በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት ተባብሰዋል፣ የተፈጠሩት ችግሮች የዘረኛውን አገዛዝ ውድቀት ያፋጥናሉ ተባለ
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አደገኛ ሁኔታ ላይ መድረሱና ለረጂም አመታት በትምህርት ላይ የቆዩ የድሃ ቤተሰብ ልጆች ስራ አጥነት እጂግ መስፋፋት የዘረኛውን አገዛዝ ውድቀት ሊያፋጥኑት እንደሚችሉ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ገለጹ። ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ በያዝነው አመት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን አጠናቀዋል ተብለው የተመረቁ ወጣቶች ቁጥር እጅግ በጣም ብዙና በመቶ […]