(ስሉሥ ወልደሂወት) “ማንም የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠነቀቅ”! መጽሓፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ፍላጎት ሁሌ የሚያድግና የማይሟላ በመሆኑ የለውጥ ጥያቄን ለመመለስ ሁሌም ሰለተሻለ አማራጭ፣ ስለተሻለ ዘዴ ወይም ስትራቴጂ ማሰቡና መነጋገሩ ተገቢና ጤናማ መሆኑ የማይታበል እውነት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ዘንድ የተቀደሰና ከነቀፋና ትችት የፀዳ የፖሊሲ አቋም ወይም የፖሊሲ አፈፃፀም የማይኖር መሆኑም እንደዚሁ። ዜጐች በግልም ይሁን በተደራጀ መልኩ በነፃነትና ከማንኛውም ተጽእኖ በጸዳ መልኩ የፖሊሲ አማራጮችን መተቸችና የመልካም አስተዳደር ግድፈቶችን ነቅሶ ማውጣት የሚችሉበት ሁኔታ ከተፈጠረ ያ ማህበረሰብ የታደለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የፖለቲካ መሪዎች በዓቅም ውስንነት፣ በግንዛቤ እጥረት፣ የግል ፍለጎት በማሰቀደም ወይም በቅንነት እጦት ምክንያት የሕዝቦችን ጥቅም አደጋ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው። በመሆኑም የፖሊሲ አማራጮችንና የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከመተቸት ባላፈ ፖሊሲውን ለማስፈፀም ሃላፊነት የወሰዱ የፖሊቲካ ድርጅቶች አመራር፣ ውስጣዊ ድርጅታዊ ህይወትና የአመራሩ የግል ማንነት ሳይቀር አብጠርጥሮ ማወቅና መተቸት በሰለጠነው ዓለም የተለመደና ውጤታማ የሆነ የዲሞክራሲ ባህል ነው፡፡ ከሰሞኑ አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር የተባሉ ዜጋ በተለየ ሁኔታ በህወሓትና ህወሓት በሚመራው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ፖሊዎችና አፈጻጸም ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአቶ ዳዊት ትችት ከግል ገጠመኝና ትዝብት በመነሳት በአጠቃላይ በስርዓቱ፣ ስርዓቱ በቆመባቸው ምሰሶችና የማስፈፀምያ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እንደዚሁም የድርጅቱና የድርጅቱ አመራር ዓቅምና ህዝባዊነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ከፖሊሲ የተሻለ ፖሊሲ፣ ከተሻለው ፖሊሲ እጅግ የተሻለ ፖሊሲ መኖሩ የማይቀር ስለሆነ፤ አቶ ዳዊት ስለተሻለ አመራር፣ […]