በ2008 አንድ ሆነን በህዝባዊ ዓመጽ ሃገር አጥፊውን ቡድን ማስወገድ በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እቅድ ውስጥ ሊገባ እና ሊተገበር ይገባል።

በአዲሱ አመት ምን አቅደዋል????? Fitsum Ze Ethiopia
ሁለትሺ ሰባት አልቆ ተራውን ለሁለትሺስምንት እያስረከበ ይገኛል። ታዲያ ይህዓመት ለኛ ለኢትዮጵያውያን ምንይዞ ይመጣ ይሆን? መልሱን ለሱ ትተን እኛ በራሳችን በወያኔ እኩይሴራ አንድነቷ ተናግቶ ህልውናዋ ተደፍሮ ስላለችው ስለሃገራችን፤ በስርዓቱጨቋኝ አገዛዝ ስለሚሰቃየው ለህዝባችን ፤በአገዛዙ ትውልድ ገዳይ ፖሊሲ እየተፋ ላለው ወጣቱ (ተተኪ) ትውልድ፤ ለሃገራቸው በተቆረቆሩ በየእስር ቤቶቹ ፍዳውን ስለሚያየው ወገናችን ፤በሃገራቸው ሃገራቸውን እና ህዝባቸውን መጥቀም ሲችሉ በየሃገሩ ተገፍተው እና ተሰደው ስለሚገኙ ወገኖቻችን፤ ኑሮን ለማሸነፍ ብለው በየዓረብ ሃገሩ ስለሚንገላቱ ወገኖቻችን በየበረሃው በየባህሩ ሰለሚሰቃዩ ወገኖቻችን፤ ወያኔ ባስቀመጠው ከፋፍለህ ግዛ ሰለባ ለሆኑትበዘር ተለክፈው ከእግዚያብሄርም ከህብረተሰቡም ተጣልተው የሚያደርጉትን ለማያውቁት ወገኖቻችን እንደወገንነትዎ በአዲሱአመት ምን መፍትሄ አስበውላቸዋል?

እንደኔ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብም እንደሚያምነው መፍትሄው አንድ እና አንድ ነው እሱም ለዚህ ሁሉ መከራ ስቃይ የሃገር ጥፋት መንስኤ እና ተጥያቂ የሆነውን አሁን በስልጣን ላይ ያለውን የወያኔ ቡድን አስወግዶ ህዝብን የሚወክል እና በህዝብ የተመረጠ ህዝባዊ መንግስት ለመመስረት የሚደረገው ትግል ላይ መረባረብ ነው። ያለምንም ልዩነት አንድ በመሆን እራሳችንን ለመስዋእትነ ት በማዘጋጀት በመደራጀት ህዝባዊ
ዓመጽ በማድረግ ሃገር አጥፊውን ስርዓት ማስወገድ ብቻ ነው። ለዚህ ሃገራዊ ተግባር የሚተጉትን ክፍሎች ማገዝ እና መተባበር ነው።

ይህ ሲሆን ለሃገራቸው የተሰዉ ሰማእታት የነጸጋየ ደብተራው እና ጓዶቹ ትግሌን አደራ ብለው ያለፉት የነወጣት ሳሙኤል ለማ እና ሌሎቹም ስርዓቱን ለመሸሽ እና ኑሮን ለማሸነፍ በየበረሃው የቀሩ ወገኖቻችን ነፍስ ትደሰታለች ህዝባችን ከስቃይ ይላቀቃል ሃገር ትድናለች በሃገራችን እንደባለሃገር እንኖራለን በያለንበት ተከብረን እንኖራለን ባንዲራችን ከለማንም ከልካይ ትውለበለባለች ህዝባችን በፍቅር በአንድነት አብሮ ይኖራል።

ስለዚህም በ2008 አንድ ሆነን በህዝባዊ ዓመጽ ሃገር አጥፊውን ቡድን ማስወገድ በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እቅድ ውስጥ ሊገባ እና ሊተገበር ይገባል።