በአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት የተዘጋጀው በሰላማዊ ትግል ላይ ያተኮረ የ5 ሳምንት ስልጠና ዛሬ ተጀመረ – ፍኖተ ነጻነት

በአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት የተዘጋጀው የ5 ሳምንት ስልጠና ዛሬ ተጀመረ፤ ስልጠናው በሰላማዊ ትግል ላይ ጥልቅ ጥናት ባደረጉት በአቶ ግርማ ካሳ ነው፡፡
አቶ ግርማ ሞገስ ኢትዮጵያ ረዥም የነፃነት ታሪክ ቢኖራትም በስልጣኔ ለምን እንዳልገፋች? እስከዛሬ ሰላማዊ ትግል ተደርጓል ወይ? የሚሉ ጭብጦች ላይ አተኩረዋል፡፡
በተለይ የሀገሪቷ ባህል ቀራፂ በነበሩ አካላት ዘመናዊ ስልጣኔ ሲያጥላሉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

በመቀጠልም ሀገሪቷ የጦርነት መዓት እንዳልተለያት እንዲሁም እስርም ታሪካችን መሆኑን እነ አምባ ግሼንን የመሳሰሉ ቦታዎችን በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡
ለአስረጂ የነተክለፃዲቅ መኩሪያ፣ ባህሩ ዘውዴ፣ ሃሮልድ ማርከስ፣ ፓንክረስት፣ ገብረህይወት ባይከዳኝ፣ ጆን ስፔንሰርን መፅሀፍት ጠቀረሰዋል፡፡

የሰላማዊ ትግሉን ትንተና የጀመሩት የአልበርት አኒስታይንን አባባል በመጠቀም ነው፡፡ “ እንደማይሰራ ያየነውን መንገድ ለመጠቀም በተደጋጋሚ መሞከር እብደት ነው” በሚል፡፡
በመቀጠል የግሪክ ፕሌቢያኖችና ፓርቲሲያኖችን ታሪክ በማቅረብ የሰላማዊ ትግል ታሪክ ሩቅ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡
በሰላማዊ ትግል ትብብር ከመንፈግ በቀር ጦር ስላለመኖሩ አሳይተዋል፡፡

አንድን የፈረንሳይ ፈላስፋ ሲጠቅሱም
“ የፈረንሳይ ህዝብ ሆይ! የሚጨቁንህ ሁለት እግር ያለው፣ ሁለት አይን ያለው፣ ሁለት ጆሮ ያለው፣ አንድ ጭንቅላት ያለው ነው፤ አንተ ግን ሚሊየን እግር፣ ሚሊየን አይን፣ ሚሊየን ጆሮ እያለህ ዝም ክልከው ተባበርከው ማለት ነው” ያለውን ጠቅሰዋል፡፡
ሊዮ ቶሊስቶይ- የሰላማዊ ትግል መንፈስ አመንጪ

ጋንዲ “ጦርነት እና ሰላም የሚለውን የቶሊስቶይ መፅሀፍ ካነበበ በኋላ ነው ሰላማዊ ትግልን ያመነው፣ ስራዬ ብሎ የያዘው፡፡
ቶሊስቶይ “በጥንቆላ ካላመንክ በቀር 30 ሺህ የእንግሊዝ ወታደሮች 200 ሚሊዮን ህንዳውያንን ሀገር ነጠቁ ማለት አይቻልም” ያለው ታሪኩን ቀየረ፡፡
ትብብር ነበር የነፈጓቸው፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግን ጨምሮ በየቅደም ተከተል እናቀርባለን

– See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5778#sthash.9YFm1sJs.dpufDSC03241DSC03242