ዴሞክራሲ በተግባር
የዛሬው የዲሞክራሲ በተግባር እንግዳችን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነው ከአዲስ አበባ። በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ አብዮት መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ሚዲያውና ሕዝቡ ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተል አወያይተነዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች “ተዳክመዋል” በሚባልበት ወቅት እንደ ቱኒዝያና ግብፅ “ሕዝባዊ እንቅስቃሴውን …
የዛሬው የዲሞክራሲ በተግባር እንግዳችን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነው ከአዲስ አበባ። በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ አብዮት መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ሚዲያውና ሕዝቡ ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተል አወያይተነዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች “ተዳክመዋል” በሚባልበት ወቅት እንደ ቱኒዝያና ግብፅ “ሕዝባዊ እንቅስቃሴውን …
በቦስተን ዩኒቨርሲቲ የፍሬዴሪክ ፓርዲ የጥናት ማዕከል ለህትመት የበቃውና የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና ጅምር ጥረት በምሳሌነት የተመለከተው ይህ ጥናት፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጥበቃ፥ እስካሁን እምብዛም ተጠቃሚ ያላደረጋቸውን አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ደሃ አገሮችንም፤ እንደ ግዙፉ አትራፊ ኩባንያዎች ሁሉ፥ የትሩፋቱ ተቋዳሽ ሊያደርግ የሚያስችል አቅም …
ከፓርቲው ተወግደዋል የተባሉ አንድ የቀድሞ ሥራ አስፈፃሚ ደግሞ አባባሉን ”ጥላሸት መቀባት ነው“ ብለውታል። ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
የእርዳታ ጠባቂው ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረው በብዙ መውረዱ ቢገለፅም የምግብ እጥረቱ አርባ ከመቶ የሚሆነው የተከሰተው በሰላም እጦት ተቸግሮ በሚገኘውና የተበታተነ የሕዝብ አሠፋፈር ባለበት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መሆኑ ሪፖርተራችን ፒተር ሃይንላይን ከአዲስ አበባ የላከው ዘገባ ጠቁሟል፡፡ ባለፈው ዓመት እንዲህ ዓይነቱ አጣዳፊ …
ለውጥ ፈላጊው የቱኒዚያ ሕዝብ ባለፈው ሣምንት አደባባይ ወጥቶ ቁጣውን የገለፀበት የተቃውሞ ሠልፍ ፕሬዚደንቱን ቤን አሊን ከነቤተሰባቸው አገር ጥለው እንዲሸሹ አስገድዷል። በግብፅ ተመሣሣይ ሕዝባዊ ቁጣ ተቀጣጥሎ ለሰላሣ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየውን የፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ መንግሥት አፍርሷል። በሠላም ሥልጣን ካላስረከቡ ከቤን አሊ …
በቦስተን ዩኒቨርሲቲ የፍሬዴሪክ ፓርዲ የጥናት ማዕከል ለህትመት የበቃውና የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና ጅምር ጥረት በምሳሌነት የተመለከተው ይህ ጥናት፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጥበቃ፥ እስካሁን እምብዛም ተጠቃሚ ያላደረጋቸውን አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ደሃ አገሮችንም፤ እንደ ግዙፉ አትራፊ ኩባንያዎች ሁሉ፥ የትሩፋቱ ተቋዳሽ ሊያደርግ የሚያስችል አቅም …
እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ2010 በኢትዮጵያ የፖለቲካ መብትና እና የግለሰብ ነጻነት በእጅጉ የተሸረሸረበት ለመሆኑ የግንቦቱ ብሔራዊ ምርጫ ማሳያ ነዉ፤» ሲል Freedom House አመለከቷል። «በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስተዳደር ስር ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከዴሞክራሲ እያፈገፈገች የሄደች ቢሆንም፤ ባለፉት ዓመታት ”ከፊል ነጻ” …
በFreedom House ዓመታዊ ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሲቃኝ! Read more »
ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በዋሽንግተን አቆጣጠር ትናንት ምሽት ላይ ለተወካዮች ምክር ቤታቸው ጥምር ስብሰባ ባደረጉት የሃገራቸውን ሁኔታ ያሣየና የወደፊት አቅጣጫ ያመላከተ ሁለተኛው ዓመታዊ ንግግራቸው ሥራ ሊፈጥሩ የሚችሉባቸውን መንገዶች እና አሜሪካን በዓለም ምጣኔ ኃብት ውስጥ ይበልጥ ተፎካካሪ አደርግባቸዋለሁ ያሏቸውን ትልሞቻቸውን …
“የሕዝቡን ኃብት ሠርቀው ወደ ውጭ አሽሸዋል” ሲል የከሰሣቸው የሃገራቸው የፍትሕ ሚኒስቴር በተገኙበት እጃቸው ተይዞ እንዲሰጠው የእሥር ማዘዣ አውጥቷል፡፡ ይህ በሥራ እጦት፣ በዋጋ ንረትና በውስጥ ችግር ሣቢያ ቱኒዚያ ውስጥ የተቀጣጠለው አብዮት ወደሌሎችም በአምባገነኖች የሚመሩ የአፍሪካ ሃገሮች እየተዛመተ ይመስላል፡፡ “ዴሞክራሲ በተግባር” ዝግጅታችን …
በኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ ያስፈልጋል? ለምን? ከፖለቲካ ድርጅቶች ምን ይጠበቃል? ከህዝብስ? ጥያቄዎቻችሁን እንዲመልሱ በህግና ብሔራዊ እርቅ ዙሪያ ፅሑፎች ያበረከቱና የሥራ ልምድ ያላቸው ሁለት ኢትዮጵያዊያንን ጋብዘናል። ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማሪያም በርዋንዳ ለተካሄደው የጅምላ ፍጅት የዓለምአቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግ ሆነው ያገለገሉ …
በዚያ የሚገኘው ሪፖርተራችን ግርማይ ገብሩ ወደ መስከረም ሆስፒታል ጎራ ብሎ ነበር፡፡ ሆስፒታሉ ከሚሰጣቸው የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶች በአንዱ ላይ አተኩሮ በጥርስ ጤናና ሕክምና ላይ ተከታዩን ዘገባ ልኳል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ፡
ዓለምአቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ምዕራባዊያን በተለይም የአውሮፓ ኅብረት መንግሥታት፣ መብት ረጋጭ መንግሥታት ከድርጊታቸው እንዲታረሙ ጫና አያደርጉም ሲል ወቀሰ። ሂዩማን ራይትስ ዋች በ21ኛው ዓመታዊ ሪፓርቱ ዴሞክራሲያዊ መርህ የሚያራምዱ ምዕራባዊያን አገሮች በፖለቲካና በኢኮኖሚ ምክንያት ሌሎች አገሮች ላይ ያላቸው …
ቀደም ሲል፥ «ዑዛዛ አሌና፤» በተሰኘው በሱዳንኛና በአማርኛ ቋንቋዎች በምትጫወተው ዜማዋ፤ አሁን ደግሞ «የህልሜ ጓደኛ፤» እና «ልቤ፤» በተባሉት ተወዳጅ አዳዲስ ዘፈኖቿ ይበልጥ የታወቀችው ወጣቷ ድምፃዊቷ ሄለን በርሄ አብራን ታመሻለች። አምና የአውሮፓውያኑን 2010 ስንጀምር፥ በጊዜው የገባነውን ቃል፤ መለስ ብለን የምንመረምርበትና መጪውን የምናይበት …
የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው በዩናይትድ ስቴይትስ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ1989ወዲህ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስታዊ ልዑካንን በመምራት የቻይና ፕሬዝደንት ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ሲጓዝ ሁ የመጀመሪያው ናቸው። በዚህ ጉብኝታቸው ሚስተር ሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአንድሩውስ ወታደራዊ የአውሮፕላን ማረፊያ በምክትል ፕሬዝደንት ጆ …
ቻይና ከዩናይትድ ስቴይትስ ጋር የጠበቀ የንግድ ግንኙነት እንጂኖራት ፕሬዝደንት ሁ ጥሪ አቀረቡ Read more »
«ይህ ማለት ግን» ይላል ካዲሳባ የደረሰን የፒተር ሃይንላየን ዘገባ «የሕብረቱ ዋና መዲና መቀመጫ ከሆነችው ጎረቤቷ ኢትዮጵያ ጋር ያላት ቅራኔ ላልቷል ማለት አይደለም።» በአፍሪካ ሕብረት የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም ተስፋዬ የሹመት ደብዳቤአቸውን ከሁለት ቀናት በፊት ለኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዣን ፒንግ አስረክበዋል፡፡ …
በአሜሪካ ድምፅ ቀርበው ቡራኬና አባታዊ ምክራቸውን የለገሱት የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና በቅድስት ሃገር ኢየሩሣሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ እንዲሁም የጋምቤላና የኢሉባቦር ሃገረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ናቸው፡፡ …
የመዘንጋት ችግር በወጣትነትና በጎልማሳነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሠዎች ላይ ሲከሰት ያለውን ሁኔታ፥ ምንነትና፤ ተዛምደው ሊታዩ የሚገቡ ዝርዝሮች፤ እንዲሁም ችግሮቹን ለማቅለል የሚረዱ ዕርምጃዎች ጨምሮ ለማየት የሚሞክር ቅንብር ነው። በእነዚህ በመርሳት ችግሮች ዙሪያ ላተኮሩት ነጥቦች ሞያዊ ትንታኔ የሚሰጡን፥ ዛሬም የአዕምሮና የነርቭ ህክምና …
ይህ የሆነው ደግሞ በብር የምንዛሪ አቅም ላይ በተደረገው ቅነሣ ምክንያት በተለይ የምግብ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ አዲሱ የዋጋ ተመን ቁጥጥር ምናልባት የዋጋውን ውድነት ሳያረግበው እንደማይቀር መንግሥት ተስፋ እንዳለው የአሜሪካ ድምፁ ዘጋቢ ፒተር ሃይንላይን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈው ዘገባ አመልክቷል፡፡ የግሽበቱ …
አሁን ያስቀመጡትን ዕቃ ጥቂት ቆይተው ያደረጉበት ይጠፋዎታል? ያሰቡትን፥ ወይም ሊያደርጉ ያቀዱትን ላለመዘንጋትስ በመስጋት አስታዋሽ ሲሹ ራስዎን ያገኛሉ? ከሆነም፥ ብቻዎን አይደሉም። የመርሳት ወይም የመዘንጋት ችግር ከተለያዩ ሁኔታዎች ጋር ቢያያዝም፤ እንዲህ ላለው ሁኔታ መጋለጥ፤ የግድ በዕድሜ መግፋትንና ተጨማሪ የጤና እክሎች መኖርን ሳይፈልግ፤ …
በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉድለት መኖሩን ቢታዘቡም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የልማት ፍላጎት ያላት ሃገር መሆኗን ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የጀርመን የኢኮኖሚ ልማትና የትብብር ሚኒስትር አስታወቁ፡፡ ሚስተር ዲርኬ ኒበል በጉብኝታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውንና ኢትዮጵያ ከሃገራቸው ዋነኛ የትብብር አጋሮች አንዷ …
እሥረኞቹ የተለቀቁት ባለፈው ጥቅምት ወር ባደረጉት ስምምነት መሠረት መሆኑንም ሣላሁዲን ማኦ አመልክተዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስምምነቱ በአንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ ግለሰብ ጋር ያደረገውና በእርሣቸው ወገን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኦብነግ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡ …
የአውሮፓዊያኑ 2011 ዓ.ም እነሆ ሁለተኛ ሣምንቱን እያገባደደ ነው፡፡ የተፈጥሮ አካባቢ ክስተቶች በምጣኔ ኃብቱ እና በፖለቲካው ላይ የሚያሣድሩት ጫናና ተፅዕኗቸው እየሰፋና እየጎላ የሚሄድ መሆኑም ይታያል፡፡ በምግብ ደኅንነት፣ በኃይል አቅርቦትና መጓጓዣም ላይ ያተኮሩት ፖሊሲዎች ሊዘረዘሩ ከሚችሉት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ዘርፎች በተፈጥሮ …
በውኃ ኃብት የበለፀገችው ኢትዮጵያ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት እና ከ30 እስከ 40 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል የወንዞች ዕምቅ አቅም ቢኖራትም እስከአሁን ግን ያለማችው መሬት ከምትችለው ከ2 ነጥብ 5 ከመቶ የማይበልጥ እና የምታመነጨው ኃይልም 2 ሺህ …
የቪኦኤን የገና ዝግጅት ያድምጡ፡፡
ጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም ማለዳ በቤይሩት ሰማይ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ይሄው አንድ አመት ሊሞላው ጥቂት ሳምንታት ቀርተዋል። የአውሮፕላኑ የአደጋ መንስዔ የፓይለት ስህተት ነበር በሚል የሊባኖስ ጋዜጦች ዘግበዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምርመራ ውጤቱ ገና አልታወቀም ሲል አስተባብሏል። የቦይንግ …
የሊባኖስ የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በፓይለት ስህተት መከስከሱን ዘገቡ Read more »
የጊቤ ሁለት ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተመርቆ በተከፈተ በጥቂት ቀናት ውስጥ በማስተላለፊያ መሥመሩ ላይ ደርሶ በነበረው የአለት ናዳ ምክንያት ሥራው ለአሥራ አንድ ወራት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሣል፡፡ ጥገናው ተጠናቅቆ የኃይል ማመንጫው አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዕሁድ ታኅሣስ 17 ቀን 2003 ዓ.ም …
በደርግ ዘመን የተፈፀሙ በደሎችንና ጥፋቶችን ሃገራዊ ይቅርታና ዕርቀሠላም ባሉት መንገድ ለመጨረስ አራት የኢትዮጵያ አብያተ-ዕምነት መሪዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጥሪ አቀረቡ፡፡ በያዝነው ታኅሣስ መጨረሻ የሠላምና የዕርቅ በዐል ለማድረግም ዕቅድ ተይዟል፡፡ የኃይማኖት መሪዎቹ ዕሁድ ታኅሣስ 10 ቀን 2003 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል …
ኢትዮጵያ በአሥሮች የሚቆጠሩ ተቀባይነት ካለው ሥነ-ምግባር ተፃራሪ በሆነ ሁኔታ የሚንቀሣቀሱ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት ማሣደጊያዎችን ለመዝጋት እያቀደች መሆኑን የአዲስ አበባው ሪፖርተራችን ፒተር ሃይንላይን ያስተላለፈው ዘገባ የመጀመሪያ ክፍል ቀደም ሲል መተላለፉ ይታወሣል፡፡ ያንን በማጭበርበርና በውንብድና አድራጎት ታጭቋል የተባለ፤ እንዲያውም ሥር ሰድዶ መንሠራፋቱና …
በአውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ2000 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት የመነደፍንና የሞትን መጠን ከሃምሣ ከመቶ በላይ መቀነስ መቻሉን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የወባ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም ዋና ተጠሪ ገለፁ፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት ከትናንት በስተያ ባወጣው አዲስ …
ከአገራቸው በልዩ ልዩ መንገድ ተሰደው፣ በሱዳንና በሊብያ አቋርጠው የወጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ማልታ ውስጥ ይገኛሉ። የተወሰኑት የፖለቲካ ጥገኝነት አግኝተው ከማልታ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ እየተጠባበቁ ያሉ ሲሆን፤ ሌሎች በርካቶች ግን፣ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆኖ እዚያው ማልታ ውስጥ ያለ ሥራ፣ በድንኳንና …
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማልታ በድንኳንና በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮች ውስጥ ለመኖር ተገደናል ይላሉ። Read more »
ተወልዶ ያደገው ናዝሬት ከተማ ነው። አብዱረዛቅ ረሽድ አደም ገና በስምንት ዓመቱ የሰርከስ ልምምድ ለማድረግ ከትምህርት ቤት መልስ ከበጎ ፈቃድ አሰልጣኙ ሙያ ሊቀስም ሲሄድ ቤተሰቦቹ ደስተኞች አልነበሩም። “ይሄንን ቧልትና ዝላይ ትተህ በትምህርትህ በርታ” ነበር የወላጆቹ ምክር። በየቀኑ ወሳኝ ክህሎቶቹን እየተማረ የነበረው …
የዘመን ቀለማት ቁጥር ሁለት የግጥም ስብስብ ለውይይቱ መነሻ የሆነን መፅሃፍ ነው። መፅሃፉ ለህትመት የበቃው፥ ከግጥም መፅሃፋቸው ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ የግጥም ሥራዎቻቸውን የማሳተም ዕድል ያላገኙ ጀማሪ ገጣምያንን ሥራዎች ለህትመት ብርሃን ለማብቃት አስበው በተነሱ አንድ ገጣሚና በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ትብብር በተከፈተ ተዘዋዋሪ …
“የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ቋንቋን ወይንም ብሄር ብሄረሰብን መሰረት አድርጎ በመከፋፈል አይሳካም” ልደቱ አያሌው ሰሞኑን ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን፤ በተለይ በመንግስቱ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የቴሌቪዥንና የሬድዮ ጣቢያዎች “ብሄር ብሄረሰቦች…” የሚሉ ሙዚቃዎች ያሰማሉ፣ ቃለ-መጠይቅ ይደረጋል፣ በዋና ከተማዋ የሙዚቃና የባህል ስነስርዓቶች ይሰናዳሉ። በየዓመቱ ከሚከበረው የብሄር …
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የፌዴራሊዝም ጉባኤ ሲተነተን Read more »
ኢትዮጵያ በአሥሮች የሚቆጠሩ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት ማሣደጊያዎችን ለመዝጋት እያቀደች መሆኑ ተነግሯል፡፡ ሃሣቡ ተቺዎቹ የሕፃናት ንግድ በሚሉትና እየተስፋፋ በመጣው በውጭ የጉዲፈቻ ተግባር ላይ ለተሠማሩ ወኪሎች ፍቃድ ማደስ ማቆምንም እንደሚያካትት ታውቋል፡፡ “ድኃይቱ ሃገር በበረከተ የውጭ ወረት እየነቀዘ ባለው ማኅበራዊ መዋቅር ላይ ዐይኗን …
(VOA) — ሥርጭቱን ለኢትዮጵያና አካባቢዋ፣ እንዲሁም ከሰሜን አሜሪካ በስተቀር በመላው ዓለም እንደሚያደርስ የገለፁት የኢሣት ቃልአቀባይ አቶ ክንፉ አሰፋ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት መግለጫ ከተመሠረተ የዘጠኝ ወራት ዕድሜ ያለው የጣቢያቸው ሥርጭት ለአራተኛ ጊዜ ለመቋረጥ ተገድዶ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ አቶ ክንፉ ሲናገሩ ፕሮግራሞቹን ተቀብሎ …
በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ደመናዎች ሰሃራ በረሃንና አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው አሜሪካን በከባዶቹ የባሕር ማዕበሎች (ሃሪኬኖች) እንደሚመቷት አንድ ባለሙያ አስታወቁ፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የከኔክቲከት ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰርና የአየርና የውኃ የተፈጥሮ ሃብቶች ተመራማሪው ዶ/ር መኮንን ገብረሚካኤል ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ የአየር ንብረት ለውጥ …
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ ፕሮግራም – ዩኤንኤድስ ጋር በመተባበር ያወጣው የቅኝት ሪፖርት በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ሥርጭት መጠንና ከኤድስ ጋር የተያያዘ ሞት መቀነሱን ገለፀ። ዓለምአቀፍ የኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ የወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቁጥጥር፣ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ላለ ዜጎች የሚደረግ ህክምና እንዲሁም …
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚያገለግለውን የእድገትና የመሠረታዊ ለውጥ ዕቅድ አፀደቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎች ለዕቅዱ ስኬት አብረው እንዲሰለፉ ጥሪ አቀረቡ። ብቸኛው የመድረክ ተወካይ ግን ዕቅዱ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የተዘጋጀ ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ለዝርዝሩ የመለስካቸው አምኃን ዘገባ …
የዘንድሮውን የዓለም ኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ተማሪዎች ለተለያዩ ጫናዎች ሳይበገሩ ጤንነታቸውን እንዲጠብቁና ከግባቸው እንዲደርሱ ያሳሰቡ ስብሰባዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ቅጥር ግቢዎች ተካሂደዋል፡፡ ተማሪዎቹም በዝግጅቶቹ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ ለግማሽ ቀን በተካሄዱት በእነዚህ ስብሰባዎች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከፍ ወዳሉ ደረጃዎች የደረሱ ሰዎች …
በደቡብ ሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ዘመን ከሃገራቸው የወጡ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ዘጎች የፊታችን ጥር 1 ቀን ለሚካሄደው የደቡብ ሱዳን የነፃነት ውሣኔ ሕዝብ ድምፃቸውን በያሉበት ለመስጠት በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ የሚገኘው ሪፖርተራችን ፒተር ሃይንላይን እዚያ በተቋቋመ የምዝገባ ጣቢያ ላይ አንድ …
ሀፍቶም ካህሳይ በመቀሌ ሐይደር ቀበሌ ውስጥ ይኖራል። ገና የአሥራ አንድ ዓመት ልጅ እያለ ነው በደረሰበት ችግር ምክንያት የዓይን ብርሃኑን ያጣው። አሁን ሃያ ሦስት ዓመት የሞላው ሲሆን፥ በዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርቱን እየተከታተለ በትርፍ ጊዜ ይሠራል። ማየት ለተሳናቸው የሚጠቅሙ መጻሕፍትም በድምፅ ለማዘጋጀት ጥረት …
በምስራቅ ሶማሊ ክልል ወደ 150ሽህ ሰዎች “ለም መሬት” ወዳለበት አካባቢ ተዛውረዋል ሲል የፌደራል ጉዳዮች ምንስቴር አስታውቋል። የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ሽፈራው ተክለማርያም ለብሉምበርግ የዜና አገልግሎት በሰጡት ቃል መንግስት በነዚህ ክልሎች የሚኖሩ ሰዎችን ኑሮ “ለማሻሻል” ይፈልጋል ብለዋል። በዚህም መሰረት በጋምቤላና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ …
የመሬት አጠቃቀምና በዓለምአቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለው መንግሥታት “ኪራይ” የሚሉት፣ የሚቃወሙት ተሟጋቾች ደግሞ “የአፍሪካን መሬት መቀራመት” የሚሉት አያያዝ የአፍሪካን ግብርና ሊጎዳ እንደሚችል አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የምግብ ሰብል በዓለም ላይ የተትረፈረፈ እንዲሆን ስለሚያስችል ዋጋውን ያወርደዋል፤ የዓለምን የምግብ ዋጋም ያረጋጋል ብለው ያስባሉ፡፡ …
ቻይና ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ አስተዋፅዖ እያደረገች ነው ማለት ግን “በምዕራቡ ዓለም የዴሞክራሲ ግንባታን ከምንረዳበት ትርጉም አኳያ ምንም ትርጉም የለውም” ብለዋል፡፡ ረቡዕ ዕለት የቻይና ፕሬዚደንት ሁ ጂንታዎ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረችበትን አርባኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያ ፕሬዚደንት …
ወደ ደደቢት በረሃ ከወጡትና ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ከመሠረቱት 11 ሰዎች አንዱ የሆኑት አቶ አስገደ ገብረሥላሴ የምሽቱ ዴሞክራሲ በተግባር ፕሮግራም እንግዳ ናቸው፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ቀውስ ፈጣሪዎች ተብለው ከተባረሩ የድርጅቱ ነባር አባላት መካከል አንዱ ሲሆኑ አሁን የአረና ትግራይ አመራር አባል ሆነው …
ከዓለም የኤችአይቪ ሥርጭት ሁለት ሦስተኛውን ድርሻ የያዙትን ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪካ ሃገሮችን ጨምሮ በቫይረሱ ሥርጭት ላይ በመላው ዓለም መሻሻል መመዝገቡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡ በኤችአይቪ አዲስ የሚያገኘውና በኤድስ ምክንያትም የሚሞተው ሰው ቁጥር በእጅጉ የቀነሰ ቢሆንም ይበልጥ ትግል እንደሚያስፈልግ ግን አሳስቧል፡፡ …
ሰሜን አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና አሜሪካዊያን የሕክምና ባለሙያዎች በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ ተሰብስበው በጤና አጠባበቅና በከፍተኛ ደረጃ ባለው የሕክምና አገልግሎት፣ እንዲሁም በድኅረምረቃ መርኃግብር የኢትዮጵያ አያያዝ ላይ መክረዋል፡፡ በዚህ ሕዝብ ለሕዝብ የሚባል ድርጅት ባዘጋጀው ለሁለተኛ ዓመት በተካሄደ የአንድ …
በትግራይ ክልል የአድዋ ሠንሠለታማ ተራሮች በመባል የሚታወቁት ከፍተኛ ቦታዎች በታሪክ በጥሩ መልኩ ቢታወሱም የተራቆቱ ስለመሆናቸው ግን እውነት ነው፡፡ በጦርነትና በድርቅ አደጋ ምክንያት አካባቢው የነበረውን የደን ሽፋን እያጣ መምጣቱ በግልፅ ይታያል፡፡ ይህም ሆኖ ግን የተራቆተውን መሬት እያዩ ብቻ ከማዘን ይልቅ በጥሩ …
ቁጥራቸው ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጋ ሥራ ፈላጊ ተዘዋዋሪ ኢትዮጵያዊያን ሃራዳ በተባለች ሰሜናዊት የየመን ከተማ ያለ ምግብ፣ ውኃና መጠለያ መሄጃ አጥተው ይገኛሉ። ሃራዳ ውስጥ መውጫ አጥተው ከሚገኙት መካከል ከሳሊም አህመድ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገናል። ሳሊም ሰይድ ከሁለት ወራት በፊት ከጂዳ ተባርረው …