በአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጉጉትና ምኞት ፣ ልጆችዋ ከርሷ የሚሰደዱባት ሳይሆን የተሰደዱት ተመልሰው ለሌሎች መጠጊያ የምትሆን፣ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት፣ የሰብአዊ መብቶች የሚከበሩባት፣ ዘር፣ ኃይማኖት፣ ጾታና መደብ ሳይባል ለሁሉም እኩል የሆነች፣ አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው። ነገር ግን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገዛዙ እያየን ያለነው፣ ልብን የሚያደማና የሚያቆስል ነው። በስድሳዎቹ ከነበረው የደርግ ስርዓት በባሰ፣ […]

” ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፈታተን መግጠም አለብን። ” የወያኔ ባለስልጣናት ” አላርፍ ካሉ ፍቃዳቸውን ሰበብ ፈጥረን እንነጥቃቸዋለን። ” የምርጫ ቦርድ ሃላፊ በኢሕአዴግ ባለስልጣናት እና በምርጫ ቦርድ መካከል መጭውን ምርጫ በተመለከተ ሰፋ ያለ ዝግ ስብስባ ተካሂዶ ነበር ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አከባቢ የተገኘ መረጃ ጠቁሟል። በአይቶ ጸጋዬ በርሄ የተንታለለ የመሃይማን ቢሮ ውስጥ የምርጫ ቦርድ ታዛዥ ሃላፊዎች እስከምሽት […]

ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር በአምባገነንነት መስመሩ ለመቀጠል የቆረጠ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው!!! በፖለቲካ አመለካከታቸው እና እምነታቸው የታሰሩ ዜጎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በድጋሚ እንጠይቃለን!! ሕወሓት/ኢህአዴግ ለአለፉት 23 ዓመታት ወደር የሌለው የዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋና የሰብአዊ መብት ረገጣ በዜጎች ላይ ሲፈጽም መቆየቱና አሁንም በዚያው የአፈናና እስር መንገድ መቀጠሉን ዓለም የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይም በሚቀጥለው ዓመት […]

ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን እንዴት ማፈን ቻለ? ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት ለግንቦት 7 ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የሞትና የሽረት ጥያቄ ነው:: በቂ ማስረጃ እስክሚሰበሰብ ድረስ አራት አቅጣቻዎችን መመርመር ያስፈልጋል:: 1) ለሻቢያ ሁሉ ነገር ከራስ በላይ ነፋስ ነው:: ራሱ ሻቢያ በተዘዋዋሪ ለወያኔ የአቶ አንዳርጋቸውን የበረራ ሰዓታቸውን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል::ይህ እንግዲህ በኤርትራ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት 7 መሪዎች ሁኔታውን በደንብ […]

ካሳለፍነው ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው በማዕከላዊ በእስር ላይ የሚገኙት ወጣቱ ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ፣ ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ም/ሀላፊ ወጣቱ መምህርና ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የአረና ፓርቲ አመራር በትላንትው ዕለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ከምሽቱ 12፡16 ላይ የአረና ፓርቲ […]

በዚህ ወር ብቻ እጅግ ከባድ የሆኑ ለጆሮ የሚቅፉ እና ለሰው ልጆች የሚያሰቅቁ የሰብአዊ መብት ገፈፋዎች እና የዜጎች ወደ እስር ቤት መወርወር የበለከተበት ከሃገር ቤትም አልፎ እስከ ጎረቤት አገር ድረስ ተዘልቆ በጉቦ የዜጎች የመዘዋወር መብት በስውር እጆች የተደፈሩበት እሱንም ተከትሎ የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮች ከየመንገዱ እና ከቤታቸው እየተያዙ ወደ እስር የተወረወሩበት ሁኒታ እያየን እየሰማን ነው። የግንቦት ሰባት […]

በአሸባሪው መንግስታዊ ዘራፊ እና አፋኝ ቡድን የታፈነው አቶ አንዳርጋቸው ጸጌ ወያኔ ለመፍታትም ሆነ ለመግደል ዝግጁ አይደለም ። ግደሉት አሊያም ስቀሉት ቢባሉ እንኳን በፍጹም አያደርጉትም። ምእራባውያኑ ከአፍ ወሬ ውጪ ምንም የሚተገብሩት ነገር የለም ፡ እስክንድር ነጋ በቂ ምሳሌ ሊሆን ይችላል ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጀምሮ እስከ አሜሪካው የውጪ ጉዳይ አናት ኬሪ ድረስ ድምጻቸውን ቢያሰሙም ለይስሙላ እና ለብሄራዊ […]

ኢትዮጵያ ሪቪው ምንጮቹን ጠቅሶ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የታፈኑት፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሳያወቁት ፣ በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የሕወሃት ደህንነት ጽ/ቤት እና በአቶ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ዉሳኔ እንደሆነ ዘገበ። ሁለቱ የሕወሃት ባለስልጣናት፣ የሆነውን ነገር ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ለመንገር እንኳን ደንታ እንደልነበራቸው ኢትዮጵያ ሪቪው፣ እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም […]

ሰላማዊ ሰዎችን ማሰር ቀለቡ ያደረገው መንግስት፣ በትላንትናው እለት ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ከአረና አቶ አብርሃ ደስታ እንዳሰራቸው ተነግሯል። ይህንን በመቃወም በፌስቡክ ኢትዮጵያዉያን ካሰፈሩት መካከል ጥቂቱን እንደሚከተለው ቀንጭበን አቅርበናል፡ ያሬድ አማረ፡ «ወደኋላ አንመለስምዘመን ተሻጋሪ ወጣቶች በቅለናልና በምንም መልኩ ለሚደረግ ማዋከብ፤እስራት እና ግድያ ከጀመርነው የሰላማዊ ትግል መስመር […]

የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት […]

አቡጊዳ – እነ ሃብታሙ ፍርድ ቤት አልቀረቡም – አብርሃ ደስታ የት እንዳለ አይታወቅም « ከትላንት በስቲያ የተያዙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በዛሬው እለት አራዳ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች እንደጠቆሙት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ም/ኃላፊ የሆነው አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም […]

ከመኢአድ/አንድነት ውህደት አመቻች ኮሚቴ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ………………………………………………………… የውህደት አመቻች ኮሚቴውን በማሰር ውህደቱን ማደናቀፍ አይቻልም!!! ኢህአዴግ ሰሞኑን የጀመረው እስር የአንድነት/መኢአድን ውህደት የማደናቀፍ አቅም እንደሌለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ማረጋገጥ እንወዳለን …………………………………………… በኢትዮጵያችን በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት እየታገሉ የሚገኙት አንድነትና መኢአድ ከጥልቅ ውይይት በኋላ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ የሚፈልገውን በመገንዘብ፤ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚችል የበተባበረ የፖለቲካ ሃይል ለመፍጠር እንዲቻል […]

አገር ቤት ያሉ መሪዎች ቁርጠኝነት ያስደንቀኛል። ግርማ ሰይፉ «ለመታሰር እንዘጋጅ» አለ። ዳንኤል ተፈራ «ገዥዎች፣ እመኑኝ ባሮጌው መንገዳችሁ በርካቶችን ነፃነት ናፋቂዎች በሰፋፊ እስር ቤታችሁ ታጉሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የዚህን ትውልድ የነፃነት መንፈስ ግን ልታስሩት አትችሉም» አለ። የፍኖት ዋና አዘጋጅ ነብዩ «ጨቋኞችን መታገል ፅድቅ እንጂ ኩነኔ እንደሌለው አምናለሁ፤ ጭቆናን እምቢ በማለቴ የምጠጣት እያንዳንዷ ፅዋ በፈጣሪ ዘንድ ወሮታ […]

ግፍና ሰቆቃ ወልዶናል – የአዲስ አበባ አንድነት ሕዝብ ግንኙነት ያሬድ አማረ ************************************************************ እንታሰራለን ስንል አንፈታም ማለት አይደለም ፤ በትግል ውስጥ አልፈን እናሸንፋለን ስንልም ላንሞት እንችላለንም ለማለት አይደለም ፡፡ ሊሰመርበት የሚገባው ግን በሰላማዊ ትግሉ ማሳ ላይ ዘር ሆነን ተዘርተን ብዙ ፍሬ እንዳፈራን በተራዳን ወቅትና ወደ ጎተራ በአንድነት ተሰባስበን በገባን ወቅት የተነሳንለት ዓላማ ጥልቅና ምጡቅ እንደሆነ ልባችን […]

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ በትላንትናው ዕለት በማዕከላዊ እስር ቤት ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ በቤተሰቦቹ እና በወዳጅ ጓደኞቹ እንዳይጎበኝ በመደረጉ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ እንዳልተቻለ የፓርቲው አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ አመራሮቹ አክለውም፣ በዛሬው ዕለት ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ያመሩት፣ የሀብታሙ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉ እና አቶ ገበየሁ እስረኛውን መጠየቅ አትችሉም ተብለው መባረራቸውን አስረድተዋል፡፡

ሐብታሙን ይህ ይገልጸው ይሆን ? ********************************* በምረቃ መጽሔቱ ፎቶ ስር‹‹የፈራ ይመለስ››ብሎ ነበር ******************************************** ሐብታሙ አያሌው ራሱን ለፈጣሪው ያስገዛ ሐይማኖተኛ ሆኖ ያገኙት ኢህአዴጎች በአነጋገሩና ነገሮችን ለመግለጽ ያለውን ውስጣዊ ድፍረት ተገንዝበው ከቤተክርስቲያን ጠለፉት ፡፡አባላቸው አደረጉት፡፡ሐብታሙ አባል የሆነበት ኢህአዴግ ጭንቅ ውስጥ ነበርና በልጁ የመናገርና የማሳመን ችሎታ ለመጠቀም ከወጣቶች አደረጃጀት አንስቶ እስከ ወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዘዳንትነት አድርሶታል፡፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር […]

የሰሞኑ የኢትዮጵያችን ሁኔታ ሀዘን፣ ቁጣ፣ ንዴት፣ እልህ፣ ብሎም የደስታ ስሜትን የቀላቀለ ነበር፡፡ የእሰሩ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ ዛሬ እንኳን ከአንድነት ፓርቲ አቶ ሀብታሙ አያሌው እና ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸውን ሰምተናል፣ አውቀናል፡፡ የዚህ መሰል አካሄድ ግን መዘዘን የሚስከትል ይመስለኛል፡፡ አሁን አሁን ሰዎች እንደጥጃ ከቤታቸው፣ ከየመንገዱ፣ ከሚሰሩባቸው ቦታዎች …እየተወሰዱ መታሰራቸው በሀገራችን እየተለመደ የመጣ አዲስ ክስተት ሆኗል፡፡ ሥልጣን […]

የፓርላማ አባልና የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአዴግ መንግስት በሰላም የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞችን የማሰሩን ጉዳይ እብድነት ብለዉታል። «እነዚህ ሰዎች አብደው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሀብታሙ አያሌውን ፖሊሶች ይዘውት እንደሄዱ ሰማው፡፡ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስም፡፡ የእነርሱን ሃሳብ የሚቃወም ሁሉ አሸባሪ እየመሰላቸው በሽብር እራሳቸውን እያናወዛቸው ያለ ይመሰለኛል፡፡ ሀብታሙን ሊያስሩት ይችላሉ በህዝብ ውስጥ ያለውን የነፃነት መንፈስ ግን ማስረ […]

ነፃነታችን እስከምንጎናፀፍ አንዲት ኢንች አናፈገፍግም!!! አሳሪዎች አዳምጡኝ፡፡ አይደለም እስራትን ሞትን የማይፈሩ ወጣቶች በቅለዋል፡፡ የኢህአዴግ አሮጌ መንገድ የሰለቻቸው ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በርክተዋል፡፡ ተቀምጦ ያለነፃነት ከመኖር ቆሞ በነፃነት መሞት እንደሚሻልም እናውቃለን፡፡ ዘመናችሁን ቀርጥፋችሁ በልታችሁ የኛን ዘመን ለማጨለም፤ የወጣቱን ዕድሜ ለመኖር የምትተጉ ባለጊዜዎች፤ ዘመናችንን ለመንጠቅ የምትቅበዘበዙ ገዥዎች እመኑኝ ባሮጌው መንገዳችሁ በርካቶችን ነፃነት ናፋቂዎች በሰፋፊ እስርቤታችሁ ታጉሩ ይሆናል፡፡ ነገር […]

የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን!!! ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ በቅርቡ ለህዝቡና ጋዜጠኞች ይፋ እንዳደረግነው ሕወሓት/ኢህአዴግ ለአለፉት 23 ዓመታት ወደር የሌለው የዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋና የሰብአዊ መብት ረገጣ በዜጎች ላይ ሲፈጽም መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው እውነታ መሆኑን፤ በአሁኑወቅትይህየሰብአዊመብትረገጣና ድፍጠጣ በእጅጉ ተባብሶ ወደ መንግሥታዊ የውንብድናና ጥቃት መቀየሩን፤ ዜጎች […]

ሃብታሙ አያሌው ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና የሺዋስ አሰፋ ወደ ማእከላዊ መዉረዳቸዉን የሚገለጽ ዜና ተመለከትኩ። በጣም አዝኛለሁ። ሃብታሙ አያሌው በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ትልቅ ሥራ እየሰራ ያለ፣ በቅርቡ ወዳጅ አባቷን ያጣችው እህታችን ባለቤት እና የአንዲት ቆንጅዬ ልጅ አባት ነው።የአንድነት ፓርቲ እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፈርመው ፣ ዉህደቱን ለማስፈጸም ያቋቋሙት የጋራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው። ያ ብቻ አይደለም […]

አገር ቤት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉ ወጣት ፖለቲከኞች መታሰራቸዉን የደረሰን ዘገባ ገለጸ። ከታሰሩት ወጣቶች ዉስጥ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋና የአረና አመራር አባል እና ታዋቂ ብሎገር አቶ አብርሃ ደስታ ይገኙበታል። በጉዳዩ ላይ የአንድነት ፓርቲ መግለጫ […]

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!! በየጊዜው እየከረረና እየመረረ የመጣው ትግላችን “ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ ጽሁፍ የዚህን የትግል ምዕራፍ ምንነትና ይዘት በአጭሩ ያብራራል። በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈሩት ዓረፍተ ነገሮች ተነበው የሚታለፉ ሳይሆን በተግባር የሚተረጎሙ ሥራዎች ናቸው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ምን ማለት ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት በጀግንነት የቆመ፤ […]

ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው […]

ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤ በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ […]

ኤርትራ የየመንን አየር መንገድ እንደምትዘጋ አሳወቀች (ምክንያቱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ነው) (ኢ.ኤም.ኤፍ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰና፣ የመን ውስጥ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ታፍኖ መታሰሩ ብሎም አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አለመታወቁ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ትራንዚት እያደረገ በነበረበት ወቅት ነበር በየመን ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በየቦታው ድምጻቸውን ለማሰማት […]

ራሱን “የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር” ብሎ የሰየመው ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት (ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት)፤ ሀገራችንን ዕለት ከዕለት ወደ ባሰ አዘቅት እንድትገባ እየጎተታት ነው። የፖለቲካ ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው የሀገራችንን ሕልውና በንጥልጥል ላይ እንዲቀመጥ ሌት ከቀን እየጣረ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ በመቆም፤ በተለያዩ ድርጅቶች ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ ከዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተዋደቁ ያሉ ታጋዮች አሉ። ይህ በዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ መንግሥትና […]

ህወሓቶች የመቐለ ህዝብ ዓፈናውን በሰለማዊ ሰልፍ እንዳያሰማ ለማፈን ያህል የነገው የመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከልክሏል። በደብዳቤ እንዲያሳውቁን በጠየቅነው መሰረት የደብዳቤው ይዘት ምን መሆን እንዳለበት ለስድስት ሰዓት ያህል ከተወያዩ በኋላ እነሆ ቀኑና ይዘቱ አዛብተው ሰጥተውናል። ስህተት አለው ስንላቸው፤ ዝም ብላቹ ያዙ እሱም በስንት መከራ ነው ብለውናል። ባጭሩ የተቀመጠው ምክንያት ክልላዊና ከተማዊ ዝግጅት ስላለን አይመችም፤ በቂ የፀጥታ […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የአዲስ አበባ ምክር ቤት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በቀረበው ሪፖርት ላይ በመወያየት የ3 ወር ሪፖርት አጽድቋል፤ የተጓደሉ የሥራ አመራር አባላትን በምርጫ አሟልቶ አዲስ የስራ ድልድል አድርጓል በዚህም መሰረት፡ – 1. አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን ………….. ሊቀመንበር 2. አቶ ደምሴ መንግስቱ ………………… ም/ሊቀመንበር 3. አቶ እንግዳወርቅ ማሞ……………… ፀሐፊ 4. አቶ ነብዩ ባዘዘው …………………….. […]

ሰኔ ቅዳሜ 21 ቀን ፣ በመቀሌ ከተማ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጠራ፣ የአረና አመራር አባል አቶ አብርሃ ደስታ ገለጹ። ሰልፉ በከተማዋ አስተዳደር እውቅና እንዳገኘ የገለጹት አቶ አብርሃ፣ በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች በርካታ ከተሞች እንደታየው የመቀሌ ሕዝብ የሕወሃት ደጋፊ እንዳልሆነ የሚያሳይበት አጋጣሚ እንደሚሆን አስረድተዋል። «የትግራይ ህዝብ እስካሁን ድረስ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጎ ይገኛል። […]

እንደሚታወቀው የኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት በሁለቱም አገሮች ከባድ የሚባል መስዋእትነት ተከፍሎበታል። ይህ ጦርነት ሲጀመር ምክንያቱ ምን ነበር? ለመንስ ተደረገ? መቸና ለመን እንዲቆም ተደረገ? በግዜው ጦርነቱ ሲጀመር አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞችና ኢህአዴግ እንዳሉት ከሆነ የኤርትራ መንግስት ኢኮኖሚያዊ ችግር ነው ይላሉ። እውነቱ ይሀ ከሆነ ሆድ ይፍጀው። ለማነኛው ዛሬ ድረስ የእነዛን ጥያቄዎች መልስ ሳይፈታ ይሀው 16 ዓመታት አልፎ ቋጠሮውን […]

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሀዋሳ ከተማ ሰኔ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረውን ህዝባዊ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ባለፈው ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ በግዜ ቀጠሮ ለአርብ ሰኔ 20 ቀን 2006 ዓ.ም የተቀጠሩ ቢሆንም በዛሬው እለት ሰኔ 18 ቀን […]

ደምወዝ ጭማሪ ..የምርጫ ጉቦ …. በደምወዝ ጭማሪ የመንግስት ሰራተኛውን የፖለቲካ ባሪያ ማድረግ አይቻልም።ደምወዝ ተጨምሮልሃል የተባለው ከመጋረጃ ጀርባ አንገቱን እንዲሰብር እየተደረገ ያለው የመንግስት ሰራተኛ ማንን እንደሚመርጥ እና ድምጹንም እንደማያባክን ጠንቅቆ ያውቃል። የደሞዝ ጭማሪው የወያኔን አጣብቂን ውስጥ መዘፈቅን ያሳያል። ውሻ ጆሮውን ቆርጠው ቢሰጡት ስጋ የሸለሙት ይመስለዋል .በሚል ወያኔያዊ የፖለቲካ ብሂል ተነስቶ ለመንግስት ሰራተኛው የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ እንደሚፈልግ […]

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)ባሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 15 ቀን 2006ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ‹‹ፍትህን ተነፍገን ትግላችን አይቆምም ››በማለት ዛሬም ለ4ኛ ቀን በርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡አባላቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ቅዳሜ እለት ጀምሮ በረሀብ አድማ ላይ ሲሆኑ በትላንትናው እለት ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ […]

ኢህአዴግ የግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም የጐፋ ሳውላ ሰላማዊ ሰልፍን እቅድ ከሰማበት ጊዜ አንስቶና ከሰልፍ በኋላም እጅግ አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህም የሰላማዊ ትግሉን ሂደት ከምርጫ 2007 የቅድመ ዝግጅት የዕለት ተዕለት ሥራው አንዱ ዲሞከራሲን የማጥፋት ተግባር በመሆኑ ለጐፋ አካባቢ ከተማ ፍ/ቤት ጀምሮ እስከ ወረዳ ፍ/ቤቶች ከፓሊስ ኃይል ጋር በመተባበር እያጠቁ ናቸው፡፡ ተግባሩን በምንከታተልበት […]

አዋሳ ሆይ እስከመቼ የዳንስ ከተማ ብቻ እንድትሆኝ ይፈረድብሻል? የፖለቲካ ከተማም ሁኝ እንጅ!!! የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት ገፍቶ በወጣ ቁጥር የአምባገነኖች መደናበር ያይላል፡፡ ሲደናበሩም ህግ ይጥሳሉ፣ ህዝብ ያሰቃያሉ፣ ሀገር ይበድላሉ፡፡ ግን እድሜ ልክ ዕየተጨቆኑ መኖር አይቻልም፡፡ ‹‹ተቀምጦ ከመኖር ቆሞ መሞት ይሻላል›› እንዲሉ፡፡ ቆሜ መሞት ይሻለኛል የሚሉ ዴሞክራሲ ናፋቂዎች እየበረከቱ ነው፤ እምቢ ከፈለግህ ይሄው እሰረኝ! የሚሉ ትንታግ ወጣቶች […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) ባለፉት 23 ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ስርዓቱ አምጦ የወለዳቸው ሀገራዊ አፈና፣ ማዋከብ፣ የመኖር ዋስትናን መንፈግ፤ ዜጎችን ማሰደድና ማሰር የተለመዱ ድርጊቶ ሆነው ኖረዋል፡፡ አሁንም በዚህ አስከፊ የአፈና መንገድ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ የስርዓቱ መንግስታዊ አፈናና ፀረ-ሕዝብ አቋም በመላ ኢትዮጵያ የተዘረጋ ቢሆንም ፓርቲያችን በእንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደታዘበው በደቡብ ክልል […]

ከአምስት ወር በፊት በአስታራ ሆቴል የተመሰረተው የኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መድረክ(ኢ.ጋ.መ) ትላንት ሰኔ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት “የፕሬስ ነፃነት፣የጋዜጠኞች ደህንነት እና ልማት” በሚል ርዕስ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበተት የፓናል ውይይት በአዲስ ቪው ሆቴል አከናውኗል፡፡ የእለቱን መርሀ ግብር በንግግር የከፈተው የኢ.ጋ.መ ም/ፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ ሲሆን በመቀጠልም ሁለት ምሁራን የውይትት መነሻ ሀሳብ አቅርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት […]

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በመሀል ፖሊሶች አስተባባሪውን እንፈልጋለን ብለው በሆቴሉ ሰዎች መልዕክት ላኩ ከነብዩ ሀይሉ ጋር ሪሴብሽን ሄጄ አገኘናቸው፡፡ እነሱም ፕሮግራሙን አቋርጣችሁ ንገራቸውና አሁኑኑ ተበተኑ የሚል ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡ ለምን ብንል? መልሱ- ትእዛዝ ነው!! የሚል ሆነ ነብዩ ፈጠን ብሎ “እሺ ለተሳታፊዎቹ እንንገራቸውና እንበተናለን” ብሎ ወደ አዳራሹ ተመለስን፡፡ አሁን ፕሮግራሙ ቀጥሏል፡፡ ፖሊሶቹም […]