እተጌ ጣይቱ በ1900 ዓ.ም በእየሩሳለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያ የጻፉት ታሪካዊ ደብዳቤ እተጌ ጣይቱ ሰኔ ፪፱ ፩፱፻ / ስኔ 29 1900 / ዓ.ም በየእሩሳለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያ የጻፉት ታሪካዊ ደብዳቤ። የተላከ፡ ከእቲጊ፡ ጣይቱ፡ ብርሃን፡ ዘኢትዮጵያ። ይድረስ፡ ለማህበር፡ ዱር፡ ሥልጣን፡ ወደብረ፡ ገነት፡ ዘኢየሩሳለም። እንዲት፡ ሰነበታችኋል። እኔ፡ እግዚአብሔር፡ ይመስገን፡ ደህና ነኝ። እናንተ፡ ብትስማሙ፡ እርስ፡ በርሳችሁ፡ ብትፋቀሩ፡ አንድነታችሁን፡ ብታፀኑ፡ ይሻላል፡ እንጅ […]

The post “ትግሬ የብቻው ነው፡ ሸዋ የብቻው ነው፡ ቢገምድር፡ ጎጃም የብቻው ነው፡ እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ” appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ምርጫ ቦርድም ነገሩን በቅንነት በማየት ጥቃቅን ግድፈቶችን ቸል በማለት ወደ ምርጫው እንዲገቡ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን:: …. እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን ለሚገነባው የመድብለ ፓርቲ( multi-party) ሲስተምና ለሃገሪቷም ትልቅ ውድቀት ይሆናል።” “ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰት በባለስልጣኖች ይፈጸማል። ሳይውል ሳያድር በዜጎች ላይ በደል የሚያደርሱት ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።የሰብአዊ መብት ጥሰት ከባድ ወንጀልና ሃጢያትም ነውና።” ዳንኤል ጣሰው በአለም […]

The post ወንጌላዊ ዳነል ጣሰው በፌስ ቡክ የለቀቁት ጽሁፍ “አንድነትና መኢአድ ጋር ያለው ችግር ተወግዶ ወደ ምርጫው እንዲገቡ ያስፈልጋል” appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ታሪኩ ዝዋይ እሥር ቤት ወንድሙን ለማየት ይገባል። እዚያም፣ “ተመስገንን ጥሩልኝ ” ሲል ፖሊሶችን ይጠይቃል። በዚህ ግዜ የመቶ ዓለቃ ማዕረግ ያለው ወታደር (ፖሊስ) ተመስገንን መጠየቅ እንደማይችል ይነግረዋል። ታሪኩም “ምን ተፈጠረ ወንድሜን እንዳልጠይቀው የተከለከልኩት ?” በማለት ለፖሊሱ ጥያቄ ያቀርባል። ፖሊሱም በማመናጨቅ “ውጣ” ይለዋል። ነገሩ ያላማረው ታሪኩ ለወንድሙ ያመጣውን ስንቅ እንደያዘ ወደ በሩ ያመራል። ነገር ግን” ውጣ” ያለው […]

The post ሰበር ዜና የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ድብደባ እና ዘረፋ በዝዋይ እስር ቤት ፖሊሶች ተፈጸመበት appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ከአንድነት  ድጋፍ ማህበር በሰሜን አሜሪካ  የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ   ጉዳዩ፡  ፡ በቅርቡ  በኢትዮጵያ  ምርጫ  ቦርድና  በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በተመለከተ፡፡   እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከምርጫ ቦርድ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ በ4 ቀን ውስጥ እንዲጠራና የፓርቲውን  መሪ በድምፅ አሠጣጥ መመሪያው መሠረት እንዲመርጥ ስለተገደደ አንድነት ፓርቲም በሆደ ሰፊነት በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ […]

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ/አንድነት/ የተሰጠ መግለጫ የአንድንታ ፓርቲ በኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲፈጠር በምንም መለኪያ በገለልተኝነት የማንጠብቃቸውን የዲሞክራሲ ተቋማት በተግባር ለመፈተን እንዲቻል የሁለት ሺ ሰባት ምርጫን በሁሉም ሂደቶች ህዝቡን በማሳተፍ እንደሚወዳደር እና ህዝብን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ እና የኢህአዴግ አገዛዝ የመጨረሻ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይህን ስንወስን እነዚህ ተቋማት ገለልተኝነታቸውን አረጋግጠው ታሪክ የሚሰሩበት እድልም ያገኛሉ […]

ከመከላከያ እስታፍ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በከፍተኛው የመከላከያ ሰራዊት እርከን ሲሰሩ የቆዩ ከፍተኛ መኮነኖች ሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ፥ ሌተናል ጀኔራል ሰዓረ መኮነን፥ ሜጀር ጀኔራል ሞላ ሃይለማሪያም፥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በላያቸው ላይ እየፈፀመው ያለውን ተግባር ትክክል አይደለም በማለት በዚህ ሳምንት ወደ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የቅሬታ ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፣ በግላቸው ከፃፏቸው ደብዳቤዎች የተወሰኑትን ለመጥቀስ […]

ጥር ፫ ቀን ፳፻፯ January 11, 2007 ህወሓት/ኢህአዴግ  አሁንም  እንደገና  በሀገሪቱ  ምርጫ ሂደት ብቻውን ሮጦ  ብቻውን ለማሸነፍ እንዲችል አስከፊ አፈናውንና እመቃውን  አጠናክሮ ቀጥሏል።  ተፎካካሪ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከፖለቲካው በተለይም ከምርጫው ሂደት ተገፍትረው እንዲወጡ ለማድረግ ሳይታክት እየሰራ ነው። በሰሞኑም በአንድነት፣ በመኢአድና በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የምርጫ ቦርድ ተብየውን በመጠቀም የሚደረገው ማዋከብ ህወሓት/ኢህአዴግ በምርጫው ሂደት ውስጥ ብቻውን ከራሱ […]

በቃል የቀረበው አቤቱታ ከድምጽ ክምችት ክፍል ጠፍቷል ተብሏል በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች እና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገብ ያሉ የሽብር ተከሳሾች በቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር መካከል ያለው አቤቱታ እስካሁን እልባት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰማያዊ፣ […]

ነገረ ኢትዮጵያ በኢቦላ ስጋት የታገቱት 21 ቀን ሊቆዩ ይችላሉ ተባለ በኢቦላ በሽታ ስጋት ከቤታቸው እንዳይወጡና እንዳይገቡ በፖሊስ እየተጠበቁ ያሉት የፈረንሳይ ሌጋሲዮን ነዋሪዎች በሽታው እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው እስኪታወቅ ድረስ 21 ቀን ቤታቸው ውስጥ ሊቆዩ እንደሚችሉ ከጤና ጥበቃ ባለስልጣናት እንደተነገራቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ከቀኑ 12 ሰዓት አካባቢ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት መጥተው የጎበኟቸው […]

ፍኖተ ነፃነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሬድዩ ፋና እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ/ኢቲቪ) በአንድነት ፓርቲ ላይ የጠነሰሱት ሴራ ተጋለጠ፡፡ አንድነት፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ያሰባስባል›› የሚል ውንጀላ እየቀረበበት እንደሚገኝ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለፍኖተ-ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ራዲዮ ፋና ‹‹አንድነት ከግንቦት ሰባት ገንዘብ ይቀበላል፣ በውጪ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካልሆኑ ሰዎች ገንዘብ ይሰበስባል›› የሚል ውንጀላ እያቀረበ መሆኑን የፓርቲው […]

በነገረ ኢትዮጵያ • ፖሊሶች የደረጃ እድገት እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል የአማራ ክልል መስተዳደር በግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ተከትሎ አመጽ ከተከሰተ ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን ስልጠና ለክልሉ ፖሊስ፣ ለማረሚያ ቤት ፖሊስ፣ ለሚሊሻና ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እየሰጠ መሆኑን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ስልጠናውም፤ ለፖሊሶች በዞን እንዲሁም ለሚሊሻና ለፀጥታ ጉዳይ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ […]

አምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም መሠረትም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ እንቅስቃሴ ገብተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቦርዱ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ካለፈው ጥር 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ቦርዱ ይፋ ካደረገውና እየተገበረው ካለው የምርጫ […]

በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ፣ ዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ መሀል የተደረገውን ውህደት በተመለከተ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በዛሬው ዕለት፣ ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7፣ ለፍትህ ለዴሞክራሲና የነጻነት፣ ንቅናቄ፣ ድርጅቶች፣ ተዋህደን “አርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ”፣ በሚባል ሥም መጠራት መጀመራችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስናበስር፣ እጅግ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል። የኢትዮጵያ […]

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርስ የነበረው ጣይቱ ሆቴል በእሳት ወደመ:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታዲያ “አቃጠሉት” እና “አቃጠሉበት” የሚሉት ድምጾች በርክተዋል:: “አቃጠሉበት” የሚለውን የጨዋታ ክር መምዘዝ ከጀመርን; የቤቱ ባለቤት ፍጹምዘአብ ጋር ያደርሰናል:: ፍጹምዘአብ የትግራይ ተወላጅ ነው:: ግን ደግሞ የትግራይ ተወላጅ ስለሆነ ከስልጣን ዙፋን ላይ አልተቀመጠም:: ይልቁንም በዘመነ ኢህአዴግ ከአምስት አመታት በላይ የወያኔን እስር ቤትን ቀምሶ የወጣ ሰው ነው:: አሁን በተቃጠለው […]

ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ተዘጋጅቶ በነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ በራሪ ወረቅት ሲበትን ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሲሳይ ዘርፉ በፌደራል አቃቤ ህግ ክስ ቀርቦበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታዬ ሲሆን በነገው ዕለት (ጥር 7/2007 ዓ.ም) የሰማያዊ እና የኦህዴህ ሊቃነ-መናብርት ለተከሳሽ ተከላካይ ምስክር ሆነው እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ ተከሳሹ አቶ ሲሳይ ዘርፉ ‹‹…‹ነጻነት […]

ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍኖተ ነጻነት የፓርቲውን የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ተክሌ በቀለን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ታህሳስ 25 ቀን 2007 ኣመተ ምህረት ባደረገው ስብሰባ መጪውን ምርጫና ከምርጫው ጋር ተያይዘው ስለሚመጡ ጉዳዮች፤ እንዲሁም ከምርጫው በሁዋላ ፓርቲዎች ሊኖራቸው ስለሚገባው ትብብርና ውህደት የሚያመቻች ኮሚቴ ተቋቁሟል። በስብሰባው፣ ፓርቲዎች በትብብርና በውህደት […]

ትላንትና ያየሁት የአንድነት ፓርቲ አባላት ፎቶ ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርጾ ዋለ፡፡ ፎቶው ላይ ምርጫ ቦርድ የጠራው አስገዳጅ ጉባኤ ላይ ለመገኘት መጥተው ፓርቲው ቢሮ ውስጥ መሬት የተኙ አባላት ፎቶነበር፡፡ አንዱን እዛ መሬት ላይ የተኛ አባል አሰብኩት፡፡ “Most probably” ብዙም የኢንተርኔት ተጠቃሚ አይደለም፡፡ ( ኦፍ ላየን ያለው ነገር ደሞ ኦን ላየን ካለው ይበልጥ ተስፋ ያስቆርጣል) አገር ቤትም ሁሉም […]

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ አንዳርጋቸው ጽጌ በህወሀት ወንድሞች ቡድናዊ የሸፍጥ ከበባ ስር ቮልቴር (ፍራንኮይስ ማሬ አሮት) እንዲህ በሚለው ምልከታቸው በስፋት ይታወቃሉ፣ “አንድ ሰው ከሚሰጣቸው ምላሾች ይልቅ በሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ምንነቱ ይገመገማል፡፡“ ቮልቴር ብልህነትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ የሚል ምልከታም በተጨማሪ አካሂደዋል፣ “ጥሩንባቸውን እየነፉ እጅግ ብዛት ያለውን ህዝብ ካስጨረሱ ገዳዮች በስተቀር ሁሉም ህይወትን ያጠፉ ነብሰ ገዳዮች […]

የጉዳያችን ጡመራ ወቅታዊ ምልከታ ኢትዮጵያ ከንጉሳዊ መንግስት ወደ ወታደራዊ ደርግ ከወታደራዊ ደርግ ወደ ኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ከተሻገረች አራት አስር አመታት አለፉ።ከአራት አስር አመታት በፊት በየካቲት፣1966 ዓም የተነሳው የለውጥ ነፋስ ኢትዮጵያ ልጆቿን ሲያሰድድ እና ሕዝቡን ሲያስነባ ዘመናትን አሳልፏል። ዛሬ በመላው አለም ከሁለት ሚልዮን ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ከቀያቸው ተሰደው በማያውቁት ቦታ በስደት ይኖራሉ።ሕዝብ የገቢው መጠን ከእለት ወደ እለት […]

አንዳንዶች ከማይቀረው ዕጣ ፈንታቸው አይናቸውን ጨፍነው ይሸሻሉ፤ የሚሸሹበት መንገድ ግን ወደማይቀረው ዕጣ ፈንታቸው በፍጥነት ያደርሳቸዋል፡፡ ሰሞኑን ኢህአዴግ በምርጫ ቦርድ በኩል የያዘውን ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ዘመቻው አንድነትን፣ መኢአድንና ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ 2007 ሜዳ ገፍቶ ማስወጣት ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በኢህአዴግ ጥቁር መዝገብ ላይ የሰፈሩበት ምክኒያት ደግሞ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በምርጫ 2007 ኢህአዴግ የሚያጭበረብርበትን መንገድ ዘግተው ከፍ ባለ […]

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት  ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ በጋራ ባወጡት መግለጫ ”ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ ደርሰናል” ብለዋል። ድርጅቶቹ አያይዘውም ”አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት […]

የአንድነትን ፓርቲና የምርጫ ቦርድ – ደብዳቤ ልውውጦች ዝርዝር ሁኔታ በማሰረጃ የተመሰረተ ታህሳስ 19-20፡ አንድነት ፓርቲ ታህሳስ 19-20/2006 ዓ.ም ልዩ ጠቅላላ ጉባዔ አካሄድ፡፡ ይህ ጠቅላላ ጉባዔ ልዩ የተባለበት ምክንያት የአንድነት አምስት ዓመት ስትራቴክ ዕቅድ ላይ በተቀመጠው መሰረት ፓርቲ ከ2007 ዓ.ም ምርጫ ቀደም ብሎ የአመራር ሽግሽግ በማድረግ ፓርቲውን በአዲሰ አመራር ወደ ምርጫ ይዞ ለመግባት በተቀመጠ ግብ መሰረት […]

”ይቺን ነው መሸሽ…” አለች ኢህአዴግ! እንግዲህ የሰላማዊ ትግል አማራጮች በተዘጉ ቁጥር ሌሎች አማራጭ ትግሎችን የመረጡ ታጋዮች ቁጥራቸው እና ህብረታቸው እየበዛ ይመጣል። ”እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም… ነገር ግን በሀገሬ ጉዳይ ገፍቶ የመጣውን ለመመከት ወደኋላ የምል አይደለሁም” እንዳሉት ጣይቱ፤ ጦርነት የሚወደድ ነገር ባይሆንም አማራጭ ከጠፋ ግን ምንም ማድረግ አይቻልም። ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ እና እንዳልነገርኳችሁ፤ በ ሁለት […]

ሰማያዊ ፓርቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤትን እስከ ጥር 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በጽሑፍ ይቅርታ ይጠይቅ በማለት የተላለፈው ውሳኔ ከሕግ አግባብ ውጪ ስለሆነ ተቃውሞውን በመግለጽ ይቅርታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ፡፡ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ ባለፈው ሐሙስ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድን ስም አጥፍቷል ብለዋል፡፡ ‹‹በተሻሻለው የምርጫ ሕግ አንቀጽ […]

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንድነት ፓርቲ በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደማይገኝ ገለጸ። ምርጫ ቦርድ በአራት ቀናት ዉስጥ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ አመራሮችን በሚስጥር አሰጣጥ መምረጥ እንዳለበት መናገሩ ይታወሳል። ሆኖም ትላንት አርብ በምርጫዉ ታዛቢ እንዲልክ በደብዳቤ የተጠየቀው ምርጫ ቦርድ “አየለ የሚባል ሰው ሌላ የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ይደረጋል የሚል ደብዳቤ ስላሰገባ፣ በሁለት ቦታ መገኘት አንችልም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። […]

ሰበር ዜና – አንድነትን ፓርቲ ምርጫዉን መሳትፍ የለበትም የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ እንደተወሰነ ፣ ከሕወሃት አመራሮች ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ገለጹ

አንድነት ፓርቲ በድጋሚ የምርጫ ቦርድን ደባ ለማክሸፍ ጠቅላላ ጉባዬ ጠርቷል:: – አንድነት ፓርቲን ከሰላማዊ ትግሉ ለማስወጣት የተደረገውን ደባ ተጋልጧል:: የወያኔው አምባገነን ጁንታ የአንድነት ፓርቲ በ2007 በሚደረገው ምርጫ ላይ እንዳይሳተፍ በሕወሓት/ኢሕአዴግ ፖለቲካዊ ውሳነ ተደርጎበት ወደ ምርጫ ቦርድ እንደተላለፈ እና ፓርቲውን ከምርጫው ለማስወጣት ደባ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቆመ:: እንደ ምንጮቹ ከሆነ ሕወሓት/ኢሕአዴግ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ከማሰር […]

ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስኞ እለት ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት ታንኮችን የጫኑ የመከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች ባህር ዳር ከተማ መግባታቸውን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለኢሳት እንዳሉት፤ ከየት አቅጣጫ እንደመጡ ያልታወቁ የጦር ተሸከርካሪዎች ሰኞ ምሽቱን ባህርዳር ወደሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት(መኮድ) ካምፕ ገብተው ካደሩ በሁዋላ በማግስቱ ጧት ወደ ጎንደር አቅጣጫ ተጓጉዘዋል። ተሸከርካሪዎቹ […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ እሁድ ጥር 3 ቀን ጠቅላላ ጉባኤው ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው። የጠቅላላ ጉባዔ መደበኛ ስብሰባ በየሶስት አመቱ ሲሆን አስቸኳይ ወይንም ልዩ የጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንደሚቻል የአንድነት ደንብ በግልጽ ያስቀምጣል፡ በአንድነት ደንብ መሰረት አስቸኳይ ወይም ልዩ ጠቅላላ ጉባዔ መጥራት የሚቻለው ከጠቅላላ ጉባኤ አባላት አንድ ሶስተኛው ሲጠይቁ ወይንም ምክር ቤቱ ሲወስን ብቻ ነው። የጠቅልላ […]

አንድነት መኢአድና ሰማያዊ ከምርጫ ቦርድ ጋር ሲካሰሱ መድረክና ኢዴፓ ውይይት ይፈልጋሉ:: አንድነትና መኢአድ የውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ በምርጫ ላይሳተፉ ይችላሉ::የሚል መግለጫ ምርጫ ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በራዲዮ ፋና መስጠታቸውን ተከትሎ;የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ስብሰባን ረግጦ መውጣቱን አስታኮ በመጭው ምርጫ ላይ ውጥረት ማጥላቱን መረጃዎች ሲጠቁሙ በሌላ በኩል መድረክ እና ኢዴፓ የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉን […]

አገቱኒ የምትለውን የግዕዝ ቃል በመጀመሪያ በመዝሙረ ዳዊት ላይ ነው ያየሁዋት ፣ መዝሙር (3)፣ እንዲህ ነበር ሰንጠር ብላ የገባችው ። ወተንሳእኩ እስመ እግዚያብሔር አንስአኒ አይፈርህ እመ አእላፍ ሕዝብ ዕለ አገቱኒ ወቆሙ ላዕሌየ ። ትርጉሙም …. እግዚያብሔር አንቅቶኛልና እና ነቃሁ ከአእላፍ ሕዝብ ከከበቡኝም አልፈራም ። ስለዚህ ( አገቱኒ =ከከበቡኝም ) ማለት ይሆናል ። መያዝም አቻ ቃል ነው […]

ከ27 – 7 ብቻ የሕወሀት መሪዎች በረሃ እያሉ የተነሱት ፎቶ ነው ። በፎቶው ከሚታዩት 27 አመራሮች 19 ኙ በተለያየ ጊዜ በመለስ ዜናዊ የተባረሩና የተገደሉ ሲሆን 7 ቱ በስልጣን አንዱ መለስ ዜናዊ ደግሞ በሞት ተለይተዋል ። በመለስ ዜናዊ የተቀነባበረ ሴራ እንዲገደሉ ከተደረጉት መካከል ተክሉ ሃዋዝ ሲሆን ለሞት ያበቃው በኤርታራ ጉዳይ ጠንካራ አቋም በመያዙ ነበር ። የደህንነት […]

የማለዳ ወግ …የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን ! * የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ *” ክብር ሞቱ ለሰማዕት “  ዛሬ የምናዘክረው ሰው የኢትዮጵያ አፈር ፍቅር ጠርቶት ለጉስቁል ተገፊው ደሃ የሀገሬ ሰው ህይዎት ትንሳኤ ተግቶ ለውጥ ስላመጣ  ጠቢብ ነው። ዝካሬ ታሪኩ ቢያስተምረን ፣ አርአያ ሰብዕናው ግብአት፣ ተሞክሮ ቢሆነን ፣ ህይዎት ንብረቱን በእኛው ቀዬ ስላፈሱሰ ትጉት ሀኪም ነው […]

የስብሃት ነጋ ባለቤት ሻለቃ ፀዓዱ ትባላለች፤ ከጣሊያንና ኤርትራ ትወለዳለች። ሁለቱም ከጫካ ጀምሮ ተመሳሳይ ባህርይ አላቸው፤ ሶስት ልጆች ከወለዱ በኋላ በ1989ዓ.ም ፀባቸው እያየለ በመምጣቱ የፓርቲው ፖሊት ቢሮ አባላት ዘንድ ይቀርባሉ። ምክንያቱም የፓርቲው ህግ ይህን ስለሚል ነበር። መለስ በሚመሩትና 8 አመራሮች በተሰየሙበት ፀዓዱ ስትናገር « ስብሃት በትዳሬ ላይ እየማገጠ ስላስቸገረኝ ፍቺ እፈልጋለሁ» ስብሃትም ቀበል በማድረግ « አንቺስ […]

ግንቦት 7 <<ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌን እንሁን!!!>> በሚል ርእስ ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን ባስነበበው ርእሰ-አንቀጽ፤በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እሁድ እለት በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በግፍ እስር ላይ የሚገኘውን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለ 10 ደቂቃ አቅርቦት እንደነበር በማውሳት፤ይህ የ10 ደቂቃዎች ምስል ለቁጥር በሚያታክት ሁኔታ ተቆራርጦ የተቀጣጠለ በመሆኑና አቶ አንዳርጋቸው በትክክል ምን እንዳለ […]

ጠንቋይ ታምራት ገለታ ለእስር የበቃበት ምክንያት ተከታዩን እንደሚመስል የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ጠንቋይ ታምራት ሸራተን ጐራ ይላል፤ አካሄዱ ስብሃት ነጋን ለማግኘት ነበር። ሲያገኛቸው ትእቢት በተሞላበት አነጋገር « እርሶ ዘንድ የላኩኝ ባለስልጣናት ናቸው። ከበቂ በላይ ገንዘብ ያለኝ ሰው ነኝ። በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘቤን ኢንቨስት ማድረግ ስለምፈልግ መሬት እንዲሰጠኝ ትእዛዝ ያስተላልፉልኝ» ይላል። ስብሃትም « ምናልከኝ?» ይሉታል። ታምራት ደረቱን ለጥጦ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተመለከተ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የማፅዳት ሃላፊነት ከተወጣ በኋላ ገዢው ፓርቲ ጥርሱን የነከሰበት ይመስላል፡፡ ብዙ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እስከማድረግም ደርሰዋል፡፡በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ ትርጉም […]

ኢሳት በሰበር ዜና እንዳቀረበው ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ከሆላንድ ኤርትራ ገቡ። ከኢሳት እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ጋዜጠኞቹ አስመራ የገቡት ትናንት ሲሆን በኤርትራ ቆይታቸውም እዚያ ያለውን ሃይል እንደሚጎበኙና ዘገባም እንደሚያቀርቡ በተጨማሪም የኤርትራ ባለስልጣናትን እንደሚያነጋግሩ ይጠቁማል። የቀድሞው የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛና የአሁኑ የኢሳት ራድዮ ከፍተኛ አዘጋጅ መሳይ መኮንን፣ እንዲሁም የቀድሞው የአዲስ ዜና ጋዜጣ ዋና […]

አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን […]

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጠበቃው በአቶ አምሐ መኮንን አማካይነት፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው ይግባኝ ላይ ክርክሩን አደረገ፡፡ ክርክሩን የተከታተለው የተወሰነበትን የሦስት ዓመታት የእስራት ቅጣት እየፈጸመ ባለበት በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ዝዋይ እስር ቤት ሆኖ በፕላዝማ ነው፡፡   ጋዜጠኛ ተመስገን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ቀርቦበት የነበረው ክስ፣ እሱ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሲሠራ […]

ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም ቁጥራቸው ከአምስት የሚበልጡ የውጭ አገር ዜጎች ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ ቦሌ ቲኬ ሕንፃ አካባቢ በፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸው ተጠቆመ፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ቻይና አፍሪካ አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው ቲኬ ሕንፃ ላይ በሚገኘው ሰንበርድ ካፌ አጠገብ ድንገት በተነሳ ግርግር በአካባቢው ለተወነሰ ጊዜ ውክቢያ ተፈጥሮ፣ አካባቢው በሰዎች ተሞልቶ እንደነበር በሥፍራው የነበሩ የዓይን […]

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳትና የኢትዮጵያ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የካርዲናልነት ማዕረግ አገኙ፡፡ ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስን ጨምሮ ለ15 ሊቃነ ጳጳሳት የካርዲናልነት ማዕረግና ለአምስት ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት ድምፅ አልባ (የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት የሌላቸው) የካርዲናልነት ሹመት ባለፈው እሑድ ረፋድ ላይ በቫቲካን በመስጠት ይፋ ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ናቸው፡፡ ቫቲካን ሬዲዮ ታኅሣሥ […]

የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ፣ አንድነት እና መኢአድ በምርጫ እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ለፋና ራዲዮ ገለጹ። የአንድነት አመራሮች ወደ ምርጫ ቦርድ ሄደው የምርጫ ቦርድን ዉሳኔ በጠየቁ ጊዜ ቦርዱ ነገ ማክሰኞ እንደሚሰበሰብና ቦርዱ እንደሚወስን ቢነገራቸውም፣ ቦርዱ ሳይሰበሰብ ምክትል ሃላፊው፣ ቀደመው በራዲዮ፣ የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲ እንደይሳተፉ መግለጻቸው፣ ከወዲሁ በሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የተወሰነና ተግባራዊ የሚሆነው ይሄ ዉሳኔ ይሆናል በሚል እንደሆነ […]

በኢንተርኔት የሚሰራጩ ፅሁፎችን፣ ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ለመቆጣጠር ታስቧል የግል የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈርሰው ከመንግስት ቻናል እንዲከራዩ ለማድረግ ታቅዷል የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ለመቆጣጠር ከስምንት ዓመት በፊት በታወጀው ህግ ላይ አዳዲስ ቁጥጥሮችን የሚጨምርና እንዲሁም የኢንተርኔት ስርጭቶችንና ድረገፆችን የሚያካትት ህግ ተዘጋጀ፡፡ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋር ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ውይይት የተካሄደበት ረቂቅ ህግ፣ ነባሩ አዋጅ ውስጥ የሰፈሩ የባለቤትነትና የፈቃድ አሰጣጥ ቁጥጥሮችን […]