ኢትዮጵያ በአስር ዓመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እገባለሁ አለች።

እስካሁን ባሉት አመልካች ሁኔታዎች ከተሄደ ኢትዮጵያ በመጪው አስር ዓመታት ጊዜ ዉስጥ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመሆን ግባቸው እንደሚሳካ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በተከፈተዉ የአፍሪቃ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቶች ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈኛ ንግግር ነው አገራቸው በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ነዳጅ አምራች ያልሆኑ አገሮች አንዷ መሆኗን የተናገሩት።

“ፖሊሲዎቻችንና ስታራቴጂዎቻችን ብቃትና ጥራታቸዉን አረጋግጠዋል። እናም አሁን ያሉትን አመልካቾች ከተከተልን፥ ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አስር ዓመታት ጊዜ ዉስጥ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመሆን ግባችንን እናሳካለን፤” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ እምነታቸውን ገልጠዋል። የዛሬውን ጉባኤ ያዘጋጀዉ ከአርባ በላይ አገሮች ብሔራዊ ምክር ቤቶች አባል የሆኑበት የፓን…