ሰበር ዜና – ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ

  • የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እስከ መስከረም አጋማሽ ፳፻፮ ዓ.ም ድረስ እንዲቋረጥ ተወስኗል
  • ደቀ መዛሙርቱ በቀጣ ርምጃዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ፡፡

ልዩ ጽ/ቤቱ ዛሬ፣ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከቀትር በኋላ በኮሌጁ የለጠፈው ማስታወቂያ፣ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ማስታወቂያው ከወጣበት ከዛሬ ሐምሌ ፰ እስከ ነገ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ አሳስቧል፡፡