የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ አማርኛዉ ክፍል ባቀረበው ዘገባ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ኢትዮጵያዉያን ከቅያቸው እንደተፈናቀሉ ታወቀ። ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢና ቀለም የተፈናቀሉ ወገኖች፣ ሲሆን፣ «ተባረርን ቤት ንብረታችን ወደመ፣ ተቃጠለ» ሲሉ የደረሰባቸውን ሰቆቃ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በዝርዝር ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የክልሉ ባለስልጣናት ዜጎች መፈናቀላቸውን ያመኑ ሲሆን፣ «ተገደው ሳይሆን ፈርተው ነው የሄዱት» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ሕወሃት/ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ […]

በዛሬው ዕለት በአዋሳ ከተማ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በሀዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ከ30 በላይ በፖሊስ የታሰሩ ሲሆን የሲአን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ ለምን ይታሰራሉ ብለው በመጠየቃቸው እሳቸውንም አስረው ከምሽቱ 3፡30 ለቀዋቸዋል፡፡ በቅስቀሳው ወቅት ወረቀቶች የተበተኑ በመሆኑ ህዝብ በነቂስ […]

ሐሳብን የመግለጽ ነጻነትና ኢህአዴግ አለማችን ለጋዜጠኞች፣ለብሎገሮችና ሐሳባቸውን በመግለጽ ተፈጥሯዊ መብታቸውን ለሚጠቀሙ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ገሃነማዊ መልክ እየተላበሰች ትገኛለች፡፡በሶሪያ፣ሶማሊያ፣ኢራቅ፣አፍጋኒስታን፣ሊቢያ ፣ግብጽና ዮክሬይን የተፈጠሩ ሰብኣዊ ቀውሶች የጋዜጠኞችና ጦማሪያን ህይወትን በልተዋል፡፡ የቀውሱ ሃይሎች ጋዜጠኞቹንና ጦማሪያኑን የመጀመሪያ ኢላማቸው በማድረጋቸውም ዛሬ በእነዚህ አገራት በሚገኙ ማጎሪያዎች ስቃይ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡በዚህ ዓመት ብቻ በእነዚህ አካባቢዎች የ27 ጋዜጠኞች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ በግብጽ እስር ቤት የአልጀዚራ […]

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በነገው እለት ሰኔ 15/2006ዓ.ም የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ ከ30 በላይ የፓርቲው አባላት በፖሊስ መታሰራቸውን ተከትሎ የሀዋሳ ከተማ ባለስልጣናትና የከተማው ፍትህ መምሪያ ሐላፊ በተገኙበት የተካሄው ስብሰባ መታሰር አልነበረባቸውም፤አሁንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው በሚሉና ማሰራችን ትክክል ነው ከተለቀቁ ነገ ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም በሚል ለሁለት ተከፍለው ሲሟገቱ ማምሸታቸውንና […]

ሰኔ 15 የሰማእታት ቀን ነው። ሰኔ 15, 1980 ዓም በሐውዜን ከ2500 በላይ ንፁሃን ዜጎች በአንድ ፀሓይ የተጨፈጨፉበት ቀን ነው። ጭፍጨፋው የህወሓት እጅ እንደነበረበት ይነገራል። ይህ ማለት ቦምቡ የጣሉት ጀቶች የህወሓት ነበሩ ማለት አይደለም። ህወሓት በግዜው በሓውዜን ከተማ ጉባኤ እንደሚያደርግ ሆን ብሎ (የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት) ለደርግ የሐሰት መረጃ አስተላልፏል። ብዙዎቹ የደርግ ጀነራሎችና መርማሪዎች የህወሓት “ስርዒት” ነበሩ። […]

“እስሩ ቅስቀሳውን አያስተጓጉለውም” አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ከተማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የፓርቲው ብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በአንድነት ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን ወ/ሪት እልፍነሽ ከበደን የተሳፈሩበትን ሚኒባስ በማስገደድ ወደ ምስራቅ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል ፡፡ ሀላፊዋ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በጣቢያው ታስረው የሚገኙ ሲሆን በምን ምክንያት ቁጥጥር ስር እንደዋሉና እስከመቼ በእስር እንደሚቆዩ ለማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል […]

በሰሜን ጎንደር ምዕ/አርማጨሆ ወረዳ አብርሃጅራ ከተማ የአንድነት ፓርቲ የወረዳ የፋይናንስና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ የሆነው አቶ ደስታው ተገኝ ከአ.አ ዩኒቨርስቲ በ2000 ዓ.ም በቢዝነስ ኢዱኬሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ካገኘ በኋላ በሐረር፣ በጎንደር ያስተማረ ሲሆን በም/አርማጨሆ ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት የመማር ማስተማር ጉዳይ ፈፃሚ ሆኖ ከ4 ዓመት በላይ አገልግሏል፡፡ በት/ቢሮው ለማስትሬት ትምህርት ዕድል ብቸኛ ተወዳዳሪ የነበረ ቢሆንም ለ3 ዓመታት ተከልክሏል፡፡ […]

የደቡብ ክልል ዋና ከተማ ናት። በርካታ ብሄረሰቦች በፍቅር የሚኖሩባት ዉብ ከተማ። ሰኔ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ደሴን፣ ባህር ዳርን፣ አዳማን፣ ጊዶሌን አዲስ አበባ እና ደብረ ማርቆስን በመቀላቀል ድምጿን ታሰማለች። አዋሳ !!!! የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትሕና ለመሬት ባላቤትነት በሚል መርህ በሐዋሳ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል። ለሰልፉ የከተማዋ ባለስልጣናት እውቅና የሰጡ ሲሆን፣ የአንድነት አባላትን ደጋፊዎች ቅስቀሳ ጀምረዋል። የሰላማዊ […]

በምስራቅ ጎጃም በነማይ ወረዳ ደንጎሊማ ቀበሌ አቶ ሞሳ አዳነ የተባሉ የመኢአድ አባል ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን ከቤታቸው ወደ እስር ቤት መሄድ አለብህ በሚሉ የብአዴን ካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ይህን ድርጊት የፈጸሙት ሁለት የብአዴን ካድሬዎች አቶ አዲሱ ጫኔና አቶ ብርሃኑ ታመነ ወደ መኖሪያቸው በመሄድ ወደ እስር ቤት ትሄዳህ በማለት ለማስገደድ ሲሞክሩ በተፈጠረ እሰጣገባ አቶ ሞሳ አዳነ […]

ቤተክርስቲያን እና መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅና ጓንት ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የማያባራ ጭቆና ማካሄድ ከጀመሩ ረዥም ዘመናት ተቆጥረዋል። ይብልጡኑ የመንግስቶች ጎህ ከቀደደ ጀምሮ በተለይ የተዋህዶ ሃይማኖት መሪዎች አስፈሪ እና አስደንጋጭ እንዲሁም አሳዛኝ ደግሞም አሳፋሪ ቃላቶችን በመጠቀም ስጋዊ እና ምድራዊ ስልጣኖችን ለገዢዎች ለማደላደል ይህ ነው የማይባል ግፍ በምእመናኖቻቸው እን በሌሎች አማኞች ላይ ፈጽመዋል አስፈጽመዋል፤ እየፈጸሙ ነው፤ እያስፈጸሙ […]

የብዙ ድርጅቶች ስብስበ የሆነው መድረክ በአዋሳ ከተማ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን በጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ሕዝብ በመገኘት ድምጹን እንዳሰማ የደረሰን ዘገባ አመለከተ። መድረኩ ከጥቂት ሳምንታት በፎኢት በአዋሳ ሕዝባዊ ስብሰባ አድርጎ የነበረ ሲሆን ፣ በአዲስ አበባ የተቃዉሞ ሰልፍ ማድረጉ ይታወሳል።

…ዕለቱ የሁለት ሺ ሶስት ዓመተ ምህረት የመስቀል በዓል የተከበረበት ማግስት፤ ሰሜናዊቷ የኤርትራ አዋሳኝ ወልቃይት ገና ከእንቅልፏ ሙሉ ለሙሉ ባለመንቃቷ፣ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ጎፈሪያቸው የተንጨ(ባረረ ፋኖዎች በውስጧ ካሉ ተቋማት ወደ አንዱ እያመሩ ስለመሆኑ የጠረጠረች አትመስልም፤ ከኤርትራ የተነሱት ፋኖዎች መዳረሻ በወረዳዋ ታዋቂ የሆነው አወርቅ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመሆኑ፤ ማንም ልብ ሳይላቸው ልክ እዚያው እንደደረሱ፣ ከፊሎቹ በሰለጠነ […]

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ተሰብስቦ በመኢአድና አንድነት እንዲሁም በዲሲፕሊን ኮሚቴ መመሪያ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ አንድነት ፓርቲና መኢአድ በተፈራረሙት ቅድመ ውህደት መሰረት የጉባኤ ጠሪ አብይ ኮሚቴ አዋቅሯል፡፡ በዚህም መሰረት ጉባኤው ጠሪው 7 አባላት ሲኖሩት ከ 7ቱ አባላት 5ቱ የሁለቱን ጉባኤ ለማመቻቸት የተሰየሙ ናቸው፡፡ እንዲሁም በፓርቲው የዲሲፕሊን ኮሚቴ መመሪያ […]

ሰኔ 1 ቀን 1997ዓ.ም፤ በአዲስ ከተማ ት/ቤት የተጀመረው ተማሪዎችንና ንጹሃን ዜጐችን በግፍ የመግደል እርምጃ ተከትሎ አብዛኛው ባለስልጣናት ልጆቻቸውን ከየት/ቤቱ በአጃቢ ያስወጡ ነበር። ወደ ካቴድራል ት/ቤት በሁለት ኮብራ ተጭነው የተላኩ 20 ልዩ የፌዴራል ፖሊሶች የጄ/ል ሰአረና የጄ/ል ብርሃነ (ወዲ መድህን) ሴት ልጆችን አጅበው ሄዱ። ሁለቱ ሴት ልጆች በማግስቱ አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ተመቶላቸው ዓርብ ሰኔ 3 ቀን […]

የእስከመቼ አዘጋጅ፤ ሰኔ ፯ ቀን ፳፻ ፮ ዓመተ ምህረት በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊ የዜና መለዋወጫ መስኮች፤ “ትግሬዎች በዚህ መንግሥት ተጠቅመዋል? ወይንስ አልተጠቀሙም?” የሚለው ጉዳይ ዓይነታ መወያያ ሆኖ፤ መድረኮቹን ሁሉ አጣቦ ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ፤ አንድን ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ታጋዮች ሲያነሱ፤ ከትግሉ ዋና ግብ አንጻር ነው። እንዲያው ለወግ ያህል ወይንም ቁጭትን ለመዘርገፍ የሚደረግ ውይይት፤ የታጋዮችን ቀልብ አይስብም። ይኼ […]

“‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ። አከብራችኋላሁ።›› ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ።…” ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ። የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ […]

ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ብቻ ተለይተው ሊፈርሱ መሆኑን በአካባው ሚገኙ ነጋዴዎች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ ነጋዴዎቹ እንደሚሉት ከተክለ ሃይማኖት ጀምሮ እስከ ጥቁር አንበሳ የሚገኙ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ፣ የጎማ መሸጫ እና ሌሎች የንግድ ሱቆች በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲፈርሱ በመንግስት ተወስኗል፡፡ ከንግድ ቤቶቹ በስተጀርባ የሚገኙ የቀበሌ ቤቶች አብረው የማይፈርሱ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ “እኛ ግብር ከፋዮች ሆነን ከሌላው […]

ሰኞ ግንቦት 18 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ ራት ከበላ በኋላ ከዩኒቨርስቲ ግቢ ባልታወቁ ኃይሎች ታፍኖ የተወሰደው ወጣት መልካሙ አምባቸው ያለበት ሳይታወቅ ቀናቶች ማለፋቸው ያሳሰበው አንድነት ፓርቲ በየፖሊስ ጣቢያው ፍለጋውን ቢያጠናክርም ሊያገኘው ባለመቻሉ ግንቦት 29 ቀን 2006 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት በግልባጭ፡ – ለትምህርት ሚኒስቴር – ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ፋኩልቲ – ለአ/አ […]

ይህን ፅሁፍ በሎሚ መፅሄት ላይ ባለፈው ሳምንት አወጣሁት፡፡ መፅሄቱ ላልደረሳችሁ ይኸው እዚህ ለጠፍኩት፡፡ በቅድሚያ እንኳን ወታደራዊ አምባገነኖች ተደምስሰው ‹‹ዴሞክራሲያዊ›› አምባገነኖች ለተተኩበት የግምቦት 20 በአል አደረሳችሁ፡፡ ዛሬ ዝምታ ሲበዛ ፍርሀት፣ ውሸት ደግሞ ሲደጋገም እውነት ይሆናልና የማውቀውንና የተሰማኝን ለአምባቢም ግልፅ ሊሆንለት የሚገባ ጉዳይን በወፍ በረር ላስቃኝ ወደድኩ፡፡ ለፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ሎሚ መፅሄት አቤል ኤፍሬም በተባለ ግለሰብ የቀረበውንና […]

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ “አይናለም” የተባለ ጣብያ (ንኡስ ወረዳ) አለ። በዛ አከባቢ ያለው ደን “የመለስ ፓርክ” ተብሎ ተከልሏል። ኗሪዎቹ “የመለስ ፓርክ” መባሉ አልተዋጠላቸውም፤ ተቃውመውታል። ባለፈው ወር ነው። “ከመለስ ፓርክ” የተወሰነ ዛፍ ይቆረጣል። በዚህ ጉዳይ የተቆጡ ካድሬዎች የአይናለም ኗሪዎችን ሰብስበው ዛፉ የቆረጠው ማን እንደሆነ ይጠይቃሉ። አውጫጭ መሆኑ ነው። ህዝቡ ላለመናገር አደመ። ህዝቡ ስላልተናገረ ለስምንት […]

በራያ ዓዘቦ ወረዳ ነው። ህዝብ ማዳበርያ አንገዛም፣ ገንዘብ የለንም በሚል አቋሙ ፀንቷል። የህወሓት ባለስልጣናትም የወረዳና የጣብያ (ቀበሌ) አስተዳዳሪዎችን ህዝብ ማዳበርያ እንዲገዛ እንዲስያገድዱ ያስፈራራሉ። አንዳንድ ካድሬዎች አለቆቻቸውን ለማስደሰት ህዝብን ያስፈራራሉ፣ ያስገድዳሉ። አብዛኞቹ ደግሞ የህዝብን ችግር፣ ጭቆናና በደል ተረድተው ከህዝብ ጎን ይሰለፋሉ። በራያ ዓዘቦ ወረዳ ህዝብ ለማሳመን (ለማስፈራራት) ማስፈራርያ የሚደርስባቸው አስተዳዳሪዎች ህዝብን ማስፈራራቱ ሰልችቷቸው ህዝብን አናስገድድም ብለው […]

አንድነት ለዴሞክራና ለፍትህ ፓርቲ የሀገራችን ውስብስብ ችግር በዘላቂነት እንዲፈታና ህዝቡ ለዘመናት ዋጋ ሲከፍልበት የኖረው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነ ይረዳል፡፡ የተቃውሞ ጎራው አንድ ጠንካራ ሃይል ለመፍጠር ከሚያስችለው ከግል ድርጅታዊ ጥንካሬና ስራ በተጨማሪ ልዩነትን አቻችሎና አጣጥሞ መሰባሰብ እንደሚገባም እንገነዘባለን፡፡ የህዝባችን ፍላጎትም የተበታተነ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳይሆን የተጠናከረና የተሰባሰበ አንድ ፓርቲ ማየት እንደሆነ […]

በሀገራችን ከድህነት እኩል የሚፈታተነን ችግር፤ ቢያንስ ግማሽ መንገድ እንኳ ሄዶ ለመደራደር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን አሊያም ቀና ልቡናውን ማጣታችን ነው፡፡ ግማሽ መንገድና የመቻቻል፣ ልዩነትን የማስተናገድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመልመድ ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ አገር በኔ ብቻ ተመርታ አገር አትሆንም ብሎ፤ ኃይለኛውና አሸናፊው ከወጣበት መሠላል ዝቅ ብሎ፤ ግማሽ መንገድ ወርዶ እንነጋገር፣ እንወያይ የማለት ባህል፤ ተሸናፊውም ከቁጭቱ፣ ከቂሙ፣ ለመጣል እንጂ አብሮ […]

ሰኔ ፪ 2006 ተሰናክለን ነበር፤ አሁን ግን ጸንተናል! «ዉጊያዉን ተሸነፍን እንጂ ጦርነቱን አልተሸነፍንም» ነበር ያሉት የፈረንሳዩ የ2ኛው ዓለም ጦርነት መሪ፤ ጀነራል ቻርለስ ደጎል፣ አገራቸው በናዚዎች ሥር በወደቀች ጊዜ። ልክ እንደ ዉትድርናዉም፣ በሰላማዊ ትግል ዉስጥ መሸነፍ፣ መዉደቅ፣ መሳሳት አለ። መነሳትም እንዲሁ፡፡ ታላቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እንዳሉትም፤ «በሕይወት ውስጥ ትልቁ ነገር ፈትሞ አለመውደቅ ሳይሆን፤ በወደቁ ቁጥር […]

መኢአድ እና አንድነት የውህደት ፊርማ ተፈራርመዋል። የአንድነት የሂሳብ ክፍል ሰራተኛን ሲፈነክቱ አንድ የመኢአድ አመራር ጥርሱን በድንጋይ አውልቀውታል። በዛሬው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች ዲፕሎማቶች ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ (አንድነት) የውህደት ፊርማቸውን በደመቀ ስነስር ስት […]

ዛሬ ሰኔ አንድ ቀን 2006 ዓ.ም በአዳማ/ናዝሬት የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት እና ለፍትህ በሚል መርህ ፣ የተጠራው ሰላማፊ ሰልፍ እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ መጠናቀቁ ከስፋራዉ በደረሰን ዘገባ ለማወቅ ችለናል። ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም የተጠነቀቀ ሲሆን፣ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ የተለያዩ ቀረርቶዎች ሲሰሙበት እንደነበረም ለማወቅ ችለናል። የተለያዩ መፈክሮች በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ሲሰሙ የነበረ ሲሆን፣ የነጻነት […]

ዛሬ ሰኔ አንድ ቀን 2006 ዓ፣ም አገር ቤት ከሚንቀሳቀሱ አንጋፋዎቹ ድርጅቶች መካከል የሚገኙት የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲዎች የቅድመ ዉህደት ፊርማ ፈርመዋል። በስምምነቱ ወቅት ዱርዬዎች ድንጋይ በመወርወር የነበረዉን ፕሮግራም ለማስተጓጎል ሞከረው ነበር። የቅድመ ዉህደቱን ስምምነት ወቅት አቶ አበባዉ መሃሪ የመኢአድ ሊቀመንበር ንግግር ሰጀምሪ ነበር የድንጋይ እሩምታ በጽ/ቤቱ ላይ የዘነበው። ከስብሰባው አዳራሽ የወጡትን የመኢአድና አንድነት ሰዎች ዱርዬዎችን […]

ሰማያዊ ፓርቲ የ2006 ዓ.ም የምክርቤት መደበኛ ስብሰባ የግማሽ አመት የስራ እቅድ ትግበራ ሪፖርትን ገምግሞ ያፀደቀ ሲሆን በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈፃሚዎች ኃላፊነት ሽግሽግም አፅድቋል፡፡ በመሆኑም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ወደ አደረጃጀት ጉዳይ ሲሄዱ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ደግሞ ከወጣቶች ጉዳይ ወደ ህዝብ ግኑኙነት ኃላፊነት ተዛውረዋል፡፡ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ በመሆን የተመደበው ደግሞ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ሲሆን የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና የመላዉ ኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ነገ ሰኔ አንድ ቀን 2006 ዓ.ም፣ የቅድመ ዉህደት ስምምነት እንደሚፈረም ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ገለጸ። ፓርቲዎች የነበሯቸዉን ጥቃቅን ልዩነቶች ሁሉ በጋራ የፈቱ ሲሆን፣ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተው ዉህደቱን ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል። ዘዝር ዘገባና የስምምነቱን ሙሉ ሰንድ እንዳገኝን ይፋ እናደርጋለን።

ከአክሱም ህዝብ ጋር ለመወያየት ለእሁድ ሰኔ 1, 2006 በከተማው ማጀጋጃ ቤት አዳራሽ ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚደረግ የአራና አመራር አባል አብርሃ ደስታ ዘገበ። በርካታ የአራና አባላት እየታሰሩ እንደሆነ የገለጹት አቶ አብርሃ ደስታ፣ በአክሱሙ ስብሰባ ብዙ ህዝብ ሊገኝ እንደሚችል ጽፈዋል። «እነሱ ያስራሉ፣ እኛ ደግሞ ህዝብን እናስተምራል። ። የነሱ ተግባር ህዝብን መጨቆን ሲሆን የኛ ደግሞ ህዝብ ለነፃነቱ በአንድነት እንዲቆም […]

የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በሚል መርህ በቁጫ ሊደረግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መተላለፉ ታወቀ። ከአዲስ አበባ የቅስቀሳ መኪና፣ ሜጋፎኖች፣ በራሪ ወረቀቶችና ፖስተሮች ይዞ ወደ ቁጭ የሰማራዉ ቡድን ከትላንት በስቲያ ሰላም በር ከተማ የደረሰ ሲሆን፣ ከዞኑና ወረዳዉ የአንድነት አመራርና አባአት ጋር በመሆን፣ ትላንት በማለደ ወደ ቅስቀሳ በሚሰማራበት ጊዜ፣ ፖሊሶች ቅስቀሳዉን አስቆመዋል። ከአዲስ አበባ የሄደው ቡድን እንዳለ እና የወረዳው […]

ወርኃ ግንቦት የቀድሞ ወታደራዊ አገዛዝ ከሥልጣን የወረደበትና አሁን አገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጣበት በመሆኑ በየዓመቱ መታወስ ከጀመረ 23 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእግርጥ በግንቦት ወር 1981 ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ከሥልጣን ለማወረድ ያሴሩ ከፍተኛ መኰንኖች የመፈንቅለ መንግሥት ያደረጉበት ጊዜም ነው፡፡ በዚሁ ወር በዓመቱ በጦር ፍርድ ቤት ሲታይ የከረመው የጄኔራሎቹ የመንግሥት ግልበጣ ወንጀል ‹‹መቋጫ›› አግኝቶ […]

አንድ ፎቶ አየሁ። ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጥቁር ጋዉን አድርጋ፤ ይመስለኛል በማስተር ዲግሪ ተመርቃ። ለርሷም ለቤተሰቦቿም እንኳን ደሳ አላችሁ እላለሁ። ኢ.ኤም.ኤፍ፣ ወ/ት ብርቱካን ወደ ፖለቲካ እንደማትመለስ፣ ምናልባትም ኑሮዋን በዉጭ አገር ልታደርግ እንደምትችል ዘግቧል። ጋዜጠኛ አበበ ገላው በበኩሉ፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለከፈለችው ታላቅ መስዋእትነት አድናቆቱን ገልጾ፣ «You are a truly phenomenal woman that must continue to fight […]

በአዳማ ናዝሬት ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 28 ቀን ቅስቀሳ ሲደረግ እንደነበረ፣ የአንድነት ፓርቲ የአዳም/ናዝሬት ቅርንጫፍ በፌስቡክ ገጹ ገለጸ። የመኪና ቅስቀሳ እንዳይደረግና በትላልቅ ፖስተሮች ማስተወቂያ እንዳይለጠፍ ፖሊሶች ያከላክሉ የነበሩ ሲሆን በቅስቀሳዉ የተሰማሩ፣ ድሬዳዋ ሆቴል አካባቢ፣ ለሰዓታት ታስረው እንደነበረ የአዳማ/ናዝሬት አንድነት ቅርንጫፍ በፌስ ቡክ ገጹ ያቀረበው ዘገባ ያስረዳል። የሰልፉን ሕጋዊነት የሚገልጥ ደብዳቤም ቀስቃሾቹ ለፖሊሶች ቢያሳዩም ፖሊሶቹ ለመልቀቅ ፍቃደኛ […]

ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 28 ቀን 2006 ዓ.ም፣ በደብረ ማርቆስ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በስፋት በራሪ ወረቀቶችን ሲያሰራጩ እንደዋሉ የሚሊዮንች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ዘገበ። ከበራሪ ወረቀቶች በተጨማሪ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ትላልቅ የማስታወቂያ ፖስተሮች የተለጠፉ ሲሆን፣ በመኪና ዉስጥ በመሆንም ፣ በድምጽ ማጉያ ቅስቀሳ ተደርጓል። ፖሊስ ሕጋዊ ለሆነው ሰልፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 10 የደብረ ማርቆስ አንድነት አባላትን አስሮ […]