አቡጊዳ – አረና በአክሱም ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሕዝባዊ ስብሰባ ነጋ ያደርጋል
ከአክሱም ህዝብ ጋር ለመወያየት ለእሁድ ሰኔ 1, 2006 በከተማው ማጀጋጃ ቤት አዳራሽ ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚደረግ የአራና አመራር አባል አብርሃ ደስታ ዘገበ።
በርካታ የአራና አባላት እየታሰሩ እንደሆነ የገለጹት አቶ አብርሃ ደስታ፣ በአክሱሙ ስብሰባ ብዙ ህዝብ ሊገኝ እንደሚችል ጽፈዋል። «እነሱ ያስራሉ፣ እኛ ደግሞ ህዝብን እናስተምራል። ። የነሱ ተግባር ህዝብን መጨቆን ሲሆን የኛ ደግሞ ህዝብ ለነፃነቱ በአንድነት እንዲቆም ማነሳሳት ነው። ህዝብን ማስተማር አንድ የዴሞክራሲ አካል ነው» ሲሉ በአራና እና በህወሃት መካከል ያለውን ልዩነትን ለማሳየት ሞከረዋል።
«አክሱም የምንገኘው ባንክን ለመዝረፍ ሳይሆን ሰለማዊ ትግልን ለመስበክ ነው። ምክንያቱም የምንታገለው የህወሓትን የኃይል መንገድ ለማስተካከል እንጂ ለመድገም አይደለም» አይደለም ያሉት አቶ አብርሃ በትግራይ ከመቼዉም ጊዜ በበለጠ የሕወሃት አገዛዝ እንደመረረዉ ይናገራሉ።