የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ፣ የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን ! – ነቢዩ ሲራክ

የማለዳ ወግ …የድሆች አባት ዶ/ር በርናርድ ተለየን !
* የኢትዮጵያ አፈር የጠራው ጠቢብ
*” ክብር ሞቱ ለሰማዕት “Nebiyu-Sirak  ዛሬ የምናዘክረው ሰው የኢትዮጵያ አፈር ፍቅር ጠርቶት ለጉስቁል ተገፊው ደሃ የሀገሬ ሰው ህይዎት ትንሳኤ ተግቶ ለውጥ ስላመጣ  ጠቢብ ነው። ዝካሬ ታሪኩ ቢያስተምረን ፣ አርአያ ሰብዕናው ግብአት፣ ተሞክሮ ቢሆነን ፣ ህይዎት ንብረቱን በእኛው ቀዬ ስላፈሱሰ ትጉት ሀኪም ነው ! ነፍሳቸውን ይማር ብለን ለሰሩት ስራ ክብር በመስጠት እናዘክራቸዋለን!  ዶክተር በርናርድ አንደርሰን ይባላሉ ! በርናርድ ዛሬ አይሰሙም ፣ አያዩንም …የዶር በርናርድን እረፍት ያረዳችኝ መነኩሴዋ እናቴ ሀዘኑ ጎድቷት ” ልጀዋ ዋርካችን ተገረሰሰ እኮ ፣ የድሆች አባትና ጠዋሪ መድሃኒታችን አጣንኮ … ” ነበር ያለችኝ … ያልጠበቅኩት ነበርና ድንጋጤው መላ አካሌን ወረረው  ። የእንባ ሳግ እየተናነቃት ሃዘኗን ያጋራችን እናቴን ከማጽናናት ባለፈ ምንም ማለት አልተቻለኝም! እናም ስለ ጠቢቡን የድሆች አባት ዶር በርናርድ አንደርሰን ላዘክር በተጎዳ ስሜት ብዕሬን ሳነሳ ጠቢቡ በሰጡት የኑዛዜ ቃል መሰረት ቀብራቸው በሚወዷት ሀገረ ኢትዮጵያ ምድር ይሆን ዘንድ በተናዘዙት መሰረት ሊፈጸም ተቃርቧል ። ውድ ባለቤታቸው የአርበኛው ደራሲ ገሪማ ታፈረ ልጅ ከሲስተር እማዋይሽ ገሪማም  ከምድረ አሜሪካ የዶር በርናርድን ቃል ለመፈጸም ዛሬ እኩለ ቀን አ.አ ይገባሉ  !  ጥቂት ስለድሆች አባት በርናርድ አንደርሰን ላጫውታችሁ …

ዶር በርናርድን ሳውቃቸው  !

ከአራት አመት በፊት ጠቢቡ ወንድም አግኝቻቸዋለሁ  ።  ስለሚሰሩት በጎ አድታጎት  በቅርብ የሚያውቋቸው ስለደግነት ቸርነታቸው አውርተው የማይጠግቡ ወገኖችን አግኝቸ ብዙ ተነግሮኛል። ከዚህም ተነስቸ ጠቡቡን ወንድም በአንድ የራዲዮ ዝግጅት ከአንጋፋው የረጅም ጊዜ የጀርመን ራዲዮ ጋዜጠኛ ከተክሌ የኋላ ጋር በመሆን በአንድ ዝግጅት ለማቅረብ ጠይቄያቸው ነበር ። ዶር በርናርድ ግን ” ምኑን ሰርቸ ታሪኬ ይነገራል ! ” በማለት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፋና ወጊና አርአያ ተግባራቸውን ለማስተዋወቅ አልተሳካልኝም ! ያም ሆኖ ጠቢቡ በርናርድ እና ባለቤታቸው ሲስተር እማዋይሽ ገሪማን  በኢትዮጵያ ባህል በተሽቆጠቆጠው ቪላቸውን ሲያስጎበኙኝ እዚህ  ስላደረሳቸው መንገድ አውግተናል ።   “አጴ ቴዊድሮስ በተወለዱበት እና ባቀኑት ሃገር የአህያ ግንባር የምታክል ማስታወሻና መዘከሪያ ቦታ እንዴት አይኖራቸውም?  ” በሚል ለቴዎድሮስ መታሰቢያ ሙዝየም ለማስፈቀድ ሲከላተሙ ያገኘኋቸው ከእውቋ ሀገር ወዳድ  ከወ/ሮ እማዋይሽ ገሪማ ጋር በመሆን የምድረ አሜሪካ የተደላደለ ኑሮ ስላፈናቀላቸው የእናት ኢትዮጵያ ፍቅር ፣ በታሪካዊዋ የጎንደር ከተማ  ስላሰሩት የአዛውኖቶች መጠለያ  ፣ ለህሙማን መርጃ ባቋቋመው የህክምና እርዳታ መስጫ ቦታና ያኔ ጅምር ስለነበረው የሆስፒታል ግንባታ መሰረት በሚጣልበት ማሳ ላይ ቆሜ ህልማቸውን አውገተውኛል ፣ ሃሳባቸውን ተጋርቻለሁ!

ለመሆኑ ዶር በርናርድ አንደርሰን ማናቸው?

በሃገረ ጃማይካ ካትሪን ደብር ተብላ በምትታዎቅ አንዲት መንደር እ.ጎ.አ መስከረም 21 ቀን 1944 ዓም ህጻን በርናንድ አንደርሰን  ከአርሶ አደር ወላጆቹ ተወለደ።  የበርናንድ ህይዎት በጃማይካዋ የካትሪን ትንሽ የገጠር መንደር መጀመሩ እንጅ ከዘር ማንዘሩ ርቆ በሌላ የአለም ጫፍ ካለችው ኢትዮጵያ ጋር በፍቅር ተቆላልፎ ህይወቱን ያሳልፋል ብሎ የሚገምት አልነበረም ። ገና ከልጅነት ህይዎቱ ጀምሮ ብሩህ አዕምሮ የታደለው በርናንድ በካሪቪያን ውስጥ አንጋፋ በሆነው የዎልማር የወንዶች ት/ቤት ተግቶ በመመማር ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር ጀመረ ፣ ከዚያም ጉዞውን ቀጠለ … የተሻለ እውቀት ጥም እያንገበገበው ወደ አደገችው ምድረ አሜሪካ አቀና ፣ በትምህርቱ በመግፋት እ.ጎ. አ 1960 ዎቹ መጀመሪያ በዋንሽን ግተን ዲሲ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ሳይንስ የመጀመሪያውን የባችለር ዲግሪ ሲቀዳጅ በከፍተኛ ማዕረግ ነበር ።  ለጎልማሳው በርናንድ በከፍተኛ የህክምና ተቋማት የላቀ ውጤት ማምጣት ተራ ትምክህት ሆኖ ሳይገታው የተሻለና የላቀ ፣ ከፍ ያለ ትምህርት የመቅሰም ህልምን ሰንቆ የማታ ትምህትቱን በመከታተሉን ገፋበት ። ይህንንም ህልም በአጭር ጊዜ ታጥቆ ለስኬት አደረሰው ። እ.ጎ. አ በ1970 ዎቹ በርናንድ በከፍተኛ ማዕረግ የዶክትሬት ማዕረግ ተመረቀ !

የዚያ ደርባባ ጎልማሳ ዶር ማንነት የተገነባው ከመደበ ኛው እውቀት ባለፈ አብሮት ከተቆራኘ ሰብዕና እንደነበር የሚያውቁት ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ። ዶር በርናርድ አንደርሰን በሙያው ያጡ የነጡ፣ ጉስቁል ፣ምንዱባንን ለመርዳትና ለመደገፍ ቆርጦ ተነሳ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ እንደ ቃል ኪዳን አድርጎ የያዘውን ተተኪ ፍለጋና ተተኪን ማፍራት ነበርና ድሎት ሳያታልለው ያደገ የተመነደገችውን ምድረ አሜሪካ ለቆ ወደሚያውቀው የድሆች ምድር አቀና  !  ወደ ጃማይካ ኪንግስተን …

ጃማይካ ኪንግስተን …

ህልሙን ለማሳካት ወደ ትውልድ ሃገሩ ጃማይካ ተመልሶ በወቅቱ ታዋቂ ከነበረው የኪንግስተን የህዝብ ሆስፒታል ስራውን ጀመረ ። የቀዶ ጥገና ጥበብ ባለሙያው ጎልማሳ ሃኪም ቅድሚያ የሰጠው በድህነት የሚማቅቁ ወገኖቹን መታደግ ነበር ፣ በህክምና ድጋፉ ፣ በተጓዳኝ ጥናትና ምርምሩ አንቱ በሚያሰኘውን ተመክሮ ራሱን እያጎለበተ ጉዞ የጀመረው ሃኪም በህክምና ድጋፍ ከመስጠት ርቆ ሔዶ በመምህርነት ሙያው ተተኪ ትውልድን የማነጽ ህልሙን አሳካ ። በዚህም ጉዞው ዶር በርናርድ አንደርሰን ለሃገሩና ለወገኑ ይህ ነው የማይባል አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ቻለ  !

ከጃማይካ መልስ በዋሽንግተን …

የጃማይካ ኪንግስተን ተልዕኮውን በሚገባ ከውኖ አቅፋ ደግፋ እውቀት ወደ መገበችው ሀገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ተመለሰ ። ዶር በርናርድ ለዚህ ላበቃው ዩኒቨርሲቲ ከእለትጉርሱ ያጠራቀመውን ከ100 ሽህ የአሜሪካ ዶላር የለገሰ ፣ ለሚሰረሰው በጎ ስረሰ ከመደሰተረ ውጭ ፣ መወደስ የማይሻ ሰብአዊም ነበር ።
ዶር በርናርድ ከጃማይካ መልስ እንደ አቻ የሙያው ባልደረቦቹ  ሃብት ንብረት የሚያካብትባቸው ሆስፒታሎ ች በከፍተ ኛ ገንዘብ ሊቀጥሩት ሲሻሙ አሻፈረኝ አለ።   ጥቅም ፍለጋ መማሰኑን ” ወዲያልኝ ” ብሎ ፣  የጤና ከለላና ሽፋን የሌላቸው ፣ በድንገተኛ አደጋ ተጎድተው ህይዎታቸው አጣብቂኝ የገቡትን የስልጡኑ ሀገር ተገፊ ምንዱባን መታደግ ወደ ሚችልበት በዲሲ ጄኔራል ሆስፒታል በአነስተኛ ደመወዝ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ ።  በሙያው ተግቶ ፣ በሰብዕናው ጸንቶ ፣ ባሳየው ስኬትም በአጭር ጊዜ አንቱታን በማግኘቱ የሆስፒታሉ ሊቀመንበርና የቀዶ ጥገናው ክፍል ዋና ዳይሬክተር ለመሆን በቃ !  በአስተዳደር እና በሙያው ክህሎት የዲሲ ጀኔራል ሆስፒታል ከፍ ወዳለ ደረጃ ያደገው በዶር በርናርድ አንድሰን አመራር እንደነበር ዝክረ ታሪኩ ያስረዳል። ዶር በርናንድ ሆስፒታሉን ከማስተዳደር ጎን ለጎን የግል ክሊኒክ በድሆቹ መኖሪያ አቅራቢያ በዲሲ ሮድ አይላንድ መንገድ በመክፈት ፣ ለቻሉት በአነስተኛ ክፍያ ፣ ያልቻሉትን በነጻ በማከም ግልጋሎት ይሰጥም ነበር ።

የዶር በርናርድ አፍሪካና ኢትዮጵያ ትስስር …

በቀጣይ ዝካሬ ዶር በርናርድ ስነሳ እንደ አባት አቅርቤ ፣ እንደ ታላቅ ትጉህ ጠቢብ አንቱ እያልኩ መተረኬ ይገባኛል ፣ መልዕክቴ ከገባችሁ ለእኔ ያ በቂ ነው!  ብቻ ያገሬ ሰው ዶር በርናርድን  “የድሆች አባት ” ስላለበት አንድምታ ዘልቀን እናወጋለን …

ታህሳስ 24, 2007  ዓም ይህችን አለም የተለዩን ያልተጨበጨበላቸው ፣ ያልተነገረላቸው የኢትዮጵያ ወዳጅ ጃማይካዊ አሜሪካዊ ዶር በርናርድ የምናዘክረው በታላቅ  ክብር ነው  !  “ዶር በርናርድ ጉስቁል ምንዱባን ን ስትደግፍ ኖረሃልና ሞትህ የክብር ሞት ነው  ! ” ክብር ሞቱ ለሰማዕት ”  በሚል ታህሳስ 29 ቀን 2007 ዓም እኩለ ሌሊት በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገ ሰፊ የጸሎትና የዝክር ስነ ስርአት ቤተሰብ ፣ ወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት የክብር ስንብት አድርገው በርናንድ በድናቸው እንዲያ ርፍ ወደ ፈቀዱባት ቅድስት ሀገረ ኢትዮጵያ በክብር ተሸኝተዋል ! በዚሁ ፕሮግራም ከተሰራጨው ዝክረ ህይዎት ያገኘሁትን መረጃ በቀጣይ እንደሚሆን አድርጌ የምናየው ይሆናል !

ለመላ ቤተሰብ ለወዳጆቻቸውና ለአድናቂዎቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ  !  ለሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪው የድሆችን አባት ፈጣሪ በቀኙ ያሰረቀምጣቸው ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው  ! ነፍስ ይማር  !

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም

Sent from Samsung Mobile

 

——– Original message ——–
From: Nebiyu Sirak
Date:2015/01/05 6:21 PM (GMT+03:00)
To: “Zehabesha. com” ,[email protected],info@abugidainfo.com,samson asfaw ,[email protected],[email protected],Golgul/ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ,[email protected],editor@awrambatimes.com,zelalem@maldatimes.com,ethiopiazare@gmail.com,Satenaw Tebeje ,EMF Media ,[email protected]
Subject: የማለዳ ወግ … ሰሚ እስኪገኝ እያነባን እንጮሃለን  !
የማለዳ ወግ … አፈ ጉባኤ አባ ዱላ …ግን ለምን አልሰሙንም ?* የኮንትራት ሰራተኛዋ አይነ ብርሃኗን ማጣትና የስም የለሿ ሟች እህት መጨረሻ   !
*  ሰሚ እስኪገኝ እንጮሃለን  !ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም ሰኞ በማለዳው ያገኘኋቸው ሁለት መረጃዎች የወጡት በሁለቱ አንጋፋ የሳውዲ ጋዜጦች በአረብ ኒውስ Arab News  እና በሳውዲ ጋዜት Saudi Gazette  ነው ። በአንዱን አይቸ ቢከፋኝ ፣  መፍትሔ ላይገኝ ይህን መርዶ ከንፈር ለማመስመጠጥ  ብቻ መረጃ ብየ ልለጥፍ ይሆን ?  እያልኩ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ነፍሴን ሳስጨንቀት በሌላኛው ጋዜጣ የወጣውን ሌላ መረጃ አንድ ወዳጀ በጓዳው የመልዕክት መሰረጫ እንደኔው ማልዶ ያጋጠመውን የወገን መከራ አደረሰኝ ። ሁለቱንም አሳዛኝ መረጃዎች ተመለከትኳቸው ፣ ያማል ብቻ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም  !

     መዲና የተባለች እህት በጽዳት ላይ እያለች አይኗ ላይ ተፈናጥሮ የገባው መርዝ የአይን ብርሃኗን አሳጥቷት በከፋ አደጋ ላይ ወድቃለች  ፣ ሴት አሰሪዋ መዲናን ለማሳከም ደፋ ቀና ቢሉም ለህክምና የተጠየቀው ወጭ ለአቅማ ቸው በላይ በመሆኑ ነገሮች የተወሳሰቡ መሆኑ ተጠቁሟል መረጃው የሳውዲ ጋዜጥ ነው  …. !  መረጃውን በፊስ ቡክ ካሰራጨሁት በኋላ ለማጣራት ሞክሬ እንደተረዳሁት ስትታመም ስትጎዳ ሊያሳክሙ ፣ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ ከለላ በጅዳ ቆንስል የመጣችው እህት ጉዳዩዋን የሚከታተልላት ቀርቶ የመዲናን ለዚህ አደጋ መጋለጥ የሚያውቅ የመንግስት ተወካይ የለም  !
    ሌላዋ እህት የሆነችውን አረብ ኒውስ በአንዲት የጋዜጣው ጠርዝ ካይ እንዲህ ሲል በአጭር አረፍተ ነገር አስፍሮታል ” ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኛ አል ጀውፍ በተባለ የሃገሪቱ ግዛት በአሰሪዋ ቤት ራሷን በመስቀል ራሷን በራሷ ገድላለች “ይላል  …መረጃው የአረብ ኒውስ ነው  …. !   ስለዚህች እህትም ቢሆን በአቅራቢያው ያለው የሪያድ ኢንባሲ መረጃ የለውም  ፣ መረጃውን ቀድመው ይወቁት አልልም ፣ ቢያንስ ከእኛ እኩል በየጋዜጣው የሚወጣውን እንኳ አለማወቃቸውን እኩለ ቀን ላይ ወደ ሪያድ ኢንባሲ ደውየ ለማወቅ ችያለሁ  ! ሁሉም ያማል  !
ከሳምንት በፊት እኔ ከምኖርበት ጅዳ ከተማ ልጆችን ወደ ት/ቤት በማድረስ ላይ እያለች በተፈጠረ መኪና ግጭት የያዘቻቸውን ህጻናት አትርጋ እሷ መስዋዕትነት የከፈለችን ትጉህ እህት ያዩ አረቦች ተገርመው በምትሰራበት ቢተ ሲጫወቱ የሰማች እህት ታሩኩን በደፈናው ብትነግረኝም ዝርዝር መረጃ አለነበረውምና በዝምታ አልፊው ነበር።  ዛሬ እኩለቀን ላይ ከላይ የጻፍኩትን የሁለቱን ጋዜጦች መረጃ የተመለከተ ወንድም አንዲህ የሚል መልዕክት ደረሰኝ ይህን “ሄሎ ነብዩ ሰላም ነህ ነብዩ በአንድ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር
ስልክህን  ልትልክልኝ በትህትና እጠይቃለህ በጣም የማከብሪህ  እና ማደንቅህ …” ይላል ፣ አመስግኘ ስልኬን ሰጠሁት ፣ ምሽቱን ደውሎልኝ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶባት ራሷን የማታውቀውን እህት ጉዳይ አንስቶ በዝርዝር አጫወተኝ ፣ ይህች እህት ያን ሰሞን የአሰሪዎቿን ልጆች አትርፋ መኪናው የዳጣት ለመሆኗ ብዙ መሄድ አላስፈለገኝ። ከወዳጀ ጋር ይህችን ምንዱብ የአልጋ ቁራኛ ለማየት ቀጠሮ ብንይዝም አልስቻለኝምና ወደ ተባለው ሆስፒታል ሄጀ የማትሰማ የማትናገረውን እህት አይቻት ሰላሜን በገዛ እጀ አጥቸ ተመለስኩ  !
    ማለዳ በሰማሁት ባነበብኩት ምሽት  ላይ ባየሁት ውስጤን  ጥሩ ስሜት አልተሰማው ምና ከንዴት በሽታ ውጭ ምንም ላላመጣ በስጨት አልኩ  ፣ ዝም ማለት ግን አልለመደ ብኝምና እናገረዋለሁ  !  … ደግሞ ብስጭቴን ስጽፈው ይቀለኛልና መቸክቸክ ያዝኩ …
ሰሚ ያጣ ጩኸት …
    መረጃ ማቀበሉ በህግ አስፈጻሚ አካላት በኩል ውጤት አለማምጣቱን አሰላስየው የአፈ ጉባኤ አባ ዱላን ሰሞነኛ የሳውዲ ጉብኝትና መፍትሔ እንደማያመጡ እያወቀ እንደኔው ባለመተንፈሱ የተበሳጨውን የጅዳና የሪያድ ነዋሪ አስታወስኩ ! ከምንሰማ ከምናየው የዜጎች አበሳ ጋር ሰሚና ሁነኛ የመብት አስከባሪ የበላይና የበታች ሹማምንት አጥተን በስቃይ ላይ ለመሆናችን ምስክሮች የምናቀርባቸው መረጃዎች ናቸው ። በሳውዲ 350 ሽህ የኮንትራት ሰራተኛ እንዳለ በመንግስት ተረጋግጦ እየተነገረን ፣ የተበተኑት መብት ሳይጠበቅ አዳዲስ መከረኞችን አምጥተን ልንደፋ  ዝግጅቱ የተጠናቀቀ ይመስላል ።  እኛ ይህ ነገር በተቀናጀ ጥናት፣ በበቂ ዝግጅት ፣ በበሳል አመራር  ካልተመራ ሌላ አደጋ አለው እያልን ነው ።  መከራ ብሶቱን ፣ አሰከፊ ምስሉን እያሳየን ” አረ ያገር ያለህ !”  እያልን እጮህን ነው  ! ሰሚ ህግ አውጭና ህግ አስፈጻሚ ግን የለም  ! ሰሚ ያጣው ጩኸታችን ሰሚ እስኪገኝ ግን ዝም አንልም ፣ እንጮሃለን  !
ግን ለምን አልሰሙንም ?የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በሳውዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል። የሰራተኛ ሚኒስትር አድል ፈቂን ጨምሮ በርካታ የመንግስ ሃላፊዎች አግኝተው እኔና መሰሎቸ ሌት ተቀን ስለምንናገረው በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ስለተላኩ የእኛ ዜጎች ለአባ ዱላ ነግረውልናል ።  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ በኮንትራት ሰራተኞች ጉዳይ ከሳውዲዎችና መብታችን ካላስጠበቁልን የሪያድ ኢንባሲና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ፣ በሃላፊዎች  ከተመረጡ  የሪያድ የጅዳ “የተከበሩ ምርጥ” ዜጎች ፣  ከኢህአዴግ የድርጅትና ከተለያዩ ጥሪ ከተደረገላቸው የ ማህበር አባላት ጋር  መክረዋል።አፈ ጉባኤውና ልዑካኑ በአንጻሩ በማህበራዊ ኑሮው ፣ በመብት ጥበቃው ፣ በኮንትራት ሰራተ ኞች የለት ተለት የመረረ እውነት ተመልካችና ገፋች የሆነውን ነዋሪ ጠርተው ቀርቶ ሊያይ ሊያነጋገራቸው ሄዶ በሆድ አደር አጋፋሪዎች ተከልክሏል። ነዋሪ ዜጋው እንዲህ ተገፍቶ  የሃገሪቱ የበላይ ህግ አውጭ የሆነው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳያዩትና ሳያነጋግሩት ሔደዋል ። የአፈ ጉባኤ አባ ዱላን ማግኘትና ብሶቱን ማሰማት የፈለገው ነዋሪ ጉጉት ምን ይሆን ? ብየ ጠያይቄም ነበር ። ያገኘሁት የምላሽ እውነታ ነዋሪው ማቆሚያ ስለጠፋው የኮንትራት ሰራተኞች አበሳ ለመናገር መተንፈስ እንጅ መጓጓቱ መፍትሔ ከባለስልጣኑ ይገኛል ብሎ አለመሆኑን ተረድቻለሁ።  እውነት ነው አባቶች  ” ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ… ” እንደሚሉት ሆነና  ነዋሪው ሆየ ብሶቱን ማሰማቱ ህመሙን ያቀልለት መስሎታል  ! ፕሬዚደንትና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ እስካሁን ሳውዲ ለመጡት ከፍተኛ ባለስልጣኖች የአለ የሌለ የተባለውን ጥያቄ አቅርቦ ምልስ እንዳልተገኘ አሳምሮ የሚያውቀው ነዋሪ በዚህና በዚያ ተስፋ  ቆርጧል… ግን ተስፋ ቆርጦም መናገር መተንፈስ ይፈልጋል !

የአስፈሪው ቀን መቅረብ  ምልክቶች …

በሳውዲ መንግስት የተዘጋው የኮንትራት ሰራተኞች ይጀመራል ተብሎ በዋና ዋና ደላሎች ወሬው ከተነዛ ወዲህ በመንግስት በኩል የረቂቅ ደንቡ መውጣቱን ሰምተናል ። ጸድቆ ጉዞው ሊጀመር ተቃረበ ሲሉን ደግሞ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ ከሳውዲ ባለስልጣነናት ጋር ስለአዲሱ ረቂቅ ህግ መምከራቸውን ሰምተናል ! ከሳውዲዎች ጋር   ስለመከሩ ስለዘከሩበት ህግ በሳውዲ ነዋሪ ከሆነው ኢትዮጵያዊ ጋር አለመምከራቸው ግን ታላቅ ታሪካዊ ስህተት ነው ባይ ብዙ ነን  !  ነዋሪው ብሶቱን ለመናገርም ሆነ ከመምከር መወያየቱ የሚገኝ ፋይዳ አለ ብሎ ሳይሆን እንደ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ ባለ ስልጣን ለምን ዜጎችን እኩል አይተው አላነጋገሩንም ? ሃሳባችን ለምን አያደምጡትም? ለምን አልሰሙንም ?  ለምን የታመቀ ችግራችን ቢያንስ አላዳመጡንም  ? በኦሮሞ ልማት የተመረጡ አባላት ሰብስበው ለቴሌቶን ብር ከመሰብሰብ በስደት ስላለው ስለከፋው ዜጋ መምከር ለምን አለቀደመም?   አፈ ጉባኤ አባ ዱላ  እንደ ኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት ሳውዲን እየጎበኙ ለምን ወደ ዘውግ አድልተው ወርደው ጊዜን ማባከብ አስፈለጋቸው? በጉብኝታቸው ሁሉንም ባንድ የኢትዮጵያ ባንዴራ ማሰተባሰበርና ማመካከር ሲገባ ቅድሚያ ለኦሮሞ ማህበር ከዚያን የኢህአዴግ አደረጃጀት እያሉ ስደተኛውን ከመበታተንና በማዕከላዊነት ያልተማከለ ፣በዘውግ አስተዳደር የከረረ  አካሄድን እንድናይ ለምን አደረጉ?   አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ከምንም በላይ በሁለት ሃገራት የሰራተኛ ውል ማዕቀፍ ውጭ ወደ ሳውዲ የመጡና  እንደ ጨው የተበተኑትን የኦሮሞ ፣የአማራ፣ የትግራይ ፣ የጉራጌ እና የቀሩትን ብሔረሰቦች የአብራክ ክፋዮች ሁኔታ ለመረዳት የጉዳዩ ባለቤትና መከራውን ገፋች ነዋሪውን አላነጋገሩትም።  መፍትሔው  መብታችን ማስከበር ቀርቶ ዜጎች ያለንበትን ሁኔታ መሸፋፈን ከሚቀናቸው ከቆንስልና ከኢንባሲ ተወካዮች እስከ ድርጅትና ማህበራት ያሉትን”ምርጥ ” የተባሉ ነዋሪዎች ማነጋገር መፍትሔ ነውን ?  አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ነዋሪውን በነቂስ ጠርተው በመሰብሰብ ለምን ስለመጡበት ጉዳይ ማብራሪያም ሆነ የነዋሪውን ሃሳብ አልወሰዱም ?  የሚሉ በርካታ ውሃ የሚያነሱ እውነት ያላቸው ጥያቄዎችን ነዋሪው ሲያሰማ አድምጫለሁ ! እኔም ሆንኩ ነዋሪው በእስካሁኑ ሂደት ያየነው ለውጥ ኑሮ ባያስደስተንም ባለስልጣን በመጣ በሄደ ቁጥር ድመጻችን ይሰማ ዘንድ እንሻለን ፣   የለውጥ ተስፋ ባይታየንም የወገናችን አበሳ ግን መናገር አናቆምም  ! አዎ  ! ሰሚ እስክናገኝ እንጮሃለን  !

እስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓም