የቅዳሜውን ሰልፍ አስመልክቶ ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ከትብብሩ የተሰጠ መግለጫ በአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ትግላችን አይቆምም! የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ባለፈው አንድ ወር ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጸን ስንቀሳቀስ ዋናው አላማችን የስርዓቱን አረመኔያዊነት ለህዝብ በማጋለጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው፡፡ እንደጠበቅነው ገና ከጅምሩ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ትግላችንን በጭካኔ ለማስቆም ጥሯል፡፡ ህዳር 27/2007 ዓ.ም የመጀመሪውን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በጠራንበት ወቅት ስብሰባውን በኃይል በትኗል፡፡ ትብብራችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያሰጋው ህወሓት/ኢህአዴግ በተለይ የህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአደባባይ አዳር ሰልፍን እንዳይካሄድ የትብብሩን አመራሮችና አባላቶቻችን በማዋከብ፣ በመደብደብና በማሰር ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ በተለይ በትናንትናው ዕለት ሰልፍ በወጣንበት ወቅት ስርዓቱ አመራሮችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ተሳታፊዎችንን እንዲሁም አልፎ ተርፎ መንገደኛውን ህዝብ በጭካኔ ደብድቧል፡፡ አፍሶ አስሯል፡፡ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በየጎዳናው ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡ በርካቶችም በየእስር ቤቶቹ ታጉረዋል፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ከ300 በላይ የትብብሩ አመራሮችና አባላት የታሰሩ ሲሆን የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ድርሶባቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቤል ኤፍሬም ራሱን እስኪስት ተደብድቧል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ የተገኙ ሴት አመራርና አባላት አንድ አገርን እየመራሁ ነው ከሚል አካል በማይጠበቅ መንገድ በጭካኔ ተደብድዋል፡፡ እነዚህ በጭካኔ የተደበደቡ አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ህክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በጥበቃ ሰራተኝነት የሚሰሩ የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር ከስራ ሲወጡ በደህንነት ኃይሎች ታፍነው የተወሰዱና እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቀ ሲሆን ይህም አገዛዙ የመጨረሻው የአረመኔነት ደረጃ ላይ እንደደረሰና […]