የአንድነት ደጋፊወቻችን እና ለኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ- ቴሌ ኮንፈረንስ እድሳተፉ ተጋብዘዋል
ይድረስ ለተከበራችሁ የአንድነት ደጋፊወቻችን እና ለኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ
በቅድሚያ ሰላምታችን ባላችሁበት ይድረሳችሁ።
ላለፉት ሶስት ወራት የተደረገዉ የመጀመሪያዉ ዙር የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ፣ በኛ ግምት በጣም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋልብለን እናምናለን። በዚህ ሂደት ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች እና ደጋፊወቻችን በሙሉላደረጉልን ድጋፍና ትብብር ምስጋናችን ከፍተኛ ነው:: የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ የሰሜን አሜሪካ አንድነት ፓርቲ ደጋፊ ግብረ ኃይል ያዘጋጀውን ቴሌ ኮንፈረንስ እድሳተፉ ብትሕትና እና በአክብሮት ተጋብዘዋል::
ተጋባዥ፥ የአንድነት ደጋፊወች እና ለኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች በሙሉ
በስብሰባው ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፥
1. የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝደንት ዶከተር ነጋሶ ጊዳዳ
2. የአንድነት ፓርቲ የህዘብ ግኑኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ
3. ከ 33ቱ ፓርቲዎች ተወካይ
በኢትዮጵያችን በአቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እእንዲሁም በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ትግላችን ላይ እነዚኽ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ባልደረቦች በቴሌ-ኮንፍረንስ ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ስለሚያደርጉ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ግብረ ኃይል በአክብሮት ጋብዞዎታል። የአንድነት ፓርቲ መሪዎችን ጥያቄዎች መጠየቅ ይችላሉ።
በዚኽ ቴሌ-ኮንፍረንስ ከተጋበዙት ሚዲያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፥
1. ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች፥ የአሜሪካ ድምጽ (አማርኛ፣ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራሞች)፣ ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ፣ የዲሲ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሬዲዮኖች በሰሜን አሜሪካ በሙሉ
2. የድረገጾች አዘጋችወች ተወካይ (EMF, ECADF, ETHSAT, zehabesha, ethiomedia, abugida, Ethiopian Review; Quatero,, ሌሎችም ድህረ ገጽ አዝአጋቾች በሙሉ)
3. ፓልቶክ ሚዲያዎች፥ ቃሌ፣ ሲቪሊቲ እና ከረንት አፌር
ለ ሚዲያ ተወካዮች የተለየ ኮድ ስለአለ በስልክ ቁጥር 612 986 0557 በመደወል ኮዱን ማግኘት ይቻላል
ቴሌ-ኮንፍረንሱ የሚደረገበት ቀን እና ሰዓት፥
· ቀን፥ ቀን፥ ቅዳሜ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. (October 5, 2013
ሰዓት፥ ከቀኑ 1፡00 ሰዓት (1:00 PM Estern Time)
በቴሌ-ኮንፍረንሱ ለመሳተፍ፥ 267-507-0240 ይደውሉ እና 201820 ኮድ ይጠቀሙ