ሰበር ዜና- ትዕዛዙ የማን ይሆን? – ከስለሺ ሐጎስ

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በመሀል ፖሊሶች አስተባባሪውን እንፈልጋለን ብለው በሆቴሉ ሰዎች መልዕክት ላኩ ከነብዩ ሀይሉ ጋር ሪሴብሽን ሄጄ አገኘናቸው፡፡ እነሱም ፕሮግራሙን አቋርጣችሁ ንገራቸውና አሁኑኑ ተበተኑ የሚል ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡ ለምን ብንል? መልሱ- ትእዛዝ ነው!! የሚል ሆነ ነብዩ ፈጠን ብሎ

“እሺ ለተሳታፊዎቹ እንንገራቸውና እንበተናለን”

ብሎ ወደ አዳራሹ ተመለስን፡፡

አሁን ፕሮግራሙ ቀጥሏል፡፡ ፖሊሶቹም ሪሴብሽን ናቸው፡፡ እኛም ለተሳታፊው ቃል ሳንተነፍስ ለፌስቡክ ተነፈስን፡፡10309209_678869368835316_8025911486027251704_n

10462473_678869572168629_3778114342008319919_n