ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝቦችን ደህንነት ከመንግስታት ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው  ተቋም ለእንግሊዝ መንግስት የገቢዎቸና ጉምሩክ መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ “ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአለም ላይ የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ለሚታወቁ አገሮች ኮምፒይተሮችን፣ የሞባይልና የስካይፕ የስልክ ግንኙነቶችን እንዲሁም የኢሜል ልውውጦችን በርቀት ሆኖ ለመከታተል የሚያስችለውን ፊን ፊሸር ወይም ፊን …

ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦሚኒበስ አፕሮፕሬሽን ቢል 2014  በድንጋጌው  ለኢትዮጵያ ወታደራዊና ፖሊስ ሃይሎች የሚሰጠው ድጋፍ በቅድመ ሁኔታ ላይ እንዲቀመጥ ወስኗል። የኢትዮጵያ መንግስት የፍርድ ቤቶችን ነጻነት ካልጠበቀ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ካላከበረ፣ የሰዎችን የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና የሃይማኖት ነጻነትን ካላከበረ፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ተቋማት ካለምንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ስራቸውን እንዲሰሩ ካልተደረገ የአሜሪካ …

ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ በርካታ ነዋሪዎች ከ40 አመታት ላናነሰ ጊዜ የኖሩባቸውን ቤቶች እንዲለቁ መታዘዛቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ደግሞ ከ300 ያላነሱ ጉሊቶች ንብረታቸውን እየተቀሙ መደብሮቻቸው እንዲፈርስባቸው መደረጉ ታውቋል።ሰዎቹ ለረጅም ጊዜ ሲገለገሉበት የነበረውን ጉሊት እንዲያፈርሱ የተገደዱት …

አንዱዓለም ተፈራ
በተደጋጋሚ ትክክለኛ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማችሁ፤ አሁንስ በዛ! ማለታችሁ አይቀርም። እኔም ይኼው ዕጣ አጋጠመኝ። ታዲያ ዝም ማለቱ ወንጀል ሆነብኝና ይኼን ጻፍኩ። እንዲህ ነው የሆነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፤ ላለንብት የፖለቲካ ምስቅልቅል፤ መፍትሔ ፈላጊዎች የሩጫ ፊታቸውን ወደ ታሪክ አዙረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይድነቃቸው ከበደ Yedenekachew Kebedeድነቃቸው ከበደ
ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው። የፕሬዚዳንቱ የንግግር ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ
«አበው ሲተርቱ ላም ባልዋለበት ኩመት ለቀማ ይላሉ። ሰላም ጠላቱ ከሆነ የአገዛዝ ቡድን ጋራ በሰላማዊ ትግል ገጠሞ ሰለማዊ ድል አስመዘግባለሁ ብሎ ማሰብ ከሰላማዊ ጭንቅላት የሚፈልቅ ሰላማዊ አስተሳሰብ ነው ብዬ አላምንም። …ትግል ሱስ አይደለም። እንደ አቦል ቡና ሱስ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም Prof. Al-Mariamየዘገዬ ፍትህ እንደተነፈገ መቆጠር የለበትምን?

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)

በአህጽሮ ቃሉ አይሲሲ/ICC እየተባለ የሚጠራው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/International Criminal Court የኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታን ጉዳይ አስመልክቶ እያደረገ ያለው ተደጋጋሚ የፍትህ ሂደቱን የማዘግየት ስራ፣ በቀጠሮ የማሳለፍ እና “የውሸት መረጃዎች” እንዲሁም “የሀሰት ምስክሮች” በማቅረብ እንደገና የመታየት ዕድል ለመፍጠር እየተነገረ እና በተግባር እየተፈጸመ ያለው አጠቃላይ ወደኋላ የመንሸራተት ሁኔታ አንቅልፍ ባያሳጣኝም ከፉኛ አሳስቦኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …


ባለፈው ሰሞንታምራት ላይኔ ታስሮ ከርቸሌ ሲገባ ያየው የደርጉ ለገሠ አስፋውዓይኔ ነው ላይኔአለ› የሚል የፌስቡክ ቀልድ ሰምቼ በሳቅ ፍርስ ብዬ ነበር። ዛሬ አመሻሽ ላይ ቤቴ እየገባሁ ሳለ የሰማሁት ነገር ደግሞ ለገሠን በቀልዱ ላይ እንደገረመው ዓይነት አስገረመኝ።
ልማቱ በተፋጠነበት፣ አስተዳደሩ ኮሽ በማይልበት ~ ምን ነካው ቄሱ?
ሰፈሬየማርያም ጠበልየሚባል አለ፤ የማርያም ቤተክርስትያን ታቦት ትላንት ጠበሉጋ መጥቶ ያድርና ዛሬ ይመለሳል። ስለዚህ መንገዴ በሰው ተጥለቅልቋል። ዘማሪዎችና ከነሱ በጎላ ድምፅ ሰባኪው ሲያስተምር በቅርብ ርቀት ከታቦት ማደሪያው አካባቢ ይሰማኛል። በመሐል የሆነ ቃል የሰማሁ መሰለኝ። ጆሮ ሰጠሁት፣ አዎ ደገመው። ስለልማት እያወራ ነው። ስለየቱ ልማት?
ልማቱ እንዲህ እየተፋጠነ እንዴት አልናገርም?” ብሎ ጠየቀ። የሚመልስለት አልነበረም፤ ሰባኪ ለነገሩ ይናገራል እንጂ አያዳምጥም። ከዚያ፣ ልማቱ በተፋጠነበት፣ አስተዳደሩ ኮሽ በማይልበት፣ አምልኮ በማይከለከልበት…” እያለ ቀጠለ፤ ንግግሩ እሱን ግምት ውስጥ ከመጣል በላይ ፋይዳ ያለው ግን አይመስልም።ተመልሼ የዚህን ሰው ድምፅ ልቅረፅ ይሆን ወይስ ይለፈኝ› እያልኩ ወደፊት ማዝገሜን ቀጠልኩ። በተዳጋጋሚልማትየሚለው ቃል የሚጠቀስበት እና ተገንብቶ ያላለቀውባቡርሳይቀር ስሙ የተነሳበትስብከትእየራቀኝ እየራቀኝ መጣ። ኋላ ላይ ያሳሰበኝ ደግሞሰባኪው ካድሬ ሆኖ ነው ወይስ ካድሬው ሰባኪ ሆኖየሚለው ነው። ዛሬ ጠዋት ደግሞ በድምፁ ሌላ ሰባኪ እንደሆነ የለየሁት ሰው ሃይማኖታዊ ብቻ የሆነ ነገር ሲናገር እየሰማሁ አለፍኩ። ሆኖም የማታው አልወጣልኝም።
በዚህ ዓይነት ኢሕአዴጉም፣ ካድሬቄሶቹም ከቀጠሉበት ከዛሬ 10 ዓመት በኋላ የሚኖረው ስብከት እንዲህ ሊሆን ይችላል፡-
እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረ በኋላአዳም ብቻውን መሆኑ ልማታዊ አይደለም፤ ስለዚህ ልማታዊት አጋር እንፍጠርለትብሎ ሔዋንን ፈጠራት።
ከዚያም ልማታዊ ዴሞክራሲ* ይተገበርባት በነበረችው በኤደን ገነት በተድላ እና ደስታ እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው። ሆኖም አዳም እና ሔዋን የኒዮሊበራሊዝም አስተሳሰብ ተፀናውቷቸው አትብሉ የተባሉትን እፀበለስ እንደ ሳጥናኤል ባሉ የውጭ ኃይሎች ግፊት በመብላታቸው እና ቀዩዋን መሥመር በማለፋቸው ምድር ወደተባለ እስር ቤት ተጣሉ።
ይህ በሆነ በአምስተኛው ሺሕ አምስት መቶ ዓመቱ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደምድር በመላክ ልቡ በኒዮ-ሊበራሊዝም አስተሳሰብ የሸፈተውን አዳምን ሞቶ ወደገነት እንዲገባ መስዋዕትነት ከፈለለት፡፡ አዳምም ሰይጣን ከዚህ ጭንቅ ያወጣኛል፣ በፈጣሪ ላይ ጫና አድርጎ ያስፈታኛል ብዬ አምኜ በድፍረት ለፈፀምኩት ስህተት እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ ብሎ ለመነ፡፡
ሆኖም፣ አዳም መልሶ፣ መላልሶ ወደኒዮ-ሊበራሊዝም ፊቱን ማዞሩን አላቆመም ነበር፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር ሌላኛው ልጁን መሲሕ መለስ ዜናዊን ወደምድር ላከ፤ ቅዱስ መለስ ዜናዊም ስለዝቡ ደኅንነት በረሃ ለበረሃ እየተንከራተቱ ታንክ ተደግፈው መጽሐፍ አነበቡ፡፡ ከዚያም ለሕዝባቸው አብዮታዊ ዴሞክራሲን ሲያስተምሩ ኖረው ተሰዉ፡፡”


*
ልማታዊ ዴሞክራሲ ድኅረ መለስ ዜናዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው። ኢሕአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ›ን በ‹ልማታዊ ዴሞክራሲ› መተካቱን ተከትሎ ኢሕአዴግ የሚለውም ኢሕለዴግ በሚል ቢተካ ጥሩ  እንደሆነ በጥምቀት በዓል ላይ የተገኙ አንዳንድ ምዕመናን ተናግረዋል። (በነገራችን ላይ፣ ‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ› በዚህ ወር ሕትመቱ ተቋርጧል፤ ‹ልማታዊ ዴሞክራሲ› ሆኖ ይመለስ ይሆን?)

ይሄይስ አእምሮ

ለውድቀት ስኬት “የምሥራች!” ወይም “እንኳን ደስ ያለን!” የማይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ የደስታ ማብሠሪያ አባባሎች በአንደኛው ጽሑፌን መጀመር ቃጥቶኝ ነበር። ለማንኛውም ሀገራችን በማንኛውም ዘርፍ በገባችበት ውድቀትና ኪሣራ ምክንያት ልባችሁ ያዘነና ቅስማችሁ የተሰበረ ወገኖቼን “እግዚአብሔር ያጽናችሁ፤ የሀገራችሁን ትንሣኤም ፈጣሪ በአፋጣኝ እውን እንዲያደርግላችሁ የእግዚአብሔርን ልብ ያራራላችሁ” በሚለው የልመና ቃል ፈጣሪን እየተማጸንኩ ወሬየን ልቀጥል። ትንሽ በንዴት እንድትንጨረጨሩ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፤ መልካም መንጨርጨር!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሥርጉተ ሥላሴሥርጉተ ሥላሴ
ይድረስ ብለናል ከወደ ሲዊዘርላንድ ዙሪክ እኔና ብዕሬ ለሞገደኛው ብዕረ ተክሌ …
ጭራሽ ተበዳይ ብዙኃኑ ተወቃሽ ሆነ? ይገርም! ጡር የሚባል ነገር አለ። በፈጠረህ ጡር ፍራ የስሞተኛው ብዕር …

ሙሉውን አስነብበኝ …

በልጅግ ዓሊ
በ ርመን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን አቆጠጠር 1971  ምሮ የዓመቱ ምርጥ ቃል ይመረጣል። ይህ በየዓመቱ የሚደረገው ምርጫ አዲስ የተፈጠሩ አባባሎች  ወይም ቃላቶች አሮጌም ቢሆኑ በአለፈው ዓመት ውስጥ የአጠቃቀማቸው ሁኔታ ታይቶ የሚካሄድ ብሂል ነው። ለአሸናፊነት የሚበቃው ቃል በሕብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው ይሆናል። ምርጫው በኮሚቴ ዳኝነት ተሳታፊዎቹን ቃላቶች አወዳድሮ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘውን አሸናፊ ያደርጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሪያ እንድሪስ የተባለች ኢትዮጵያዊት ወጣት በ6 የሱዳን ወጣቶች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስትደፈር የሚያሳይ  ቪዲዮ ኢሳት  የደረሰው ሲሆን ፣ ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አረጋ ልጂቷ መደፈሩዋን አምነው ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ግን ከፍተኛ ባለስልጣኖች መፍቀድ አለባቸው በሚል ዝርዝር ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። …

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እየተባለ የሚጠራው አንጋፋው የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ባወጣው 129 ልዩ መግለጫ  ” የሚለቀቁትን ሳይጨምር በሰላም በር ፖሊስ ጣቢያ 198 ሰዎች ፣በአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤት 212 ሰዎች ” መታሰራቸውን እና  ከሚደርሰው መንገላታት እና ጥቃት ለማምለጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች …

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እ.ኤ.አ በ2013 ለሁለተኛው አጋማሽ ማለትም ከጁላይ እስከ ዲሴምበር የአስቸኩዋይ የእለት ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልገው 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ሕዝብ የሚውል 162 ሺህ176 ሜትሪክ ቶን ምግብ ውስጥ ማሙዋላት የተቻለው 69 በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑን፣ 6 ሚሊየን ያህል ስር የሰደደ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ቤተሰቦች በሴፍትኔት መታቀፋቸውን የግብርና ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ …

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ የምርምር ተቋም ውሳኔውን ታሪካዊ ብሎታል። በኮንግረሱ የጸደቀው ኦምኒበስ አፕሮፕሬየሽንስ ቢል እየተባለ የሚጠራው ህግ (Omnibus Appropriations Bill) አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ ዜጎችን ለማፈናቀል እንደማይውል፣ ይህንንም ተከትሎ ሰብአዊ መብቶች እንዳይጣሱ ያረጋግጣል። በኦሞ ሸለቆና በጋምቤላ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ነዋሪዎችን በማፈናቀል በሚደረገው ልማት ላይ የአሜሪካ እርዳታ ጥቅም ላይ …

ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች፤ የገቡት የተኩስ አቁም ስምምነት ገቢራዊ መሆኑ አጠያያቂ እየሆነ ነዉ። የደቡብ ሱዳን መንግሥትና አማፅያን የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ ርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ሲሆን ፤ ጦርነቱን ፈርተዉ ወደ ጎረቤት ሃገራት የተሰደዱት የደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች፤ በሃገራቸዉ ሰላም ይመጣል የሚል ተስፋ የላቸዉም።

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መረጃ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ኬንያ የሚገኙት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ሱሉብ አህመድና አሊ ሁሴን በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል። መሪዎቹ የታፈኑት ናይሮቢ ውስጥ ሲሆን፣ ከመንግስት ጋር ለሚደረገው ሶስተኛ ዙር ውይይት ዝግጅት እያደረጉ ነበር። ግንባሩ በመግለጫው ከዚህ ቀደምም የመንግስት የጸጥታ …

ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት ቶማስ ብሩኒጋርድ ” እስክንድር አፋኝ የፕሬስ ህግ ባለበት አገር በድፍረት ለመጻፍ በመቻሉ ሽልማቱ እንደተሰጠው ገልጸው፣ የኢትዮጵያ መንግስት እስክንድርን ጨምሮ በአሸባሪነት ታስረው የሚገኙትን ሰሎሞን ከበደ፣ ውብሸት ታየ፣ ርእዮት አለሙ እና የሱፍ ጌታቸውንም እንዲለቅ ጠይቀዋል። የፔን አለማቀፍ  ሽልማት ለፕሬስ ነጻነት ለሚታገሉት ጋዜጠኞች በእየአመቱ የሚሰጥ ሽልማት ነው። …

የኬሚካል ባለሙያ የሆነው እና የኣጥፍቶ ማጥፋት ጥቃቶችን በባቀድ እና በማቀነባበር የሚታወቀው ኣህመድ መሓመድ ኣሜ እስኩ ዱቅ በሚል መጠሪያው ይበልጥ ይታወቃል። ካለፈው ኣንድ ዓመት ወዲህ በተለይ በሞቃዲሾ እና በተለያዩ አካባቢዎች ከተሰነዘሩ የኣጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶች በስተጀርባ መኖሩ የሚነገርለት ኣሜ

የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ብራስልስ ላይ ከአውሮፓ ህብረት ኮምሽን ፕሬዝደንት ጆሴ ማኑኤል ባሮሶ እና ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኸርማን ቫን ሮምፖይ ጋ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

አጥንት ከሰዉነት ክፍል ጠንካራዉ አካል ነዉ። እንደ ጥንካሬዉ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ለጉዳት በሚዳረግበት አጋጣሚ ወደቀድሞ ይዞታዉ ለመመለስ ቀላል አይሆንም። አጥንት ከአካል እድገትና ከእድሜ መጨመር ጋ እያደር እያደገና እየጠነረ ሄዶ በጉርምስና እድሜ ማብቂያ ላይ እድገቱን ያቆማል።

አለማየሁ መሰለ

ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመ መሪያው ጽሁፍ ተከታይ ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የዓረና ትግራይ 3ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ በትግራይ ከተሞች ተከታታይ የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች በማካሄድ በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር ምንጩና መፍትሄው፣ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የፖለቲካ ራኢና ኣማራጭ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የማስቀረት ብቃት ለማሣየት አስመልክቶ ከህዝብ ለመምከርና በትግራይ ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ እቅድ ተይዞ ከመጀመርያው የጥቅምት ወር 2006 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ ለማካሄድ እንቅስቃሴ ተጀመረ። ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባው በቅደም ተከተላቸው በውቕሮ፣ በማይጨው፣ በዓብይ ዓዲ ከተሞች ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ሲካሄዱ ህዝብ ወደ ስብሰባው እንዳይመጣ የማደናቀፍ ተግባር በገዢ ፓርቲው የአከባቢ ካድሬዎች የታየ ቢሆንም ህዝቡ የማዳመጥ ፣አስተያየት የመስጠት መብቱን ለመጠቀም ባሳየው ፍላጎት በስብሰባው አዳራሽ በመገኘቱ ውጤታማ የህዝብ ስብሰባዎች ማካሄድ የተቻለ ሲሆን በሽረ ከተማ የህዝብ ስብሰባ ለማካሄድ ህዝቡ ወደ ስብሰባ ኣዳራሽ እንዲመጣ በሚገባ ከተቀሰቀሰ ህዝቡም ጥሪውን ኣክብሮ ወደ ኣዳራሹ በጥዋቱ እንደመጣ የከተማው ኣስተዳደርና በፓርቲው መዋቅር በተደራጀ ረብሻ የህዝብ ስብሰባው ሳይካሄድ መቅረቱን ይታወሳል፡፡ በዕቅዱ መሰረት ፓርቲያችን በምስራቃዊ ዞን ዋና በዓዲግራት ከተማ ጥር 18 ቀን 2006 ዓ/ም የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባ ለማካሄድ ኣዳራሽ እንዲሰጠን ለከተማው ኣስተዳደር ተጠይቆ ኣዳራሽ ተይዞኧል ኣይቻልም የሚል መልስ በመስጠታቸው እንግዲያው ስብሰባው በኣደባባይ እናደርገዋለን ሲባሉ ተመልሰው ኣዳራሽ ተፈቅዶላችኃል የሚል ምላሽ ተስጥቶን በስብሰባው ቀን ህዝቡ ተገኝቶ ዓረና ባዘጋጀው ኣጀንዳ እንዲመክር ለማስቻል የዓረና ከፍተኛ ወጣት ኣመራሮችና ኣባሎች በዓዲግራት ከተማና ኣከባቢዋ ተሰማርተው በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡ ሃሳብነ በነፃ የመግለፅና የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንቀሳቀሰ ነፃነት የሚያረጋግጡ መብቶች በመጠቀም በህዝባዊ ስብሰባው የሚመክርባቸው ኣጀንዳዎችና የስብሰባው ቀን፣ ስዓትና ቦታ የሚገልፀው ፅሑፍ በማደል ተሰማርተዋል፡፡
ለህዝቡ የሚታደለው ፅሑፍ የሚፈነዳ ቦንብ ኣልነበረም ወደ ህዝቡ ህሊና ዘልቆ የሚገባ ሓሳብ ብቻ ነበር፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ዓረና ትግራይ የመሬት ባለቤትነት የመንግስት መሆኑ ቀርቶ የህዝብ/ዜጎች እንዲሆን የመሬት ሊዝ ኣዋጅ እንዲሻር፣ ዜጎች ለመኖርያ የሚስፈልጋቸው ቦታ በሕገ መንግስቱ መሰረት ያለ ሊዝ የማግኘት መብታቸው እንደሚረጋገጥ፣ ለወጣት ሴቶችና ወንዶች በግፍ ለስደት መዳረግ ምክንያት የሆነው ብልሹ ኣስተዳደር በማስወገድ በሃገራቸው ሥራ የማግኘት መብታቸው እንደሚረጋገጥ፣ የሙያ ብቃት መስፈርት መሰረት ባደረገ መርህና የሙያና የኣካዳሚ ነፃነት በማረጋገጥ የመመህራንና የመንግስት ሠራተኞች ችግር ለማስወገድ እንደምንሰራ፣ በኣስገዳጅ የማዳበርያ ግዢ ለገዢው ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ብዝበዛ የተጋለጡና በእዳ ተጭነው ለጎስቋላ ኑሮ የተዳረጉት የትግራይ ገበሬዎች ችግር ለማስወገድ የማደባርያ ግዢ በውዴታ እንደሚሆንና ግብርናውና ገበሬው ለመደገፍ ለገበሬው ድጎማ ማድረግ እንደማያስፈልግ፣ ትምህርት ቤቶች ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ እንደሚሆኑ ዋና ስራቸው የፓርቲ ኣባል ምልመላና በትምህርት ቤቶች ለሚነሱ የመብት ጥያቂዎች ማኮላሸት የሆነ የህ.ወ.ሓ.ት (ኢህኣደግ) የ 1-5 የትምህርት ኔትወርክ እንደሚቀር፣ በትግራይ ህዝብ ደምና ኣጥንት የተገኘው ሙሉ በሙሉ የትግራይ ህዝብ ሃብትና ንብረት የሆነው ት.እ.ም.ት ከህወሓት መንጋጋ ኣውጥቶ ተጠሪነቱ ለክልሉ መንግስት በሆነ በነፃ የባለሙያ ቦርድ እንዲተዳደር በማድረግ የክልሉን ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት እነዲውል የማደረግ መሆኑ፣ በት.እ.ም.ት ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ሠርተው የሚያገኙት ትርፍ በትግሉ ለተጎዱ ታጋዮችና ሲቭል ኣርበኞች እንዲሁ የሻዕብያን ወራራ ለመመከትና ሃገራቸውን ለመጠበቅ ለጉዳት የተዳረጉ ኣርበኞችና ቤተሰባቸውን ለመደገፍ እንደሚውል፣በሕገ-መንግስቱ እንደተደነገገው ገዢው ፓርቲ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲያቆም የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ እነዚህ የአማራጭ ፖለቲካዊ ፕሮግራም ኣጀንዳዎች ሙሉ በሙሉ ሓሰቦች እንጂ የሚፈነዱ ፈንጂዎች ኣልነበሩም ! እነዚህ በጠራራው ፀሃይ ለህዝቡና ለህ.ወ.ሓ.ት ኣባላትና ደጋፊዎች ጭምር የቀረቡ ኣጀንዳዎች ነበሩ፡፡
እነዚህ ለህዝቡ የቀረቡ የአማራጭ ፖሊሲ ኣጀንዳዎች በሳዕሲዕ ፃዕዳ እንባ ወረዳ ዋና ከተማ ዕዳጋ ሓሙስ ለህዝቡ ሲታደሉ አንዲት ወረቀት ሳትቀደድ ኣንድ ሰው እንኳን ኣልቀበልም ሳይል ሁሉም በደስታ ተቀብሎ ለወጣት ኣመራሮቹ በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ሙሩቕና የዓረና የሥራ ኣስፈፃሚ ኣባልና የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ ኣቶ ዓምዶም ገ/ስላሴና መም/ ሃይለ ገብረፃዲቕ ያሳየው አክብሮት የሚደነቅ እንደነበረ ይመሰክሩለታል፡፡ በሻዕብያ የወደመችው የጎሎመኸዳ ወረዳ ዋና ከተማ የነበረችው ውብዋ ዛላንበሳን በመተካት የከተመችው የፋፃ ከተማ ነዋሪዎችና የኣካባቢው ገበሬዎች የስብሰባው ኣጀንዳ፣ ጊዜና ቦታ የሚገልፀው ፅሑፍ ሲታደላቸው ህዝቡ በሰላም ተቀብሎ እንዳስተናገዳቸው ” ቀድመን መመጣታችሁ ብናውቅ ኖሮ ሻይ ቁርስ ኣዘጋጅተን እነቆይ ነበር” በማለት በኣክብሮት እንደተቀበላቸው በኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅና የዓረና ትግራይ የድርጅት ጉዳይና የፅሕፈት ቤት ሓላፊ የሆኑት ኣቶ ስልጣኑ ሕሸ ና ኣቶ ሃይለኪሮስ ተፈሪ የህዝቡ ጨዋነት እንግዳ ተቀባይነትና ለኣማራጭ ሓሳብ ያለው ጥማት ይመሰክሩለታል፡፡ የዓዲግራት ከተማ ህዝብ ኣቀባበልም ተመሣሣይ ነበር፡፡
የህዝቡን የልብ ትርታ ያለማራቸው የዘኑ የገዢው ፓርቲ ኣስተዳዳሪዎች ዓረናና ህዝቡ የማይገናኙበት፣ የህዝቡ ስብሰባ የማካሄድበትና የዓረና ወጣት ኣመራሮች ሞራላቸው ተጎድቶ የሚያርፍበት እኩይ ብልሃት መዘየድ ጀመሩ፡፡ በዕዳጋ ሓሙስ የህ.ወ.ሓ.ት መታወቅያቸውን በማሣየት ለህዝቡ የስብሰባ ጥሪ የሚያድሉ የዓረና ኣባላትን ማቆም ጀመሩ፤ በፓርቲ መታወቅያ የመንግስት ሥራ መስራት ኣትችሉም ሲባሉ ሁሉም በእጃቸው ሁሉም በደጃቸው የሆነላቸው የህወሓት አባላቱ ወድያው ፖሊስ ጠርተው የዓረና ኣባላትን ኣቶ ዓምዶም ገ/ስላሴንና መም/ሃይለ ገ/ፃድቅን ወደ ፖሊስ ጣብያ በእስር ወሰዱ፡፡ አባላቶቻችን መታወቅያቸውን እንዲያሳዩ ተጠየቁ ኣሳዩ፡፡ (1) መመ/ሃይለ ገ/ፃድቅ የዓረና መታወቅያ ስለሌህ የዓረና ፅሑፍ ማደል ኣትችልም ተባለ (2) የሚታደሉት ፅሑፍ የዓረና ማህተም ስለሌለው ለህዝብ መሰጠት ኣትችሉም ተባሉ (3) ፅሑፍ እያደላችሁ የመኪና መንገድ ትዘጋላችሁ ኣሉ የህወሓት ካድሬዎቹ በድፍረት !? በስንት ንትርክ ለሚያጋጥማቹሁ አደጋ በራሳችሁ ሓላፊነት ተብለው ሥራቸውን ቀጠሉ፡፡ በራሳችሁ ሓላፊነት? ሲባል ብትደበደቡ ብትዋረዱ ብትገደሉ የሕግ ከላላ ኣንሰጥም ማለት ነበር፡፡ ያለምንም እንከን ህዝቡ በሰጣቸው ሞራል ስራቸውን በሚገባ ፈፅመው በደስታ ወደ ዓዲግራት ተመለሱ። ይህ የሆነው ዕለት ሓሙስ ጥር 15 ቀን 2006 ዓ/ም ነበር፡፡ በዓዲግራት ኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴና ኣቶ ኣብርሃ ደስታ እንዲሁም መም/ፍፁም ግሩምና መመ/ገዛኢ ንጉሰ ኢሉ፡፡ ሓሙስ ጥር 15 ቀን 2006 ዓ/ም የስብሰባ ጥሪ የሚገልፀው ፅሑፍ በዓዲግራት ማደል ማደል ተጀምረዋል፡፡ ዕለተ ዓርብ ጥር 16 ቀን 2006 ዓ/ም የዓዲግራት ከተማ ሰፊ በመሆኑ ኣቶ ስልጣኑ ሕሸ፣ ኣቶ ሃይለኪሮስ፣ መም/ገዛኢ ንጉሰ፣ መመ/ፍፁም ግሩም በቀበሌ 01 ሲንቀሳቀሱ ህዝቡ ምግብና ውሃ እየሰጠ የስብሰባው ጥሪ እየተቀበለ በክብር እንዳስተናገዳቸው ይመሰክራሉ።
ይህንኑ እውነት እየተከታተሉ ይታዘቡ የነበሩ የጥፋት መልእክተኞች የዓረና መመራርና ኣባላት ለማወክ ተዘጋጅተው ኖረው የስብሰባው ጥሪ ለህዝቡ የሚያድሉ ወደ ሆስፒታል ኣከባቢ ሲደርሱ የቀበሌ ካድረ የሆኑ ሴቶች ወረቀቱን ተቀብለው መቅደድ ጀመሩ፡፡ ዕድሜኣቸው ከ12-16 ዓመት እንደሆኑ የሚገመቱ ህፃናትም መሰብሰብ ጀመሩ ሆ! እያሉ መረበሽ ጀመሩ፣ ሴቶቹ መብታቸው በማለት አደፋፈሩ። የማወክ መብት? ህፃናቱ የተላኩ እንጂ የራሳቸው ኣጀንዳ የሌላቸው መሆኑ በተግባር ለመፈተን የወዳደቁ የስኳርና የቡና መጠቃለያ የደብተርና የጋዜጣ ፅሑፎች ሲሰጣቸው የዓረና ፅሑፍ መስሎአቸው ሳያዩት ተቀብለው ወድያው ይቀዱታል ልክ የስብሰባው መጥሪያ ፅሑፍ ተቀብለው እንደቀደዱት፡፡ ለህፃናቱ መብታችሁ ነው እያሉ የሚያጅቡ ትላልቅ ወንዶችና ሴቶችም ነበሩበት ። ህፃናቱ ሁሉም ሊባል በሚችል ሲጋራ ያጤሳሉ ፣ ስትቀርባቸው መጠጥ መውሰዳቸው የሚሳውቅባቸው በእጅጉ ጠጅ ይሸቱ ነበር። የአከባቢው ሰዎች በሰጡት መረጃ መሰረት የተለያየ ሱስ ተጠቃሚዎች ለመሆናቸው በከተማው ፖሊስ የሚታወቁ ናቸው።በዚህ የውንብድና ተግባር በዓረና ከፍተኛ ወጣት አመራሮችና አባሎች የአካልና የሞራል ጉዳት ተፈፅሞአል ፣ የቀበሌ ሴቶች በፌስታል አፈር እያቀበሉ ህፃናቱ በአዓረና አባላት በላያቸው ላይ አፈር በማፍሰስና እክታ በመትፋት አሳፋሪ ወንጀል ሲፈፀም በዓዲግራት ከተማ የሚገኙት የከተማው አስተዳደርና ፖሊስ የዞኑ አስተዳደርና ፖሊስ መብታቸው ነው እያሉ ያሳዩት የወንጀል መተባበር አሳፈፋሪ ተግባርና መንግስታዊ ውንብድና የሚያሰኝ ነው።
በዛው ጨዋ ህዝብ ፊት እነደዚህ ያለ የውንብድና ተግባር ተፈፀመ፡፡ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ተግባሩ የተቀነባበረው በዞኑ በከተማው መስተዳድር ስለመሆኑ ኣስተዳዳሪዎች፣ ፖሊስ ያሳዩት ተግባራቸው ይመሰክርላቸዋል፡፡
በነዚህ ጥቂት ቀናት የዞኑ መስተዳድር የፀጥታ ኣደጋነቱን በተግባር ሲያስመሰክር ህዝቡ ደግሞ የሕግ ኣስከባሪነት ሚናው መወጣቱን በገሃዱ ዓለም ቁጭ ብሎ ታይቶኣል፡፡ መስተዳደሩ በራሳችሁ ሃላፊነት የህግ ከለላ ኣንሰጣችሁም ሲል በዓረና ኣመራሮችና ኣባላቶች ሊያወርዱት የከጅሉት ወንጀል ጠቋሚ ነበር። የህዝብ ስብሰባው እንዳይካሄድ የተፈጠረው ውንብድና የመስተዳድሩ እጅ እንዳለበት የሚያሳየው –
የዞኑና የከተማው መስተዳደርና ፖሊሲ በኣባሎቻችን የተፈፀመውን በዓይናቸው ያዩት ወንጀል ማጠራትና ማስቆም ሲገባቸው ፍርደ ገምድል እንዲሉ በሞባይል ስልክና፣በካሜራ ቀርፃችሁናል ህፃናቱም ቀርፃችሁኣል ትፈተሻላችሁ ብለው የሁሉም አባሎቻችን ሞቫይልና ካሜራ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ መቦርበራቸው፣
በተደራጀና በህፃናት ከለላ የተደበቀ የወንብድና ተግባር ሲፈፀም መስተዳደሩና ፖሊሱ እያዩ በጠራራ ፀሃይ በኣባላቶቻችን ላይ ኣሰቃቂ ግፍ እነዲፈፅሙ ሙሉ ፍቃድ ማሳየታቸው የሚያስቆጥራቸው በመሆኑ ፣
በሕግ የተቋቋመ ፓርቲ የቆመለትን ራኢና ፖሊሲ ለህዝቡ ለማስተዋወቅና በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የሚገራበት መንገድ ከህዝቡ ለመምከር ያደረግነው ጥሪ እንዳይሳካ ለማወክ የተላኩ ህፃናት መብታቸው ነው እያሉ የሕገ-ወጥ ተግባር ከለላ መስጠታቸውና ለባሰ ጥፋት እንዲዘጋጁ ማበረታታቸው የወንጀሉ ተሳታፊ የሚያደርጋቸው መሆኑን
የከተማ ፖሊስ የኣረና ኣባላት ባረፉበት ሆቴል ማታ አልጋ በያዙበት ሆቴል ከምሽቱ 4፣00 ሰዓት ተገኝቶ እሁድ ለሚካሄደው ስብሰባ የእግር ኳስ፣ የብስከሌታ ውድድር ስላለ በቂ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለቱ ስብሰባው እንዳይካሄድ በማደናቀፍ ምክንያት መሆኑን
በተደራጀ ወንብድና የኣካል ጉዳት የደረሰባቸው የኣረና ኣባላት በከተማው ጤና ጣብያ ተመርምረው የራጀ ምርመራ እንደሚያስፈልጋቸውና ሆስፒታል እንዲወሰዱ በሃኪም የተሰጠ ትእዛዝ በፖሊስ ኣለመፈፀሙን፣
የተፈፀመው የወንብድና ተግባር ለማድበስበስ በሃሰት ክስ፣ በኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴና መም/ፍፁም ግሩም የተቀነባበረው ወንጀላ እየተፈፀመ መሆኑን ነው ።
ህ.ወ.ሓ.ትና መስተዳድሩ ወደዚህ የፖለቲካ ቅሌት የሚገፋፋቸው ያለው በዓረና የኣማራጭ ፖሊሲ ልዕልና መርበትበቱንና ወደ እራቆቱ የወጣ በጠራራ ፀሃይ የኣማራጭ ፓርቲ ወጣት መሪዎችን በማፈን ማንበርከክ መምረጡንና የትግራይ ህዝብና ወጣት ልጆቹ የከፈሉት መስዋእትነት ጭራሽ ከምድረ ትግራይ ጠራርጎ ለማጥፋት መቑረጡን የሚያሳይ እኩይ ተግባር በመሆኑ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የተቃውሞ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለትግራይ ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያሰማል፡፡ ዓረና ትግራይ የትግራይ ህዝብ የከፈለው የ17 ዓመታት የትግል ዘመን ብህ.ወ.ሓ.ት ተቀብሮ እንዳይቀር በማደስ የተነሳ ፓርቲ እንደመሆኑ በህ.ወ.ሓ.ት የሽብር ተግባር የማይታጠፍ መሆኑን በማረጋገጥ በህዝባችን ፊት የሚከፈለውን ሁሉ መስዋእትነት እየከፈልን ብፅናት የምንቀጥልበት መሆኑን ለመግለፅ ይወዳል፡፡
የዓዲግራት ከተማ ወጣቶች የተደረጁ ኣሸባሪ ወንጀለኞችን በመመከት የኣባለቶቻችን ህይወት ለመታደግ ያሳየው ድፍረት እንዲሁም የዕዳጋ ሓሙስ ከተማ ነዋሪዎችና የፋፂ ከተማ ነዋሪዎች ዓረና ለህዝቡ የቀረበው ጥሪ በማክበር ያሳያችሁት ኣክብሮትና ፍላጎት ኣክብሮታችን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ዓረና ትግራይ ፓርቲ በዚሁ የወንብድና ተግባር ሳይንበረከክ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ህዝብ በኣጠቃላይና በዓዲግራትና ኣከባቢዋ የህዝብ ስብሰባ በመጥራት ከህዝቡ መምከር በፅናት እንደንቀጥልበት በእርግጠኝነት ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
ጥር 18 ቀን 2006 ዓ/ም
መቐለ

ምንሊክ ሳልሳዊ:-ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው::ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡

«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

አክራሪነት አሉታዊ ትርጉም ሲኖረው የራስን እምነትና አመለካከት በሌሎች ላይለመጫን መሞከር ነው፡፡ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር ራሱ አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት የፖሊቲካ ገጽታ ያለው ነው፡፡ ኾኖም ግን ሃይማኖትን ማጥበቅ አክራሪነት አይደለም፡፡ሃይማኖት ፍጹም እውነታን በፍጹም እምነት ስለሚቀበል ከሌሎች ግላዊ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ የሃይማኖት መገለጫዎችን መጠቀም የዚያን ሃይማኖት ጥልቀት የሚያሳይ እንጂ እንደ ችግርም የሚወሰድ ወይም አክራሪነት ሊኾን አይችልም፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተአምልኮን መፈጸም ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባልአይችልም፤» ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡

የአክራሪነትና የአጥባቂነት ፅንሰ ሐሶቦች በጥሩ ኹኔታ ተለይተው ተገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች ወያኔም ለይስሙላ የገለበጣቸው ሰነዶቹ አክራሪነትንና አጥባቂነትን በአግባቡ ለይተውና ተንትነው ያስቀምጣሉ፡፡ በዚሁ መሠረትአጥባቂነትን፣ ‹‹የግል ሃይማኖትን ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሳይንጠባጠብ ሁሉንም ትእዛዛት መፈጸም ነው፤» በማለት ሲፈታው አክራሪነትን ደግሞ፣ «ከራስ እምነት ወጥቶ ሌላውን መተንኮስና የሌሎችን ሃይማኖት መኖር አለማመንና አለመፍቀድወይም ሌሎቹን አስገድዶ የራስ እምነት ተከታዮች ለማድረግ መጣር ነው፤» ይላል፡፡ በተግባር ላይ አለመዋሉ እና በጣልቃ ገብነት መተርጎሙ ጉዳት አመጣ እንጂ::

ከዚህ ብያኔ ስንነሣ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም ከርሱ ውጭ የኾኑትን የሌሎቹን መኖር የማይቀበልና ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አስገዳጅ እስከኾነ ድረስ እርሱን አክራሪ ማለት ይቻላል፡፡መብትን መጠየቅ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መሸሽ አክራሪነት አይደለም:: በዚህ መልኩ አክራሪው ይህንኑ ድርጊት ሊፈጽም የተነሣውን ቡድን ብቻ እንጂ «አክራሪው ቡድን» የወጣበትን/የተገኘበትን ቤተ እምነት ሊወክል አይችልም፡፡ ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ የአክራሪ ክርስትና እና እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም፤ ለሌላው ቤተ እምነትም እንዲሁ፡፡ ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ

ዓረና ትግራይ ራኢዩን የትግራይ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ በማድረግ ወደፊት ይገሰግሳል እንጂ በህወሓት የሽብር ተግባር አይታጠፍም !!! (ከዓረና ትግራይ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ) የዓረና ትግራይ 3ኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ተግባራዊ ለማድረግ በትግራይ ከተሞች ተከታታይ የህዝብ ፖለቲካዊ ስብሰባዎች በማካሄድ በክልሉ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር ምንጩና መፍትሄው፣ የዓረና ትግራይ ፓርቲ የፖለቲካ ራኢና ኣማራጭ ያንሰራፋው ብልሹ ኣስተዳደር የማስቀረት ብቃት […]

በጀርመን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን አቆጠጠር 1971 ጀምሮ የዓመቱ ምርጥ ቃል ይመረጣል። ይህ በየዓመቱ የሚደረገው ምርጫ አዲስ የተፈጠሩ አባባሎች ወይም ቃላቶች አሮጌም ቢሆኑ በአለፈው ዓመት ውስጥ የአጠቃቀማቸው ሁኔታ ታይቶ የሚካሄድ ብሂል ነው። ለአሸናፊነት የሚበቃው ቃል በሕብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው ይሆናል። ምርጫው በኮሚቴ ዳኝነት ተሳታፊዎቹን ቃላቶች አወዳድሮ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘውን አሸናፊ ያደርጋል። በዚህ ውድድር ማንም ሰው ሊያሸንፍ […]

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን መልካ ሶዳ ወረዳ ኩሮ ነጌሌ ቀበሌ በቦረና እና በጉጂ ኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት ከ8 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማጣታቸውን የፍኖት ነፃነት ምንጮች አስታወቁ፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱ ምንም አይነት የማረጋጋት እርምጃ አለመውሰዱ ጉዳቱን እንዳባባሰውም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ የአካባቢው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳስታወቁት ለጊዜው መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም በተነሳ የሁለቱ […]

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ፤ ፓርቲያችን አንድነት በአፅንኦት እንደሚያምነው የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የዴሞክራሲ ዕጦት ሰለባ ነው፡፡ ስርዓቱ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል እንደሚያደርገው በትግራይም ሰብዓዊ መብት ይረግጣል፣ ፍትህ ይደፈጥጣል፣ በካድሬዎች ይደበደባል፣ ይንገላታል፣ እንዲሰደድ ይደረጋል፡፡ ስርዓቱና በስርዓቱ ውስጥ የደላቸው ሹማምንት በስሙ ከመነገድ በዘለለ ዋጋ የተከፈለበትን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ዘርግቶ ተጠቃሚ ማድረግ አልቻለም፡፡ ህወሓት/ኢህአደግ ክልሉን እንደዋና […]

አዲሱ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ አዲስ መንግሥት መሰረቱ ። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የተሰየሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሬ ዛባያኬ ባቋቋሙት በአዲሱ ካቢኔ ሰባት ሴቶች ይገኙበታል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ2 ቀናት በፊት ሲሾሙ ፕሬዝዳንት ካትሪን ሳምባ ፓንዛ ደግሞ ባለፈው ሀሙስ ነው ቃለ መሃላ የፈፀሙት ። ፕሬዝዳንት ሳምባ ፓንዛ

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባሩ የቀድሞው የህወሀት ታይ እና አሁን የአረና ከፍተኛ አመራር አቶ አስገደ ገብረስላሴ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጻፍ የሚታወቀው ና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር አብረሃ ደስታ እንዲሁም የፓርቲው የአመራር አባል አቶ አምዶም ገ/ስላሴ እሁድ እለት ከአዲግራት ህዝብ ጋር ለመነጋገር ወደ ስፍራው ቢያቀኑም በከተማው የደህንነት ፣ የፖሊስና የቀበሌ ሹሞች የሚመሩ ወጣቶች …

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞችና በተዋረድም ከህዝቡ ጋር እተደረገ ባለው የሽብርተኝነት ህግ ውይይት፣  ነዋሪዎች ጥላቸውን እንኳን ማመን እንደሌለባቸው በአሰልጣኞች እየተነገራቸው ሲሆን፣ በስልጠናው ላይ የተካፈሉ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች፣ ስለሽብረተኝነት ልንማር ሂደን ተሸብረን መጣን ሲሉ ተናግረዋል። በመንግስት  ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የማሰልጠኛ ሰነድ ኢሳት እጅ የገባ ሲሆን፣ …

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 16፣ 2006 ዓም ባስቻለው ችሎት በእነ አቶ ደፋሩ ዶሬ መዝገብ የተከሰሱ 13 ሰዎች በሙሉ በ2 አመት ከ9 ወራት እስር እንዲቀጡ ወስኗል። በውሳኔው መዝገብ ላይ እንደተመለከተው እስረኞቹ የተፈረደባቸው “ እኛ ወይም ቁጫ የጋሞ ብሄረሰብ አይደለንም በሚል ህዝብን አነሳስታችሁዋል፣ ህገወጥ ስብሰባ አድርጋችሁዋል፣ …

ጥር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ባልመረጥነው መጅሊስ  አንተዳደርም!  ያላመንንበትን የሀይማኖት አስተምህሮ አንቀበልም! የህዝበ-ሙስሊሙ የትምህርት ተቋም የሆነው አወሊያ ትምህርት ቤት  በገለልተኝነት ይተዳደር” የሚሉ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳታቸው የ አሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው የሙስሊም አመራሮች ወደ ወህኒ ከወረዱ ከሁለት ዓመታት በላይ ተቆጠሩ። ለሁለት ዓመታት ከዘለቀው የፍትህ ሂደት በሁዋላ  በቅርቡ  ለብይን  በተቀጠረው  ችሎት ላይ በብዘዎች …

ቀድሞ የግብጹ መሓመድ ዓሊ ንጉሳዊ ግዛት አካል የነበረው የሱዳን ምድር እጎኣ በ1956 ዓም ነጻ መንግስት መሆኑን ተከትሎ በኣገሪቱ በተቀሰቀሰው የመጀመሪያው የሱዳኖች የእርስ በርስ ጦርነት ምክኒያት ደቡብ ሱዳን ያኔ የራስገዝ ኣስተዳደር ለመሆን በቅታ ነበር። በ 1972 ዓም።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በመባል የሚጠራው ቡድን ፤ ስለ ኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት የቀረበዉን ረቂቅ ህገ-መንግስትን በተመለከተ ዋሽንግተን ዲሲ ይዩናትድ ስቴትስ ውስጥ ህዝባዊ ዉይይት አደረገ።

ሜንሽን ፎር ሜንሽን፤ ሰዎች ለሰዎች የተሰኘዉ ምግባረ ሰናይ ድርጅት፤ በ13 ዓመታት ዉስጥ በሰሜን ሸዋ በተለይ በመረሃቤቴ አና በሚዳ ወሪሞ አካባቢዎች ያከናወናቸዉን በርካታ የገጠር ልማት ሥራዎች ለተጠቃሚዉ ህብረተሰብ አስረከበ ።