አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ንቅናቄ ይፋ ማድረጉና የንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም መንግስት ህገወጥ እስር እያካሄደ ይገኛል፡፡ ለቅስቀሳ ስራ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ ተንቀሳቅሰው የነበሩ አራት የፓርቲው […]

ያለ መታደል ጎንደርን በአካል አላውቃትም። ነገር ግን እንደ ማንም ኢትዮጵያዊ በልቤ ዉስጥ ልዩ ቦታ አላት። ያለ ጎንደር ኢትዮጵያ የምትባል አገር ትኖር ነበር ለማለት ያስቸግራል። ግራኝ መሃመድ በቱርኮች እየተረዱ፣ አብዛኛዉ የኢትዮጵያን ክፍል ተቆጣጥረዉ በነበረ ጊዜ፣ ስመ ጥሩ ያልነበሩ፣ ብልሹዉ የሸዋ ንጉስ፣ አጼ ልብነህ ድንግል ይሞታሉ። አጼ ገላዉዲዮስ ይተኳቸዋል። የግራኝ ጦር በመጠንከሩ ሽሽት ወደ ሰሜን፣ ወደ ጎንደር […]

በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው […]

ሕገመንግሥቱን ማቋረጣቸውንና ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲን ከሥልጣናቸው ማስወገዳቸውን የግብፅ ወታደራዊ አዛዥ አስታወቁ፡፡

በያመቱ ፣ እ ጎ አ ከ 1901 ዓ ም አንስቶ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቀውን የኖቤል ሽልማት ለማግኘት የማይመኝ የሳይንስ ተማራማሪ ይኖራል ብሎ መገመት ያስቸግር ይሆናል። ተሳክቶላቸው በየጊዜው ከፍኛውን ሽልማት የሚያገኙትና በሙያው አንቱ የሚሰኙት ሊቃውንት

የቀድሞይቱ ዩጎዝላቪያ ሬፑብሊክ ክሮኤሺያ ባለፈው ሰኞ 28ኛዋ የአውሮፓ ሕብረት ዓባል አገር ለመሆን በቅታለች። ሕብረቱ ክሮኤሺያን የተቀበለው በጋራ ምንዛሪው በኤውሮና በርከት ባሉ ዓባል መንግሥታት የበጀት ቀውስ ተወጥሮ በሚገኝበት ወቅት ነው።

ሙርሲ በቴሌቪዥን ሲነጋሩ ደጋፊ-ተቃዋሚዎቻቸዉ እዚያዉ ካይሮ ዉስጥ ይገዳደሉ ነበር።ጄኔራል ሲሲ የቆረጡት ገደበ-ሠዓትም አብቅቷል።እና ታንክ መትረየስ አስጠምደዉ ካይሮ ቤተ-መንግሥት ቢገቡስ? ምርጫዬ አሉ ሙርሲ «ሞት»

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ትናንት በሴኔጋል፣ በደቡብ አፍሪቃ እና በታንዛንያ ያካሄዱትን የአንድ ሣምንት ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ። ኦባማ በጉብኝታቸው ወቅት በአህጉሩ ያለውን ግዙፍ የኤኮኖሚ ዕድል በማመልከት፣ ሀገራቸው በዚሁ ዘርፍ ከአፍሪቃ ጋ ግንኙነትዋን እንደምታስፋፋ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያናብራዚል ግንኙነታቸዉን እንደሚያስፋፉ እና እንደሚያጠናክሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የበረራ መስመር ወደሪዮደጄኒሮ እና ሳኦፖሎ በዘረጋበት ወቅት አሳወቁ።

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተማ ወረዳ በገንዳሆ ከተማ ሰኔ 25፣ 2005 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰአት ከ30 ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና ጸረ-ሽምቅ እየተባሉ በሚጠሩ ሀይሎች መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከ4 እስከ 7 የሚደርሱ  ታጣቂዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ፣ 2 የወረዳው ባለስልጣናት ደግሞ ቆስለዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባን ለ5 አመታት ሲመራ የነበረው የኩማ አስተዳደር  ሐሙስ ሰኔ 27 ጀምሮ  ለአዲሱ ኢህአዴግ መራሽ ካቢኔ ሥልጣኑን እንደሚያስረክብ ተጠቆመ፡፡ በመልካም አስተዳደር ችግር፣ በሙስናና ብልሹ አሰራር የሚተቸው የኩማ አስተዳደር የምርጫ 97 ቀውስን ተከትሎ ከተመሰረተው የባለአደራ አስተዳደር ስልጣኑን በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም በምርጫ ስም የተረከበ ሲሆን ባለፉት አምስት …

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል በጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በመንግስት ሀይሎች  እንቅፋት እየተፈጠረበት መሆኑን አስታውቋል። ፓርቲው የመጀመሪያውን  የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም፤ መንግስት …

አሁን ያለንበት ወቅት አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ልጆቻችን ቤት ውስጥ መዋል የጀመሩበት፣ ወይም የክረምት መክረሚያ ነገሮችን ማከናወን የጀመሩበት ጊዜ ነው፡፡ በበጋ ከነበረው የወላጆች ወከባ ዐረፍ ብለናል፡፡ ልጆችን ትምህርት ቤት ማድረስ፣ የቤት ሥራ ማሠራት፣ ግዙ፣ አምጡ፣ ኑ፣ ሂዱ ከሚሉ የትምህርት ቤቶች ትእዛዞች ዐረፍ ያልንበት ሰሞን ነው፡፡ አሁን ልጆቻችንን ስለሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ለመነጋገር ምቹ ጊዜ ነው፡፡ እኔ ሁለት ጉዳዮችን መርጫለሁ፤ ዛሬ አንደኛውን እናንሣው፡፡
ጉዳይ አንድ
ባለፈው ሰሞን አንዲት እናት ወደ ቢሮዬ መጥተው እንዲህ አወጉኝ፡፡ ‹‹ልጄ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅና የ 5ኛ ክፍል ተማሪ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የማይበት ጠባይ ግራ የሚያጋባኝ እየሆነ ተቸግሬ ነበር፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ የእኔን ሽቱ ይቀባል፡፡ እኔም ይህን ሳይ የልጅ ነገር አድርጌ ትቼው ነበር፡፡ በኋላ ግን ከሌላው ነገር ጋር ሲደረብብኝ ነው ግራ የተጋባሁት፡፡ ፀጉሩን እንደ ሴቶች ማስተኛት ይፈልጋል፡፡ ጥብቅ ያለ ሱሪ ካልገዛሽልኝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን ትምህርት ቤት አድርሼው መኪናዬን አዙሬ ልመለስ ስል ከኋላ ያለውን መኪና እንዳልነካው ዞር አልኩ፡፡ ያን ጊዜ ያየሁትን ነገር ዓይኔ ሊያምን አልቻለም ነበር፡፡ ከአንድ ሌላ ወንድ ልጅ ጋር ከንፈር ለከንፈር ሲሳሳሙ አየኋቸው፡፡ ከኋላዬ የነበረው መኪና በጡሩንባ እየጮኸብኝ እንኳን የማየውን ተጠራጥሬ ለረዥም ሰዓት ፈዝዤ ነበር፡፡

 ሥራ ከገባሁ በኋላ እጅግ ፈዝዤ ነበር፡፡ የቢሮ ሰዎች ሁሉ እየደጋገሙ ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ ግን ለማን ምን ብዬ ልንገረው? ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው የሆነብኝ፡፡ ቢቸግረኝ ወደ አንዲት ጓደኛዬ ባለቤት ጋር ደወልኩ፡፡ እርሱ ሐኪም ነበርና ምናልባት ከረዳኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ በስልክ አነጋገሬ አደጋ የደረሰብኝ ይመስል ስለነበር እየከነፈ ቢሮዬ መጣ፡፡ ከእርሱ ጋር ተያይዘን ወጣንና አንድ ቦታ ቁጭ አልን፡፡ በልጄ ላይ ያየሁትን ነገር ሁሉ ነገርኩት፡፡ እርሱም ከሌሎች የሰማቸውን የባሱ ነገሮች እየነገረ አጽናናኝ፡፡ ከዚያም የበለጠ ርግጠኛ ለመሆንና ችግሩንም በሚገባ ለመረዳት ልጄ በማይኖርበት ሰዓት የልጄን ዕቃዎች እንድፈትሻቸው ነገረኝ፡፡

አንድ ቀን አባቱ ወደ መዝናኛ ቦታ እንዲወስደው ነገርኩትና እኔ ዕቃዎቹን መፈተሽ ጀመርኩ፡፡ ያኔ ነው የልጄን ጉዳይ በጥልቀት የተረዳሁት፡፡ እኔ ያልገዛሁለት አንድ ቀይ ቲሸርት አገኘሁ፡፡ ቲሸርቱ ላይ በእንግሊዝኛ ‹I am a gay› የሚል ተጽፎበታል፡፡ ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ አልጋው ላይ ተቀምጬ ለረዥም ጊዜ አለቀስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ መቀጠል አልቻልኩም፡፡ ልጄን እንዳጣሁት ገባኝ፤ ልጄን እንደማላውቀው ገባኝ፤ ልጄና እኔ በተለያዩ መንገዶች እየተጓዝን መሆኑ ገባኝ፡፡
የጓደኛዬ ባለቤት በጉዳዩ ላይ እንዴት ከልጄ ጋር ልወያይ እንደምችል መንገዶችን አመላከተኝ፡፡ አንድ ቀን ከልጄ ጋር ከአዲስ አበባ ወጣ አልን፡፡ አብሬው ስጫወት ዋልኩና ለሻሂ ዐረፍ ስንል አንድ ስልክ አነሣሁ፡፡ እንደ ደነገጠ ሰው ሆኜ ነበር የማወራው፡፡ ልጄም ድምፄን እየሰማና ሁኔታዬን እያየ ተደናገጠ፡፡ ስጨርስ ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ፡፡ ‹‹አንዲት ጓደኛዬ ከባድ ነገር እንደ ደረሰባት፡፡ ልጇ ግብረ ሰዶማዊ እንደሆነባት፡፡ በዚህም ምክንያት በሕግ ሊጠየቅ መሆኑን›› ነገርኩት፡፡ እጅግ ደነገጠ፡፡ ‹‹የእኔ ልጅ መቼም እንዲህ ያለ ነገር አያደርግም›› ብዬ ተውኩት፡፡ አፍጥጦ ዓይን ዓይኔን ያየኝ ነበር፡፡ ‹‹በጣም ከባድ ነገር ነው የገጠማት፤ ግብረ ሰዶማዊ ማለትኮ በሃይማኖታችንም ትክክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግብረ ሰዶማውያንን አጥፍቷቸዋል፡፡ ከዚያም በላይ ግብረ ሰዶማውያን በኅሊናቸውም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮአቸው ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው፤ ከሕዝቡም እንደሚገለሉ፤ አኗኗራቸውም ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ እንደሆነ፤ ወንድ ከሴት ጋር ሴትም ከወንድ ጋር እንጂ ወንድ ከወንድ፣ ሴትም ከሴት ጋር የሚደረገው ግንኙነት እንስሳት እንኳን የማይፈጽሙት መሆኑን፡፡ የወሲብ ግንኙነት ማንኛውም ወንድ ከ ተፈቀደለት ሴት ጋር ብቻ፣ ባህሉና እምነቱ፣ ሕጉም በሚፈቅደው እድሜና ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑን›› እየዘረዘርኩ መግለጥ ጀመርኩ፡፡ ዝም ብሎ ነበር የሚያዳምጠኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ልጆቻቸውን ግብረ ሰዶማውያን እንደሚያደርጓቸው፤ እነዚህ ልጆችም ሌሎችን ልጆች አባብለው ወደዚህ እንደሚያስገቧቸው፤ እንዲያውም  ‹I am a gay› የሚል ልብስ የሚለብሱ እንዳሉ ነገርኩት፡፡
ግራ ሳይገባው አልቀረም፡፡ ስለ እርሱ እንደምናገር ገምቷል፡፡ ስጨርስ ‹‹የኔ ልጅ አንተ ግን እንደዚህ አታደርግም አይደል?›› አልኩት፡፡ ምንም አላለኝም፡፡ ዝም አለኝ፡፡ መሬት መሬት ያይ ጀመር፡፡ ‹‹ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ እንዴ›› አልኩት፡፡ ዝም አለ፡፡ ‹‹አደራህን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልጆች ሌሎች ልጆችን ሳያውቁት ወደዚህ ነገር እያስገቧቸው ነውና ተጠንቀቅ›› አልኩት፡፡ እሺም እምቢም አላለኝም፡፡ ‹‹አንተ ይህንን ስታደርግ ካየሁ፤ እኔ ወዲያው ነው የምሞተው›› ስለው ተስፈንጥሮ መጥቶ ጭኔ ላይ ተደፋ፡፡ ሲያለቅስ ይሰማኛል፡፡ ዕንባውም እግሬን ሲያሞቀው ይታወቀኛል፡፡ እኔም እያለቀስኩ ነበር፡፡
ከብዙ የዝምታ ልቅሶ በኋላ ‹‹እማዬ እኔኮ ጌይ ሆኛለሁ›› አለኝ፡፡ ቀድሜ ባውቅም ያ ሰዓት ግን መብረቅ የመታኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ ከልጄ አንደበት ይህንን ስሰማ ኩምሽሽ ብዬ ትንሽ የሆንኩ መሰለኝ፡፡ የማደርገው ጨነቀኝ፤ ምን ልመልስለት? ምን ልበለው? ግራ ተጋባሁ፡፡ ‹‹ለምን ልጄ? ለምን?›› አልኩት፡፡ ከእኛ ራቅ ብለው የሚያዩን ሰዎች ሁኔታዬ ግራ አጋብቷቸው ሁሉም እኔን ያያሉ፡፡
‹‹እኛ ትምህርት ቤትኮ ብዙ ልጆች አሉ›› አለኝ፡፡
‹‹ምን ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት
‹‹ሽቱ ተቀብተው ይመጣሉ፤ ደግሞ አንድ ዓይነት ማስቲካ ነው የምንበላው፤ ‹I am a gay› የሚል ቲሸርት እንለብሳለን›› አለኝ፡፡
‹‹ቲሸርቱን ማን ነው የሰጣችሁ?›› አልኩት
‹‹አንድ ልጅ ነው ያመጣልን፤ ለሁላችን ሰጠን፡፡ ግን ከዩኒፎርማችን ሥር እንድንለብሰው ነግሮናል››
‹‹ሌላስ?››
‹‹ደግሞ አንድ ልጅ የጌይ ፊልም በዕረፍት ጊዜ ያሳየናል››
‹‹የት ነው የሚያሳያችሁ?››
‹‹በኪሱ የሚያመጣው ሞባይል አለ፡፡ እናቴ ናት የምትጭንልኝ ብሏል››
የምሰማውን እንዴት ልመነው?
‹‹እርሱኮ [የልጁን ስም እየነገረኝ] አባቱ ትምህርት ቤት ሲሸኘው ሁልጊዜ ከንፈሩን ይስመዋል›› አለኝ፡፡ ይኼኔ ነቃሁ፡፡ አስታወስኩ፡፡ ሰውዬውንም ዐወቅኩት፡፡ እኔም ደስ አይለኝም ነበር፡፡ አባት ወንድ ልጁን፣ እናትም ሴት ልጇን ከንፈራቸውን መሳም እዚህ ትምህርት ቤት የማየው ነገር ነው፡፡ ይህ ነገር ልጆቻችን ይህንን መሰሉን ተግባር ከዕድሜ ቀድመው እንዲለምዱት ያደርጋል፡፡ ከዚያም አልፎ ነገ ሌሎች ግብረ ሰዶማውያን በልጆቹ ላይ ይህንን መሰል ተግባር ሲፈጽሙባቸው ምንም እንዳይመስላቸውና የፍቅር መግለጫ አድርገው እንዲወስዱት  ያደርጋቸዋል፡፡ ከባህላችን ያፈነገጡ ነገሮችን በልጆቻችን ላይ ማድረግ እነዚህ ነገሮች በልጆቻችን ላይ በሌሎች አካላት ሲደረጉባቸው እንዳያስተውሉት እንዳይጸየፉትም ያደርጋቸዋል፡፡
‹‹ለመሆኑ አብራችሁ ስትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?›› አልኩት፡፡
‹‹አንዳንድ ወንዶች ልጆች ይሳሳማሉ፤ እኔ ግን ይደብረኛል፤ ደግሞ ይተሻሻሉ›› አለኝ፡፡ ከገጽታው የመቅፈፍ ስሜት አየሁበት፡፡ ይህንን ስሜት ስመለከት ወደ ችግሩ ውስጥ ዘልቆ እንዳልገባበት ተረዳሁ፡፡ እኔ የማዝነው በባህላችን ተከብሮ የኖረውን የወንድም ለወንድም፣ የእኅት ለእኅት ግንኙነት ግብረ ሰዶማዊነት እያጠፋብን በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ከአክስቶቼ ልጆች ጋር አብሬ እየተጫወትኩ፣ አብሬ እየተኛሁ ነው ያደግኩት፡፡ ልጆቻችን ግን እንዲህ ማድረግ ላይችሉ ነው፡፡ ከአጎታችን፣ ከአክስታችን ጋር መተኛት ለኛ ደስታችን ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዘመዶች በዘመዶች ላይ እንዲህ የሚፈጽሙ ከሆነ ዝምድናችን ሊጠፋብን ነው፡፡ መምህሮቻችንን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የቤት ሠራተኞችን፣ የጥበቃ ሠራተኞችን እየተጠራጠርን ልንኖር ነው፡፡ ግብረ ሰዶምነት ባህላችንን እጅግ አድርጎ ነው የሚያበላሸው፤ ማኅበራዊ ግንኙነቶቻችንን ነው የሚበጣጥሰው፤ እንዴት ያለ ችግር ውስጥ ነው የገባነው በእግዚአብሔር?
በኋላ ከአንዳንድ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር ስንነጋገር  ብዙ ነገር ሰማሁ፡፡ በከተማችን ውስጥ የግብረ ሰዶማውያን ማዘውተሪያዎች የታወቁ ናቸው፡፡ የራሳቸው የመግባቢያ ‹ቋንቋም› አላቸው፡፡ ትልልቆቹ ግብረ ሰዶማውያን ድራግ በመውሰድ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ለሕፃናቱ ድራጉን በከረሚላ መልክ ይሰጧቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ለመደበቅ ሲሉ ልጆቹ ግለኛነትን ይመርጣሉ፡፡ ከሌሎች ልጆች ወይም ከዘመዶቻቸው ጋር ከመጨዋት ይልቅ ከጌምና ከቴሌቭዥን ጋር ብቻ መሆንን ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ፌስ ቡክን በሚገባ ለዚህ አስተሳሰብ ማራመጃ ይጠቀሙበታል፡፡ ወላጆች ኢንተርኔትን ልጆቻችን ያለእድሜያቸው እንዳይጠቀሙበት ማድረግ አለብን፡፡ ስለ ኢንተርኔት አጠቃቀም፣ ስለ ጥቅምና ጉዳቱ ሳንነግራቸው ነው የምንፈቅድላቸው፡፡ ይኼኔ ከበጎው ይልቅ ክፉውን የመያዝ ዕድላቸው ይሰፋል፡፡ በቤታችን ውስጥ ያስገባናቸውን የቴሌቭዥን ቻነሎችንም መቆጣጠር አለብን፡፡ ልጆቻችን ክፉውንም ደጉንም ዝም ብለው እንዲያዩ ማድረግ የለብንም፡፡ ግብረ ሰዶምን የሚያበረታቱ ቻነሎች አሉ፡፡
‹አሁን ልጅዎ ከችግሩ በሚገባ ወጥቶልዎታል?›› አልኳቸው፡፡
‹‹ሙሉ በሙሉ ከችግሩ ወጥቷል ማለት አልችልም፤ አሁንም እጠራጠራለሁ፡፡ ፍርሃቱ ገና አልለቀቀኝም፡፡ ነገር ግን ክትትሌን አላቆምኩም፤ ከልጄ ጋር ያለኝን ቀረቤታም ጨምሬያለሁ፤ ስለ ብዙ ነገሮችም እንነጋገራለን፤ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማርም እያደረግኩ ነው፡፡ አንድ የማውቀው የሥነ ልቡና ባለሞያ ስለ ግረ ሰዶም ጉዳት በሚገባ ነግሮታል፡፡ በተለይ በዚህ ክረምት የተለየ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡ ትምህርት ቤቶቻችንን ግን ከትምህርት ጥራትና ከክፍያቸው ባለፈ ወላጆች መከታተል አለብን፤ ልጆቻችንም የተለየ ነገር ሲያዩ እንዲነግሩን ማሳሰብ ይገባል፡፡ ዘመኑ ወላጅነት ከባድ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ ›› አሉኝ፡፡
ወላጆች ሆይ
እስኪ በጉዳዩ ላይ እንምከርበት፡፡ ከልጆቻችንም ጋር እንነጋገር፤ መምህራን በተማሪዎች ላይ ይህንን ነገር ፈጽመዋል ተብለው የሚከሰሱበት ጊዜ ላይ ነንና ልጆቻችን እንዳይታለሉ እንንገራቸው፤ ከሃይማኖት፣ ከሥነ ምግባር፣ ከባህል፣ ከጤናና ከማኅበራዊ ኑሮ አንጻር የሚያስከትለውን ችግር እንንገራቸው፡፡ እኛም ስለዚህ ጉዳይ መረጃ እንዲኖረን እንጠይቅ፣ እናንብብ፣ እንመካከር፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ከምሰማው አንጻር በተለይ በከተሞች ውስጥ ችግሩ ሳይታሰብ ሥር እየሰደደ ነው፡፡ ሰሞኑን የቀረበ አንድ ይፋ ያልሆነ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በሚማሩ 2000 ተማዎች ላይ በተደረገ ጥናት 48% ተማሪዎች የጌይና ሌዝቢያን ደጋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እኒህ እናት እንዳሉት በዚህ ዘመን ወላጅነት ፈተና ውስጥ ገብቷል፡፡ ኃላፊነቱ ሰፍቷል፡፡ መሰናክሉ በዝቷል፡፡ እስኪ የፈጣሪን ርዳታ እየጠየቅን ይህንን ነገር የሰሞኑ የቤተሰብ አጀንዳ  እናድርገው፡፡

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ ከሥልጣናቸው እንደማይነቃነቁ በቁርጠኝነት አስታወቁ፡፡

ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የወጣት ሾል አጥነት ላይ የመከሩት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ችግሩን ለመፍታት የሚውል 6 ቢሊዮን ዮሮ ለመመደብ ተስማ…

ዉጪ አገር ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኖረዋል። ወደአገራቸዉ ሲመለሹ ያደጉበት አካባቢ ተጎሳቁሎ፤ ደኑ ተራቁቶ ቢያገኙት ልባቸዉ ተነካ። መንፈሳቸዉ ተነ…

አሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል የምትፈልገዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት ሰራተኛ ኤድዋርድ ስኖዉደን በ 21 ሀገራት

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡ የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መልሚ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ …

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አር አይ ኤ የተባለው የዜና ማሰራጫ የሮስቦሮን ኤክስፖርት አርምስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አሌክሳንደር ሚካሄቨን ጠቅሶ እንደዘገበው ሩሲያ 18 ኤስ ዩ 30 ከ የተባሉ የጦር ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ በድርድር ላይ ናት። ጄቶችን ለመሸጥ ከኢትዮጵያ ጋር እየተነገጋገርን ነው። የጄቶችን ቴክኒካዊና ታክቲካዊ ብቃት ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር …

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በነደፉት የአሜሪካና የአፍሪካ ግንኙነቶች የሚመሠረቱበት አዲስ አቅጣጫና አካሄድ ከፍ ያሉ የምጣኔ ኃብት ዕድሎ

አፍሪቃዉያን ፖለቲከኞች በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት ለምሥራቅ-ምዕራብ ሐያላን ማደራቸዉ ለአፍሪቃ ሕዝብ በጦርነት፥ በረሐብ፥ በሽታ ከማለቅ፥ መሰደድ ሌላ ያ

አፍሪቃውያን መሪዎች « ረሀብን ማጥፋት » በሚል ርዕስ ላይ ዛሬ በአዲስ አበባ በአፍሪቃ አዳራሽ ውይይት አካሄዱ። በዚሁ ጉባዔ ላይ የአራት ሀገራት፣ ማለትም

የቀድሞው የግብፅ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ሆስኒ ሙባረክ፤ በየካቲት ወር 2003 ዓ ም ፤ ሦስት ሳምንት ገደማ በተካሄደ ብርቱ ህዝባዊ አመጽ፣ ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ፤ …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና  ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው  987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡ ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ  …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ዜናውን ይፋ ካደረገው በሁዋላ የሟቹ ጓደኛ የሆነ አንድ ግለሰብ መረጃውን ለሟቹ ባለቤት በሚስጢር ማስተላለፉንና ባለቤቱ እና ልጆቹ በጋራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በመሄድ አስከሬኑን መለየታቸው ታውቋል። ባለቤቱ አስከሬኑን ለመለየት የቻለችው በሰውነቱ ላይ ባለው ልዩ ምልክት ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራትም ወደ ቤተመንግስት በመሄድ የባለቤቷን አድራሻ መጠየቋ ታውቋል።   ከቤተ-መንግስት …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በከባድ የማታለል ወንጀል የተከሰሱት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኀበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ሊቀትጉሃን አስታጥቄ አባተ የቀረበባቸው ክስ እንዲቋረጥ ለፍትህ ሚኒስትር ደብዳቤ እስከመጻፍ የደረሱት ከሊቀመንበሩ ጋር የቅርብ ትስስር ስለነበራቸው እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓርብ  በፖሊስ ተይዘው ችሎት የቀረቡት የ82 ዓመቱ አዛውንት ሊቀትጉሃን …

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን በዋና ሼል አስፈጻሚነትና በቢሮ ኃላፊነት ሲመሊ የቆዩት አቶ ሽፈራው ዓለሙ፣ ሥራቸውን ከሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራቸውን   መልቀቃቸው ተዘገበ። አንዳንድ ወገኖች ሼል አስኪያጁ  ሥራቸውን የለቀቁት ከጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ በፈቃዳቸው ነው ሲሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ የሙስና ክስ ስለተመሰረተባቸው ሥራቸውን ይለቁ …

አቶ ስዬ አብርሃ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አሰከባሪ ተቋም ውስጥ በወታደራዊ አማካሪነት በጥሩ ደመወዝ መቀጠራቸውን ምንጮች ጠቆሙ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ከወንድሞቻቸው ጋር ለስድስት አመት ታስረው የተፈቱት ስዬ በተፈቱ ማግስት የአሜሪካን ድምፅ ራዲዬን ጨምሮ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ÂŤ ፖለቲካ ከልጅነቴ ጥርሴን የነቀልኩበትና አብዛኛው እድሜዬን ያሳለፍኩበት በመሆኑ ከትግሉ መድረክ ልርቅ ጨርሶ አልችልም» በማለት አስረግጠው መናገራቸውን […]

አንድነት በየትኛውም የመንግስት ህገወጥ ጫና ሰልፉን እንደማይሰርዝ ይፋ አድርጓል በጎንደር ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 4 የአንድነት አባላት በፖሊስ መታሰራቸው በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ አንድነት ምንም አይነት ህገወጥ እስር በጎንደር የተዘጋጀውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደማያስቆመው አሳውቋል፡፡ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ በጎንደር ሰኔ 30 የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የሚመለከት በራሪ ወረቀት በማሰራጨት ላይ […]

የአባይን ወንዝ የመጠቀም የረዥም ጊዜ ህልም ነዉ ለኢትዮጵያ፤ ለግብፅ ደግሞ ሃሳቡ የዘመናት ስጋቷ ነዉ። የአባይ መመንጫ የሆኑት ሃገሮች አባይ ላይ የሚሰሩ

Al-Shabab spokesperson Abu Mus’Ab, on the killing of two top leaders of the militant group /in Somali/

Teferra Beyene, NBI Exec. Dir, Full interview