ፀረ ሽብር የተባለውን ደንብ ነቅፈናል። አንቀጹ የሚያሻማ፣ ግልጽ ባልሆኑ አንቀጾች የተቀመጠ ነው። ሰዎች በዚህ ሳቢያ ራሥረዋል። ስለሆነም የህግ አውጪው ፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው ዘርፍ ፤ ነጻነት በተሃድሶ ለውጥ ሊቀየር ብለን እናስባለን ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች የታሣሪዎች ይዞታ እንዲታይ የሚል አቋም ነው ያለው ።

ዘንድሮ 50ኛ ዓመቱን በማሰብ ላይ የሚገኘው የነጻ ነጻ የአፍሪቃ መንግሥታት ማኅበር –የአፍሪቃ ኅብረት ፣ እንደ ኤኮኖሚውና ንግዱ ግንኙነት ፣ ከአውሮፓው ኅብረትም ሆነ ከአባል ሃገራቱ ጋር በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ የሚያደርገው ትብብር ምን ይመስላል?

ውሳኔው በአዲስ አበባና በጎንደር ከተማ ተፈናቅለው ወደ እሥራኤል ለመግባት በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቤተ እስራኤላውያን ቤተሰቦችን አስጨንቋል ።

የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ፀሃፊ የፀረ ሽብሩ ህግ ይሰረዝ የሚል ድምፅ ለማሰባሰብ አዲስ አበባ ውስጥ የተንቀሳቀሱ 51 አባላቱ ያለአንዳች ምክንያት ታስረው በዋስ መለቀቃቸውን ተናግረዋል ።

ናይጀሪያ የሱዳኑን ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽርን ለዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ይዛ ባለመስጠቷ እየተወቀሰች ነዉ። ፕሬዝደንት አልበሽር በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ናይጀሪያ ላይ በተካሄደዉ የአፍሪቃ ኅብረት የHIV/AIDS ጉባኤ ላይ መገኘታቸዉን የአገሪቱ የመብት ተሟጋቾች ተቃዉመዋል።

ከተፈሪ በላይ (የዲሲ ነዋሪ)

ይህን መጣጥፍ እንዳዘጋጅ የገፋፋኝ ጋዜጠኛ አቶ ክንፉ አሰፋ በኢትዮ ሚድያ በኢትዮጵያ ዛሬና EMF ድረ ገጽ ላይ ዲሲን ለቀቅን አስመልክቶ “ዲሲ 2013” በሞል ርእስ የጻፈውን ጽሁፍ ነው። ከጽሁፉ መግነቢያ ላይ ተገለጸወን ሃተታ ማለትም ፈረንጆች በአገራችን ኢትዮጵያ በቆዩ ቁጥር የሚጽፉት ያጣሉ የሚልወን አባባል ባልቀበለውም ወግ ለማጣፈጫ እንደገባ ቅመም ልቁጠረውና ልለፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከአርባ ሁለት በላይ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች፣ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ዛሬ እንደታሰሩ ፍኖት ነጻነት ዘገበ። ከታሰሩት ዉስጥ ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ አብዛኞቹም ወጣቶች ናቸው። በጎንደርና በደሴ የተደረጉ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፎችን ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ ከተማ 23ቱ ወረዳዎች ያሉ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ፣ በተመሳሳይ ሰዓት በወረዳዎች ሁሉ በመሰማራት፣ ሕዝቡን በማነጋገር ፔቲሽኖች ሲያስፈርሙ ነዉ […]

የዛሬ ሃያ ዓመት ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ እንደተመረቅኩ የመምህርነት ሥራዬን የጀመርኩት እነዋሪ በምትባል በሰሜን ሸዋ ውስጥ ከምትገኛና ከአዲስ አበባ 165 ኪሎ ሜትር በምትርቅ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ እነዋሪ ከመርሐቤቴ እስከ ዜና ማርቆስ የሚኖረው ቆለኛና ደገኛው ጅሩዬ የሚገናኙባት የቀለጠች የገበያ ከተማ ናት፡፡ በተለይም በፍራፍሬ ምርቷ ትታወቃለች፡፡ ኤፍሬም እሸቴ የእነዋሪን ሙዝ ‹ከማጠሯ መጎጠሯ› እያለ ይቀልድባት ነበር፡፡
ከእነዋሪ እየተነሣሁ እስከ ዠማ ወንዝ ድረስ ለሠርግም፣ ለንግሥም ቆላውን እወርድ ነበር፡፡ ገበሬዎቹ ከቆላው ይመጡና እኔን በቅሎ ላይ አውጥተው በትከሻቸው ላይ ውጅግራ ጠበንዣቸውን ደልደል አድርገው ተሸክመው የጋቢያቸውን ግማሽ ጠቅልለው አናታቸው ላይ በማስቀመጥ፣ ከግራና ከቀኝ በቅሎዋን እየነዱ፣ ያንን እንደ ያሬድ መዝሙር በጆሮ የሚንቆረቆረውን ወጋቸውን እያወጉ፣ እንደ ዝንጀሮ ገደሉን በኩራት ይወርዱታል፡፡ ተረታቸው፣ ቀረርቷቸው፣ ፉከራቸው፣ ዘፈናቸው፣ የታሪክ ትረካቸው፣ ስለ ጀግኖቻቸው የሚገጥሙት ግጥም አሁንም በጆሮዬ እንደ መስክ ነፋስ ሲያልፍ ይሰማኛል፡፡ 

አንድ ቀን ታድያ አይዋ ሰጥ አርጌ የሚባሉ ቆፍጣና ገበሬ አብረውን ወደ ዠማ ሲጓዙ ታች በሌ ስለሚባል ሽፍታ አወጉኝ፡፡ ታች በሌ በተለይ በሞረቶች ዘንድ በጣም የታወቀ አስቂኝ ሽፍታ ነው፡፡ አንድ ሰው ያላሰበበትን፣ ያልተዘጋጀበትንና ያለ ዐቅሙ የሆነውን ነገር ጀመረ ሲባል ዠማዎች ‹‹ምን የእርሱ ነገርኮ የታች በሌ ሽፍትነት ነው›› ይሉታል፡፡ አንድ ሰው በስሜት ብቻ ተነሣስቶ እንዴው የጀብደኛነትን ሥራ ሲሠራ፣ አንድን ነገር አስቦ ከመሥራት ይልቅ ከሠራ በኋላ ሲያስብ ዠማዎች እንዲሁ ‹ታች በሌ› ይሉታል፡፡ ለምን?
ታች በሌ የዠማ ሰው ነው፡፡ የኖረው ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመት በፊት በሸዋው አስፋ ወሰን ዘመን ነው  አሉ፡፡ በዚያ ዘመን ሞረትን ይገዙት የነበሩት ጥዱ የተባሉ ኃይለኛ በላባት ነበሩ፡፡ እንዲያውም ጥዱና አስፋ ወሰን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩም የሚፈታተኑም ኃይለኞች ስለነበሩ ግጥሞቻቸው ዘመን ተሻግረው ደርሰውናል፡፡ አስፋ ወሰን ሞረትን ማስገበር ስለፈለጉ
ለሞፈር ለቀንበር የሚሆነኝን
ሳልቆርጠው አልቀርም ዘንድሮ ጥዱን፤
ብለው ለአዝማሪ ነገሩ አሉ፡፡ ይህን የሰሙት ጥዱም
አስፋ ወሰን ይፋት ጠንክረው ይረሱ
ሞረት ጥዷል ብለው ከሚመላለሱ፤
ብለው መለሱላቸው ይባላል፡፡
ጥዱ ኃይለኛ አስገባሪ፣ አስጨንቆ ገዥ ነበሩና ብዙ ገበሬዎችን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው፣ እንደ ጫማ ረግጠው ይገዙ ነበር፡፡ ከተገዥዎቹ ገበሬዎች አንዱ የነበረው ታች በሌ መረረው፡፡ በልጅነቱ በሰሜን ሸዋ በረሃዎችና ጫካዎች ሸፍተው ገዥዎችን ስላስጨነቁ ሽፍቶች እየሰማ ነበርና ያደገው መሸፈት አማረው፡፡ አንድ ቀን ከብት ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መሸፈቱን ነግሮ የአጎቱን ቁመህ ጠብቀኝ መንትፎ ሸፈተ፡፡ ሸፍቶም ጫካ ገባ፡፡ አገሩም ‹ታች በሌ ሸፈተ› እያለ ከሚዳ እስከ እነዋሪ አወጋ፡፡ አንዳንዱ አደነቀ፤ ዘፈነለት፤ አንዳንዱ ተጠራጠረ፣ አንገቱን ነቀነቀበት፡፡ ‹በምን ልቡ ነው የሸፈተው›› ያሉም ነበሩ፡፡ ጥዱም እገለዋለሁ ብለዋል ተባለ፡፡
ታች በሌ ዠማ ወንዝ በረሃ ውስጥ ወርዶ አንድ ጫካ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ መጀመሪያ ስሙ በድፍን ሸዋ ሲገንን፣ ስሙ በየሠርግ ቤቱና በየድግስ ቤቱ የዘፈን መቋጠሪያ ሲሆን እየታየው ልቡ በደስታ ሞቆ ነበር፡፡ ዋል አደር ሲል ግን ታች በሌን ጥያቄዎች ጭንቅላቱን እየሞሉ ያስጨንቁት ነበር፡፡ ለመሆኑ በቂ ስንቅ ይዘሃል? የሸፈትከውኮ በጀግናው ጥዱ ላይ ነው፤ ለመሆኑ በቂ ጥይት ታጥቀሃል? ለመሆኑ ቢመጡብህ የምትሸሽበት የማምለጫ ስርጥ መርጠሃል? አንተ መንደርህ እያለህ አንድ ቆቅ እንኳን አድነህ የማታውቅ እንዴት ጥዱን ለመዋጋት ጫካ ገባህ? ለመሆኑ ዛሬ የታጠቅከውን ቁመህ ጠብቀኝ ተኩሰህበት ታውቃለህ? ቢበላሽ ማን ይጠግንልሃል? ከዛሬ በፊት ለመሆኑ ጫካ ውለህ አድረህ ታውቃለህ? ከአውሬ ጋር ታግለህ ታውቃለህ?
እነዚህ ጥያቄዎች ጭንቅላቱን ሲወጥሩት ታች በሌ መልስ አልነበረውም፡፡ የዠማን በረሃ ወደ መርሐ ቤቴ ሲያልፍበትና ወደ ጅሩ ሲወጣበት እንጂ ውስጡ ገብቶ ሥር ማንሥሩን አይቶት አያውቅም፡፡ እንዲያውም አሁን ሲያስበው ትንሽ ፍርሃት ሳይኖርበት አይቀርም፡፤ እንደ ሌሎቹ እንኳን ቅራት (ከብትን በረሃ ውስጥ ሌሊት መጠበቅ) ለብቻው አድሮ አያውቅም፡፡ ደግሞ አሁን ሸፍቷልና የሚያወያየው እንኳን የለም፡፡ እየዋለ እያደረ ሃሳብ ሲበዛበት ታች በሌ ይጨንቀው ነበር፡፡ ሽፍትነት ሲያስቡትና ሲሸፍቱት አንድ አልሆነለትም፡፡ እርሱ እዚህ በረሃ ውስጥ ምን እንደሚያደርግ ጨንቆታል፣ እዚያ መንደር ውስጥ ግን በስሙ ይዘፈን ይሆናል፡፡ የልቡን ማን አየለት፡፡ ለእርሱ ከሚዘፍኑለት ስንቅና ትጥቅ ቢያቀብሉት ነበር የሚሻለው፡፡
ታች በሌ ለአንድ ሳምንት በረሃው ውስጥ ተቀመጠ፡፡ ስንቅና እድሜ እያደር ይቀላል እንዲሉ የያዘው ነገር ሁሉ እያደር ያልቅበት፣ እርሱም ብቸኛነትን አልለመደውም ነበርና እያደር ሆድ ይብሰው ጀመር፡፡ አንዳንዴም ሲያስበው መሸፈት እንዳልነበረበት ራሱን ይሞግታል፡፡ አሁን እንዴት አድርጎ ወደፊት መጓዝ እንደሚችል ያስባል፤ ግን ምንም ሃሳብ ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ሰው ምን ይለዋል? አንዳንዴ የተወለደበትን ቀን ትቶ የሸፈተበትን ቀን ይረግማል፤ አንዳንዴ ደግሞ እንኳን ሸፈትኩ ይላል፡፡ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ጥዱም ሆኑ የጥዱ አንጋቾች ወደ አካባቢው ዝር ሊሉ አልቻሉም፤ ታድያ ሳይዋጋ ሽፍታ ተብሎ እስከ መቼ ሊቀመጥ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነኮ ጥቂት ቆይቶ ይረሳል፡፡
ታች በሌ እየቆየ ነገር ዓለሙ መረረው፤ መሸፈቱንን እንጂ ለምንና ምን ሊያደርግ እንደሸፈተ ለኅሊናው ማስረዳት አልቻለም፤ ቀጥሎ ምን እንደሚያደርግና ከዚያስ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ እገሌ ሸፈተ ሲባል እንጂ ሽፍትነት ምን እንደሆነ፣ ሸፍቶ ምን እንደሚደረግ በልቡ ምንም ነገር አልያዘም፡፡
አንድ ቀን ታች በሌ ድንገት የሚኖርበት መንደር ያለች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅዳሴ ሰዓት ከች አለ፡፡ አገርም ጉድ አለ፡፡ ካህናቱም ጨዋውም እያየው አፉን ይዞ ቀረ፡፡ ታምር ተሰምቶ የሰንበት ቂጣ ሊታደል ሲል ታች በሌ ድንጋይ ይዞ ሕዝቡ እግር ሥር ወደቀና ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው ብሎ በዚያ መከረኛ ላይ አላክኮ ካህናቱ ድንጋዩን አነሡለት፡፡
አንድ ሰሞን የታች በሌ ነገር የሞረቴ ሁሉ አፍ ማሟሻ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ ለሞረቴ መሸፈት ቀላል አልሆነም፤ ‹‹ደግሞ እንደ ታች በሌ ሲርብህ እንዳትመጣ›› የሚባለው ብዙ ነው፡፡ እንዲያውም አንድ ሰው ሸፈተ ሲባል አቅራሪዎቹ
ምከሩት፣
ምከሩት፣
ምከሩት፣
ይህንን ታች በሌ ለምን አትመክሩትም፤
ይህንን ታች በሌ ለምን አትነግሩትም፤
ልብ ካልሸፈተ እግር አይሸፍትም ….. ሃ!
እያሉ ይመክሩት ነበር፡፡ ታች በሌ ሳያስቡ ለሚወስኑና ሳያስቡ ለሚያደርጉ ሁሉ የሚሰጥ ቅጽል ሆነ፡፡
ታች በሌያዊ አስተሳሰብ የሀገራችን ተቋማት አንዱ ችግር ነው፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች፣ ማኅበራት፣ ድርጅቶች፣ ኩባንያዎችና ስብስቦች ሳይታሰቡ ተመሥርተው ሃሳብ የጠፋባቸው ናቸው፡፡ ለሃሳብ ተቋም ከመመሥረት ይልቅ ለተቋማቱ ነው ሃሳብ እየተፈለገ ያለው፡፡ ቁጭት ሁሉ፣ ብስጭት ሁሉ፣ ስብስብ ሁሉ፣ ገንዘብ ሁሉ፣ አጋጣሚ ሁሉ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ተቋም፣ ማኅበር ለመመሥረት መዋል የለበትም፡፡ እነ ዕገሌ ስለ መሠረቱ፣ እነ እገሌ ስለተሰባሰቡ፣ የዕገሌ አካባቢ ሰዎች በስማቸው ፓርቲ ስለመሠረቱ፣ የዚህ ዓይነት ሞያ ሰዎች ማኅበር ስላቋቀቋሙ፣ የዚያ ሀገር ሰዎች ኮሙኒቲ ስለ ፈጠሩ፣ እንቶኔና እንቶኔ ኩባንያ ስላቋቋሙ እኛም ማቋቋም የለብን፡፡  
መጀመሪያ ሃሳብ ይቅደም፡፡ ማሰብ ማለት ደግሞ ሃሳብን ብልጭ ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ ይህማ ታች በሌን መሆን ነው፡፡ ብልጭ ያለውን፣ ቁጭት የፈጠረውን ሁሉ ሳያስቡበት ተጣድፎ ማድረግ፡፡ ማሰብ እንዲህ አይደለም፤ ግራ ቀኝ የታሰበበት፣ የተጠናና የተነበበበት፣ ከቀደምቶች ልምድ የተቀሰመበት፣ ከተሳካላቸውም ካልተሳካላቸውም ትምህርት የተወሰደበት፣ እንዴት እንደሚኬድ፣ ግቡ ምን እንደሆነ፣ የተሻለው መንገድ የትኛው እንደሆነ፣ የሚያስፈልጉ ነገሮች ምን እንደሆኑ፣ ከነ ማን ጋር መተባበር እንደሚገባ፣ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል፤የፍልስፍና መስፈንጠሪያው ምን እንደሆነ አጥልቆና አልቆ መመርመር ነው- ማሰብ፡፡
አንዳንድ ሰው አስቤያለሁ ሲል ‹‹ይህ ነገር በአእምሮዬ መጥቶልኛል›› ማለቱ ነው፡፡ ይህኮ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያጋጥመው ነው፡፡ በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቱ መረጃዎች ወደ አእምሮው ሲገቡ ልክ በቁልፍ እንደሚነሣ መኪና ቅንጭሌውን ሊያስነሡት ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ግን መኪናው በቁልፉ ስለተነሣ ብቻ ሄደ እንደማይባለው ሁሉ ሰውዬውም አሰበ አያስብለውም፡፡ መጀመሪያ የመኪናው ባትሪ ቀጥሎ ሞተሩ መነሣት አለበት፡፡ ሞተሩ ደግሞ ሌሎችን ሁሉ አንቀሳቅሶ ሙሉ መኪናው መሥራት አለበት፡፡ ያን ጊዜ መኪናው ሄደ ይባላል፡፡
ሰውም ሃሳብ ብልጭ ስላለለት፣ የሆነ ቁጭት ስለተፈጠረበት፣ ከሆነ ሰው አንዳች ነገር ስላገኝ፣ በአጋጣሚ አንድ መረጃ ስለደረሰው፣ ቅናት ስላደረበት፣ ዕድል ስለተፈጠረለት፣ ዘመዶቹ ክፈት እንረዳሃለን ስላሉት ብቻ ተቋም፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ማኅበር መመሥረት የለበትም፡፡ አንዳንዶች የሆነ ነገር ለማድረግ አስበው ከመሰባሰብ ይልቅ ተሰባስበው ምን እንናድርግ? ብለው ያስባሉ፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች እንደ ታች በሌ ሳያስቡ የሸፈቱ ናቸው፡፡ የተለየ ሃሳብ፣ የተለየ ፍልስፍና፣ የተለየ አቋም፣ የተለየ መንገድ ሳይኖራቸው እንዴው በፓርቲዎቻችን ቁጥር ላይ አንድ ለመጨመር ያህል ብቻ የተመሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተ በኋላ ነው ፕሮግራም፣ መመሪያ፣ ፍልስፍና፣ መንገድ፣ የሚያዘጋጁት፡፡ በሃሳብ ስለማይመሠረቱ ከተመሠረቱ በኋላ በሃሳብ ይለያያሉ፡፡ ሳስበው እንዲያውም ለሁሉም ችግሮቻችን መፍትሔ ስጡ ስንባል ኮሚቴ ማቋቋም የሚቀናን ለማሰብ ጊዜ ስለማንሰጥ ይመስለኛል፡፡ የስብሰባ፣ሞቅታ የፈጠራቸው ኮሚቴዎች ሃሳብ አጥተው ሲላጉ አባሎቻቸውን አንጠባጥበው መቼ እንደፈረሱ እንኳን ሳይታወቅላቸው ይፈርሳሉ፡፡ ታች በሌዎች በቁጭት ብቻ ተነሥተው የመሠረቷቸው የሞያ ማኅበራትም ከዓመታዊ ጉባኤ ያለፈ ሃሳብ ሊመጣላቸው ስላልቻለ፡፡ በአንድ ሊቀ መንበር ሃያ ዓመት እያዘገሙ እንዴት ናችሁ? ሲባሉ ‹አለን›› እያሉ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ይኖራሉ፡፡
አንዳንዶችም አሉ፤ ምን እንደሚጽፉ ሳያስቡ መጽሐፍ ለመጻፍ የሚነሡ፡፡ ምን እንደሚገጥሙ ሳያስቡ ግጥም ለማሳተም የሚውተረተሩ፡፡ ምን እንደሚያቀርቡ ሳያስቡ ፊልም ለማዘጋጀት ገንዘብ የሚያሰባስቡ፡፡ የተለየ ሃሳብ ሳይኖራቸው የሬዲዮ የዐየር ሰዓት የሚገዙ፡፡ ምን እንደሚጠይቁ ሳያስቡ የቃለ መጠይቅ ማይካቸውን ተጠያቂው ላይ የሚተክሉ ቀልደኞች፡፡ ለነገሩ በሠፈር አንድ ሱቅ ሲከፈት የሠፈሩ  ሰው ሁሉ አጥሩን እየቀደደ ሱቅ መሥራት የተለመደበት ሀገር ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ያዋጣል ወይ? ከጎረቤቴ በምን እለያለሁ? እኔ ምን አዲስ ነገር አመጣለሁ? ብሎ ሳያስብ ነው ሱቁን ቦግ የሚያደርገው፡፡ ሱቁን ከሠራና ዕቃ ካስገባ በኋላ ነው ማሰብ የሚጀምረው፡፡ ይህ ነገር ወደ ተቋሞቻችንም ተጋብቷል፡፡ ምን ተቋሞቻችን ብቻ ትዳሮቻችንም እንዲህ እየሆኑኮ ነው፡፡ ማግባት የሚፈልግ እንጂ እንዴትና ለምን እንደሚያገባ፣ የጋብቻው ጠባይና አካሄድ ምን እንደሚመስል አስቀድሞ የሚያስብ ጥቂቱ ነው፡፡  የሆነ ቦታ ለመሄድ እያሰብኩ ነው፤ የሆነ ነገር ሳልከፍት አልቀርም፤ አንድ የሆነ መጽሐፍ ልጽፍ እያሰብኩ ነው፤ የሚላችሁ ሰው ሳያስብ አንዳች ነገር ሊያደርግ የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡
አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው፡፡ ገበያ መውጣታቸውን እንጂ ምን ሊገዙ እንደወጡ፣ ቤት መሥራትና መግዛት እንጂ ምን ዓይነት ቤት እንደሚገዙ ወይም እንደሚሠሩ፣ ውጭ ሀገር መሄድ እንጂ ለምንና እንዴት እንደሚሄዱ፣ የማያስቡ አሉ፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች የነበረውን መንግሥት ስለመቀየር እንጂ በቅያሪው ስለሚመጣው መንግሥት ስላልታሰበበት የመጣው ከሄደው የባሰበት ጊዜ አለ፡፡ ለዚህ ነው ታች በሌያዊ የሆነውን መንገድ ትትን ሃሳብ ከተቋም ይቅደም የምለው፡፡ ሃሳብ ከድርጊት ይቅደም፡፡ ሃሳብ ከመመሪያም፣ ከዐዋጅም፣ ከማፍረስም፣ ከመሥራትም፣ ከመሸለምም፣ ከመቅጣትም፣ ከመሄድም ከመምጣትም ይቅደም ፡፡
አንድ ሰው እንዲያውም ይህንን ነግሮኛል፡፡ የአንድ ገበሬ ውሻ ሁልጊዜ መንገድ ዳር እየቆመ አላፊ አግዳሚውን መኪና ለመያዝ እየተከተለ ይጮኻል፡፡ የገበሬው ጓደኛ ይኼ የውሻው ጠባይ ይገርመዋል፡፡ አንድ ቀን ገበሬውን ‹‹ለመሆኑ ይኼ ውሻህ መኪናውን ተከትዬ እይዘዋለሁ ብሎ ነው እንዲህ መከራን የሚያየው?›› ይለዋል፡፡ ገበሬውም ሳቅ ብሎ ‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው›› አለው ይባላል፡፡ ታች በሌያዊ  አስተሳሰብ ማለት ይህ አይደለም ታዲያ፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ጽ/ቤቱ ከመንግሥት በመነጋገር የደኅንነት ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል የልዩ ጽ/ቤቱን ለቃችኹ ውጡ ትእዛዝ ‹‹ሕግን የጣሰና ለከሳሽ ያደላ›› በሚል ተቃውመውታል የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ እና የጠ/ቤ/ክህነቱ ዋ/ሥራ አስኪያጅ ደቀ መዛሙርቱን እያረጋጉ ነው የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ ከደቀ መዛሙርቱ ጎን ቆመዋል ተብሏል ኹኔታው ያሳሰባቸው የማታ ተማሪዎች ተወካዮች ከቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጋራ ተወያይተዋል የኮሌጁ መምህራን አቡነ ጢሞቴዎስ …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሺዋ ዞን የደብረ ብርሃን ከተማ ኗሪዎች የመንግስት ሹማምንት የሚያደርሱባቸውን በደሎች በመዘርዝር ለመንግስት አቅርበዋል። ክልሉ በቅርቡ በጀመረው የህዝብ ብሶቶችን መስሚያ መድረኮች ላይ ነዋሪዎች ” በአደባባይ እንደበደባለን ፤እንታሰራለን፤ በአገራችን በሰላም ለመኖር አልቻልንም” ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡በተደጋማሚ በሚደርስባቸው በደል አገር ጥለው የሚሰደዱ ዜጎች መበራከታቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ሹመት የሚሰጠው በዘመድ ዝማድ …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በያዝነው ወር ብቻ 500 ሲቪሎች፣ ከጅጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ዋርዴር እና ጎዴ በደህንነት ሀይሎች ተወስደው እስር ቤት ገብተዋል። አዲሱ የእስር ዘመቻ የተከፈተው በቅርቡ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና ወታደሮች ከድተው እጃውን ለኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ከሰጡ በሁዋላ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ከታሰሩት መካከል በርካታ ህጻናትና ሴቶች ሲገኙበት፣ አብዛኞቹም ጅጅጋ አካባቢ በሚገኝ ወታደራዊ …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 11 ሺ 93 ስዎች ከነፍስ ግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ባካሄደው  የዳሰሳ ጥናት በ10 አመታት ውስጥ ከነፍስ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ሺ 64 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 11 ሺ 93 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። በጥናቱ ውስጥ እንደተመለከተው ድብደባ መፈጸም ቀዳሚነቱን ሲይዝ  አካል ማጉደል እና …

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ህብረት በጤና ጉዳይ ላይ ለመመካከር በናይጀሪያ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሰብሰባቸውን ሳይጨርሱ ወደ አገራቸው የተመለሱት ፣ አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የናይጀሪያ መንግስት ይዞ እንዲያስራቸው አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ካቀረበ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ ሰኞ እለት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ በድንገት አገሪቱን ለቀው መውጣታቸው …

ብሔርተኝነትን መግለፅ ለኤርትራዉያን ወጣቶች የሚመጣ ችግርን መከላከያ ጥሩ ሥልት ነዉ።ሌላ ቢሎ መዘዙ ሌላ ነዉ።አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ትንሽ ሐገር እራሷን ከተቀረዉ ዓለም ዘግታለች።ከሠላሳ ዓመት ጦርነት በሕዋላ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ ነፃነትዋን በይፋ ያወጀችዉ በ1985 ነዉ።

ከዛሬ አምስት ዓመት ተኩል ወዲህ ደግሞ ጋንዲ በሲና በረሃ በግብፅ በሊቢያና በቱኒዝያ እስር ቤቶች የሚሰቃዩ ባመዛኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን እየረዳ ነው ። ጋንዲ ሲና በረሃ የታገቱ በርካታ ስደተኞችን ከአፋኞቻቸው ነፃ ለማውጣት በቅቷል ።

በኢጣልያ የሊጋ ኖርድ ፓርቲ እንደራሴ እና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ሮቤርቶ ካልዴሮሊ በሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሚንስትር ዶክተር ሴሲል ኪዬንጌ ላይ አሳፋሪ አስተያየት የሰነዘሩበት አነጋገር ከተለያዩት የሀገሪቱ ፓርቲዎች እና ከሕዝቡ ብዙ ተቃውሞ ቀስቀሰ።

መጾም መራብ ሳይሆን ተፈጥሯዊ የሆነ የአኗኗር ስልት ነዉ ይላሉ የዚህ ሃሳብ አራማጆች። ዓላማቸዉ በየደረጃዉ ተዘጋጅተዉ ለገበያ በሚቀርቡት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምግቦች ምክንያት ወደአካላችን ገብቷል የሚሉት አላስፈላጊ ንጥረ ነገር እነሱ መርዝ የሚሉትን በተፈጥሯዊ ስልት ከሰዉነት ለማስወገድ ነዉ።

እስራኤል በምድሯ የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂ አፍሪቃዉያንን ወደየመጡበት አስገድዳ መመለሷን የመብት ተሟጋቾች አወገዙ። ከትናንት በስተያ እስር ላይ ካቆየቻቸዉ ሁለት ሺህ ኤርትራዉያንና ሱዳናዉያን መካከል 14 ኤርትራዉያንን ወደአስመራ መላኳን አንድ የእስራኤል የመብት ተሟጋች ድርጅትና ሂዉማን ራይትስ ዎች ይፋ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ዕሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ. ም በጎንደርና በደሴ ከተሞች የተካሄዱትን ትዕይንተ-ሕዝቦች ይደግፋል። ”የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!” በሚል መሪ ሃሳብ ሥር በአንድነት ፓርቲ አቀነባባሪነት የተጀመረው የሕዝብ እንቅስቃሴ፤ የተጋረጠበትን እንቅፋት ሁሉ አልፎ እነሆ በደሴና በጎንደር ከተሞች በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ የፍራቻ ድባብን ሰብሮ በይፋ ለመግልጥ መቻሉ ሁሉንም […]

ሃብትና ስልጣን አስክሮአቸው፣ በዚህች ደሃ ሃገርና ሕዝብ ላይ ተፈናጠው ሁለት አስርተ አመታት ያስቆጠሩ አምባገነን መሪዎቻችን የሃገርና የሕዝበ ፍቅር አጥተው በምዝበራ ለመክበር ብቻ፣ ሕዝብንም በሃገሩ በሰላም የመኖር መብቱን ቀምተው ተደላድለው ለመቀመጥ ዘንድሮም እንደ አምናው በሽብር ስም በጫኑብን የአፈና መረብ ሸብበው ሕዝቡን ከዳር እዳር ማስጨነቃቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ ለዚህ እኩይ ተልኳቸው ላሰለጠኑዋቸው የስርዓቱ ሰዎች (ደህንነቶች) በዴሞክራሲና በመልካም […]

ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም መንግስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን የወረዳ አመራሮችንና አባላትን በዘመቻ ማሰር ጀምሯል፡፡ እስከአሁኗ ሰዓትም 42 የሚሆኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት በፖሊሲ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኞች ተዘዋውረው እንደዘገቡት 42 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላት በፖሊስ እንዲታሰሩ ተደርጓል፡፡ የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ እያሰራጨ ያለውን ህጋዊ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በማደላቸው […]

የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እስከ መስከረም አጋማሽ ፳፻፮ ዓ.ም ድረስ እንዲቋረጥ ተወስኗል ደቀ መዛሙርቱ በቀጣይ ርምጃዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ፡፡ ልዩ ጽ/ቤቱ ዛሬ፣ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከቀትር በኋላ በኮሌጁ የለጠፈው ማስታወቂያ፣ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ማስታወቂያው ከወጣበት ከዛሬ ሐምሌ …

የተቃዉሞ ሠልፍ መደረጉን፥ አንዳዶች ገዢዉ ፓርቲ ላለፉት ስምንት ዓመታት ይከተለዉ ከነበረዉ መርኹ የመለሳለሱ ምልክት ይሉታል።ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመጠናከራቸዉ ማሳያ ነዉ-ባዮችም አሉ። ሌሎች ደግሞ ቢያንስ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚደግፈዉ ሕዝብ ተቃዉሞዉን ለማሰማት ዶክተር ነጋሶ እንዳሉት የመቁረጡ አብነት ነዉ።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ፤«የሚሊዮኖች ድምፅ ለነጻነት »በሚል መሪ ቃል ለ 3 ወራት ያወጣውን የህዝብ ንቅናቄ እቅድ ትናንት በጎንደርና ደሴ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲከናወን በማድረግ ጀመረ። ከትናንቱ ሰልፍ በፊት ፣ ህዝብ ለሰልፍ እንዲወጣ

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርብ ፣ ሀምሌ 6 2005 ዓም በእነ አቶ ተሻለ ኮርኔ መዝገብ የተከሰሱ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ፍርድ ቤት የሚወስዳቸው ፖሊስ ያጣሉ። በቅጽል ስሙ ሻእቢያ እየተባለ የሚጠራውን የእስር ቤቱን ሀላፊ ሲጠይቁት ቀጠሮአቸው ለ4 ወር መራዘሙን ይነግራቸዋል። እስረኞቹም ” ከ2 አመታት በላይ የላፍትህ ታስረን በመጨረሻ …

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በደሴና እና በጎንደር የተሳኩ የተቃውሞ ሰልፎችን ባካሄደ ማግስት ከ30 በላይ አባሎቹ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ፊርማ ሲያሰባስቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለፉት ሳምንታትትም በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ እና የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ አባላት አሉ። አንድነት ፓርቲ ለ3 ወራት በሚቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ  በዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን …

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም በመጠየቅ ትናንት በአመታዊ የሥላሴ ክብረ በዓል ላይ  መፈክሮችን ሲያሰሙ ውለዋል። ተማሪዎቹ ሲያሰሙዋቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል፦የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!፣የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!፣ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ! …

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን በቅርቡ ባካሄደው የአሰራር ሥርዓት ጥናት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የግዥ አፈፃፀም ለሙስና እና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ ነው ብሎአል፡፡ በፖሊስ ኮምሽኑ የተጠና የጠቀሜታ ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ አዘገጃጀት አሰራር አለመኖር፣ ግዥዎችን በዕቅድና በፕሮግራም አለመፈፀም፣ በጀት መኖሩ ሳይረጋገጥ የግዥ ሂደቶችንማከናወን፣ በግዥ መመሪያው ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ግዥ …

በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚያካሂዱት ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ምእመኑ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርበዋል አቡነ ጢሞቴዎስ ደቀ መዛሙርቱን በፖሊቲከኝነት መወንጀል ጀምረዋል የተማሪዎች መማክርት የኮሌጁን አስተዳደር በሕግ ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ከመሳለምና ገንዘብ ከመስጠት/ከመመጽወት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ በመጠየቅ ቀጥተኛ ተሳታፊ መኾን እንደሚገባቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አሳሰቡ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ማሳሰቢያውን ያስተላለፉት፣ …

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው! የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት! ልጆቹን የማይጠይቅ አባት አለን? ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን! የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ! ጢሞቴዎስ ሆይ፣ አደራህን ጠብቅ፡፡ (፩ኛጢሞ. ፬÷፳) ችግራችንን የሚሰማንና መፍትሔ የሚሰጠን አባት ዐጣን! የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ትኩረት ይስጡን! ሙስናን በቃል ሳይኾን በተግባር እንዋጋ! ተማሪዎች ሙስናን በመዋጋታቸው […]

ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም የጎንደር ከተማ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎችን ታላቅ አሳፋሪ አፈና ጥሶ በመሄድ ድምጹ በታላቅ ጀግንነት አሳምቷል። የአንድነት ድህረ ገጽ ላይ የወጣ በኦዶዮ የታጀበ ዝርዝር ሸገባ እንደ እንደሚከተለዉ አቅርበናል። እዚህ ይጫኑ !

አንድ ቢሊዮን ገደማ ህዝብ ባለው ክፍለ ዓለም 54 አባል ሃገራትን ያቀፈውና ዘንድሮ 50 ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የአፍሪቃ ኅብረት በየጊዜው በሚከሠቱ የአህጉሩ ችግሮች መፈተኑ አልቀረም ። የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ወይዘሮ እንኮሳዛና ድላማኒ

ክልሉ የፍትሕና ጸጥታ ዘርፍ እንዲሁም የፖሊስ ሓላፊዎች ለሁከት ፈጣሪዎቹ ወግነዋል

ደቀ መዛሙርቱ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን የኮሌጁን የምግብ ቤት አገልግሎት ተከልክለዋል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ደቀ መዛሙርቱ ወደ ክረምት ዕረፍት ከመሄዳቸው በፊት የማጠቃለያ ፈተና እንዲወስዱና ተመራቂዎቹ እንዲሸኙ ጥረት እያደረገ ነው፤ በፓትርያሪኩ የመወሰን አቅም ላይ ጥርጣሬ የገባቸው የሚኒስቴሩ ሓላፊዎች ልዩ ጽ/ቤቱ ደቀ መዛሙርቱን በኀይል ከኮሌጁ ለማስወጣት ያቀረበውን የድጋፍ ጥያቄ ውድቅ ባደረጉበት አቋማቸው ጸንተዋል ፓትርያሪኩ በሚይዟቸው አቋሞች ረዳት ሊቀ ጳጳሱ …

የነገው አበባ ለምን ለፌደራል ፖሊስ ይሰጣል? ዳዊት ሰለሞን (ፍኖት ዘጋቢ) ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም አበባ የሰው ልጆች በአንድ ድምጽ «ፍቅራችንን ወክልልን» በማለት የመረጡት ይመስል የፍቅርን አደራ ተሸክሟል፡፡ከሶስተኛው አለም እስከ አንደኛው የሚገኙ የአዳም ልጆች «አበባን» የፍቅር ስጦታ በማድረግ ለሚወዱት ይቸሩታል፡፡የሚወዱት ሲሞትባቸውም ፍቅራቸውን ለሟቹ ለመግለጽ አስከሬኑ ላይ አበባ ያኖሩለታል፡፡ ወደ ደሴና ጎንደር እንምጣ፣ ነገ ከሌላው ጊዜ […]