ባለፈው ሳምንት ሰማያዊ የተባለ አዲስ ፓርቲ የምሥረታ ጉባኤውን ሲያካሂድ በአብዛኛው አባላት ከአንድነት ፓርቲ ጋር በታክቲክም ሆነ በስትራቴጂ አብረው ሊሠሩ ያልቻሉ፤ ሆኖም ግን ለሃገርም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ አስተዋፅኦ እናደርጋለን ያሉ ኃይሎች ፓርቲ መሠረቱ፡፡ በፓርቲ ምስረታቸውም ዕለት የአንድነት ፓርቲ በእንግድነት እንዲገኝላቸው ጥሪ አደረጉ፡፡ አንድነት ፓርቲ ጥሪያቸውን በማክበር አጀንዳ ይዞ ውይይት ካደረገ በኋላ የፓርቲው ሊቀመንበር የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶ […]

ሀገራችን ኢትዮጵያ ረጅም የመንግስትና የፖለቲካ ታሪክ ካላቸው ሀገሮች ተርታ የምትመደብ ናት፡፡ ይችው እድሜ ጠገብ ውድ ሀገራችን መንግስት በማቋቋም፣ በስልጣኔ በንግድና ሉዓላዊነቷን በመጠበቅ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ ጥንታዊ ሀገሮች የምትመደብ ቢሆንም ቀዳሚነቷን አስጠብቃ መጓዝ ግን አልቻለችም፡፡ ኢትዮጵያችን በድህነትና በኋላቀርነት፣ እንዲሁም በበሽታና በእርዛት መታወቅ መቻሏ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በቁጭት የሚያንገበግብ፤ የእኛ ባህሪ የሆነውን አይነኬነት የሚፈትንና እልህ የሚያስይዝ ጉዳይ ነው፡፡ […]

ለቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረ ግጭት ሁለት የሕግ ተማሪዎች ሞተው ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈፀሙን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ አንድ የውስጥ አዋቂ እደሚሉት ከሆነ ደግሞ “ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝ ነው” ይላሉ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ሲራጅና ከማል የተባሉ ሁለቱ የሕግ ተማሪዎች መሞታቸውንና ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው የተፈፀመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት […]

በዋሽንግተን ዲሲ በተሰናዳ የቀድሞው የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ቫትስላቭ ሃቨል መታሰቢያ የብርማዋ አንሳንሱቺ፣ ፕሬዝደንት ኦባማ፣ ዳሊ ላማና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች መልእክት አስተላልፈዋል

የትምህርት ነጻነታችን ይከበር በሚል አዲስ አበባ የሚገኘው የአወሊያ ት/ቤት፣ በወለጋ ዩኒቨርስቲ የምግብ ጥራት መጓደል፣ በሆሳእና ደግሞ የስራ መጥፋት ተማሪዎችን ለተቃውሞ አነሳስተዋል።

የትምህርት ነጻነታችን ይከበር በሚል አዲስ አበባ የሚገኘው የአወሊያ ት/ቤት፣ በወለጋ ዩኒቨርስቲ የምግብ ጥራት መጓደል፣ በሆሳእና ደግሞ የስራ መጥፋት ተማሪዎችን ለተቃውሞ አነሳስተዋል።

[email protected] ዶር ብርሃኑ ነጋ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዙሪያ ለአንባቢያ ያቀረብኳቸው ሁለት መጣጥፍት ከፍተኛ የአንባቢያን አስተያየቶችን እንደጫሩ ለማየት ችያለሁ። የድጋፍም ሆነ የተቃዉሞ ኤሜሎች በብዛት የደረሱኝ ሲሆን፣ በአቡጊዳ ድህረ ገጽ ላይ የቀረቡ አሰትያየቶች ከወትሮ እጅግ የበዙ ነበሩ ። በጽሑፌ ቅር የተሰኙ ፣ ለምን ቅር እንደተሰኙ በአግባቡ ለመግለጽ ያልቻሉ፣ ያቀረብኳቸዉን ነጥቦች ትክክል እንዳልሆኑ ለማሳመን የራሳቸዉን መከራከሪያ […]

የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስና፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራርና አባላት ለወራት ፍርድ ቤታ ሳይቀርቡ መታሰራቸው፤ ህገመንግስታዊ መብታቸውን ተጻሯል ሲሉ ተቃዋሚዎች ተቹ

መግቢያ፥ ይህ አዲስ ዘመን፣ ያሳለፍነው የ‘አጥፍቶ-ልማት ጥፋት ዘመን’ ፍጻሜ ማግስት ነው ብለን ማመን ይገባል። ሁለንተናችን በምንላት እናት አገራችን ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው ወገን፣ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ከገዢውና አገልጋዩ በስተቀር ያልተጎዳ ሰው አለ ማለት ክህደት ይሆናል። ወያኔ ከፈለቀበት ምድርም ቢሆን የከፋ ዕልቂት የፈጸመ መሆኑ ለታሪክ በተረፉት ሰዎች አፍ እየተነገረ ሲሆን፣ በየሸለቆውና ሜዳው ያለው እጽም ደግሞ […]

በዘረኛው ቡድን አማካኝነት የአገራችን የሞራል እሴቶች ሆን ተብለው እየተዋረዱ ነው።ድሮ ድሮ “እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር” የሚባል መልካም አባባል ነበረን። ዛሬ ይህን የመሰሉ አባባሎች ከል እንዲለብሱ በመደረጉ እውነትን  የሚናገር በግዞት ተይዞ የመከራ እንጀራ ይበላል የመከራ ውሃም ይጠጣል። እንደ ንጉስ አክዓብ በዙሪያው ብዙ ሃሰተኛ መማክርትን የሰበሰበው መለስ ዜናዊ የእውነትን ድምጽ የመስማት ልምድ የለውም።ሃሰት የኑሮው መሠረት ነች። ሃሰት […]

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጥላ ሥር ከሌሎች የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ተባብሮ ለመታገል መወሰኑን ገሃድ ማድረጉን ተከትሎ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከትናንትና በስቲያ መግለጫ አውጥቶአል። “የጋራ ትግል የጋራ አገር” በሚል ርዕስ ግንቦት7 ባወጣው በዚህ መግለጫ “በኢትዮጵያ የሰፈነውን ዘረኛ አምባገነን ሥርዓት አስወግደን በምትኩ የግልና የወል መብቶች የተከበሩባት፤ ፍትህና […]

የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በፍርሃት ለማሸምቀቅ ተብሎ በዘረኛው መለስ ዜናዊ የተቋቋመው የጸረ ሽብር የመረጃ መእከል የተባለው መሥሪያቤት ለግልና ለመንግስት ባንኮች ባወረደው መመሪያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊም ሆነ የውጭ አገር ዜጋ ከ200 ሺ ብር ጀምሮ በባንኮች ለማስቀመጥ ወይም ለማውጣት በሚሄድበት ጊዜ፣ ባንኮች የግለሰቦችን ስምና ማንነት ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማእከል ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የጸረ ሽብር ግብረሀይሉ ከህወሃት ቁንጮዋች […]

አቶ አስገደ ከፍርድ ቤት ሆነው በስልክ ለፍትህ ጋዜጣ እንደገለፁት ከሆነ፣ ከሳሻቸው የቀድሞው የሕወሓት አባል የሆነው ብስራት አማረ ሲሆኑ ጉዳዩን የያዘቺው ዳኛ ደግሞ የቀድሞዋ የህወሓት ታጋይ ኪዳን አብርሃ ናት ተብሎአል። ክስ የቀረበባቸውም ከዚህ ቀደም በፃፉት “ጋሀዲ” በተሰኘው መፀሀፍ እንደሆነ አቶ አስገደ ተናግረዋል፡፡ አቶ አስገደ ከአሁን በፊት በዚህ ጉዳይ ቀዳማዊ ወያኔ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ተዘግቶ የተሰናበቱ […]

ህዝብን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍሎ መግዛት ብቸኛ የህይወት እስትንፋሱ የሆነው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፤ ቀደም ሲል በአገራችን ሙስሉም ህብረተሰብ ዘንድ ፈጽሞ የማይታወቅ አህባሽ የተባለ የእምነት ትምህርት በሃይል ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን ዘመቻ በተለያየ የአገራችን ክፍል የሚኖሩ ሙስሊም ወገኖቻችን እየተቃወሙት መሆኑ እየተዘገበ ነው። በመለስ ዜናዊ የሚመራው የወያኔ አገዛዝ በሃይል ለማስፋፋት የወሰነውን ይህንን አህባሽ የተባለውን አዲሱን የሙስሊም ትምህረት በመቃወም በአዲስ […]

በጋምቤላ ክልል ጐደሬ ጥብቅ ደን ክልል ውስጥ ለህንዱ ኩባንያ በተሰጠው የእርሻ መሬት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተቃውሞ እየበረታበት ባለበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ…