Amharic News 1800 UTC – ጃንዩወሪ 02, 2014
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech
ሶማሊያ መዲና መቅዲሾ በሚገኝ አንድ ሆቴል አጠገብ ትናንት ምሽት በተከታታይ በደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 13 ከፍ ማለቱ ተዘግቧል ። ከሟቾቹ መካከል ፖሊሶችም ይገኙበታል ። የሶማሊያው ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስዷል ።
የሳዉዲ መንግስት የሰጠዉ የምህረት አዋጅ የጊዜ ገደብ ካለቀ በኋላ በሪያድ መንፉአ በኢትዮጵያዉያን ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ከደረሰ ወዲህ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸዉም ሆነ ካመጣቸዉ አሠሪ ጋ የማይሠሩ ማናቸዉም ዜጎች እንደህገወጥ እንደሚቆጠሩ በማሳሰብ፤
የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተደራዳሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የሰላም ንግግር ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። አደራዳሪዎቹና ተደራዳሪዎቹ ግን ድርድር የሚጀምሩበትን ትክክለኛ ቀን እስካሁን በይፋ አላሳወቁም ።
የጎርጎሪዮሳዊውን የቀን ቀመር ለሚያሰሉ አዲስ ዓመት ማለትም 2014 ከጠባ ዛሬ ማግስቱ ነው። የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ አቀባበልን በአውሮጳ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን እንዴት ይመለከቱታል? ከዝግጅቱ የምናገኘው ይሆናል።
“ሲፒጄ የሃገራችንን ስም ለማጥፋት ስለሚፈልግ ነው እንጂ፣ በጻፈው ጽሑፍ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም፡፡ 3 ጋዜጠኞች የታሠሩት አሸባሪ ተብለው ነው” ~ አቶ አንተነህ አብርሃም (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት /ኢብጋኅ/ ፕሬዚደንት)“[ሲፒጄ] ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛ ናት ብሏል፡፡ ይሄ ከዚህ በፊትም ሆኖ የማያውቅ ግነት ነው፡፡ የታሰረ የለም።” ~ አቶ ወንደወሰን መኮንን (የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማኅበር /ኢነጋማ/ ሊቀመንበር)“በጻፈው ተፈርዶበት የታሰረ አለ ከተባለ ዶክመንቶችን ማገላበጥ ያስፈልጋል፡፡ ማንም ደግሞ አልታሰረም። ይህ አልሆነም፡፡ ከምላሴ ላይ ፀጉር ይነቀላል፡፡” ~ አቶ ሽመልስ ከማል (የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ)
‹‹…ሊቋቋሙ ይችላሉ መብታቸው ነው፡፡ ነገር ግን እነማን ናቸው የሚያቋቁሙት፣ እንዴት ነው የሚቋቋሙት፣ ከጀርባ እነማን አሉ —- ይሄን ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ ትልቅ ጉዳይ አይደለም፤ ኖረንበታል፡፡ ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም፡፡…››
በፍራቻ የተዋጡ የመንግስት ሰራተኞች = የፍትህ ያለህ ….
ጥቅማ ጥቅምን ሽፋን አድርጎ የመንግስት እና የፓርቲ ስራ ደባልቆ መስራት ከባድ አደጋ አለው::
መርዛማዊ ሃይል ያዘለ የፖለቲካ መስፋፋት የመንግስት ሰራተኛውን የመስራት እንዲሁም የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ ከቶታል::
ምንሊክ ሳልሳዊ :- በኢያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ሁሉንም ፖለቲካኛ የማድረግ እና ለፖለቲካ ፍጆታው ለመጠቀም የሚፈልገው ሕወሓት መራሹ መንግስት ህገመንግስታዊ የዜጎችን የመስራት/ሰርቶ የመኖር መብት እየደፈጠጠ ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው የከተማው ነዋሪ በመንግስት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል:; ይህ ዜጋ በተለያዩ አስተሳሰቦች እና እምነቶች የራሱ በሆነ ሂደት ውስጥ የሚጓዝ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው::በተለያዩ ጊዜያት የተፈራረቁ መንግስታት ኢላማ የሆነው የመንግስት ሰራተኛው ዛሬም የፍትህ ያለህ የነጻነት ያለህ በማለት ላይ ነው::
በየትኛውም የአለም ክፍል ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የሚያገለግለው ለቀጠረው ህዝባዊ አካል ሲሆን በመንግስት ሰራተኛው መሃል የተላያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ድጋፎች እና ተቃውሞዎች የመኖራቸውን ያህል ለፖለቲካ ግድ እስከሌለው ጀምሮ ፖለቲካ መስማት እስከማይፈልጉ እና ስራቸው ላይ ብቻ ማተኮር የሚፈልጉም ዜጎች አሉ :: ይህ ደሞ ህገመንግስታዊ መብታቸው እስከሆነ ድረስ ሊከበርላቸው ይገባል::
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው መርዛማዊ ሃይል ያዘለ የፖለቲካ መስፋፋት የመንግስት ሰራተኛውን የመስራት እንዲሁም የመኖር ህልውና አደጋ ውስጥ ከቶታል::ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ አለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ድርጅቶችም ይህንን በመንግስት ሰራተኞች ላይ የሚፈጸመውን በመስራት/በመኖር ላይ ያነጣጠረ ደባ አሳሳቢነት በይፋ ገልጸዋል::ከመንግስታዊ ጥቅማ ጥቅምም እንዲታገዱ እየተደረገ እንደሆነም ጩኸታችንን አሰምተናል::መንግስት ስንል ህዝብ ማለታችን መሆኑን ይገንዘቡልን..መንግስት የሚለው ቃል ወያኔን አይወክልም::
ወያኔ በህዝቦች ላይ የሚያራምደው አደገኛ የአገዛዝ ስልት የሚመለከቱ አብዛኛዎች የፓርቲው አባላት እና ካድሬዎች የትግል ቁርጠኝነታቸው ከመላሸቁም ሌላ ከፓርቲ ስራዎች ይልቅ በጥቅማዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸው ያሳሰበው ወያኔ አንድ ለአምስት በሚባል አደረጃጀት የፓርቲውን ስራ ከመንግስት ስራ ጋር ጎን ለጎን ለመተግበር ደፋ ቀና በማለት የዜጎችን ህልውና አደጋ ውስጥ ጥሎታል::የወያኔን ድርጅታዊ ስራ ከመንግስት ስራዎች ጋር ቀይጦ ለመተግበር መሞከር አደጋው ወደማይወጡበት አዘቅት ሊከት እንደሚችል መታወቅ አለበት ::
ወያኔ የስልጣን ጊዜውን ለማስረዘም ብቻ በሚያደርገው መፍጨርጨር በህዝብ እና በሃገር ላይ ሊመጡ የሚችሉትን አደገኛ እንቅፋቶች ከግንዛቤ አለማስገባቱ በላይ ማንጫውን ዜጋ ህዝብን በሚያገለግልበት የመንግስት ስራዎች ላይ መፈጸም የሚገባውን እንዳይፈጽም እና በድርጅታዊ ስራ ስፋን ለቢሮክራሲ ለሙስና ለህዝቦች እንባ በር መክፈት መሆኑን ልብ አለማለቱ የወያኔ ዝቅጠት ገሃድ አድርጎታል::
በልማት ስም እየተፈጸሙ ያሉት ደባዎች እና ሴራዎች አልበቃ ብሎት በኢኮኖሚ ድቀት እየተንገፈገፍ ያለን ህዝብ በድርጅታዊ ስራ ለመወጠር ማሰብ የፈነዳ እለት የሚያስከትለውን ችግር ማንም ሊወጣው እንደማይችል ለማረጋገጥ እንወዳለን ስለዚህ በመንግስት ሰራተኞች ዙሪያ እየተካሄደ ያለው እሽክርክሪት ሊታሰብበት ይገባል::
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መምህራኑ አድማውን የጀመሩት ያለፍላጎታችን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ደሞዛችን እየተቆረጠብን ነው በሚል ነው። መምህራኑ ለይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር፣ ለጌዲዮ ዞንና ልክልሉ ትምህርት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ” ከ ሀምሌ 2005 ዓም ጀምሮ ለህዳሴ ግድብ የሚቆረጠው ገንዘባችን እኛ ያለፈቀድነውና ያልተስማማንበት በመሆኑ ጥቅምት 28፣ 2006 ጀምሮ ስራችንን በአግባቡ እየሰራን …
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች ከአንዳንድ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለዋል። ኩባንያዎቹ የተሰማሩባቸው መስኮች የኃይል፣ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎች መሆናቸውን የዘገበው …
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲሲቷ አፍሪካዊት አገር የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት በሺ የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ የሁለቱም ተፋላሚ ሀይሎች ተደራዳሪዎች በአዲስ አበባ ቢገኙም አሁንም ጦርነቱ ቀጥሎአል። በአዲስ አበባ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የሰላም ድርድር የተኩስ አቋም ስምምነት እንዲፈረም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር በበኩላቸው የተኩስ ማቆም ስምምነት …
ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞቃዲሹ አየር ማረፊያ አካባቢ የሚገኘው ጃዚራ ሆቴል ውስጥ በሁለት መኪኖች የተጠመዱ ቦንቦች ፈንድተዋል። ፍንዳታው ከመድረሱ በፊት በጠባቂዎች እና ፍንዳታውን ባደረሱት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። በአሁኑ ፍንዳታ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ አልታወቀም። ባለፈው ሳምንት በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። አልሸባብ አሁንም የደቡብ የሶማሊያ …
ESAT Radio Jan 01
ባለፈው ኅዳር 14 እና 15 ,2006 በለንደን ብሪታንያ፤ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ባዘጋጁት ዓለም አቀፍ የዕውቀት ልውውጥ ነክ ጉባዔ ተሳትፈው ከተመለሱት አንዱ ናቸው። በጎንደር ዩንቨርስቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ «ባዮ -ሜዲካል እና ላበራተሪ ት/
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family
ጎርጎሪዮሳዊዉን የዘመን ቀመር የሚከተለዉ ዓለም አዲሱን 2014ዓ,ም ዛሬ አንድ ብሏል።
የዓለም ዜና
የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ልዑካን ወደ 3 ሳምንታት ከተጠጋ የአርስ በርስ ውጊያ በኋላ ለሰላም ድርድር ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ተነግሯል።
የጀርመን መራኂተ መንግሥት ወ/ሮ አንጌላ ሜርክል፣ ዛሬ ያባተውን አዲሱን 2014 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት መንስዔ በማድረግ ለህዝባቸው ንግግር አሰምተዋል።
As Posner (2004) notes, elites struggle to win the maximum rights and privileges for their ethnic groups. This condition fuels ethnic competition with the hope of gaining influence in national politics (Wantchekon 2003). On the other hand, for Chandra (2004, 2006) the quality of democracy will not be affected by the domination of ethnic-based parties. Another scholar, Birnir (2007) also voiced similar argument and claimed that ethnic-based parties might contribute for the improvement of the quality of democracy.
በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሁፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰበሰቡን ሰማን። ጽሁፉን ያሳተመው መጽሄት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምእራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማረገብ ጀመሩ። አንድ የዳች ጋዜጣ አጼ ምኒሊክን ከሂትለር ጋር አመሳስሎ በመጻፍ ጋዜጣውን በዚህ […]
* ዱባይ በአስደናቂ 400 ሽህ ርችቶች አለምን አስደመመች! * እፁብ ድንቅ ርችቶች የአለምን ሪኮርድ ሰብረዋልም ተብሏል * ሳውዲና ባህሬንን በሚያገናኘው ድልድይ ተጨናንቋል * እኛም እያዘንን ለመደሰት በመሞከር ላይ ነን ከአመታት በፊት 828 ሜትር እርዝመት ያለው የቡርጅ ከሊፋን ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በመገንባት የአለምን ሪኮርድ የሰበሩት ኢምሬቶች ዛሬ በጀመርነው አዲሱ አመት 400 ሽህ እፁብ ድንቅ በህብረ ቀለማት […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የ ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው
KING MENELIK HAS INVESTMENTS HERE; Abyssinia’s Ruler Said to be a Heavy Buyer of American… ታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።
ኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።
አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።
ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ”የታሪክ” ፅሁፎች ውስጥ ”በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ” የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ”ትርፋማ” ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።
ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው ”ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ” እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።
”ማን ያውራ የነበረ” እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ –
– ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣
– የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣
– አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣
– የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣
– ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና
– እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣
የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።
የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።
ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው
ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ አብዮቶች (የተሳኩትም ሆነ የከሸፉት) ሰላማዊውንና ህጋዊውን መንገድ የተከተሉ ባለመሆናቸው ዛሬም ይዘገንናሉ፤ ለወደፊቱም ባልተደገሙ ያሰኛሉ፡፡ ስለምን ቢሉ? ግድግዳው ላይ የተቸከቸከው ፅሁፍ እንዲህ የሚል ምላሽ ያስነብባልና፡- በጭቁን ሕዝብ ስም የብዙሀኑን ቤት አፍርሰዋል፤ ሀገርና ታሪክ ለመቀየር የማይሳናቸው አፍላ ወጣቶችን እርስ በእርስ አጫርሰዋል፤ ‹አንቱ› ሊባሉ የሚችሉ ምሁራንን በአንድ ጀንበር ወደ ትንታግ ነፍሰ-ገዳይነት ቀይረዋል፤ ክስረቱም ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ጠባሳ ሆኖ ዛሬ ላይ ደርሷል…
በርግጥም ያ ወቅት መደማመጥ፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ መቻቻልን… የመሳሰሉ ምክንያታዊ እሴቶች ህቡዕ ገብተው፤ መጯጯኽ፣ መነቋቆር፣ መፈራረጅ፣ መገዳደል… የገነኑበት ነበር፤ ለዚህም ይመስለኛል ሀገር ሊረከብ የተዘጋጀ አንድ ትውልድ፣ በተኮረጀ ርዕዮተ-ዓለም፣ ባልጠራ ፕሮግራም እቅሉን ስቶ ‹ማርክስ እንደፃፈው›፣ ‹ሌኒን እንዳብራራው›፣ ‹ማኦ እንዳስተማረው›፣ ‹ሆጃ እንደመከረው›… በሚል ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ስቶ-በማሳት፣ ሀገር ምድሩን የጦር አውድማ አድርጎ ማለፉ የትላንት የቁጭት ትዝታ የሆነብን፡፡ በአናቱም ዛሬ ‹‹ነፃ አወጣናችሁ›› እያሉ ጃሎታ የሚመቱት የኢህአዴግ መሪዎች ከዚሁ ምንጭ የተቀዱ፣ ግና በቃላት ስንጠቃና በጎሳ ጠባብ አስተሳሰብ የተለዩ የትውልዱና የመንፈሱ ተጋሪ በመሆናቸው፣ የሁነቱ ‹ታሪክ›ነት ለተሰዉት እንጂ፣ ለእነርሱ ‹ሀገር እየመራንበት ነው› የሚሉበት ‹ፖለቲካ› ነውና፣ የነገይቷ የምንወዳት ኢትዮጵያችን መፃኢ ዕድል ገና ከእርስ በእርስ ግጭት ስጋት አለመላቀቁን ያመላክታል፡፡ በዚህ ፅሁፍም የምንዘመርለት የ‹አትነሳም ወይ?› ድምፅ አደገኛውን ስርዓት የመቀየሪያው ጊዜ አሁን በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ግን እነኢህአፓ ተቸንፈው የተሰናበቱበትም ሆነ ኢህአዴግ ድል አድርጎ የመጣበት መንገድ ለዘመኑ መልካም ተሞክሮ ሊሆን ይችላል እንደማለት አይደለም፤ ምክንያቱም በእኔ እምነት የእነርሱ ‹ፋኖተሰማራ…› ጊዜው በበየነበት ሙዚየምና የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ ብቻ ካልተገደበ ጉዳቱ በቀላሉ የሚጠገን ካለመሆኑም ባለፈ፣ የምንመኘውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልምና ነው፡፡
የሆነው ሆኖ ለትውልዱ ክቡድ ጥያቄ ስኬታማነት መንገድ መሪ አብርሆት መሆን የሚችሉ የደም ግብር ያልጠየቁ፣ ፍፁም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ በከተሞች ተካሂደው ሀገርና ህዝብ ያለ ብዙ ኪሳራ በአሸናፊነት የወጡባቸው በርካታ አብነታዊ አብዮቶች (እንደ አረቡ ፀደይም ሆነ እንደ አውሮፓውያኑ ጆርጂያና ዩክሬን ብርቱካናማ-አብዮቶች) መኖራቸው እውነት ነው፤ እንዲሁም በእነርሱ መንፈስ መቀደስ፣ በእነርሱ ፀበል መጠመቅ የአምባገነኑንና የበደለኛውን ሥርዓት እድሜ ለማሳጠር የሚያበረታ ኃይል ማስረፁ እውነት ነው፡፡
ከተማን እንደ ጠላት
የ‹ያ ትውልድ› የጠብ-መንጃ ትንቅንቅን በድል የተሻገረው ኢህአዴግ (ከልቡ አምኖበት ባይሆንም) ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለው በተለይም ለአርሶ አደሩ ጥቅም መሆኑን በአገኘው አጋጣሚ ሳይናገር አያልፍም፡፡ በግልባጩ ደግሞ የከተማ ነዋሪዎችን ‹ጠላት› አድርጎ በመፈረጅ ሲገነግን ተደጋግሞ ተስተውሏል፤ በርግጥ የዚህ መግፍኤ በብሔር እና በሀይማኖት የከፋፈለውን ሕዝብ፣ በመደብም ለያይቶ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ለማድረግ እና በየአምስት ዓመቱ በሚያካሄደው የይስሙላ ‹ምርጫ› ኮረጆ ገልብጦ ሲያበቃ የፈረደበት ምስኪን አርሶ አደር ‹መርጦኛል› ለሚለው የተለመደ ሰበቡ ‹ይጠቅመኛል› በሚል ለማመቻቸት ‹አዛኝ ቅቤ…› ተቆርቋሪ በመሆኑ ይመስለኛል፡፡ ይህም ሆኖ ድርጅቱ ይህንን የማጭበርበሪያ ስልት በደደቢት በረሃ ራሱ የቀመረው ነው ብሎ ለመከራከር የሚያስችል ገፊ ጭብጥ ይኖራል ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም በአንዳንድ የዓለማችን ሀገራት የፖለቲካውን ኃይል ከጨበጡ በኋላ በሕዝባቸው ላይ ነጋሪት ጎስመው ሞትን ከነዙ፣ ስቃይን ከረጩ እርኩሳን መሪዎች (ፓርቲዎች) ድርሳናት ቃል-በቃል የተገለበጠ መሆኑን የሚያስረግጡ (በስነ-አመክንዮ) የተቀኙ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላልና፤ እንደምሳሌም አንዱን በአዲስ መስመር እንምዘዘው፡-
የ‹ኬመር ሩዥ› መንገድ
በተለምዶ ‹ኬመር ሩዥ› (Khmer Rouge) በመባል የሚታወቀውና አክራሪ ኮምኒስታዊ የገበሬዎች ድርጅት እንደሆነ የሚነገርለት ‹‹Communist Party of Kampuchea /CPK/›› እ.ኤ.አ ከ1975-1979 ዓ.ም ድረስ፣ በወጣት የገበሬ ሠራዊት ታግዞ በካምቦዲያ መንግስታዊ ሥልጣን ተቆናጥጦ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ጨካኝና አፍቃሪ ቻይና የሆነው የፓርቲው ሊቀ-መንበር ፖል ፖትም (Pol Pot)፣ ማኦ ዜዱንግ ‹‹የሀገሬን ኢኮኖሚ ያሳድግልኛል›› በማለት ያረቀቀውንና በግብርና ላይ የሚያተኩረውን ‹‹Great Leap Forward›› ፕሮግራም፣ ‹‹Super Great Leap Forward›› በሚል ተቀጥላ እንደወረደ በመኮረጅ ‹‹ሙሉ የካምቦዲያን ሕዝብ ወደ ‹እርሻ መር-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ› (Agrarian Society) እቀይራለሁ›› ብሎ ያደረገው ሙከራ ወጪ-ኪሳራን ያወራረደው ሁለት ሚሊዮን ዜጎቹንለህልፈት በመዳረግ እንደ ነበር የታሪክ መፃህፍት ያትታሉ፡፡
ከሁሉም የከፋው ግን ፖል ፖትና ጓዶቹ ‹‹እውነተኛ ዜጋ ገበሬ ብቻ ነው›› በማለት የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ከፈረጁ በኋላ ‹‹ማህበረሰባችንን ለማንፃት›› በሚል የቁም-ቅዠት ምዕራባዊ አስተሳሰብ የተንፀባረቀበትን ማንኛውንም ጉዳይ፣ የከተማ ሕይወትን፣ ኃይማኖትን፣ ትምህርትን፣ አንድ ብርም ቢሆን በግል መያዝን… በአዋጅ ማገዳቸው ነበር፤ እንዲሁም ኢምባሴዎችን፣ ጋዜጣና ቴሌቪዥን ጣቢያን ዘግተዋል፤ በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎችን በማፈናቀል ወደ ገጠር አግዘው፣ በግዳጅ የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተዋል፤ ከዋና ከተማዋ ‹ፈኖሞ ፔንህ› (Phnom Penh) ብቻ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች ወደገጠር በእግር እንዲጓዙ በመገደዳቸው ሃያ ሺህ የሚሆኑት በጉዞ ላይ ወድቀው እንደወጡ ቀርተዋል፤ ገጠር የደረሱትንም ቢሆን ‹የግድያ ወረዳዎች› እያሉ በሚጠሯቸው የእርሻ ሥራ ላይ አሰማርተው ለአንድ ሰው በነፍስ ወከፍ በየሁለት ቀኑ አንዴ 180 ግራም ሩዝ ብቻ በመስጠት በረሀብ፣ በበሽታ፣ ብስቅየት እና በግድያ እንዲያልቁ አድርጓል፡፡ በመጨረሻም አገዛዙ በቬትናም ጣልቃ ገብነት እ.ኤ.አ በ1979 ዓ.ም በኃይል በመወገዱ፣ ፖል ፖት ከእነተከታዮቹ ሀገሩ ከታይላንድ ወደምትዋሰንበት ጠረፍ አካባቢ በመሸሽ፣ የትጥቅ ትግል እንደአዲስ ጀምሮ ለረዥም ዓመታት ከታገለ በኋላ፣ እ.ኤ.አ በ1997 ዓ.ም እርጅና ተጭኖት በህግ ቁጥጥር ስር በዋለ፣ በዓመቱ ከልብ ጋር በተያያዘ ህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል (በነገራችን ላይ ይህ ድርጅት የሽምቅ ውጊያ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ በኋላ የተጠናከረበትን ምስጢራዊ መንገድ ጨምሮ የተከተለው ስልት ከሞላ ጎደል ከኢህአፓና ህወሓት አፈጣጠር ትርክት ጋር ተመሳሳይነት አለው)
ኢህአዴግ እንደ ‹ኬመር ሩዥ›
ከሁለት አስርተ ዓመታት የሥልጣን ቆይታም በኋላ፣ የከተማ ነዋሪዎችን በጠላትነት ካሰፈረበት ጥቁር መዝገቡ ላይ መሰረዙ ያልሆነለት ኢህአዴግ ‹እንደ ኬመር ሩዥ ሁሉንም የጭካኔ ተግባራት በአደባባይ ፈፅሟል› ተብሎ ባይወነጀልም፣ ተመሳሳይ ስልቶችን በመኮረጅ በረቀቀ መንገድ አለዝቦ መተግበሩን ግን መካድ አይቻልም፡፡ እንዲሁም የሁለቱ ድርጅቶች ዋነኛ ልዩነት ወደ እንዲህ አይነቱ የጥላቻ ጠርዝ
የተገፉበት ምክንያት ይመስለኛል፤ ይኸውም ፈላጭ ቆራጩ ፖል ፖት በከተሜው ላይ የከፋ ቂም የቋጠረበት መነሾ፣ ከገበሬ ቤተሰብ መገኘቱን ጨምሮ፣ ከአስተዳደጉ ጋር በሚያያዙ ‹ህመማቸው-ህመሜ› በሚል ሲባጎ የተቋጠረ ሲሆን፣ መለስና ጓዶቹ ደግሞ የሥልጣን ዕድሜያቸውን ለማራዘም በማስላት ብቻ መሆኑ ነው፤ መቼም መሬት የረገጠውን እውነታ ተመልክቶ የሀገሬ አርሶ አደር ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በዘለለ፣ ከከተሜው የተለየ የመልካም አስተዳደርም ሆነ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ አለመሆኑን መረዳቱ አዳጋች አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ የኢህአዴግ ‹ፀረ-ከተሜነት› እንዲህ በግላጭ አፍጥጦ የወጣው ከምርጫ 97 በኋላ ነው፤ በወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ፣ ድርጅቱ በከተሞች መሸነፉን ከገለፀ በኋላ፣ በገጠር ሙሉ በሙሉ ስለተሳካለት መንግስት ለመመስረት የሚያስችል የመራጭ ድምፅ ማግኘቱን አውጇል፤ ይህንንም ተከትሎ ግንባሩን ያልመረጡ የከተማ ነዋሪዎች በተቀነባበረ ሴራ የጥቃት ዒላማ መሆናቸውን የሚያመላክቱ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ በተለይም በድህረ-ምርጫው ከተሜውን ዒላማ ያደረጉ በስራ ላይ የዋሉ አፋኝ ህጎች እና ፖሊሲዎችን ጨምሮ በደባ የተፈፀሙ መንግስታዊ ጥፋቶችን ዘርዘር አድርገን እንያቸው፡፡
መሬትን በተመለከተ የወጣውን የሊዝ አዋጅ በቀዳሚ ምሳሌነት እናንሳው፤ ፓርቲው በ1987 ዓ.ም ባፀደቀው ህገ-መንግስት የመሬት ፖሊሲውን አንዱ ዕማድ አድርጎ በማካተቱ፣ የመንግስት ጭሰኝነትን (Tenants of the state) በገጠሩ ክፍል ሲያሰፍን፣ የመሬት ከፊል ባለቤትነትን ደግሞ ለከተሞች እንዲፈቅድ አድርጎት ነበር፡፡ እናም የግል ይዞታን መሸጥ (መንግስት ለሚፈልጋቸው ‹‹ልማቶች››ም ሆነ
በሊዝ ለመቸብቸብ ዜጎችን የማፈናቀል መብት ከማግኘቱ ውጪ) እስከ 97ቱ ድህረ-ምርጫ ድረስ ተፈቅዶ የዘለቀበት ሂደት፣ በዚህ የሊዝ አዋጅ በመሻሩ የተነሳ፣ ነዋሪው መሬት በመሸጥ ሊያገኝ ይችል የነበረው ገቢ ተጨምቆ ወደ መንግስት ካዝና እንዲሻገር ሆኗል፡፡ የዚህን አዋጅ ‹ፖለቲካዊ ንባብ› ውስጥ የምናገኘው ጭብጥ፣ በከፊልም ቢሆን መሬት ላይ የቆመውን የሀብት መሰረት በመናድ፣ የተቃውሞ ኃይሉ የድጋፍ መዕከል እንደሆነ ያመነውን የማህበረሰብ ክፍል ክፉኛ ማድቀቁን ስንረዳ ነው፡፡ አዋጁን እንለጥጠው ካልን ደግሞ ግንባሩ በገጠሩ ያነበረውን የዜጎች የመንግስት ጭሰኝነት በጠመዝማዛ መንገድ፣ በተለይም በአዲስ አበባ የመፈጸም ዕቅዱ አድርገን ልንወስደው እንችላለን፡፡
የኢህአዴግ ከተማንና ከተሜዎችን የመፍራት አባዜ ከጫካ ትግሉ ጋርም በረዥሙ የሚተሳሰር ነው፡፡ በወቅቱ በጥላቻ ከመተያየት አልፎ ደም የተቃባቸው ኢህአፓን መሰል ኃይሎች መሰረታቸው ከተሞች ላይ እንደነበረ ይታወቃል፤ በአናቱም በትግሉ መጠናቀቂያ ዋዜማ እና ማግስት ሊገዛለት ያልቻለው (ማማለሉ ያልተሳካለት) ልብ በተለይ የአዲስ አበቤዎችን ነበር፤ በ1980ዎቹ መጀመሪያም ፓርቲው አንገት ላይ ታንቆ ሊደፋው የነበረው ዋነኛ ጉዳይ፣ ብሔር ተኮር ስርዓቱ ህገ-መንግስታዊ ድጋፍ ሲያገኝና የብሄር ፖለቲካ ብቸኛው የድጋፍም የተቃውሞም ተዋስኦ እንዲሆን መደረጉ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያዊብሔርተኝነት መንፈስ ከተገራው የአዲስ አበቤ ብሔር ዘለል ማንነት ጋር እንዲህ በፊት ለፊት መጋጨቱ፣ ከተማይቱን በወረራ የያዛት እስኪመስል ድረስ በጥላቻ እንዲዘምቱበት አነሳስቷል፡፡
ሁለተኛው ምዕራፍ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ የመጣው የአሰብ ወደብን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲካለል የመፈለግ የከተሜዎቹ ግፊት ነው፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃና የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ሲገደዱ የነዋሪው ቁጣ ብርቱ እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ይህ እውነትም ሌላኛው ፓርቲውን ቂም ያስቋጠረ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ በድህረ-ምርጫ 97 የፀደቀውና አፋኝነቱ በተግባር የተረጋገጠው የሲቪል ማህበረሰቡን የሚመለከተው አዋጅም ‹የብዙዎች ተቋማት ዋናመቀመጫ አዲስ አበባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የወጣ ነው› በማለት ከየአቅጣጫው ይነሳ የነበረውን የተቃውሞ ውግዘት አጣጥሎ፣ በሥራላይ ባዋለበት ዓመት በርካታ ተቋማትን ከማፈራረሱ አኳያ፣ መጀመሪያውንም ለእንዲህ አይነቱ ክፉ እርምጃ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ወደሚል ጥርዝ ይገፋል፡፡ በተጨማሪም ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት ሙሉ በአይኑ መዓት የሚያያቸው ምሁራን፣ የነፃው ፕሬስ አባላት እና በየዘመኑ ከባድ ተግዳሮት የፈጠሩበት የተቃውሞ ስብስቦች ጠንካራ መሰረት በከተማይቱ ውስጥ መሆኑ ጥላቻ እና የጭካኔ እርምጃዎቹን አብዝቶታል፡፡
ሌላው አገዛዙ በከተሜዎች (በሸማቾች) ላይ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ የሚያሳዩት፡- ከምርጫው በኋላ ጤናማ ያልሆነ የዋጋ ንረት በከፋ ደረጃ ማሻቀቡ፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ የተለያዩ የግብር ህጎች በእንጀራ እና ሽንኩርት ቸርቻሪዎች ላይ ሳይቀር መተግበራቸው ነው፡፡ በተለይም ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ የተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ዋነኛ አባባሽ ኃይል የምግብ ዋጋ መናር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ
የምግብ ዋጋ መናር በዋነኝነት ቋሚ ደሞዝ ተከፋዩ የከተማ ነዋሪው ተጎጂ መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናትም ይቀበላሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከሁለት ወራት በፊት በ‹‹አዲስ ዘመን›› መፅሄት የተጠየቀው የፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ‹‹በ2006 ዓ.ም የሚጨመር ደሞዝ አይኖርም›› ከማለቱ ባለፈ ‹‹ነገ ይችን አገር ወደተሻለ የሚያደርስ በጎ መስዋዕትነት ነው›› ሲል በከተሜው መከራ ላይ አላግጧል፡፡ በርግጥ ይህ ሁሉ መዓት ከመውረዱ በፊት በ1998 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ራሱ አቶ መለስ በደቡብ ክልል ወደምትገኘው ይርጋለም ከተማ ድረስ ሄዶ የሙዝ አምራች አርሶ አደሮችን ሰብስቦ ካነጋገረ በኋላ፣ እንዲህ ለፍተው የሚያገኙትን ምርት ለከተሜው በርካሽ መሸጣቸው አግባብ አለመሆኑን ቀስቅሶ ዋጋውን በአራት እጥፍ እንዲጨምሩ በማድረጉ የተፈጠረው የገበያ እጥረት፣ ምንም እንኳ መልሶ አምራቾቹን ሰለባ ቢያደርግም፣ ኩነቱ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቀጣይ ዕቅድ የሚያመላከት ነበር፡፡
በከተሞች ውስጥ እየተደረገ ያለው ‹‹የሰፈራ ፕሮግራም››ም (Urban Resettlement) አንዱ ሊነሳ የሚገባው ነጥብ ነው፡፡ በእርግጥ በዚህ ዕቅድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሻለ የመኖሪያ ቤቶች ተጠቃሚ እንደሆኑ ማየት እንችል ይሆናል፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ግን፣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎችን ከሌሎች የፈረሱ የከተማዎቹ ክፍሎች ከሚመጡት ጋር በአንድ አዳብሎ በኮንዶሙኒየም ቤቶች አጥሮ የማስቀመጡ አንደምታ ላይ ነው፡፡ የዚህ ዕቅድ ክፉ ገፅ የሚገባን በረዥም የአብሮነት መስተጋብር (ሶስት መንግስታትን መሻገር የቻለ የአንድ አካባቢ ነዋሪነት) የተገነባው የጋርዮሽ ፖለቲካው አረዳድ እና የእርስ በእርስ ፍፁም መተማመን፣ 97ን ጨምሮ በተለያዩ ወቅቶች በተነሱ ተቃውሞዎች ወጥ ምላሽ እንዲሰጡ ማደፋፈሩን (አራት ኪሎን የመሳሰሉ አካባቢዎች) አስታውሰን፣ በመልሶ ማስፈሩ ደግሞ የአንዱን አካባቢ ነዋሪ በታትኖ ወደተለያዩ ሳይቶች መውሰዱን ስንመለከት ነው፤ ይህ መራራ እውነታም የገዥዎቻችን ጥላቻ ስር የሰደደ መሆኑን እና የአምባገነናዊ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም ያለመ እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡
(ስርዓቱ በከተሜዎች ላይ የሰረፀበትን ጥልቅ የጥላቻ ፅንፍ እንዲህ ከተመለከትን፣ የከተማ አብዮት፣ ማኦኢዝም ከሚያዘው ከገጠር ከሚነሳው ብረታዊ ትግል ጋር ያለውን ልዩነት፣ በአረቡ ፀደይ ተሞክሮ በመንተራስ መፈተሹን፤ እንዲሁም የኢህአዴግ ግድፈቶች (Achilles’ heel) የከተማ አብዮትን ለማስነሳት ያላቸውን አስተዋፅኦ፣ በአደባባይ ሊያሰባስቡ የሚችሉ ጥያቄዎች ምን ቢሆኑ የተሻለ ነባራዊውን እውነት ያንፀባርቃሉ… የሚሉትን ጉዳዮች እና መንገዱን ስለሚመሩ የሚችሉትን መልከአ-ቡድኖች ማንነት ሳምንት እመለስበታለሁ)
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
melakou fanta, case adjourned
south sudan, talks, addis ababa
ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሳዑዲ መንግስት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጽያዊያን ማባረሩን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ኤጀንሲዎች መካከል ከ100 በላይ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ ኤጀንሲዎች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን ከአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ በኢትዮጽያ በአጠቃላይ 470 የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች …
ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንዳሳዩት በአፍሪካ ባለፉት 6 ዓመታት በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ ከተላኩት 34 ሺ 342 ህጻናት ውስጥ 63 በመቶ ወይም 21 ሺ 365 ሰዎችን በመላክ ቀዳሚ ናት። በሃገሪቱ በሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፈቃድ የተሰጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ጉዳይ አስፈፃሚ የጉዲፊቻ ደላሎች ተበራክተዋል፡፡ በአብዛኛው ለጉዲፈቻ በሚቀርቡ ህፃናት …
ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመሰራት ላይ ያለው አዲስ ፊልም ኦነግ ፤ ኦብነግ እና ግንቦት ሰባትን በሽብርተኝነት የሚያወግዝ ነው። ኢህአዴግ በዚህ ሰአት ፊልሙን ለምን ለመስራት እንደፈለገ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። አንዳንዶች እንደሚገምቱት ከሆነ ግን ገዢው ፓርቲ በድርጅቶች እንቅስቃሴ ስጋት እየገባው ነው። እየተሰራ ባለው ፊልም ውስጥ ኢሳትንም ለመወንጀል እየታሰበ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል። …
ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኤ ኤፍ ፒ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ለውይይት በአዲስ አበባ ይገኛሉ። ማቻር የሰላም ድርድሩን የተቀበሉት የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ አገራቸውና የኢጋድ አባላት በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት አማጽያኑን እንደሚወጉ ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ ነው የሚለውን …
ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎርጎሪያን ካላንደር የሚቆጥሩ አገሮች አዲስ ዓመታቸውን በልዩ ድምቀት እያከበሩት ይገኛሉ። በጎርጎሪያን ቀመር መሰረት ኢየሱስ በዳዊት ከተማ በኢሩሳሌም በምትገኘው ቤተ-ልሔም ከተወለደ 2014 ዓመት ሆኖታል ። እንደ ቢቢሲ ዘገባ አዲስ ዓመትን ከሁሉም ቀደም ብላ የተቀበለችው አገር ኒውዚላንድ ነች። ቤጅንግን ጨምሮ የምስራቅ እስያዎቹ ጃካርታ እና ሲንጋፓር አዲስ ዓመቱን በደመቀ ሁኔታ …
ኢትዮጵያና ኤርትራ ዜጎቻቸውን እያወጡ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የአቶ መላኩ ፈንታን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን ያለውን ፍርድ ቤት ለመለየት የሚያስችለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሣኔ ዛሬም እንዳልደረሰው አስታውቋል፡፡
ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን የችሎት ውሎ ዘገባ ያዳምጡ፡፡
News, Ask the Doctor, Agriculture and Business
ማቸር ለመደራደር ፍቃደኛ ከመሆናቸዉ ጋር ተኩስ እንደማያቆሙ እንዳስታወቁ ሁሉ ፕሬዝዳት ሳልቫ ኪርም ዉጪ ጉዳይ ሚንስትራቸዉን ለድርድር ወደ አዲስ አበባ ከመላካቸዉ እኩል ሥልጣን እንዲለቁ ወይም አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ተቃዋሚዎች ያቀረቡትን ሐሳብ ዉድቅ አድርገዉታል
ዛሬ እኩለ ለሊት የምንሸኘው የጎርጎሮሳውያኑ 2013 በአውሮፓ የሥራ አጡ ቁጥር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ያሻቀበበት ፣ የወጣት ሥራ አጦችን ቁጥር ለመቀነስ የክፍለ ዓለሙ መሪዎች መፍትሄ ይሆናል ያሉትን ያቀዱበት ፣
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ አዲስ አበባ ውስጥ እሁድ ታኅሣሥ 20 ቀን፥ 2006 ዓም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራውን በከፍተኛ ድምፅ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል።
ነገ አምና ለመባል የሰዓታት እድሜ የቀረዉ የጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር 2013 የተለያዩ የተፈጥሮ ቁጣና አደጋዎችን አስተናግዷል። የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ኃያል ማዕበልና ሞገዶች፤ ጎርፍና ድርቅ።
የጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር 2013 የተለያዩ የተፈጥሮ ቁጣና አደጋዎችን አስተናግዷል። የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ኃያል ማዕበልና ሞገዶች፤ ጎርፍና ድርቅ።
ሰሞኑን፣ በተለይ የዌስት ጌት ሞል ላይ በአልሻባብ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ጥበቃው ተጠናክሯል። በወቅቱ በድንጋጤ ሲዘነዘሩ ከነበሩ አስተያየቶች ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ጥቃት የማይፈፀመው በደኅንነቱ ሥራ መጠናከር ነው የሚለው አስተያየት አመዝኖ ተደምጧል። መንግሥትም ፀረ–ሽብር እንቅስቃሴ ላይ አተኩሬ የምሠራው ይህንኑ ፈርቼ ነው የሚመስል ትንታኔ በኢቴቪ በኩል አሾልኳል።
ይሄ ሁሉ ይባል እንጂ፣ የዌስት ጌቱ ድንጋጤ አዲስ አበባን ዛሬም በፍርሐት እያራዳት ነው። በተለይም ደግሞ የእግር ኳስ ፈንጠዝያው ዕለት ራሳቸው ላይ ባርቆባቸው ሞቱ የተባሉት አሸባሪዎችና በአልሻባብ ስም በትዊተር ገፅ ፒያሳ እና ቸርችል ቦምብ ቀብረናል ብለው ያልታወቁ ሰዎች የነዙት ወሬ ድንጋጤውን አባብሰውታል። ከዚያም በኋላ ኳስ ግጥሚያዎች ባደባባይ ስክሪኖች እንዳይተላለፉ በማገድ መንግሥትም መፍራቱን አረጋግጧል።
በዚህ ድንጋጤ ወቅት ምክንያቱ በቅጡ ባይገባኝም፣ ብዙ የማኅበራዊ አውታር ተጠቃሚዎች የዚህ ዓይነቱ ጥቃት ሰለባ ይሆናል ብለው የገመቱት ኤድና ሞልን እንደሆነ በግልጽ ሲናገሩ ነበር። ምናልባትም የመዝናኛ ስፍራ ስለሆነና የውጭ ዜጎችም ስለሚበዙበት ዓይን ውስጥ ይገባል በሚል ይሆናል። ኤድና ሞልም መልዕክቱ አሳስቦት ይሁን በመንግሥት ትዕዛዝ “የተጠናከረ ፍተሻ” ጀምሯል።
በነገራችን ላይ አንድ ቀን፣ አንድ ሰው ኤድና ሞል ውስጥ በፌስታል ይዞት የገባውን ዕቃ ረስቶ በመውጣቱ ሁካታና ድንጋጤ ተከስቶ ፊልም እስከማቋረጥም ደርሶ እንደነበር ሰምቻለሁ።
የኤድና ሞል ፍተሻ የተጠናከረ ሰሞን ጥበቃዎቹን ‘ያ ሁሉ አብጠርጥሮ መፈተሽ ለምን እንደሆነ’ ስጠይቃቸው እዚያ የሚገቡ ኮረዶችና ጎረምሶች ሐሺሽ ይዘው እየገቡ አስቸግረዋቸው እንደሆነ ነገሩኝ። ባይዋጥልኝም ለፍተሻ መተባበሬ አልቀረም። የኤድና ሞል ፍተሻ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቶ አሁን ላፕቶፕ ይዘው የሚገቡ ሰዎች የያዙት ላፕቶፕ መሆኑን ለማረጋገጥ አብርተው ማሳየት አለባቸው።
በሌላ በኩል ጥበቃዎቹ ለሚያደርጉት ክትትል መጋነን የደኅንነት አባላት እጅ አለበት የሚል መረጃም ደርሶኛል፤ ደኅንነቶቹ፣ ፍተሻው የላላበት የሚመስላቸው ቦታ በጋዜጣ ሽጉጥ ጠቅልለው ያሳልፉና ለአስተዳደሩ ፍተሻው ደካማ መሆኑን የሚናገሩበት አጋጣሚ አለ። ስለዚህ ጥበቃዎቹ ይህ እንዳያልፋቸው ሁሉንም አብጠርጥረው በመፈተሽ ያሳልፋሉ።
ይህ ዓይነቱ ፍተሻ፣ በሁሉም ሆቴሎች፣ ሕንፃዎችና አንዳንድ ካፍቴሪያዎች ሳይቀር እየተጠናከረ ነው። መልካም ነው፤ ለደኅንነታችን ሲባል የሚደረጉትን ጥንቃቄዎች በሙሉ ቢያታክቱም በቀና መቀበል ይኖርብናል። ችግሩ፣ ‘ደኅንነታችን በርግጥ በዚህ መንገድ ይጠበቃል?’ የሚለው ነው።
የዌስት ጌት ጥቃትን ብንመለከት የተፈፀመው በቡድንና በተደራጀ መሣሪያ ሲሆን በኤድና ሞልና ሌሎች የሚደረጉ ፍተሻዎች ግን በሠላማዊ መንገድ፣ በነጠላ ገብተው ጥቃት ለማድረግ ያሰቡ ሰዎችን ብቻ ለማስቆም እንጂ የተደራጁ ሰዎችን ለመግታት አያስችልም።
ጎረቤታሞቹ ጁፒተርና ራዲሰን ብሉ ሆቴሎች ግን እንዲህ ዓይነቱ ወሬ የመጣ ሰሞን የፍተሻ ድንኳኖቻቸውን ከሎቢዎቻቸው ውጪ በመትከል የተሻለ አማራጭ ተከትለዋል። ይህ የተደራጀ አደጋ ከመፈጠሩ በፊት ገና ከደጅ ለመከላከል ያስችላል።
ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንዲያገልግሉ ብቻ ሳይሆን በትምህርትና በተግባራዊ ልምምድ ለከፍተኛ ክብርና ማዕርግ እንዲበቁም ትሠራለች ገዳማት እና አድባራት የልማት ፈንድ ያቋቁማሉ /ምንጭ፡- ኢትዮ – ምኅዳር፤ ቅጽ 02 ቁጥር 51፤ ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 23 ቀን 2006 ዓ.ም./ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን ለሀ/ስብከቱ ባለድርሻ አካላት ለውይይት ያቀረበው የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነድ ካህናቱንና ምእመናኑን […]![]()
የሀገራችን የተቃውሞ ፖለቲካ ወደ አንድ ጠንካራ የለውጥ አማራጭነት እንዲሰባሰብ እና ገዥውን ፓርቲ የሚገዳደር ወሳኝ ኃይል ሆኖ እንዲወጣ ማስቻል የብዙ ቀና አሳቢ ኢትዮጵያውያን ፍላጎት እንደሆነ ይሰማኛል። እኔም ራሴን ይህ ዓላማ ከፍፃሜ እንዲደርስ ከሚፈልጉ ወገኖች ውስጥ እንደ አንዱ በማድረግ እቆጥረዋለሁ። ውህደት እንዲኖር መፈለግ አንድ ነገር ሆኖ፤ ማን ከማን ጋር ነው የሚወሃደው? የውህደት መስፈርቱን ምን መሆን ይኖርበታል? የሚለውንም […]
ESAT Radio Daily Broadcast to Ethiopia. Frequency Details: 7 days a week Short Wave (SW) from 8:00 pm to 9:00 pm (Local Ethiopian Time) 19 Meter Band 15355 kHz, 15360 kHz, 15365 kHz, 15370 kHz, 15380 kHz, 15385 kHz and 15390 kHz Download/Listen
ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል። የህወሃቱ ነባር ታጋይ፣ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ፣ በአሁኑ ጊዜ በም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመብራት …
ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ 1 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከቦርና ቢንቲዩ ግዛት መውጣታቸውን እና 650 የሚሆኑት ወደ ኢትዮጵያ ቀሪዎቹ ደግሞ ዋና ከተማዋ ጁባ መግባታቸውን ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ እንዳሉት ሁኔታዎች እየከፉ የሚሄዱ ከሆነ ቀሪዎቹን ዜጎች የማውጣት እቅድ አለ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በግጭቱ ውስጥ …