍ 18 ዓመት ተፈርዶበት ቃሊቲ ይገኛል። ትላንት ቃሊቲ የተወለደው ናፍቆት ዛሬ ነብስ አውቆ፣ የልጅነት መቦረቂያ ጊዜውን አባቱ ጋር እየተመላለሰ ማሳለፍ ዕጣ ፈንታው ሆኖ ነበር። እስክንድርም ከእስሩ በላይ የልጁ መንከራተትና ስቃይ በየዕለቱ እረፍት እንደነሳው በተደጋጋሚ ይገልጽልኝ ነበር። ከዚህም ባሻገር ‹‹ይህ ህፃን ጥላቻ ይዞ ማደግ የለበትም፣ ቂም ይዞ ማደግ የለበትም›› በሚል መነሻ ናፍቆትን ይዤ ከሀገር ለመውጣት ተገድጃለሁ።

የስደት ሕይወትን እንዴት አገኘሽው?
————–

የስደትን ህይወት እንዲህ በቀላሉ መግለጽ እቸገራለሁ። የስደት ህይወት ሁሉንም ነገር ከዜሮ ያስጀምርሃል። የእውነት ሀገርህ የሚናፍቅህ፣ የእውነት መንደርህ የሚናፍቀው በስደት ዓለም ውስጥ ነው፤ በተለይ እንደእኔ በማኅበራዊ ህይወት ትስስር ቁርኝት ላደገ ሰው።
አሜሪካ በርህን ዘግተህ ጎረቤት አታውቅ፣ ጎረቤትህ አያውቅህ፣ መንገድ ላይ ረጅም መንገድ ብቻህን ብትሄድ አንድም ሰው ላታይ በምትችልበት ሀገር፣ ራስን ከዚያ ጋር ማላመዱ ትንሽ ያስቸግራል። ሀገርህ ላይ ያለው ማኅበራዊ ህይወት ቢናፍቅህም፣ በሌላ ጎኑ ያለው ነፃነት ደግሞ እጅግ ያሥገርማል። የሰውን መብት እስካልነካህ፣ ያሻህን ብትሆን ቀና ብሎ የሚመለከትህ እና የሚያስፈራራህ አንዳችም ሀይል የለም። ‹‹ስጋት ውስጥ ይጥለኛል›› ብለህ የምትጠነቀቀው ወይም የምታስበው አይኖርም። አሜሪካ የሁሉም ነች፡፡ ሁሉም እኩል ይስተናገድበታል። ሁሉም እኩል መብት አለው። …ይህ ግን የሥደትን ህይወት ጣፋጭ አያደርገውም። …ከነምናምኗ ሀገርን የመሰለ ምንም ነገር የለም።

ባለቤትሽ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት ወንጀል 18 ዓመት ተፈርዶበት በቃሊቲ እስር ቤት ይገኛል፡፡ አንቺም ከማዕከላዊ እስከ ቃሊቲ በነበረው እስሩ በጥየቃ አብረሽው ነበርሽ፡፡ አሁን ከልጃችሁ ናፍቆት ጋር በአሜሪካ ቨርጂኒያ ትገኛላችሁ፡፡ ባለቤትን ከጎን አጥቶ ሕይወትን መኖር እና ልጅን ለብቻ ማሳደግ እጅግ ከባድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እስኪ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለሽን ስሜት አጋሪን?
—————————-

እስክንድር “አሸባሪ” የሚል የሀሰት ታርጋ ተለጥፎበት ከታሰረ አራት ዓመት ሊሞላው ትንሽ ወራቶች ይቀሩታል። እስክንድር ሀገሩን እና ወገኑን የሚወድ ኢትዮጵያዊ እንጂ፣ ተሸባሪዎቹ እንደሚገልጹት “አሸባሪ” ወይም ህዝብና ሀገርን የሚጎዳ አንዳችም ነገር አድርጎ እንደማያውቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ እነጆን ኬሪ በአደባባይ የመሰከሩለት ሀቅ ነው። የኢህአዴግ መንግሥት በግፍ፣ ማዕከላዊ ውስጥ (ለጊዜው ስማቸው ይቆየን) በሃላፊዎች ደረጃ ንፅህናው እየተነገረው ግን ‹‹ከአቅማችን በላይ ነው››፣ ‹‹ይታሰር ተብሏል፣ ትዕዛዝ ነው›› እየተባለ የታሰረ የግፍ እሥረኛ ነው። እስክንድር ላመነበት ነገር የሚያስከፍለውን ሁሉ ለመቀበል የተዘጋጀ ጠንካራ ሰው በመሆኑ፣ እኔም ለብቻዬ ልጃችንን ለማሳደግ በብዙ ማይልሶች ርቀት ላይ ብገኝም፣ ከሁለታችንም በኩል ጥንካሬ ብቻ እንደሚጠበቅብን አምናለሁ። በተለይ የእኛ ጥንካሬ፣ ለእስክንድር ሞራል እንደሚሆነው ስለማውቅ ልጅን ለብቻ ማሳደጉንም ሆነ ተለያይቶ በመኖሩ ጊዜያዊ አድርጌ ነው የምቆጥረው። ደግሞም እግዚያብሄር ይችላል!

በስደት ዓለም ሆናችሁ፣ ሰዎች ስለእስክንድር እና ስለእናንተ ያላቸው ያላቸው ቦታ …
————————-
….ከእኔ ልጀምር፣ ‹‹በእጅ የያዙት ወርቅ እንደመዳብ ነው›› ይላል የሀገሬ ሰው። እስክንድር በውጪ ዓለም በዚህ ደረጃ አድናቂ እና ተከታይ እንዳለው በጭራሽ አላውቅም። በተጓዝንበት ሥፍራ ሁሉ፣ ለእስክንድር ያላቸውን ክብር የሚገልጹ ሥደተኛ ወገኖቼ፣ ለእኔ እና ለናፍቆት የተለየ እንክብካቤና ፍቅር እያደረጉልን ይገኛሉ። ሁልጊዜ አዲስ ነው የምንሆንባቸው።

እስክንድር በእስር ላይም ሆኖ፣ መንፈሰ ጠንካራነቱ ወደር አይገኝለትም፡፡ ጠያቂ ሊያበረታታው ሄዶ ጠያቂውን አበረታቶ የሚመልስ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ስለእስክንድር የዓላማ ጽናት፣ ውስጣዊ ጥንካሬና ብርታት እሱን ለምታውቂው አንጻር ይህ ብትታቱ እነና ጽናቱ ከምን የመነጨ ነው?
———————-
የእስክንድር ፅናትና ብርታት ከምን የመነጨ እንደሆነ ለመግለፅ፣ ለመናገር ከቃላት በላይ ነው። በአጭሩ ማለት የምችለው፣ ከላይ (ከፈጣሪ) የተሰጠው ፀጋ አድርጌ ነው የምመለከተው። ምክንያቱም የሰው ልጅ የሆነ ቦታ ላይ ሲደክመው ወይም ተስፋ ሊቆርጥ ይችላል። እስክንድር ግን ብዙ መከራና ግፍ፣ እንግልት፣ በየጊዜው ቢደርስበትም፣ ለአንዲትም ቀን ‹‹አሁንስ ደከመኝ›› የሚል ነገር አስቦ አያውቅም። አካላዊ ስጋው ቢጎዳም መንፈሱ ግን ሁልጊዜ አዲስ፣ ሁልጊዜ ጠንካራ፣ ከራሱ አልፎ ሌላውን የሚያበረታታ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ነው። የእሱ መከራ መቀበል ከቆመለት ዓላማ ትንሽም እንደማያነቃንቀው በተግባር ያሳየ የዘመኑ ጀግና ነው። ሞራሉን ለመግደል በሀሰት ተወንጅሎ 18 ዓመት ቢፈረድበትም፣ ‹‹ለዴሞክራሲ መከፈል ያለበት ዋጋ ነው›› ብሎ ውስጡ ፀፀት እንደሌለበት አውቃለሁ። ውስጡ ትልቅ ሰላም እንዳለውም አውቃለሁ። ላመነበት ነገር የሚከፍለው ዋጋ ጥንካሬ እንጂ፣ ቁጭትን እንደማይፈጥርበት አውቃለሁ። ከምንም በላይ በሀሰት የተፈረደበት በመሆኑ፣ ለአሳሪዎቹን እንጂ የእሱ ጭንቅላት ነጻ በመሆኑ የጥንካሬው ምንጭም ሊሆን ይችላል – የሚፀፀትበትን ነገር ባለመፈፀሙ።

በባለሽበት ስቴት፣ በቅርብሽ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከልጇ ሃሌይ ጋር አሉ፡፡ በ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው ችግር፣ ከሁለቱም ጋር በቃሊቲ አብራችሁ ታስራችሁ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በስደት ዓለም አብራችሁ ትገኛላችሁ፡፡ አጋጣሚውን እንዴት ታይዋለሽ?
——————————-

እንዳጋጣሚ ሆኖ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ንግሥት ገብረህይወት (የቅንጅት ማዕከላዊ ኮሚቴ) …አሁን ደግሞ የቀድሞው የመንግሥት ጉዳዮች ኮሙኑኬሽን ሚኒስትር ደኤታ የነበሩት አቶ ኤርምያስ ለገሰ በአንድ አካባቢ እንገኛለን። ይህ ደግሞ፣ ቅርበታችንን ከጓደኝነት አልፎ ቤተሰብ እስከመሆን አድርሶናል። አንዳችን ሌላኛችን ቤት ለመድረስ ከአምስት ደቂቃ በላይ አይጠበቅብንም። በስደት ሀገር እንደዚህ ከምታውቀው እና ከምትግባባው ሰው ጋር አንድ አካባቢ መኖር፣ ውስጥህ ያለውን ብቸኝነት በትልቁ የሚቀርፍ ነው። በአጋጣሚ በአንድ አካባቢ መገኘታችን ለእኔ ትልቅ ደስታ ሰጥቶኛል።

በማኅበራዊ ድረ-ገጽ ላይ በንቁ በመሳተፍ እመለከትሻለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ መረር ያሉ የቁጭት፣ የሀዘንና ልብን የሚነኩ ጽሑፎችን ትጽፊያለሽ፡፡ የጠቀስኳቸውን ስሜቶች ምን ፈጠራቸው?
————————-

በማኅበራዊ ድረ-ገፅ ላይ የሚጠበቅብኝን ወይም በምፈልገው መጠን እየተንቀሳቀስኩ እንዳልሆነ ይታወቀኛል። የዚህም ምክንያቱ፣ ልጄን በብቸኝነት ለማሳደግ የምሮጠው የህይወት ሩጫ በመጠኑም ቢሆን ገድቦኛል። ልጅ ትምህርት ቤት ማመላለስ፣ የልጄን ትምህርት በአግባቡ መከታተል እንዲሁም ለመኖር የሚያስችለንን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መከወን በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ይህ ማለት ግን፣ ተሳትፎዬ ይቀንስ እንጂ፣ የሀገሬን ማንኛውንም ነገር ከመከታተል ወደ ኋላ ብዬ አላውቅም። ለተጠየኩት ጥያቄ መልሴ ግን፣ ባለችኝ ጊዜ የምፅፋት ነገር ምሬት እንደሚበዛባት አውቃለሁ። የዚህ ምሬት ምክንያት ደግሞ፣ ከሀገሬ መራቄ አንዱ ምክንያት ነው። ከሀገርህ ርቀህ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ማድመጥ በጣም ያማል። ምናልባትም ከመላመድ ብዛት፣ ውስጡ ሆነህ (ሀገርህ ላይ) እምብዛም አይታወቅም፡፡ ራቅ ስትል ግን፣ ‹‹እንደዚህ ለምን ይሆናል?››፣ ‹‹..እስከመቼ?›› የሚለው ነገርን ነገር በተደጋጋሚ እንድታስበው ያደርግሃል። በትንሹም ቢሆን የእኔም መረር ያለ ፅሁፍ ከዚህ የመነጨ ነው ብዬ አስባለሁ።

በአሜሪካ ሆነሽ፣ እስክንድርን በተመለከተ ምን እያደረግሽ ነው?
————————–

ባለሁበት ሀገር፣ እስክንድርን በተመለከተ፣ ከተለያዩ አካላት ጋር እገናኛለሁ። ስቴት ዲፓርትመንት ከጎንግረስ ማኖች (Congress man)፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ስለእስክንድር የማያውቁት ነገር ባይኖርም፣ በተጨማሪ እኔም ስለሚገኝበት ሁኔታ እና በእስር ቤት ውስጥ ስለሚደርስበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሳውቃቸዋለሁ። የሚገርመው ነገር በየሄድኩበት ትላልቅ ተቋማት በእስክንድር ጉዳይ ላይ ከበቂ በላይ መረጃ ያላቸው መሆኑን ነው። ‹‹እስክንድር አሸባሪ ነው›› የሚለውን የሀሰት ፍረጃ ጠንቅቀው እንደሚያውቁ በተደጋጋሚ በአንደበታቸው ሲገልፁ ይሰማል። ከኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በተጨማሪ፣ በትልቅ የኃላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ ባለሥልጣኖች ለእስክንድር ያላቸውን ክብር መስማት የተለመደ ነው። …ገፍተው ሌላ ነገር ማድረግ ባይችሉም እስክንድርን የሚመለከቱት በተለየ መነፅር ነው። ለጊዜው በዚህ እንቅስቃሴ ላይ እገኛለሁ። ወደፊት ግን እስክንድርን በተመለከተ ለመስራት የታሰበ ሰፊ ሥራ አለ። ጊዜው ሲደርስ የምገልጸው ይሆናል።

በግልሽ እስክንድር ከእስር ወጥቶ በቅርቡ እንገናኛለን የሚል እምነት አለሽ?
—————————
እስክንድር የጊዜ ጉዳይ እንጂ ከእስር እንደሚፈታ ጥርጣሬ የለኝም። መቼ? ለሚለው ግን እስክንድር ከዚህ በፊት እንደገለጸው ጊዜው ሊያጥርም ሊረዝምም ይችላል። ነገ ይፈታል፣ ከነገወዲያ ይፈታል ብዬ የቀን ስሌት አላስቀመጥኩም። አንድ የማምነው ነገር፣ የሀገሪቷ ችግር ሲፈታ፣ እስክንድርም አብሮ እንደሚፈታ ነው። እስከዚያው ከጨለማው ስር የሚወጣውን ብርሃን እጠብቃለሁ።

በሀገር ጉዳይ ላይ፣ ከሴት እህቶቻችን ምን ይጠበቃል?
———————-

በሀገሬ ጉዳይ ላይ ከሴት እህቶቻችን ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሀገር ወዳድ ወገኖቻችን ንቁ ተሳትፎ በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ማድረግ አለባቸው እላለሁ። በሀገራችን ጉዳይ ላይ ለመሳተፍ የግድ ፖለቲከኛ መሆን አይጠበቅብንም። ከዚህ ባለፈ ሩቅ ሆኜ፣ እንዲህ ቢደረግ፣ እንዲያ ቢደረግ የሚል ነገር ለማስተላለፍ የሞራል ብቃቱ የለኝም። ‹‹እንዲህ አድርጉ›› ለማለት ከህዝብ ጋር ሆነህ በሀገር ላይ ተቀምጠህ እንጂ፣ በርቀት ሆኜ የምናገረው አንዳችም ነገር የለም።

በሀገር ውስጥ ለሚገኙ (ለሚያውቁሽና ለማያውቁሽ) ወገኖችሽ ያለሽ መልዕክት …
———————-
በመጨረሻ… ለሚያውቁኝ ወገኖቼ የማስተላልፈው መልዕክት፣ እስክንድር ከታሰረ ጀምሮ በሞራልም በገንዘብም ከጎናችን ላልተለያችሁን ወገኖቼ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ የሚል ነው፡፡

አቡበከር አህመድ እንደዘገበው:- መንግስት በሴኩላሪዝም ስም ህብረተሰቡን በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከእምነቱ ለማስወጣት የሚያደርጋቸውን ጥረቶች አጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን የዚህ እቅድ አንደ አካል የሆነውን ድርጊቱን ማንኛዉም አይነት የእምነት አዲስ ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳይገነቡ በሚል መመሪያ ማዉጣቱን ምንጮች አስታዉቀዋል። በየትኛዉ እምነት አማኞች ፈጣሪያቸውን በአንድነት የሚያመልኩበት ቦታና የእምነቶቻቸውን ጥሪ የሚያደርጉበት ቦታ የእምነት የእምነት ተቋማቸዉ ሆኖ እያለ ከተማዋ […]

The post በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ appeared first on ሳተናው .

በሕወሓት መሪነት የሚዘወረው የደህንነት ተቋሙ በኢሕአዴግ ውስጥ የዘለቀውን የመበስበስ አደጋ ተከትሎ በስልጣናችን ላይ ችግር ይፈጥራሉ ለድርጅቱ ሳይሆን ለሕዝብ እያደሉ ነው::ከተቃዋሚ ሃይላት መረጃ አምጡ ሲባሉ የሚዘናጉ እና አላስፈላጊ መረጃ ይሰጣሉ::ከአውሮፓ ዲፕሎማቶች ጋር ለምን አላማ እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ ግንኙነት ፈጥረዋል ወዘተ ያላቸውን አስራ ስምንት አባላቱን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ከደህንነት ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል:: በሙስና እና የዘረፋ ቡድን […]

The post በደህንነት ቢሮ ውስጥ የተጀመረው ማጥራት ቀጥሏል::18 አባላቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል:: appeared first on ሳተናው .

የዘንድሮ ምርጫ ኣሸንፎ ለመውጣት የህወሓት መንግስት ኣርባው ሲያስወጣ “…ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ ፈጥሬ ድጋፍ ኣገኛለው…” ብሎ ኣስቦ ነበር። ይሁን እንጂ ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ በመውለድ ያሁሉ ጥረቱ መና ሁኖ መቅረቱ ህወሓት ተረድተዋል። ድሮም በወከባ የሚገኝ ህዝባዊ ድጋፍ እንደሌለ የሚታወቅ ነው። ህወሓት ጥረቱ ከንቱ ሲቀር የዘየደው መላ በትግራይና የሚያዋስኑት የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ኤርትራ የጦርነት ድባብ በመፍጠር የምርጫው ኣቅጣጫ […]

ተጻፈ በ  ደረጀ ጠገናው የእግር ኳስ ቤተሰቡ እምብዛም በዝርዝር እንደማያውቀው የሚነገርለት የቴክኒክ ኮሚቴና ቴክኒክ ዲፓርትመንት ሚናና አደረጃጀት ለአገሪቱ እግር ኳስ ቁልፍ ከሚባሉት ኃይሎች አንዱና ዋናው ነው፡፡ ይህ የሙያ ዘርፍ አሠልጣኞችንና ተጫዋቾችን ከመገምገምና የቡድን ግንባታው ላይ እሴት ከመጨመር ጀምሮ በትልልቅ ውሳኔዎች ላይ ተሳታፊና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አመንጪ ሊሆን እንደሚገባውም ይታመናል፡፡ ይሁንና በፌዴሬሽኑ ይህንን ሥልጣንና ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም […]

The post እግር ኳስ ፌዴሬሽን ‹‹በጭቃ›› የተሸፈነውን እሾህ ቢያጠራ? appeared first on ሳተናው .

ከሁለት ዓመታት በኋላ ከቆዩበት የሕግ ከለላ በማግኘት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ (ዱባይ) በቅርቡ የተመለሱት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ በቅርቡ የአክሰስ ሪል ስቴት አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መመረጣቸው ታወቀ፡፡ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ባደረገው ድርድር ከ2,000 በላይ ከሚሆኑ ከአክሰስ ሪል ስቴት ቤት ገዢዎች ጋር በተደረሰ ስምምነት ከየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በሪል ስቴቱ ውስጥ ሥራ የጀመሩት አቶ […]

The post አክሰስ ሪል ስቴት አቶ ኤርሚያስ አመልጋን የቦርድ ሰብሳቢ አድርጐ ሰየመ appeared first on ሳተናው .

ተጻፈ በ  ታምሩ ጽጌ -ከ30 ሺሕ በላይ ዜጐችን በሕገወጥ መንገድ ማዘዋወራቸው ተጠቁሟል በኬንያ በማድረግ በታንዛኒያ በማቆራረጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሕገወጥ መንገድ በኮንቴይነር ውስጥ አሽገው ሲያስተላልፉ፣ ታንዛኒያ ውስጥ እንዳሉ ሕይወታቸው ላለፉት 47 ኢትዮጵያውያን ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያዊያት ፍርድ ቤት ቀርበው፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠየቀባቸው፡፡ አስካለ ዴዴሳ ዴዴቦ በቅጽል ስሟ ‹‹ቤቲ›› እና ሰሚራ ሐሰን ዓሊ የተባሉት […]

The post በታንዛኒያ በ47 ኢትዮጵያውያን ግድያ የተጠረጠሩ ፍርድ ቤት ቀረቡ appeared first on ሳተናው .

ከኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ነባር አመራሮች አንዱ የነበሩት አቶ መስፍን መንግሥቱ ተንሸራተው በመውደቃቸው ሳቢያ ሕይወታቸው በማለፉ፣ መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተፈጸመ፡፡ አቶ መስፍን በተለያዩ ርዕስ ጉዳዮች ላይ ሪፖርተርን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች ሐሳባቸውን በማካፈል የሚታወቁ ፖለቲከኛ የነበሩ ሲሆን፣ ከ1995 ዓ.ም. ጀምሮ የኢዴፓ አባል በመሆን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሠርተዋል፡፡ ለአምስት ዓመታት ያህል የኢዴፓ […]

The post የኢዴፓ ነባር አመራር የነበሩት አቶ መስፍን መንግሥቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ appeared first on ሳተናው .

ከኢትዮጵያ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ የዘለቀ ወዳጅነት የነበራቸው ዕውቁ አሜሪካዊው የፖለቲካ ሶስዮሎጂስት ፕሮፌሰር ዶናልድ ናታን ሌቪን፣ መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. አረፉ፡፡ ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ስለኢትዮጵያ በጻፏቸው “Greater Ethiopia” (‹ታላቋ ኢትዮጵያ› በሚል ርዕስ አቶ ሚሊዮን ነቅንቅ ወደ አማርኛ መልሰውታል)፣ “Wax and Gold” እና “Interpreting Ethiopia” በተሰኙ መጽሐፎቻቸው የሚታወቁ ሲሆን፣ ለአምስት አሥር ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ ትኩረት […]

The post የኢትዮጵያ ወዳጅ የነበሩት ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን አረፉ appeared first on ሳተናው .

ሆያሆዬ ሳይደርስ ሆያሆዬ .. ዉሮሸባዬ ሳይከፈት እስክስታ..ካለጊዜ ያውራዶሮ ገደል ማሚቱ ከመሆን አንድም ይሰውረን አንድም ያድነን::ምርቃት የማይደርስበት እርግማን እንደክፋት ላይገን ያደባበት የጊዜ ጀግንነት ለመደረብ የምንራወጥበትን ሰከን ብለን በሰውነት ጀግንነት የምንለካ ያድርገን::ጊዜን በአግባቡ እንደ ወርቅ ለመድመቅ ልንጠቀምበት የሚገባዉን ከአንዱ ይህ እይታውን ያደላዋል::የሚገባው በሚገባው ዘመን ላይ የማይገባው በሚያላዝንበት መደድ ላይ መሆናችንን መዘንጋት የለብንም:: በማንኛውም ደረጃ ላይ ቢሆን በትክክል […]

Semayawi Party in Stockholm, Sweden. በስዊድን የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር ራሱን አስተዋወቀEthiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. April 7, 2015)፡- ቅዳሜ አፕሪል 4 ቀን 2015 ዓ.ም. (ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.) የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ማኅበር በስዊድን ተመስርቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በመግለጽ፤ የድጋፍ ማኅበሩ ራሱን አስተዋውቋል። በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ዓላማና ተግባርን ጥሪ ለተደረገላቸው ተሰብሳቢዎች ያስረዱት አቶ ሰለሞን ጌታነህ የድጋፍ ማኅበሩ ሰብሳቢ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(በቴክኖሎጂስት ዳንኤል አማረ)

ማር ስኳር እስከተገኝበት 16ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ተፈጥሯዊ ማጣፈጫ በመሆን ያገለግል ነበር የአሰራር ሂደቱ በጣም አስደናቂ ከመሆኑም ባሻገር በብዙ ሰዎች ተወዳጅና ተመራጭ የምግብ ዓይነት ነው። በፍሩክቶስ(fructose) ይዘቱ በጣም የበለፀገ ስለሆነ ብዙ የህክምና ጥቅሞች አሉት እነሱም እንደሚከተለው ይቀርባሉ።

1. የካንሰርና የልብ ህመም ይከላከላል
የተፈጥሮ ማር ፍላቮንድና አንቲ ኦክሲዳንት(antioxidant) በውስጡ ይዟል እነዚህ ነገሮች በካንሰርና የልብ ህመም የመጠቃት እድልን ይቀንሳሉ።…

  በቨርጂኒያ ሀገረ ግዛት ፣ በሬገን ብሄራዊ የአየር ማረፊያ ተርሚናል ውስጥ አብርሀም ዘመድአገኘሁ የተባለ፣ መስማት የተሳነው እና የጎዳና ተዳደሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ምንም በማያውቀው እና ባልፈፀመው ወንጀል አይፓድ ሰርቀሀል በሚል በፖሊስ ተይዞ ለስድስ ሳምንታት በወይህኒ ቤት አሳልፏል። አሰግድ ታመነ  

The post መስማት የተሳነው ኢትዮጵያዊ በቨርጂኒያ ፖሊስ ታሰረ appeared first on ሳተናው .

የሰውነት ቃጠሎን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን?

(በቴክኖሎጂስት ዳንኤል አማረ)

አነስተኛ የሰውነት ቃጠሎዎችን በቀላሉ በቤት ውስጥ በፍጥነት የመጀመሪያ እርዳታ ህክምና መስጠት ሲቻል ከበድ ያሉ ቃጠሎዎች ሲሆኑ ግን ወደ ህክምና መስጫ ተቋሞች መሄድ ተገቢ ነው።
በሙቅ ውሀ ወይም ዘይት ቃጠሎ ሲደርስብን ቤታችን ውስጥ በሚገኙ ነገሮች እንዴት የመጀመሪያ ህክምና እንደምንሰጥ በዝርዝር እንመልከት

1. ማር
ማር በፀረ-ባክቴሪያ ባህሪውና ቁስል በፍጥነት እንዲያገግም በማድረግ ወደር አይገኝለትም። ይህም…

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊ/መንበር አቶ በቀለ  እንደተናገሩት በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ድርጅታቸው በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች እጩዎችን ቢያሰማራም፣ እጩዎቹ እየታሰሩና እየተደበደቡ በመሆናቸው መድረክ ቀጣዩን ሂደት ለመወሰን እየተነጋገረ ነው። አቶ በቀለ በሆድሩ ጉድሮ አባሎቻቸው ቅስቀሳ እንዳያደርጉ መከልከላቸውን፣ በሜታ ሮቢ  ከ50 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸውን፣ በግንደበረት የወረዳው አስተዳደር ሽጉጥ …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት _IOM ባወጣው ዘገባ ህይወታቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 131 ኢትዮጵያውያንን ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መልሷቸዋል። ከተመላሾቹ መካከል 100 ያህሉ ኢትዮጵያውያ ወደ የመን ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ድርጅቱ አስታውቋል። 28 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከየመን ወደ ጅቡቲ በባህር ላይ ጉዞ አድርገው የደረሱ ናቸው። በሰላም ወደ አገራቸው ከተመሰሉት መካከል …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በአለፋ ጣቁሳ ወረዳ በሻውራ ከተማ የከተማዋ ነዋሪዎች ካለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ ውሃ በማጣታቸው መቸገራቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 20 ብር ለመግዛት ተገደናል የሚሉት ነዋሪዎች ምክንያቱም ሙስና ነው ይላሉ። የወረዳው መስተዳደር 300 ሺ ብር የተገዛውን ጄኔረተር 800 ሺ ብር እንደተገዛ አድርጎ ማቅረቡን የሚናገሩት …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሱዳን ትሪቢውን የግንባሩን ሊቀመንበር ተዋት ፖል ቻይን ጠቅሶ እንደዘገበው ፣ የደቡብ ሱዳን አማጽያን፣ የሳልቫኪር መንግስት ለኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ግንባር ወታደራዊ ስልጠና፣ የገንዘብ እንዲሁም የሎጅስቲክ ድጋፍ ያገኛል በሚል ያቀረበው ወቀሳ ተቀባይነት የሌለው ነው። አማጽያኑ የፖል ቻይ ጦር ወደ ጋምቤላ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም አስቧል በማለት ክስ አሰምተው ነበር። ፖል …

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንድ ራዲዮው ዘገባ  ትናንትና አንዲት ወጣት አይነስውር ድልድዩን ስትሻገር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል። ይህ  ቀጭኔ መድህኒ ዓለም አካባቢ ያለው ድልድይ በቀኝና በግራ በኩል አደጋ መከላከያ ድጋፍ የሌለው በመኾኑ ለሰዎች መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምወጣቱን የ አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካል ጉዳተኞችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ከደረጃ በታች የሆኑ ድልድዮች  በከተማው …

(በቴክኖሎጂስት ዳንኤል አማረ)

መነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ ህመም ተሰቃይተዋል? የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ ላይከሰት ይችላል የአቀማመጥ ሁኔታ፣ የሚጠቀሙት ጫማ፣ ከመጠን ያለፈ ዉፍርትና ከባድ ነገሮችን ማንሳት የላይኛዉና ታችኛው ጀርባ ህመም ያስከትላል።
በሴቶችና ወንዶች ላይ የጀርባ ህመም የሚያስከትሉ መነሻ ምክንያቶችን በዝርዝር እንመልከታቸው፦
1. የቢሮ ወንበር

የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ…

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ 4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044; Tel: (214)703 9022  www.globalallianceforethiopia.org; E-mail: [email protected] ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚታወቀው፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” በመባል ለሚታወቀው ለሮዶልፎ ግራዚያኒ፤ አፊሌ በምትሰኝ የኢጣልያ ከተማ አንድ የመታሰቢያ ኃውልትና መናፈሻ ተቋቁሞለት፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ …

ጋዜጣዊ መግለጫ – የፋሺሽቱ የግራዚያኒ ኃውልት ስያሜ መወገድ Read more »

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

አቡበከር አህመድ  መንግስት በሴኩላሪዝም ስም ህብረተሰቡን በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከእምነቱ ለማስወጣት የሚያደርጋችውን ጥረቶች አጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን የዚህ እቅድ አንደ አካል የሆነወን ድርጊቱን ማንኛዉም አይነት የእምነት አዲስ ተቋማት በአድስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳየገነቡ በሚል መመራያ ማዉጣቱን ምንጮች አስታዉቀዋል። በየትኛዉ እምነት አማኞች ፈጣሪያቸውን በአንድነት የሚያመልኩበት ቦታና የእምነቶቻቸውን ጥሪ የሚያደርጉበት ቦታ የእምነት የእምነት ተቋማቸዉ ሆኖ እያለ ከተማዋ እጅጉን […]

የኢትዮጵያ መንግስትን በጦር ሀይል ለመጣል ሚታገሉት “የኢትዮጵያ የተባበሩት አርበኞች ግንባር” በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ ከፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ሀይል ጎን ተሰልፎ የተቃዋሚውን የሪክ ማቻርን ሀይሎች ይወጋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ. በሪክ ማቻር የሚመሩት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች በቅርቡ እንዳስታወቁት ከሆነ በምእራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ሚንቀሳቀሰውና በቀድሞው የአካባቢው አስተዳዳሪ በሆኑት በቶዋት ፓልቻይ የሚመራው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ኢትዮጵያን ለመውጋት […]

The post የኢትዮጵያ አማጺያን በደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች የቀረበባቸውን ክስ አጣጣሉ appeared first on ሳተናው .

በቨርጂኒያ ሀገረ ግዛት ፣ በሬገን ብሄራዊ የአየር ማረፊያ ተርሚናል ውስጥ አብርሀም ዘመድአገኘሁ የተባለ፣ መስማት የተሳነው እና የጎዳና ተዳደሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ምንም በማያውቀው እና ባልፈፀመው ወንጀል አይፓድ ሰርቀሀል በሚል በፖሊስ ተይዞ ለስድስ ሳምንታት በወይህኒ ቤት አሳልፏል። አብርሀም ከተያዘበት ሰአት ጀምሮ ለሀያ አራት ሰዓታት በምን ምክንያት እንደታሰረ ካለማወቁም በተጨማሪ ያረፈበት የእስር ቦታ ( jail ) መስማት […]

የኬንያ መንግስት የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያን ሊዘጋ መሆኑን የጀርመን የዜና ወኪል ዘገበ። በጣቢያው የሚገኙ ከ500 ሺ በላይ የሶማሊያ ስደተኞች የአሸባብ ታጣቂ ቡድን ወደ ማይገኝባቸው የሶማሊያ ግዛቶች እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል። የኬንያ መንግስት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በጋሪሳ ከተፈጸመው ጥቃት በኃላ መሆኑን የዜና ወኪሉ ጨምሮ ዘግቧል።