ሳውዲ አረቢያ በተለይም በመንፉሃ ሪያድ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ መረጃዎችን ስንለዋዎጥ ባጅተናል ። አሰቃቂውን የወገን ጉዳት አብረን አውግዘን ፣ ወገኖቻችን ደራሽ ያገኙ ዘንድ ኢትዮጵያውያን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በመላ አለም ያሰማነው ድምጽ ፍሬ አፍርቷል ! ደስ ሲል … በሁከቱ የተፈጠረውን ችግር ፣ የፈሰሰውን እንባና ደም የአይን ምስክሮችን በአካል ላነጋገረና ህመሙን ሲታመም ለከረመ የእኔ ቢጤ ዛሬ የተገፊው ወገን […]

እኛን በታሪክ አስቦት የምንኖረውን የኢትዮጵያ ትውልዶች ሲያኮራን የኖረው በአያት ቅድማያቶቻችን ተጋድሎ በነጻነት መኖራችን ነው። እንዲህ ሆነ። እዚህ ዳላስ ለብዙ ጊዜ የማውቀው የውጭ ዜጋ በተገናኘንበት ጊዜ ሁሉ የጣሊያንን የሁለተኛው አለም ጦርነት ሳያስታውሰኝ አያልፍም። እናም ሊያስታውሰኝ የሚከጅለው ለትንሽ ከቅኝ ግዛት አመለጣችሁ ይለኛል። እኔም እንደልማዴ በጀሮ ከአባቴ የሰማሁትን ገድል ሳልነግረው አልፌ አላውቅም። እርሱም የበለጠ እንደምበሳጭ ስለሚያውቅ አይ እንግሊዝ […]

ትናንት እንደ ቀልድ … በያዝነው የፈረንጆች 2013 ዓም በወርሃ መጋቢት አጋማሽ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ” ህጋዊ ሰነድ ያልያዙትን አስወጣለሁ !” ብላ አወጀች ። ቀጠለና አፈሳ አሰሳው ተከተለ! አስፈሪው ያ ክፉ የጭንቅ ቀን በሳውዲው ንጉስ ሌላ የምህረት አዋጅ ተተክቶ ህገ ወጥ የተባሉትን ህጋዊ በሚያደርግ ህግ ተተካና የምህረቱ አዋጅ በያዝነው ህዳር መባቻ እንደሚያልቅ በተጠቆመው አዲስ የምህረት አዋጅ […]

አይኖቼ በደም ቀሉ። ልቤ ተሰበረ። ከሳዉዲ አረቢያ፣ ከባህር ማዶ፣ የወገኖቼ ጩኸትና ሮሮ፣ ከጣራዬ በታች የመነጨ ይመስል፣ በጆሮዬ በቅርበት ያቃጭላል። በርግጥ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ መዋረዳችንን አየሁ። በተለይም ደግሞ በአሁኗ ሰዓት፣ እንደ ወገን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ዉስጤ ደበነ። የማድርገዉን ሳጣ መሬት ተንበረከኩ። አይኖቼን ወደ ላይ አንስቼ፣ እጆቼን ዘረጋሁ። «ሄሮድስ ሊገድልህ ፈልጎ በነበረ ጊዜ፣ […]

የሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ የወጡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታሰሩ፡፡ ከጽ/ቤታቸው ተነስተው ወደ ሰላማዊ ሰልፉ ቦታ ሲሄዱ 4 ኪሎ የኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጎን በሚገኘው ወታደራዊ ገራዥ መታሰራቸውን ዘጋቢያችን ከቦታው አድርሶናል፡፡ ከመታሰራው ቀደም ብሎ ከፖሊስ ጋር እንሂድ አትሄዱም በሚል ጭቅጭቅ ላይ እንደነበሩ ሰምተናል፡፡ ሌሎች የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተበታትነው ወደ ሳውዲ አረቢያ […]

ጥላቻው እያደገ ሔዷል ፣ ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞቻቸውን ድሮ ድሮ በአረቦች ዘንድ የተከበርን ፣ የታፈርን የእኛን የሃበሻ ልጆች “ጨካኞች ፣ የማይታመኑ !” እያሉ ጥላቻቸውን መገልጽ ጀምረዋል። November 14,2013 የወጣው አረብ ኑውስ Recent clashes make Saudis wary of Ethiopian maids በሚል ርዕስ ስር ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ለማባረር እየዛቱ ነው ! ይህ የአረብ ኒውስ ዘገባ […]

ሰኞ ኖቨምበር 18 በ ዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ለመሳተፍ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ለመሄድ እንዲቻል የሚክተሉት ግለሰቦች የማስተባበር ህላፊነት የተሰተጣቸው ስለሆነ የሚከተሉትን ስልኮች በመደወል ክቅዳሜ ክሰአት በፊት ቦታ እንድትይዙ አዘጋጅ ግብረሃይሉ ይጠይቃል። 1.እዮብ 617 513 7514 2.ካሳይ 857 928 8677 3.አበራ 617 304 2584 4.አብይ 617 953 7126 5.ዮናስ 617 447 8007

ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል[1]። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው […]

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በአባቶቻችን ደም ታፍራና ተከብራ የኖረችው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በገዢው ፓርቲ ቸልታ፣ የፖሊሲ ችግርና የሀገር ፍቅር ማጣት የተነሳ ዜጎቿ በውርደት እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ዛሬም መገለጫችን ስደት፣ ጦርነት፣ በዜግነታችን ክብር ማጣትና ሞት ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ሀገራዊ ውርደትና ሞት ከተበላሸ ሥርዓት የሚወለድ፣ ካልተስተካከለ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚፈጠር ነው፡፡ ፓርቲያችን የተሻለ ኢኮኖሚ ፍለጋ፣ የተሻለ ማህበራዊ ፍትህ […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እየታካሄደ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዞን ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመገኘት በሀገራችን ኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ፤ የዲሞክራሲ እና የፍትህ እጦት እንዲሁም ሁሉንም ኢትዮጵውያንን የሚያሣትፍ የኢኮኖሚ እድገት ባለመኖሩ ምክንያት ብዙ ዜጎች ወደ ደቡብ አፍሪካ ሃገራትና ወደ አረብ ሀገራት በእግር ሳይቀር ለመሰደድ ከመገደዳቸው በተጨማሪ በጉዞ ወቅት በአውሬ መበላት በበሽታ […]

ሰሞኑን የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል አይፈራም የሚል ጉዳይ ከፓርላማ ተነስቶ ወደ መገናኛ ብዙኃንም ደርሷል። ጉዳዩ የተነሳው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ አዲሱ ፕሬዚዳንታችን በፓርላማ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ባቀረቧቸው የማማሻሻያ ሐሳቦችና ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡት ምላሽ ዙሪያ ነው። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዝ ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓም በአወጣው ዕትሙ ‹‹’ፈሪ’ መንግሥት?›› በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ ጥሩ […]

እንደ ሰው አንድ የሚያደርገን ባሕርይ፣ እንደ ኢትዮጵያዊነትም ሁላችንንም የሚመለከተንና የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ልዩነት የማይነጣጥለው በደል በሳዑዲ አረብያ ግዛት እየተፈጸመ ነው። የጥቃት ዒላማዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። የጥቃቱ ልክ የለሽነትና አሰቃቂነት ደግሞ ይበልጥ የጎላው በሴት እህቶቻችን ላይ ነው። ይህ ዛሬ በሳዑዲ አረብያ የሚደረገው ጥቃትን ማስቆምና ቁጣችን መቆምያ እንደማይኖረው ማሳየት ለነርሱ ብቻ ሳይሆን ለራሳችን ደህንነትም ጭምር የምናደርገው ነው። ምክንያቱም […]

መጽሐፍ ወሬ ነጋሪ ደራሲ መሐመድ ይማም ግምገማ በልጅግ ዓሊ በሚያዚያ ወር የሰሜን አሜሪካ ክረምት ገና ሙሉ በሙሉ ሳይለቅ በፊላደልፊያ ከተማ ውስጥ በማይታወቅ ሰው ኢትዮጵያዊቷ ጀግና ተገደለች። በምሳ ሰዓት አካባቢ ወደ ቤት የተመለሰችው እህቷ ጠዋት በሰላም የተለየቻትን በደም አበላ ውስጥ ተዘፍቃ አገኘቻት። ፖሊስም ጠራች። የፍላደልፊያ ፖሊስ ይህንን የተቀነባበረ ግድያ የፈጸመውን ወንጀለኛ መያዝ ስላቃተው እንቆቅልሹ ያልተፈታ በሚል […]

በሪያድ መንፉሃ በተከሰተው ሁከት ግራም ነፈሰ ቀኝ ተጎጅዎች እኛ ነን ! እንኳንስ ሰው ተደብድቦ ፣ ሞቶባቸው ፣ እንኳንስ መኪና ተሰብሮባቸው እንዲያውም እንዲው ናቸው ። ከማለዳ እስከ ሌሊት የዘለቀውን ሁከት መቆጣጠር ይቻል ዘንድ ገና ሲጀመር አቅጣጫውን አይተው የመንግስት ተወካዮችን የመከሩ በርካታ ነበሩ። የሰማ አካል ግን የለም ! ስልክ ተደውሎ የማይነሳበት ፣ አልፎ አልፎ መስመሩ ሲነሳ ሃላፊዎችን […]

ዛሬ ረፋድ ላይ … በሳውዲ ዋና ከተማ ዛሬ ከረፋዱ ጀምረው እስከ እኩለቀን በሪያድ መንፉሃ ወደ ሃገራችን ስደዱን በሚል መንፉሃ ባንክ አልራጅህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተቃውመው ወጡ! ቤተሰቦቻቸውን እና ሻንጣቸውን ይዘው አውራ መንገድ የወጡት ኢትዮጵያውያን ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ግማሾቹ ወደ ሪያድ ኢንባሲና ኮሚኒቱ መስሪያ ቤት በእግራቸው ያመሩ ሲሆን መንፉሃ አካባቢ የቀሩት ከፖሊስ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) ከጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ትቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስድስተኛው የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡ ፓርቲያችንም ይህንን ጉባዔ በአንክሮ እየተከታተለው ሲሆን በርካታ የአፍሪካ ሚዲያ ባለሙያዎች የፕሬስ ነፃነት ባልተረጋገጠበት፣ የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች ተልካሻ ሰበብ እየተፈለገ በሚዘጉበት፣ ጋዜጠኞች ሀገር […]

ክፍል 1 ሰሞነኛ አዲሱን አመት ተቀብለን ሁለት ወራት ሳንሻገር ጥቅምት 11 ቀን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ እና ሥራ አሥኪያጁ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ደግነው ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ፤ በዳግም ቀጠሮ ዕረቡ ጥቅምት 20 ቀን በሐዋሳ ከተማ ጋዜጠኞቹ ለፍርድ ቤት ቀጠሮ ሄደው በስልት የተቀናበረ በሚመስል ሆኔታ ለመኪና አደጋ ተዳርገው ጋዜጠኛ ኤፍሬም የከፋ አደጋ […]

በእኛ አገር መንግስትና ፓርቲን መነጠል አይቻልም፡፡ህገ መንግስቱ ሳይቀር በብዙ አንቀጾቹ የገዢው ፓርቲ ፕሮግራም ግልባጭ መሆኑ ትስስሩን ላቅ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ መንግስት ሲለወጥ ባንዲራ፣ህገ መንግስት፣ብሄራዊ መዝሙር እንቀይራለን፡፡የመንግስት ስርዓት መዘርጋት አለመቻላችን ያመጣብን ጣጣ ልንለው እንችላለን፡፡ ህዝቡ በፓርቲው እምነቱን አጣ ማለት መንግስትንም አያምነውም ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የመንገስታት ታሪክ አመኔታ በማጣት ረገድ ግምባር ቀደሙ ይመስለኛል፡፡እምነት የጠፋበት አጋጣሚም ከኢህአዴግ የትጥቅ […]

ይድረስ ያልኩት በቀጥታ ባይደርሶትም መስማትዎ እንደማይቀር እገምታለሁ፡፡ ሰላም የምሎት ሰላምታ የእግዚአብሄር በመሆኑ ነው፡፡ እንጂ ጫንቃችን ላይ ተጎብራችሁ የዜግነት ክብንርን አውርዳችሁ የዜግነት ክብር የምታዘምሩ በሆናችሁ፣ በብሄር ፣በጎሳ ከፋፍላችሁ…ሰብዓዊ መብታችንን ገፋችሁ..ኑሮን መቋቋም እንዳንችል አድርጋችሁ ለስደት ስለዳረጋችሁን ሰላምስ ማለት አይገባም ነበር፡፡ ለስምም ሆነ አልሆነ በአሁኑ ሰዓት ለሀገሪቷ ጠ/ሚኒስትር በመሆንዎ ነው ይድረስ ያልኩት ለእርሶ ይሁን እንጂ ለሚመለከታቸው ባለስልጣኖች ሁሉ […]

እለተ ሰኞ – ጥቅምት ሊሸኝ ህዳር ሊገባ የቀሩት ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው። በሳውዲ አረቢያ በህጋዊ መንገድ ገብተው ከአሰሪዎቻቸው ጋር ባለመግባባትና ፈርጀ ብዙ በሆነ ምክንያት መኖሪያ ፍቃድ የተበላሸባቸው ማደስ እንዲችሉ ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው ያለ ህጋዊ ሰነድ በግል ሲሰሩ ለነበሩ ፣ ከአምስት አመታት በፊት በህጋዊ መንገድ በሃጅ በኡምራ ገብተው ወደ ሃገራቸው ሳይመለሱ በህገ ወጥ መንገድ ያለ መኖሪያ […]

በለገጣፉ ፖሊስ ከቢሮው ቅዳሜ ዕለት የተወሰደው ጋዜጠኛ ሚልዮን ደግነውና ሰኞ ማለዳ የስራ አጋሩን የተቀላቀለው ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ በእስር ከቆዮ በኋላ ትናንት አመሻሽ እያንዳንዳቸው 600 ብር ዋስ በማስያዝ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡ ጋዜጠኞቹ ለእስር የተዳረጉት በኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ በለገጣፉ የተፈጸመን የመሬት ሙስና የሚያትት ዜና እና ዘገባ በመስራታቸው መሆኑም ታውቋል፡፡ፖሊስ ቅዳሜ የያዘውን ሚልዮንን በማረፊያ ቤት በማቆየት ቃሉን የተቀበለው ሰኞ […]

እንዴት ነሽ ኢትዮጵያ፡ ስላም ነው? እንደዘበት ትቼሽ ወጥቼ ከቀረሁ ያለፈው መስከረም ገብርኤል ሃያ ዓመት ሆነኝ። ከጠቅላላ ዕድሜዬ ከሲሶው በላይ መሆኑ ነው። ጊዜው እንዴት ይሮጣል? ያኔ ትቼሽ ስወጣ ወደኋላ እንዳላይ ብዬ ድንጋይ ወርውሬ መውጣቴን ስለምታውቂ ምነው ይህን ያህል ዘመን ጠፋህ የምትዪኝ አይመስለኝም። ምን ላድርግ። አይንሽ እያየ አይገፉ መገፋት አስገፋሽኝ። ዘር አስቆጠርሽብኝ። መገፋቴን ለምን እንደማለት በመገፋቴ ከንፈር […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከመላው ኢትዩጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ለመዋሃድ በምክር ቤቱ በማስወሰን በጽህፈት ቤቱ አማካኝነት ለመኢአድ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ሁለቱ ፓርቲዎች ለመዋሃድ በሚያስችሏቸው ሂደቶች ዙሪያ ለመነጋገር ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡ ፓርቲዎቹ ለመዋሀድ ለመዋሀድ የሚበቁበትን ሃላፊነት በመውሰድ የኮሚቴው አካል የተደረጉት ፓለቲከኞች በመጀመሪያው ቀን የውይይት ስብሰባቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የውህደት ውይይቱን ለማድረግ መስማማታቸውም ሂደቱን በመግባባት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን […]

ወጣቱ የነፃነት ሰላማዊ ታጋይ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ዋለ የፃፈው ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› ገበያ ላይ ዋለ፡፡ አንዷለም አርአያ ክብር ነው፡፡ ምሳሌና አርአያ ብናደርገው የምንጠቀምበት ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በቅርበት ስለማውቀው ብቻ እራሴን እንደ ዕድለኛ እቆጥራለሁ፡፡ ማርቲን ሉተር ኪነግንና ማህተመ ጋንዲን አንስቶ አይጠግብም፡፡ ስለፍቅር ሲል ሁሉን አሳልፎ መስጠት የሚችል፤ ስለ ኢትዮጵያ የሚሰስተው የሌለው ውድ ወጣት ነው፡፡ ለአላማው በፅናት መቆምን […]

የኛ ነግር መልሶ መላልሶ ሆኗል። በገራችን አቆጣጠር በ1960ዎቹ የተማሩና የነቁ ወጣቶች አቢዮት ማካሄድ በጀመሩ ጊዜ የተነሱ ልዩነቶች አንዳንዴ ቅርጻቸውን በመጠኑ ይቀይሩ ይሆናል እንጂ ዛሬም ድረስ ባንድ ወይ በሌላ በኩል የልዩነትና የፍዳችን ምንጭ ሆነው ቀጥለዋል። እነዚህ ልዩነቶች መረቀቂያዎች፤ መጣያያዎች ቢያመች መገዳዳያዎቻችን ናቸው። ችግር የሆነው ጎራ ለይተው በነበሩ ፖለቲከኛች የሀሳብ ልዩነቶቹ መፈጠራቸው ወይ መኖራቸው አልነበረም። ወይ ልዩነት […]

በአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት የተዘጋጀው የ5 ሳምንት ስልጠና የመጀመሪያው ክፍል (1) እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ረጅም የነፃነት ዘመን ሲኖራት በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋችም። ስለዚህ ስልጠና ክፍል አንድ “ኢትዮጵያ ምን ስትሰራ ነበር?” የሚል ጥያቄ አንስቶ ሁለት አብይ ክሎች ያሉት ሰፊ ታሪካዊ መልሶች ሰጥቷል። በመቀጠል ክፍል አንድ (2) የሰላማዊ ትግልን እድገት አስመልክቶ ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ ዛሬ እስካለንበት ዘመን […]

ባሰላው ባሰላው እንቢ አለኝ እንዝርቱ፣ ከታችም አይደለ ከላይ ነው ጥመቱ። የጎንደር ሕዝብ እንጉርጉሮ ኦክቶበር 28 እንደ ሃገሩ አቆጣጠር ጠዋት ጉልበተኛ ነፋስ ከባሕር ተነስቶ በደቡብ እንግሊዝ በኩል አድርጎ እያቆራረጠ ወደ ሰሜን ተፈተለከ። የባሕሩ ሰይጣን የላከውን ጉልበተኛውን ነፋስ የፈራው አዳሜ ፈረንጅ ሁሉ ተርበትብቶ እኛንም በሬዲዮንና በቴሌቪዚዮን ሲያርበተብተን ሰነበተ። “ይህንን ቀን ከቆመ የተቀመጠ፣ ከተቀመጠም የተደበቀ ነው የሚያልፈው። ደፍሮ […]

“የአፄ አብርሃም ያዬህን ጽሑፍ አንብበን ስንጨረስ ነገር ማብላላታችንን ትተን ዝም ብለን መጋደም አልቻልንም፡፡ ዘመናችን ብዙ የሚሠራበት ሣይሆን ብዙ የሚወራበትና የሚጻፍበት መሆኑን እናውቃለንና አግራሞታችን ወሰን አልነበረውም፡፡ ጥሎብን ‘ሌላ ሥራ የላቸውም ወይ?’ እስክንባል ድረስ በዬቀኑ ብዙ እናነ(ብ)ባለን፤ ይህም ሲሆን በምንታዘበው ሁሉ እናነባለን፡፡ ሕዝባችንን የሚጠቅም ነገር ለማከናወን የዛሬ አሥራ ሁለት ዓመት ገደማ ብዙ ብንጥርም የአማራ ኤሊቶች እያወኩን ጥረታችን […]

እረፍት አደርግ ብየ ከማህበራዊ መገናኛ መድረኩ ገለል ባልኩባቸው እንደ ብርሃን ፍጥነት በሚወረወሩት ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበርካታ ወዳጆቸ በርካታ መልዕክቶች ይደርሱኛል ። ብዙው መልዕክት ደግሞ የሚያጠነጥነው በጅዳ እና በአካባቢው በተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች አሰቃቂ ስቃይ ላይ ያተኮራል …ለነገሩ የአብዛኞቹ መልዕክቶች ብቻ ሳይሆኑ ከመልዕክቶች ጋር የሚላኩልኝ መረጃዎች እረፍት የሚነሱ ናቸው! … አዎ ተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር በመረጃነት የታጨቀባቸውን የመልዕክት […]

በአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀውና በሰላማዊ ትግል ላይ ሰፊ ምርምር ባደረጉት በአቶ ግርማ ሞገስ በሰላማዊ ትግል ላይ እየተሰጠ ያለው ሳምንታዊ ስልጠና ቀጥሏል፡፡ በስልጠናው በሰላማዊ እና ትጥቅ ትግሎች መካከል ንጽጽራዊ ትንተና የተሰጠ ሲሆን ትንተናው በስድስት ክፍሎች የተከፋፈለ ነበር፡፡ የሰላማዊ ትግል እና የትጥቅ ትግል ልዩነቶች በመንግስት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች (የስልጣን ምንጮች) ጥያቄ ዙሪያ፣ መንግስት በማስወገድ ጥያቄ […]

የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብርካው አስተዳደር ላይ ያለቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን ሰብስቦ መልስ እንደሚሠጣቸው ቃል ገብቶ እንደነበር ታውቋል፡፡ ነገር ግን በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በለቱ የወጣው […]

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በሚሊዩኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት መምህር አበበ አካሉ ትናንት 14/02/06 ዓ.ም የደህንነት መስሪያ ቤት አባላት ነን ባሉ ሶስት ቅጥረኞች የግድያ ሙከራና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ለፍኖተ ነጻነት ይፋ አድርገዋል፡፡ ሰላማዊው ታጋይ እንደተናገሩት በምሳ ሰዓት ኮተቤ መሳለሚያ አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ ህገ ወጦቹ […]