᎐ተከላከሉ ከተባሉት ተከሳሾች መካከል አራቱ ሴቶች በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ለእስር ተዳርገው ‹‹ስብሰባ በማወክና በማነሳሳት›› የተከሰሱት እነ ሚካኤል ያሬድ ለሦስተኛ ጊዜ መከላከያ ምስክሮቻቸውን አቅርበው የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 8/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡ ዛሬ ነሀሴ 28/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ […]

  የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌውና ሌሎች የፖለቲካ አመራሮች የልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተመሰረተባቸው ክስ በነፃ ካሰናበታቸው በኋላ ነገ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተለይ ሀብታሙ አያሌው እንደሚቀርብ ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሔም ገለፀች፡፡ ቤተልሔም እንደተናገረችው ባለቤቷ በነፃ እንዲሰናበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ባልታወቀ ሁኔታ እስርቤቱ አለቅም ማለቱንና ላልተለቀቀበት አግባብ ምንም አይነት […]

በሶማሊያ ሀገር ህይወታቸው እያለፈ ያሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው እየተላኩና ህይወታቸው እያለፈ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ እንደሆነ ከተለያዩ ያገራችን አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስታወቀ.በሶማሊያ ሃገር እየሞቱ ያሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥራቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሟቾቹ ቤተሰብ በየግዜው በቴለፎን መርዶ እየደረሳቸው እንደሆነ የገለፀው መረጃው በተለይም የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለምንድነው […]

ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ መታሰራቸውን ተቃወሙ

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትና በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታት ገቢ ማድረግ የነበረባቸውን 500 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የሚል ጥርጣሬ በመኖሩ ኦዲት እያስደረገ መሆኑን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት ገለጸ፡፡

 

መርማሪ ቡድኑ ነሐሴ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪውን ይዞ ቀርቦ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪው ለግል ጥቅማቸው አውለውታል ከተባለው 500 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ፣ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም የሚገኙ የቦታዎችና የቤት ሰነዶችን በማሰባሰብ ለፎረንሲክ ምርመራ መላኩን ገልጿል፡፡ ያልተያዙ ግብረ አበሮችን አድኖ መያዝ፣ የስምንት ምስክሮችን ቃል መቀበልና ሌሎች የምርመራ ሥራዎች እንደሚቀሩት በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ 

ተጠርጣሪው አቶ ወንድሙ በበኩላቸው ባቀረቡት መቃወሚያ እንደገለጹት፣ እሳቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ በሕገ መንግሥቱ የተሰጣቸው ያለመከሰስ መብት ሳይነሳ ሕገ መንግሥቱ ተጥሶ መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ጠይቀዋል፡፡ እሳቸው የክልል ባለሥልጣን በመሆናቸው የማሰርም ሆነ የመጠየቅ መብት ያለው የክልሉ መንግሥት እንጂ የፌዴራል መንግሥት አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውመዋል፡፡ 

ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት መያዛቸው ሕገወጥ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በተያዙበት ወቅት 22 ሺሕ ብርና መኪናቸው የት እንዳለ አለማወቃቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ በሰጠው ምላሽ ተጠርጣሪው ባቀረቡት ተቃውሞ ላይ ፍርድ ቤቱ ቀደም ባለው ችሎት ብይን የሰጠበት መሆኑን አስታውሷል፡፡ 

ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ፍርድ ቤት ቀርበው በነበሩ ጊዜ ተመሳሳይ ተቃውሞ አቅርበው ትዕዛዝ የተሰጠበት መሆኑን አስታውቋል፡፡ በድጋሚ እንደማይቀበልም ገልጾላቸዋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን በፍጥነት አከናውኖ እንዲያጠናቅቅ አሳስቦ፣ ለተጨማሪ ምርመራ አሥር ቀናት ፈቅዶለታል፡፡ 

 

በስምንት ግራም ቶሪየም 100 አመት ያህል መኪና ሊያስነዳ የሚችል ማዕድን አግኝቼያለሁ. ሃኪም ንጉሴ አሰፋ. “አገር አቀፍ የባህል መድኃኒትና የህክምና ቀን” በኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒትንና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአለም የጤናድርጅት ጋር በመተባበር ከትላንት በስቲያን በሃርመኒ ሆቴል ባካሄደው ስብሰባ ላይ ላለፉት ሃያ አመታት በባህል የህክምና ሙያ ላይ የቆዪት ሃኪም ንጉሴ አሰፋ ላለፋት 15 አመታት በቶሪየም ማዕድን […]

የፋብሪካው ሠራተኞች ሥጋታቸውን ገልጸዋል

ታዋቂው ነጋዴ ሐጂ በዳዳ ጫሊ ጅሩ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆኑባቸው ድሬ ኢንዱስትሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ሞጆ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር፣ ቦረን ሪል ስቴትና ድሬ ኃይላንድ አክሲዮን ማኅበር አክሲዮኖችን ለሦስተኛ ወገን እንዳይሸጡና እንዳይተላለፉ ታግደው እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነሐሴ 13 ቀን 2007 ዓ.ም.  የሰጠውን ጨምሮ ውሳኔ በተለያዩ ጊዜያት በሰጠው ትዕዛዝ በወጋገን ባንክ፣ በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በተለያዩ ቅርንጫፍ ባንኮች የተቀመጠ ገንዘብና አክሲዮንም ካለ ታግዶ እንዲቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የታዋቂው ነጋዴ ሐጂ በዳዳ አክሲዮኖችና ገንዘብ እንዲታገዱ ምክንያት የሆነው፣ ለ50 ዓመታት የትዳር አጋራቸው መሆናቸውን የገለጹት ወ/ሮ ልኬለሽ ያዴሳ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት የፍች ጥያቄ ምክንያት ነው፡፡

ወ/ሮ ልኬለሽ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 81 መሠረት የፍች ውሳኔ እንዲሰጣቸው ያቀረቡት፣ ሐጂ በዳዳ ትዳራቸውን አክብረው መኖር ሲገባቸው ቤታቸውን ጥለው በመውጣት ከጋብቻ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር መኖር መጀመራቸውን በመግለጽ መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡

ሐጂ በዳዳ በራሳቸው፣ በባለቤታቸውና በአራት ልጆቻቸው በተቋቋመው 112.9 ሚሊዮን ብር ዋጋ ካለው ድሬ ኢንዱስትሪዎች አክሲዮኖች ውስጥ 86,580 አክሲዮን ወይም 86.5 ሚሊዮን ብር ድርሻ ያላቸው መሆኑን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ከፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የገዙት ሞጆ ቆዳ ፋብሪካም ከ25 በላይ ባለአክሲዮኖች ያሉት ሲሆን፣ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ሐጂ በዳዳ መሆናቸውን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

ባለቤታቸው ባቀረቡት የፍች ጥያቄ ክስ ምክንያት የባንክ ገንዘባቸውና አክሲዮኖቻቸው የታገደባቸው ሐጂ በዳዳ፣ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ 

ሐጂ በዳዳ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ ከባለቤታቸው ጋር መስማማት ባለመቻላቸው ለ50 ዓመታት የጠበቁትን ትዳራቸውን ለመተው መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ከራሳቸው ይልቅ ለቤተሰባቸውና ለአገራቸው ዕድገትና ልማት በማሰብ ሁሉን ነገር ሆነው ፋብሪካዎች ማቋቋማቸውንና ከ1,200 በላይ ሠራተኞች እንዳሏቸው አስረድተዋል፡፡ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ልዩ ልዩ ብድር እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ ፍች ለጠየቁት ባለቤታቸው በ2,310 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ መኖሪያ ቤትና ሦስት ሚሊዮን ብር በመስጠት ትዳራቸው ሳይፈርስ ለየብቻ እንዲኖሩ በማቀድ በሰላም እየኖሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ 

በሸሪዓ ሕግ መሠረት ሌላ ሰው በማግባት ልጆች ወልደው እየኖሩ መሆኑንና ከሳሽ ባለቤታቸውን ጨምሮ ሁሉም ሰው የሚያውቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም እንዲከፋፈሉና ትዳር እንዲፈርስ የተጠየቀው አግባብ ባለመሆኑ ክሱ ተሰርዞ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡ ሐጂ በዳዳ ባቀረቡት ሌላ አቤቱታ ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዩ ዕዳዎች እንዳለባቸው በድጋሚ ጠቅሰው፣ በገቢና በወጪ ንግድ ላይ ተሰማርተው ለአገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያስገቡ መሆኑን በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ ወደ ክርክር እንዲገቡ የሚያደርግ ከሆነ ክርክሩ በዝግ እንዲሆን ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበላቸውም፡፡ 

ሐጂ በዳዳ በበኩላቸው በወ/ሮ ልኬለሽ ያዴሳ ስም በአዋሽ ኢንተርናሽል ባንክ የተቀመጠ ገንዘብ በአራዳ ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ያለ የኤሌክትሮኒክስ መደብር፣ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሰዴን ሶዶ ወረዳ አሌ አበባን ቀበሌ የሚገኝ ንብረትና ድሬ ኢንዱስትሪዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ግቢ ውስጥ የሚገኝ መጋዘን ውስጥ ያለ ንብረት ታግዶ እንዲቆይ ጠይቀው፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ዕግድ ጥሏል፡፡ 

በድርጅቶቹ ከፍተኛ ባለድርሻ ሐጂ በዳዳና የአክሲዮን ድርሻና የባንክ ባለቤት ሒሳብ ላይ ፍርድ ቤቶች የሚጥሉት ዕድግ እንዳስፈራቸው የሞጆ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር መሠረታዊ ሠራተኞች ማኅበር  ገልጿል፡፡ ባለሀብቱ ፋብሪካውን ከገዙት በኋላ ውጤታማ እየሆነ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ፣ 992 ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኛ በፋብሪካው መኖሩን ገልጾ፣ በተለይ በባንክ ሒሳብ ላይ ዕግድ በመጣሉ የላብ አደሩ ደመወዝ እንዴት እንደሚከፈል ሥጋት እንደገባው አመልክቷል፡፡ ችግሩ የፋብሪካ ሠራተኞቹ ብቻ ሳይሆን ከ5,000 በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር መሆኑን ጠቁመው፣ የሚመለከተው አካል ችግሩን በቀላሉ እንዲፈቱት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

  

 

 

የመኢአድ ፕሬዚዳንት በነፃ ተሰናበቱ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ለመቀላቀል ሲጓዙ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው አራት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የምስክርነት ቃል ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን የሽብር ድርጊት ወንጀል ክስ እየመረመረ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ምስክሩን ያሰማው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተመሠረተባቸውን ክስ እንደማይቃወሙና ድርጊቱን መፈጸማቸውን በማመናቸው፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ የጠቀሰውን አንድ ምስክር አሰምቷል፡፡ 

የዓቃቤ ሕግ ምስክር ሆነው የቀረቡት ግለሰብ እሳቸውም የሰማያዊ ፓርቲ አባል እንደነበሩ አስታውቀው፣ የፓርቲው የተለያዩ ክፍሎች አመራሮች የነበሩትን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ እየሩሳሌም አስፋውንና ፍቅረ ማርያም አስማማውን የሚያውቋቸው በፓርቲው ውስጥ በነበሩበት ጊዜ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ተከሳሽ ብርሃኑና እየሩሳሌም የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰላማዊ ትግሉ እንደማያዋጣ ተነጋግረው ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ለመሄድ ሲንቀሳቀሱ ምስክሩም አብረው ባህር ዳር ድረስ መሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡ 

ባህር ዳር እንደደረሱ እሳቸው (ምስክሩ) ሐሳባቸውን በመቀየር ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ያስረዱ ሲሆን፣ ተከሳሽ ብርሃኑ ‹‹ለምን ትመለሳለህ? ቢያንስ ጎንደር የምናገኘው ሰው ስላለ እሱን ካገኘህ በኋላ ትመለሳለህ፤›› ቢላቸውም ሳይስማሙ ቀርተው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በወቅቱ ስሜታዊ ሆኜ መወሰኔ አግባብ እንዳልሆነ ስለተረዳሁ ነው፤›› በማለት ‹‹ለምን ሐሳብህን ቀየርክ?›› ለሚለው መስቀለኛ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምስክር ለመሆን መገደድ አለመገደዳቸውን፣ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው፣ ታስረው እንደነበርና ግንቦት ሰባት ነፃ አውጪ ወይም አሸባሪ ድርጅት መሆኑን እንዲያስረዱ በተከሳሾቹ ሲጠየቁ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሟል፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀን ድርጅት መጠየቁ አግባብ አለመሆኑን ዓቃቤ ሕግ በማስረዳቱ፣ ፍርድ ቤቱም የተከሳሾቹ ጥያቄ እንዲታለፍ በይኗል፡፡ ምስክሩ በአራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ላይ የምስክርነት ቃል አልሰጡም፡፡

ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

ይህ በዚህ እንዳለ አይኤስን ለመቃወም መንግሥት ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ የተፈጠረውን ብጥብጥ በማደራጀትና በመምራት ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የመኢአድ (የቀድሞ) ሊቀመንበር  አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ ተለቀዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አቶ ማሙሸትን በነፃ ያሰናበታቸው፣ ሰላማዊ ሠልፉ በተደረገበት ዕለት እሳቸው ከምርጫ ቦርድ ጋር በነበረባቸው ክርክር ፍርድ ቤት መዋላቸውን የሚያስረዳ ሰነድ በማቅረባቸው ነው፡፡ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል የተጠና መሆኑን በመቃወም ጠበቃቸው ለፍርድ ቤት በማስረዳታቸውና ምስክሮቹም የተለያየና የማይገናኝ የምስክርነት ቃል መስጠታቸው ለአቶ ማሙሸት በነፃ መሰናበት ምክንያት ሆኗል፡፡

 

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በሃመር ብሄረሰብና በዞኑ ፖሊስ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የአንድ ሻለቃ ጦር አባላት በርካቶቹ ኮብልለው በመጥፋታቸው ፣ ለወታደሮቹ መጥፋት ምክንያት ናቸው የተባሉ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት መካካል የሚታየው አለመተማማንና ልዩነት በመስፋቱ እርስ በርስ እስከመጋጨት ደርሰዋል። ከወር በፊት …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፣ ታምራት ታንቱ ባጫ የተባለ ወጣት፣ ቤቱ ለሶስተኛ ጊዜ በመንግስት አፍራሽ ግብረሃይሎች መፍረሱን ተከትሎ፣ ራሱን ያጠፋ ሲሆን፣ ባለቤቱም ራሱዋን ስታ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ውስጥ ጸሎት እየተደረገላት ነው። ወጣት ታምራት ትናንት ነሃሴ 26 የቀብሩ ስነስርአት ተፈጽሟል። ሚሚ ባቴ የተባለች የአንድ ሳምንት መጫትም በላዩዋ ላይ …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ከምርጫ 2007 በፊት ህብረተሰቡ መሳሪያ እንዲታጠቅ በመፍቀድ ህጋዊ ያደረገውን የመሳሪያ ፈቃድ በመንጠቅ መሳሪያዎችን ለመሰብሰብ ስልቶችን እየቀየሰ መሆኑ ምንጮች ለኢሳት አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት ህገወጥ የጦር መሳሪያ ህጋዊ ለማድረግ ምዝገባ ካካሄደ በኋላ የመሳሪያ ፍቃድ በመስጠት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲከላከልበት መፍቀዱን ተከትሎ፣ ከአጎራባች ክልሎች በተለይም ከትግራይ …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ 221 አመራሮችንና 4 ሺ 100 ሰራተኞችን ገምግሞ ጥፋተኛ ብሎአቸዋል። ሰራተኞቹ በህግ ይጠየቃሉ ተብሎአል። ኢሳት የሰራተኞችን ግምገማ በተመለከተ ከወር በፊት ባቀረበው ዘገባ፣ አብዛኞቹ ሰራተኞች እና አመራሮች ዝቅተኛ ነጥብ እንደተሰጣቸውና ሊባረሩ እንደሚችሉ ገልጾ ነበር። በዚሁ ግምገማ ምክትል ከንቲባው አቶ አባተ ስጦታውም ዝቅተኛ የግምገማ ነጥብ የተሰጣቸው በመሆኑ፣ ከሚቀነሱት …

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስደተኞቹን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ከባድ መኪና በናካንዳ የድንበር የፍተሻ ጣቢያ አቅራቢያ ፓሊስ የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ተይዘዋል። ሕገወጥ ስደተኞችን በማዘዋወር ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የዛንቢያ ዜጎችም አብረው ተይዘዋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአስር እስከ ሃምሳ ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። ስደተኞቹ በአሁኑ ወቅት በኳቤ የደኅንነት እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙና …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ነኅሴ ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ወኪል የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት የታሰሩ 20 ሴቶች እንዲፈቱ ዘመቻ ይጀምራሉ። ከ20 ዎቹ ሴት እስረኞች መካከል ብሌን መስፍን፣ ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንድይፍራው ከኢትዮጵያ፣ ዋንግ ያኑ፣ ጋዎ ያኑና ሊዩ ዚያ ከቻይና፣ ካጂያ ኢስማዮላ ከአዘርባጃን፣ አስቴር ዮሃንስ ከኤርትራ፣ ማትሉዩባ ካሚሎቫ …

አብዛኛው ሰው በሀገሩ ኑሮ ሲጠበው፣ በሀገሩ ሰላም ሲያጣ ፣ በሀገሩ ነገሮች አልሆኑለት ሲሉ ራሱን ሊለውጥ አለያም ይደርስብኛል ሲል የሚሰጋበት ሰብአዊ መብት ረገጣ ሽሽት ወደስደት ይወጣል። አንዳንዱ እድለኛ ታስጠልለኛለች ብሎ ያላት ምድር ስቃ ትቀበለዋለች አንዳንዱን ደግሞ ህይወቱ የባሰ ቅጥአንባሩ ይጠፋውና ምነው በዚያው የሀገሬ ጅብ በበላኝ ሲል ይማረራል ለአንዳንዶች ግን ያስጠልለናል ካሉት ቦታ ሳይደርሱ በመንገድ ይቀራሉ! አንዱ […]

ባደጉት አገሮች የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የሳይንስ ትሩፋቶች የሰው ልጅን የዕለት ተለት የኑሮ እንቅስቃሴ እየለወጡት ነው። ኡበር የተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ አፕልኬሽን የታክሲ አገልግሎት ከፍተኛ ተቀባይነት ቢያገኝም በተለምዷዊው ስርዓት አገልግሎት አቅራቢዎች ግን ከፍተኛ ትችት ሲሰነዘርበት ይደመጣል።

ሰበር መረጃ “ዛሬ ጠዋት አርበኞች ግንቦት ሰባት ባሳቻ በሰነዘረው ጥቃት ስፍር ቁጥር የሌለው የወያኔ ጋሻጃግሬዎች ሲደመሰሱ ገሚሱ ትግራይ ቦርደር ሆስፒታል እየተባለ ወደ ሚጠራዉ የህክምና ተቋም ቁስለኛ ወታደሮች ለህክምና ሲትም መዋሉን ከስፍራው ያይን ምስክር በተለይም ለ አፈትላኪ ዜና ምንጭ ዘግይቶ አድርሶናል። ይህበንዲህ እንዳለ ማይ ጻይ እየተባለ ከሚጠራዉ አካባቢ የሚነሱ ሄሊኮፍተሮች በአየር መቃወሚያ ወሰን ኢላማ ዉስጥ ገብተዋል።በተያያዘም […]

ወያኔ በመቶወቹ የሚቆጠሩ የ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙህራንን ጠራርጎ ካበረና በካደሬ ከሞላው ጀምሮ ዩኒቨርስቲው በሙስና ከመጨማለቁና የካድሬ መፈንጫ ከመሆኑ ባሻገር ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ኦዲት ተደርጎ የማይታወቅ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ የዩኒቨርስቲው ዶርሚተሪወች ወደ ግለሰቦች መኖርያና ክራይ እየተቀየሩ ስለመሆኑ ውስጥ አወቅ ምንጮች ዘግበዋል።ይህ በንዲህ እንዳለ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋየና ምክትላቸው ዶ/ር ጄሉ ኦመር ከሀገር መውጣታቸውን […]

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርቁ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት የሚመገቡት ባለመኖሩ አብዛኛው ወጣቶች ወደ ጠረፍ ከተማ በመሰደድ ላይ ናቸው። በሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ ዞን ያሉ ነዋሪዎች በድርቁ ምክንያት እንስሳት አልቀዋል፤ መሬት የሌላቸው ወጣቶች የቀን ስራ በመስራት ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ ምግብ ፍለጋ ወደ ጠረፍ ከተማ እየተሰደዱ ነው። መሬት የሌላችው ወጣቶች በየአካባቢያቸው መሬት ተከራይተው …

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆኑት አቶ ጌትነት በሱፈቃድ በወላይታ ዞን ቦሎቶሶሬ ወረዳ አረካ ከተማ ላይ ተደብድበው መዘረፋቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ ጌትነት የሰማያዊን ጠቅላላ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ ነሃሴ 20/2007 ዓ.ም አረካ ላይ ተደብድበው ስልካቸውንና የአንገት ሀብላቸውን ተቀምተዋል። የቀማቸው ሰው እጅ ከፍንጅ ቢያዝም ፖሊስ እርሳቸውን አስሮ ወንጀሉን የፈፀመውን ሰው …

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነትና ከአስተዳደር መብት ጋር በተያያዘ ለአመታት የዘለቀው የቁጫ ህዝብ ጥያቄ፣ ምላሽ ባላገኘበት ሁኔታ፣ አሁንም የሚታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከ140 በላይ የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ካለፉት ሁለት አመታ ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ ሰሞኑን ሌሎች የመንግስት ሰራተኞችም መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት …

ነኅሴ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር የዘመተው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት በመሃከላዊ ሶማሊያ በገልጋዱ ግዛት ውስጥ አራት ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎችን በግፍ መግደሉንና ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ መምህራን መሆናቸው ተገልጿል። ”በአካባቢያችን በኢትዮጵያ ታጣቂዎች እንደዚህ ዓይነት አስቀያሚ እርምጃዎች እየተወሰዱብን እኛ ከዚህ በላይ ልንታገስ አይገባንም።ይቅርታ ልናደርግላቸውም አይገባንም።ካለርህራሄ አራት …

ለክብረ በዓሉ እና ጽኑ ኦርቶዶክሳውያንን ለማጽናናት ምእመናን እንዲሳተፉ እየተጠየቀ ነው ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን እና እሑድ ጳጉሜን 1 ቀን ለሚደረገው ጉዞ ምዝገባ እየተካሔደ ነው በክብረ በዓሉ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የመሠረት ድንጋይ በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይቀመጣል *           *          * ከሥራቸው ታግደው በፈጠራ ክሥ የታሰሩት የሰበካ ጉባኤ አባላት ቤተሰቦች ችግር ተባብሷል የወረዳው ፍ/ቤት ለወሰነባቸው ከ6 – 9 …

‹‹የሳምንት አራስ ጎዳና ላይ ወድቃለች›› በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ መርካቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጎላ መንደር ‹‹ህገ ወጥ የቤት ግንባታ›› በሚል በመንግስት ለሶስተኛ ጊዜ ቤቱ የፈረሰበት ወጣት ታምራት ታንቱ ባሳ ራሱን ማጥፋቱን ምንጮች ከሶዶ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ወጣት ታምራት ታንቱ ባሳ በዚህ መንደር ረዘም ላለ ጊዜ እንደኖረ የገለፁት ምንጮች ለሶስተኛ ጊዜ ‹‹ህገ ወጥ […]

ከወጪ ንግድ 14 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል

-ዕቅዱ 119 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት አለው

ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ ተግባራዊ የሚደረገው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣትና ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው የዓለም አገሮች የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ማሠለፍ ራዕይ አድርጓል፡፡ ለዚህም ዕቅድ መሳካት 2.4 ትሪሊዮን ብር ይጠይቃል፡፡

 

ለዕቅዱ እንደ መነሻ የተወሰዱት የአገሪቱ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መልካም ውጤት እያስገኙ መሆናቸው፣ በመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ወቅት የተጀመሩና በግንባታ ላይ ያሉ ኢኮኖሚያዊ የልማት ፕሮጀክቶች በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ተካተው መጠናቀቅ ያለባቸው መሆኑን ግንዛቤ ይዟል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ የተስማማችባቸው የድኅረ 2015 የልማት ግቦችም የዕቅድ ዝግጅቱ መነሻ ያደረጋቸው ጉዳዮች መሆናቸውን  ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በዚሁ መሠረት በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ማለትም በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገቱ 11 በመቶ እንዲሆን ማድረግ በመሠረታዊ የዕድገት አማራጭ የተቀመጠ ግብ መሆኑን የተገኙት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በከፍተኛው የዕድገት አማራጭ ደግሞ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ 12.2 በመቶ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ በከፍተኛው የዕድገት አማራጭ መሠረት በአገሪቱ መዋቅራዊ ለውጥ መምጣት የሚችልበትን ሥርዓት መጣል ትልቁ ዓላማ ነው፡፡

በዚሁ በከፍተኛ የዕድገት አማራጭ ረቂቅ ዕቅድ መሠረት የግብርና ዘርፉ የምርት ዕድገት ተጠናክሮ በመቀጠል አማካይ ዓመታዊ ዕድገቱ ስምንት በመቶ እንዲሆን ታቅዷል፡፡ ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር ዕውን ለማድረግ በዕቅዱ ዘመን የኢንዱስትሪ ዘርፉን አማካይ ዓመታዊ ዕድገት 19.8 በመቶ ለማድረስ ረቂቅ ግብ መጣሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ የግብርና ዘርፍ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት የሚኖረው ድርሻ በ2007 ዓ.ም. ከነበረበት 41 በመቶ በ2012 ዓ.ም. ወደ 35.6 በመቶ እንዲወርድ በዕቅዱ ተይዟል፡፡

የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከሁሉም ዘርፎች ቅድሚያ የተሰጠው በመሆኑ በላቀ ፍጥነት ያድጋል የሚል ግምት ተሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት የሚኖረው ድርሻ በ2007 ዓ.ም. ከነበረበት 15.6 በመቶ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ዘመን መጠናቀቂያ ላይ የ22.8 በመቶ ድርሻ እንደሚኖረው በረቂቅ ዕቅዱ ተቀምጧል፡፡ የአገልግሎት ዘርፉ ድርሻ ከግብርናና ከኢንዱስትሪ ዘርፎች ድርሻ ውጪ ያለውን 41 በመቶ እንደሚይዝ የተገመተ ሲሆን፣ ይኼም በ2007 ዓ.ም. ከነበረበት 43.4 በመቶ እንደሚቀንስ ያሳያል፡፡

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማገባደጃ ላይ የሸቀጦች የወጪ ንግድ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት የሚኖረውን ድርሻ 11.8 በመቶ እንደሚሆን ውጥን ተይዟል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የየዘርፉ የወጪ ንግድ ገቢ ተሰልቶ በረቂቅ ዕቅዱ ተቀምጧል፡፡ በዚህም መሠረት ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ 7.7 ቢሊዮን ዶላር በ2012 ዓ.ም. ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ ከኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ ደግሞ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል፡፡

በወጪ ንግድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው ልዩ ዘርፎች መካከል የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት አንዱ ሲሆን፣ በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ 636 ሚሊዮን ዶላር የማግኘት ዕቅድ ተይዟል፡፡ በማዕድን ዘርፍ በመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የተገኘው የንግድ ገቢ 508 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን 2.1 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል፡፡

ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የማኑፋክቸሪን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዓላማ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ውስጥ ዘርፉ በሁሉም መለኪያዎች በኢኮኖሚው ውስጥ የቀዳሚነት ሥፍራ እንዲይዝ ማድረግ ነው፡፡

በዚህ መሠረት የመካከለኛና የከፍተኛ ኢንዱስትሪ ኤክስፖርት ገቢ በየዓመቱ በአማካይ በ98 በመቶ እንዲያድግ ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፣ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ 4.6 ቢሊዮን ዶላር እንዲደርስ ታስቧል፡፡

ከፍተኛ ግምት የተጣለባቸው ጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ዘርፎች ሲሆኑ፣ ከጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ አንድ ቢሊዮን ዶላር የኤክስፖርት ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡ 

በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ 800 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡

ለዚህ ዘርፍ ይረዳ ዘንድ እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ ሰባት ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬት የማምረቻ ቦታዎችን በማዘጋጀት ለባለሀብቶች ለማቅረብ ታቅዷል፡፡ አራት የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፖርኮች ፓይለት ፕሮጀክቶችን በማልማት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ምርቶች ከኢንዱስትሪ ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ 

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን ከማስፋፋት ፕሮግራም በተጨማሪ አዳዲስ ዘርፎችን በማምረት፣ በእነዚህ መስኮች ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለማስፋፋት ትኩረት እንደሚሰጥ ረቂቅ ዕቅዱ ያስረዳል፡፡ ከዚህ አኳያ ዓለም አቀፍ የእሴት ሰንሰለትንና የአገሪቱን ዕምቅ ሀብት የገበያ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የባዮ ቴክኖሎጂ፣ የፔትሮ ኬሚካል፣ የኤሌክትሪካልና የኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በተለይም የሶፍትዌርና የሐርድዌር ልማት ለማስፋፋት ታቅዷል፡፡

በመንገድ ዘርፍ ልማት ጠቅላላ የመንገድ ርዝመትን በ2007 ዓ.ም. ከተደረሰበት 120,000 ኪሎ ሜትር ወደ 220,000 ኪሎ ሜትር ለማድረስ ታቅዷል፡፡

በባቡር መሠረት ልማት በመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ታቅደው የነበሩትን መስመሮች ማጠናቀቅ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፣ ተጨማሪ አምስት አገር አቀፍ የባቡር መስመሮችን ጥናት ማካሄድና ፋይናንስ የማፈላለግ ሥራ ለማከናወን በዕቅዱ ተካቷል፡፡

በመሆኑም እስከ 2012 ዓ.ም. መጠናቀቅ የሚገባቸው የባቡር መስመሮች 2,782 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሲሆን፣ እነሱም መቐለ-ሐራ ገበያ፣ ሐራ ገበያ-አሳይታ፣ አሳይታ-ታጁራ ወደብ፣ አዋሽ-ሐራ ገበያ፣ አዲስ አበባ-ሰበታ-ኢጃጂ-ጂማ-በደሌ-ቴፒ-ደማ የሚደርሰው 740 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር፣ እንዲሁም 905 ኪሎ ሜትር የሚሽፍነው የሞጆ-ሐዋሳ-ወይጦ-ሞያሌ መስመሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በተጨሪም በአዲስ አባባ ከተማ የተዘረጋውን 34 ኪሎ ሜትር ቀላል የከተማ ባቡር መስመር በሁለት አቅጣጫዎች በድምሩ 41 ኪሎ ሜትር ለማስረዘም ታቅዷል፡፡

ጥናትና የገንዘብ ማፈላለግ የታቀደባቸው የባቡር መስመሮች ደግሞ ከወልዲያ-ወረታ-ፍኖተ ሰላም፣ ከወረታ-መተማ፣ ከመቐለ-ሽሬ፣ ኢጃጂ-ኩምሩክና ኢተያ-ጊኒር ሲሆኑ፣ አምስት መስመሮች ጠቅላላ ርዝመታቸው 1,820 ኪሎ ሜትር የሚደርሱ ናቸው፡፡

በኢነርጂ ረገድ በ2007 ዓ.ም. የተደረሰበትን 2,220 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም፣ በ2012 ዓ.ም. ወደ 17,347 ሜጋ ዋት ለማድረስ ታቅዷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከውኃ ኃይል አሁን የሚገኘውን 1,953.5 ሜጋ ዋት ኃይል ወደ 13,957 ሜጋ ዋት ለማሳደግ ታቅዷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከንፋስ የሚገኘውን 171 ሜጋ ዋት ወደ 1,222 ሜጋ ዋት ለማድረስ ታቅዷል፡፡

በአጠቃላይ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በአምስት ዓመት ፕሮግራም ውስጥ 2.4 ትሪሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ረቂቅ ዕቅዱ ይተነትናል፡፡

ይኼንን ወጪ ለመሸፈን በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የሚኖረው የአገር ውስጥ የገቢ አቅም 2.03 ትሪሊዮን ብር ነው፡፡ በመሆኑም የበጀት ጉድለቱ ዕርዳታን ጨምሮ 341.2 ቢሊዮን ብር ይሆናል የሚል ታሳቢ በረቂቅ ዕቅዱ ተይዟል፡፡

ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈለገው የውጭ ምንዛሪም 119.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 30 በመቶ፣ የአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 41.7 በመቶ እንደሆነ ተተንትኗል፡፡ 

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ከአለፉት 24 ዓመታት ወዲህ በስልጣን ላይ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ትናንት ባጠናቀቀው ድርጅታዊ ጉባዔ የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ነው ተባለ። የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ችግሩ መፍትሄ ካላገኘ ለስርዓቱ አደጋ ሊሆን እንደሚችል ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በዚህ ምስል ላይ የምታዩት ፊልስጤማዊው አባትና ልጁ ነዋሪነታቸው የእርስ በርስ ጦርነት እንዳይሆኑ ያደረጋት ሶርያ ውስጥ ነበር፡፡ ከ210 000 በላይ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የሶርያው ጦርነት ከመኖሪያቸው ካፈናቀላቸው ሚሊዮኖች አንዱ የሆነው አብዱል፣ ልጆቹን ለማሳደግ ያለው ብቸኛ አማራጭ በቤይሩት ጎዳናዎች ላይ እስክሪብቶ እያዞረ መሸጥ ሆነ፡፡ ሪም የተሰኘችው ሴት ልጁን ተሸክሞ ጎዳና ላይ እስክሪብቶ ሲሸጥ የተመለከተው አንድ ጋዜጠኛ ምስሉን […]

የኢሕአዴግ አሥረኛ ጠቅላላ ጉባዔና የሥልጣን ቅብብሎሹ

በጥር ወር 1983 ዓ.ም. የትጥቅ ትግል ላይ እያለ የመጀመርያ ጠቅላላ ጉባዔውን በትግራይ ክልል በቆላ ተምቤን የጀመረው ኢሕአዴግ አሁን አሥረኛ ጉባዔውን በመቐለ ከተማ በማካሄድ ላይ ነው፡፡ ‹‹ሕዝባዊ አደራን በላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን››

በሚል መሪ ቃል ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ ያለው ኢሕአዴግ  የመጀመርያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ፣ ለሁለተኛው ዕቅድ ተግባራዊነት የሚረዱ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሰሞኑን በአራቱ አባል ድርጅቶች (ሕወሓት፣ ብአዴን፣ ኦሕዴድና ደኢሕዴን) በተካሄዱ የተናጠል ጉባዔዎች በሥራ ላይ ያሉት ሊቀመናብርትና ምክትሎቻቸው በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡ በኢሕአዴግ ደረጃም ለውጥ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ነገር ግን በአመራር የመተካካት አሠራር መሠረት የአባል ድርጅቶቹና የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የትጥቅ ትግል ተሳትፎ የነበራቸውና ከ20 ዓመታት በላይ በአመራር ላይ የቆዩ አባላት ሙሉ በሙሉ ይተካሉ በሚለው፣ በ2002 ዓ.ም. ይፋ የሆነው ፖሊሲ ተግባራዊነት ላይ ጥያቄዎች መነሳት ጀምረዋል፡፡ በምሥሉ ላይ ከግራ ወደቀኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርና የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ በመቐለ የጉባዔ አዳራሽ ውስጥ ሲመካከሩ ይታያሉ፡፡ በግንባሩ አባል ድርጅቶች በተመረጡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ገጸ ታሪክና በመተካካት ፖሊሲው ማዕቀፍ ላይ የተዘጋጀው ዘገባ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ወይም በ ፖለቲካ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡

 

የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ በየዓመቱ ሰኔ 20 በጀት ከተሰራ በኋላ ከትርፉ ድጎማ እንዲያገኙ ከፋብሪካው ጋር ስምምነት እንዳላቸው የገለፁት የፋብሪካው ሰራተኞች ፋብሪካው ትርፋማ ቢሆንም ድጎማቸው ስላልተሰጣቸው በዛሬው (ነሃሴ 25/2007 ዓ.ም) ዕለት የስራ ማቆም አድማ እንዳደረጉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አንድ የፋብሪካው ሰራተኛ ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በዘንድሮው ዓመት ፋብሪካው ከፍተኛ […]

ጠ/ ምኒስቴ ሃይለማርያም ለሰቆጣ ህዝብ ዛሬ የሻዳይ በህል ለማየት ነው ለእግረመንገዳቸው መጎብኘት የነበረባቸው? የሰቆጣ የላሊበላ ኣውራጃ ህዝብ በድርቅ በተለያዩ የተፈጥሮ ችግር በመልካም ኣስተዳደር በፍትህ እጦት ምክንያት ወደስደት መበታተን ከጀመረ ኣመታት ኣሰቆጥራል በተለይ ባለፉት ሁለት ኣመታትና ዘንድሮ የኣገው ህዝብ እንስሳ ዘቤቱ ኣልቀው የቀሩት ተሽጠው ወጣት ሴቶችና ወንዶች ኣገር አቃርጠው ጠፍተዋል የወለዱ ሴቶች ህፃናት ወደ ኣጓራባች ክልልና […]

The post የሃደለማርያም ደሳለኝ ሽመትና የሰቆጣ ጉብኝት – አስገደ ገብረስላሴ appeared first on ሳተናው (Satenaw)-Latest Ethiopian News & Breaking News.

የህወሓት የቀድሞ አየር ኃይል አዛዥ የነበረው ሜ/ጀነራል ሞላ ኃ/ማሪያም ያለበት እንደማይታወቅ ተነገረ አርበኞች ግንቦት 7 በድሆች ድህነት ለመክበር በመሯሯጥ ላይ ላሉ ለዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት መልህክት አስተላለፈ በደኢህአዴን አመራሮች መካከል ውጥረት ነግሳል የወያኔ ጥቅመኞችና ሳዑዲ ዓረቢያ ዳግም  የሠራተኞች ቅጥር ስምምነት ሊፈራረሙ ነው ተባለ በሰሜናዊው የኢትዮዽያ ተጠናክሮ የቀጠለው ትግል ወያኔን አስፈርቶታል ጃፓን ከኢትዮጵያ የሚላከውን ቡና አግዳ ብትቆይም፣ አሁንም በሚላክላት […]

የህወሃት የጉባኤ ተሳታፊዎች ነሃሴ 17 ቀን 2007 ዓ/ም አባይ ወልዱ ትግራይን የመምራት አቅም የለውም ድህነትና ሙስና እንዲስፋፋ አድርጎ ህዝባችንን እያሰቃየ ነው የሚል ሃሳብ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል። ለ12ኛ ጊዜ የተካሄደው የይስሙላ የህወሃት ጉባኤ የተሳተፉ ሰዎች ነሃሴ 17 ቀን 2007 ዓ/ም ካቀረቡት ሃሳብ መካከል አባይ ወልዱ የትግራይ ክልልን መምራት የለበትም በሱ ፋንታ አርከበ ዕቑባይ መምራት አለበት ካሉ […]

በጀኔራል ሳሞራ የኑስ እየተመራ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የመከላከያ ከፍተኛ አዛዦች ግምገማዊ ስብሰባ ያለመፍትሄ መበተኑን ለማወቅ ተችሏል።በመረጃው መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የተመራው የገዥው መንግስት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ከነሃሴ 12 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ እንደቆየ የገለፀው መረጃው፤ የስብሰባው አጀንዳም መንግስት አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አሰልጥኖ ይለቃል ወደ እናንተ ሲደርስ ግን በርካታው […]

እራሱን ጽናት እያለ በሚጠራው ጀሌ ላይ በቀረበው ጽሁፍና ማስተባበያ ለቀረበበት «ዘረፋ» ግልጽ የሆነ ማስረጃ !‏‏ ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ እንቅልፍ አጥቶ ማደርየጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ የታወቃል ።ህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ ለይስሙላ ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ መብት በመተላለፍ የህዝቦችን መብት በጠመንጃአፈሙዝ ጨፍልቆ ለጸሎት አደባባይ የወጣውን አዛውንት ሴት ወጣት ሳይል ያገኘውን ሁሉ በደም በጨቀዩ ልዩ ኮማንዶዎቹበጥየት ረሽኗል ፤ ከሞት የተረፈውን በቆመጥ ደብድቦ በክሚዎን በማጋዝ ወዳልታወቀ ስፍራ ወስዶ አስሮ በማሰቃየት ላይይገኛል። ታዲያ ይህን ሁሉ ግፍና ስቆቃ የተቀበለው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ሰላማዊ ተቃውሞውን የበለጠበማጠናከር ሳይገድል እየሞተ ለአምባ ገነኖች የአላማ ጽናቱን በተግባር አሳይቷል በማሳየትም ላይ ይገኛል። ይህ የህዘበሙስሊሙ አንድነትና ለሃይማኖቱ ነጻነት ያለው ቁርጠኝነት እንቀልፍ የነሳው ሀወሃት መራሹ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት የበግልምድ ለብሶ ውሎና አድሩን ህዝበ ሙስሊሙ ጉያ ውስጥ በማድርግ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዑለማዎችየሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በኃይል አሊያም በግዜያዊ ጥቅም በማግባባት ለዚህ እርኩስ ሴጣናዊ ተግባሩማስፈፀሚያ ግበአት እንዲሆኑ ለማድረግ ሃገር ውስጥና በውጩ አለም እየዞረ  ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልቦጠጠው ተራራየለም። ለአብነት ያህል የፖለቲከኛውን ጁሃር መሃመድ አሳዛኝ ታሪክ ወደ ጎን ትተን በእስቷዝ ሃስን ታጁ ስም አዲስ አበባ ላይቀደም ሲል የተበተነውን ከፋፋይ የሆነ ባለ10 ገጽ ጽሁፍ ማስታወስ ከበቂም በላይ በቂ ማስረጃ ነው ።በእስቷዝ ሃስን ታጁጽሁፉ ላይ «ሰላማዊ ትግሉን የተቀላቀሉ ወጣቶች አላዋቂ፣ስሜተኛ፣ጃሂል አድርጎ ለማቅረብ ከተደረገው ጥረት ባሻገርየተቃውሞ አካሔድ ሌላ መንገድ ቢፈለግለት በሚል አሳፍሪ አቋም በተለይም የጁሙዓ ተቃውሞዎች መቋረጥእንዳለባቸውና ኮሚቴዎቻችን ይቅርታ ጥይቀው እንዲወጡ » ህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ህዝበ ሙስሊሙን ተመስሎበዑለማዎቻችን አንደበት ያሻውን መልዕክት በድፈረት ይስተላለፈበት ያ ! ፈታኝ የትግል ዘመን የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው ዛሬ ከዚህ አፍራሽ ተዕልኮ ባልተለየ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ና ሪያድከተማ ውስጥ ብዙሃኑ ተመስለው ሊያሰሙን በሞከሩት ጩኋት በአካባቢው ያሉትን ስመጥር የሃይማኖት አባቶችና እሩቅያሉትን የህዝበ ሙስሊሙን ነጻ ሚዲያዎች ቀልብ አሳስተው ለዚህ መስሪ ተግባራቸው ግበአት በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙአንድንተ ላይ አደጋ ከመጋረጥ አልፈው በአቋራጭ የግል ኑሮቸውን ለማደርጀት ሲያደርጉ የነበረው ጥረት በሃገር ሽማግሌናበኃይማኖት አባቶች ተጋልጦል ዝርዝር መረጃውን ሊንኩን ይጫኑ   ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ posted by Aseged TameneFiled under: NEWS Tagged: Addis Ababa, Addis Ababa University, Africa, African Commission on Human and Peoples’ Rights, EPRDF

አለም ባስመሳይ ሴረኞች ትማስናለች የሴራ ፖለቲካ ቁንጮዋ ደግሞ አሜሪካ ነች።የአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢንላደን በሕይወት በባህማስ ደሴቶች ውስጥ እንደሚኖር ኤድዋርድ ስኖውደን ተናገረ:: የአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢንላደን በሕይወት በባህማስ ደሴቶች ውስጥ እንደሚኖር እና በየወሩም ከአሜሪካ የስለላ ድርጅት መቶ ሺህ ዶላር ደምወዝ እንደሚከፈለው የአሜሪካንን ጥብቅ ሚስጥሮች ሰብስቦ ወደ ሩስያ የኮበለለው የቀድሞው የ NSA ሰራተኛ ኤድዋርድ ስኖውደን ለMoscow Tribune […]

በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የተመረጡ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የምክር ቤት አባላት ፣ የኢህአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ደኢህዴን 1 ጓድ ኃ/ማርያም ደሳለኝ 2 ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ 3 ጓድ ደሴ ዳልኬ 4 ጓድ ተስፋዬ በልጅጌ 5 ጓድ ሲራጅ ፈጌሳ 6 ጓድ ሬድዋን ሁሴን 7 ጓድ መኩሪያ ኃይሌ 8 ጓድ መለሰ ዓለሙ 9 ጓድ ተ/ወልድ አጥናፉ ኦህዴድ 1 ጓድ ሙክታር ከድር 2 ጓዲት አስቴር ማሞ 3 ጓድ ወርቅነህ ገበየሁ 4 ጓድ ዳባ ደበሌ 5 ጓድ ድሪባ ኩማ 6 ጓድ አብዱልዓዚዝ መሐመድ 7 ጓድ በዙ ዋቅቤካ 8 ጓድ ኡመር ሁሴን 9 ጓድ በከር ሻሌ ህወሓት 1 ጓድ አባይ ወልዱ 2 ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 3 ጓድ ዶ/ር ቴድሮስ ኣድሓኖም 4 ጓድ በየነ ምክሩ 5 ጓዲት አዜብ መስፍን 6 ጓድ አለም ገ/ዋህድ 7 ጓድ ጌታቸው አሰፋ 8 ጓድ ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ 9 ጓዲት ፈትለወርቅ ገ/ሄር ብአዴን 1 ጓድ ደመቀ መኮንን 2 ጓድ ገዱ አንዳርጋቸው 3 ጓድ አለምነው መኮንን 4 ጓድ ብናልፍ አንዱ አለም 5 ጓድ ተስፋዬ ጌታቸው 6 ጓድ ዶ/ር አምባቸው መኮንን 7 ጓድ አህመድ አብተው 8 ጓድ ከበደ ጫኔ 9 ጓድ ካሳ ተ/ብርሃን የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ህወሓት 1. ጓድ ኪሮስ ቢተው 2. ጓዲት ኣረጋሽ በየነ 3. ጓድ ምኪኤለ ኣብርሃ 4. ጓድ ማሙ ገ/ሄር 5. ጓድ ጎይትኦም ይብራህ 6. ጓድ ኢሳያስ ታደሰ 7. […]

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 25, 2015) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የተቀነባበረ ጥቃት መሰንዘሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ባለፈው ሚያዚያ ወር መጨረሻ ተፈጸመ በተባለው በዚሁ ጥቃት፣ ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና በአንድ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ አማሮች ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ ከሶስት ወራት በፊት በተፈጸመው …

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሱዳን ባለሀብቶች መተማ ዮሃንስ ከተማ ውስጥ “ትራክተር መንዳት የሚችል 11 ሰዎችን እንፈልጋለን” የሚል ማስታወቂያ መለጠፋቸውን ተከትሎ፣ ውድድሩን ካለፉት መካካል 8ቱ በሱዳን ታጣቂዎች ታርደው ተገድለዋል። ባለሀብቶቹ በርካታ አመልካቾችን ቢያገኙም፣ አስራ አንዱን ብቻ ይዘው ወደ ሱዳን መሄዳቸውን ፣ ይሁን እንጅ ሱዳን ውስጥ ሲገቡ፣ ወታደሮቹ መንገድ ላይ ጠብቀው ከመኪና …

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነሃሴ 19 ቀን በኦሮምያ ክልል በቡሌሆራ ከተማ፣ በ1949 የተገነባውን የገበያ ማእከል በማፍረስ የመኪና መናሃሪያ ለማድረግ፣ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት ህዝቡ ያሰማውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ ከ150 በላይ ሰዎች በድብደባ ሲቆስሉ፣ ወገኖ ወንዳቸው የተባለ ወጣት በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ገብቶ እየታከመ ነው። የከተማው ባለስልጣናት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ሳይስማሙና …

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ወኪላችን እንዳለው ባለፈው ቅዳሜ ህወሃት ለኢህአዴግ ጉባኤተኞች ባዘጋጀው የእራት ግብዣ፣ ከ2 ሺ ያላነሰ ሰው ተገኝቷል። ለእንግዶቹ የተለያዩ ምግቦች፣ ቁርጥ ስጋ እና ውስኪ እንደ ልብ ቀርቦላቸዋል። ግብዣው የተደረገው 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የሚላስና የሚቀመስ እንደሌለው ሪፖርት በተደረገበት ወቅት ነው። በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ ድርቅ መግባቱን …

ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በትላንትናው እለት በርካታ የኮሎራዶ ነዋሪዎች በተሳተፉበት ስብሰባ ላይ የከተማው ኣርበኞች ግንቦት ፯ ክፍል ለጫራታ ያዘጋጀው መኪና በ47 ሺ 200 ዶላር ተሽጧል። በዚህ ሀገርን የማዳን ጥሪ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ የምክርቤት አባል ኣቶ ቸኮል ጌታነህ በአካል ተገኝተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጋዜጠኛ አበበ ገላው የትግልን አስፈላጊነት በተመለከተ ንግግር …

በሕገወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ለመንግሥት ተመለሰ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በ2008 በጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በሙስና ተጠርጥረው በክስ ሒደት ላይ ከሚገኙ ሰዎች፣ 28 ቤቶችን በፍርድ ቤት ማሳገዱንና ስድስቱ ቤቶች በዱባይና በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ የሚገኙ መሆናቸውን ገለጸ፡፡ ኮሚሽኑ […]

ነሀሴ 14,12,07ዓ.ም የታክሲ ሾፌሩ ከነመኪናው ወደ ቤቱ አልተመለሰም የመኖርያ ስፍራው ከወይራ ሰፈር ወደ ቤተል ሲኬድ ፓስታቤት አካባቢ በቅ/ጊዮርጊስ ክሊኒክ መግብያ 100ሜ ገባ ብሎ ነው ፡፡ በነጋታውም የለም፡፡ ቤተሰቦቹ ተደናግጠው ለፖሊስ አመለከቱ። ፖሊስም ከአንድ ሳምንት የአሰሳና የምርመራ ቆይታ በሁዋላ በ20, 12,07 ዓ.ም ይዞት የመጣው ዜና ግን የሾፌሩን ቤተሰቦች ብቻ ሳይሆን የቤተል እና አካባቢውን ነዋሪዎች ያስደነገጠና አንገት […]

  በሑመራ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው አርበኞች ግንቦት 7 የተገደሉትን የኢህአዴግ ሰራዊት አዛዦች ለቤተስባቸው የሚሆን ገንዝብ እንዲያዋጡ እየተገደዱ መሆናቸው ተገለጸ።ባለፈው ግዜ በትግራይ ምእራባዊ ዞን አካባቢ የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው አርበኞች ግንቦት 7 ለተገደሉት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ቤተሰቦች የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጡ ሑመራ ከተማ ለሚገኙ ባለሃብቶች እያስገደዷቸው መሆናቸውንና በርካታ ገንዘብ ተዋጥቶ እየተሰበሰበ መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ። […]

በትግራይ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ አስተዳደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ እንደሚገኙ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ያገኘነው መረጃ አመለከተ።በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአዲግራት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አፅብሃ ወልደገብርኤል የተባለው ለሆዱ ያደረ የህወሓት ኢህአዴግ ካድሬ ነሃሴ 12 /2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቤቱ ውስጥ ተገድሎ እንደተገኘ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ። ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት በሚል የተወሰነ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ነዋሪው […]