የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንዳገኘ መዘገቡ ይታወቃል። አንድነት ሰልፉን መጋቢት 28 ቀን ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር በተባለው ቀን እውቅና ባለመስጠቱ፣ የተለያዩ ዝግጅቶ በመኖራቸውና የአመት በዓላትም ጊዜ በመሆኑ፣ ወደ ሚያዚይ 26 መሸጋገሩን የአመራር አባልቱ ይገልጻሉ። በዚህ ሂደት ከአስተዳደሩ ጋር በርካታ የደብዳቤ ልዉዉጦች የተደረጉ ሲሆን፣ […]

የአንድነት ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደጠራ፣ ከአዲስ አበባ አስተዳደሩ አስፈላጊዉን እውቅና እንደገኘ መዘገቡ ይታወቃል። በተመሳሳይ ሁኔተ የሰማይዊ ፓርቲ ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዚያ 19 ቀን በጃን ሜዳ ሰልፍ መጥራቱን ገልጿል። አስፈላጊዉን የማሳወቂያ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ እንዳሰገቡ ሰማያዊቾ ቢገልጹም፣ በተባለው ቀን ከአስተዳደሩ እውቅና ይሰጣቸው አይሰጣቸው እስከ አሁን የተወቀ ነገር የለም። ሰልፉን በጋራ መጥራት ለምን […]

በአፍሪቃ እስካሁን 3000 ቤቶች ሌት ብርኃን እንዲያገኙ አስችሏል። ኤሌክትሪክ ፈፅሞ ባልነበረበት ቦታ የኤሌክትሪክ ኃይል ይዘን እንመጣለን ይላል። ሞቢሶል የተሰኘው ከፀሀይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መሣሪያ የሚፈበርከው ድርጅት።

«ህግን አክብረን ለድርድር የማናቀርበውን ህገመንግስታዊ መብታችንን አሳልፈን አንሰጥም። ታላቁ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 26፣2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይደረጋል፡፡» ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ገለጹ። ፓርቲዉ ከአዲስ አበባ አስተዳደር አስፈላጊዉን እውቅና ያገኘ ሲሆን ፣ ከትንሳኤ በዓል በኋላ በሃያ ሶስቱም የአዲስ አበባ ወረዳዎችና በአዲስ አበባ […]

ማክሰኞ፤ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ጠዋት ላይ ያልታወቁ ታጣቂዎች፣ በቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልል 28 ሰዎች አሣፍሮ ይጓዝ በነበረ ከፍተኛ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ ከፍተው 9 ተሣፋሪዎችን ሲገድሉ በሰባቱ ላይ ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የማቁሰል አደጋ አድርሰዋል።

ፖሊስ የጥቃቱን ምክንያት እያጠና መሆኑን ገልጿል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ – ኦፌኮ ባለፈው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ በጠራው ህዝባዊ ስብስባ ኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለማስተሳሰር በወጣው ማስተር ፕላን ላይ ተቃውሞውን ገልጿል፡፡

ኦፌኮ ይህንን ያሳወቀው ያካሄደውን ምክክር ተከትሎ ባወጣው የአቋም መግለጫ የከተሞቹን ነዋሪዎች የሚጎዳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ መሆኑ ታውቋል፡፡

“የኦሮሞ ገበሬዎች  እየተነቀሉ ቦታቸው በሊዝ የሚሰጠው ለመሬት ቅርምት እንጂ ለልማት አይደለም” በማለት ኦፌኮ ተቃውሞውን አሰምቷል።

ዋና ፀሐፊው አቶ በቀለ ነጋ ለቪኦኤ የሰጡትን መግለጫ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

 

የደቡብ ሱዳን ፀረ-መንግሥት ኃይሎች የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማይቱን ቤንቲዩን መቆጣጠራቸውን የመንግሥቱ ኃይል የሆነው የሱዳን ሕዝብ አርነት ሠራዊት – ኤስፒኤልኤ ዛሬ አረጋግጧል፡፡

መንግሥቱ አክሎም ተቃዋሚዎቹ ምናልባት ድጋፍ ከኻርቱም አግኝተው ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም መልዕክት ቢያስተላልፉም አማፂያኑ ግን ይህንን የጁባን ውንጀላ ፈጥነው ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ቤንቲዩ ላይ ሁለቱም ወገኖች ገና እየተፋለሙ መሆናቸውን የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያደምጡ፡፡

 

ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ህፃናትን ሞት ቁጥር በሁለት ሦስተኛ መቀነስ ብትችልም በሚሌኒየሙ የልማት ግቦች የሠፈረው ግብ ላይ እንዳልደረሰች ተገለፀ።

የእናቶችን ሞት ለመቀነስ አሁንም ብዙ እንደሚቀር ተገልጧል።
የአውሮፓ ኅብረት እነዚህን ግቦች ለመምታት ያግዝ ዘንድ አርባ ሚሊዮን ዶላር ለግሷል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካችው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ ልኮልናል።

(2007-2008 ዓ.ም)
የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች

ሥር የሰደደ ድኅነትና ረሃብን ማጥፋት፤
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስ፤
የፆታዎች እኩል መሆንን ማስተማር እና የሴቶችን ውሣኔ ሰጭነት ማስፋት፤
የሕፃናት ሞትን መቀነስ፤
የእናቶች ጤናን ማሻሻል፤
ኤችአይቪ/ኤድስን፣ ወባንና ሌሎችም በሽታዎችን…

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ሳምንት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነዉ። የዘርፉ ባለሙያዎች ከተማዋ የትራፊክ አደጋ እንደሚበዛባት፤ አደጋዉም በሶስት ዓበይት ምክንያቶች እንደሚከሰት ያስረዳሉ።

ምሥራቅ ዩክሬን ውስጥ መፍቅሬ ሩስያ ሚሊሽያዎች ዛሬ ስድስት ብረት ለበስ ወታደራዊ መኪናዎችን መያዛቸውን ዩክሬን አስታወቀች ። የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር መኪናዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ መጀመሪያ በአካባቢው ነዋሪዎች ከታገዱ በኋላ አክራሪ ኃይሎች እንደወሰዱዋቸው ዛሬ ተናግሯል።

የዓለም ባንክ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት ለመርዳት የሚያስችለው አዲስ የልማት መርሀግብር አወጣ። ባንኩ በዓለም ድህነት አንፃር የጀመረውን ዘመቻ ለማሳካት ከሚመለከታቸው ሀገራት ጋ ፣ ከኢትዮጵያ ጋ ጭምር ተባብሮ ይሰራል።

ነገረ ኢትዮጵያ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡
በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ PDF ያንብቧት

– ፕሮፈሰር አለማየሁ፣ ታምራት ታረቀኝ፣ ግርማ ሞገስና ታዲዮስ ታንቱ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውባታል፡፡
– የተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ማቆም አድማ፣ የአርሶ አደሮች ሰቆቃና ሌሎችም አዲስ ወሬዎች ተካተውባታል፡፡
– በላይ ማናዬ የብሄርፌደራሊዝሙን ቅዝምዝሞሽ ይተነትንልናል፡፡
– ዮናታን ተስፋየ ለምን ፈራን ይለናል፡፡
– እያስፔድ ተስፋዬ የስርዓቱን ሰለባዎች (ከማሞ መዘምር እስከበቀለ ገርባ ዳስሷል፼፡፡ –
– ጌታቸው ሺፈራው ኢህአዴግ ምንም እንደማያሟላ ይሞግታል፡፡
– ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የእስር ቤት ትዝታውን አቅርቦባታል፡፡ ወጣቱ አቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ፍትህ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
– የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስራ አስኪሃጅ በደሎች ተዘርዝረውበታል፡፡

በግርማ አንድሪያስ  (ኔዘርላንድ፡ ኣምስተርዳም)

”….ጋዜጠኞችና ኣስታሚዎች በጥብቅ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የጀመሩት የፕሬስ ኣዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ከሶስት ወር በኋላ  ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የካቲት 1984 በአትዮጵያ ኣቆጣጠር። ታስረው በፕሬስ ህጉ የተከሰሱና ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤት ተከራክረው ነጻ የወጡት፣ በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው የአዲስ ዘመን ጋዘጣ ኣዘጋጆች ናቸው። ኣዘጋጆቹ የታሰሩትና የተከሰሱት በጋዜጣው ላይ በ ኢትዮጵያ የዲሞክራሲን ጎጂና ጠቃሚ ገጽታዎች የሚዳስስ  ጽሑፍ በማውጣታቸው ነው።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ። የሰልፉ ቀን ወይንም ቦታ እንዲቀየር የመጠየቅ እንጂ በጥቅሉ ለቀረቡት የሰልፍ ጥያቄዎች እውቅና አንሰጥም የማለት መብት አስተዳደሩ እንደሌለው በመጥቀስ፣ በአስተዳደሩ የተላከዉን […]


(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣመጋቢት/፳፻፪ .):- ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት ፤ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነውከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ:: ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው::
ሰኞ —- መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። ይህ ቀን አንጽሖተ ቤተመቅደስ የፈጸመበት ሰኞም ይባላል ።ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትንቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለችማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።
ማክሰኞ —- የጥያቄ ቀን ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታበምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ ?”ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ማር ፲፪፥፪
ረቡዕ —- ምክረ አይሁድ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል ።ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ።ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል።ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮ የመዓዛ ቀን ይባላል። ይህች ሴት ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።
ሐሙስ —- ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድህነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። 
ዓርብ —- የስቅለት ዓርብ፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
ቅዳሜ —- ቀዳም ስዑር ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ታባላለች ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል ።ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ያባላል።
Deje Selam is a venue of news, views and opinions about or related to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. [email protected]

የፌደራሉ አቃቢ ሕግ ከሁለት ወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን አይሮፕላን ወደ ጄኔቭ ከተማ በወሰደው ረዳት አብራራ ኃይለመድኅን አበራ ላይ ክሥ መሠረተ፡፡

አቃቢ ሕግ ኃይለመድኅንን የከሰሰው በማገት ወንጀል ነው፡፡

በመቶ ሺሆች ዩሮ የሚገመት ጉዳት መድረሱም በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

 

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚታዩ የተለያዩ ችግሮች በመንግሥቱ የተሣሣቱ ፖሊሲዎች ምክንያት የተፈጠሩ ናቸው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ክሥ አሰማ፡፡

ለችግሮቹም በአስቸኳይ መፍትኄ እንዲሰጥ፣ ካለበለዚያ ሥልጣኑን እንዲለቅቅ የሚጠይቅ ሰልፍ እጠራለሁም ብሏል፡፡

መንግሥት በበኩሉ “አሉ” ስለሚባሉት ችግሮች የሚቀርቡት ክሦች የተጋነኑ ናቸው ይላል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ኃይሎች ነዳጅ ዘይት አምራቿን የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማ ቤንቲዩን መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውጊያው ከተማይቱ ውስጥና በአካባቢዋ እንደቀጠለ መሆኑን የሃገሪቱ የጦር ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

አንድ ማንነቱን መግለፅ ያልፈለገ የቤንቲዩ ነዋሪ የተፈጠረውን ሁኔታ ለቪኦኤ በስልክ አረጋግጧል፡፡

የተቃዋሚዎቹ መሪዎች የነዳጅ ዘይት ምርቱን የማቋረጥ ሃሣብ እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ግጭት ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ። የርስ በርስ ግጭቱን ለማስቆም እዚያ የሚገኘውን የፈረንሳይና የአፍሪቃ ህብረት ኃይል ለማገዝ የአውሮፓ ህብረት ወታደሮችን ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ። በዚሁ ዘመቻ ጀርመን ተካፋይ ብትሆንም ተሳትፎዋ መገደቡ ግን አስተችቷታል።

የአዉሮጳ ኅብረት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ። በሉክዘምበርግ ትናንት የተሰባሰቡት የኅብረቱ የ28 ሃገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ንብረት የማንቀሳቀስና የቪዛ እገዳ ለማሳረፍ በሙሉ ድምፅ መስማማታቸዉ ተገልጿል።

የአየር ንብረትን አስመልክቶ በተመድ የተካሄደ አንድ ጥናት ታዳሽ የኃይል ምንጭን መጠቀም አማራጭ እንደሌለዉ አመለከተ። በርሊን ላይ ይፋ የሆነዉ ይህ ጥናት በርካታ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከተከማቸበት ከቅሪተ አፅም ከሚገኘዉ የኃይል ምንጭ ዓለም ባስቸኳይ ተላቆ ከባቢ አየርን ከጉዳት እንዲያድን ይማጸናል።

በዓለም ደረጃ በአጠቃላይ ለጦር መሣሪያ ግዢ የሚወጣው ገንዘብ ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር በትንሹ ዝቅ ብሏል። ይህም የሆነበት ምክንያት ትናንት ስቶኮልም ላይ ይፋ የወጣው አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ዮናይትድ ስቴትስ ለኢራቅ ጦርነት የምታወጣው ገንዘብ በመቀነሱ ነው።

አልጀሪያን እጎአ ከ1998 አንስቶ ለ16 ዓመታት በሦስት የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው አንቀጥቅጠው ገዝተዋል፤ ፕሬዚዳንት አብደልአዚዝ ቡተፍሊካ። ካለፈው ዓመት አስንስቶ በነርቭ ዕክል በሽታ የሚሰቃዩት የ77 ዓመቱ አዛውንት ስልጣን ዛሬም አልበቃኝም፥ ለአራተኛ ጊዜ መጥቻለሁ ብለዋል። የፊታችን ሐሙስ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።

(አማትና ምራት በአንድ ላይ የሚያነቡት)
አንድ ጊዜ አንዲት እናት ይህንን ታሪክ ነግረውኝ ነበር፡፡

እኔና ባለቤቴ የተጋባነው ልጆች ሆነን ነው፡፡ ያኔ እንዳሁኑ ተያይቶ፣ ተጠናንቶ፣ ሰንብቶ፣ ቆያይቶ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም የኛ ጊዜ ዘመናይ ነው ተብሎ የተወሰነ ጊዜ ትተያይና ወላጆቹ ለወላጆቿ ሽማግሌ ይልኩና፣ በስንት መመላለስ፣ አጥንትህ ጉልጥምትህ ተጠንቶ፣ ሀብት ንብረትህ ታይቶ ነበር የሚፈቀድልህ፡፡ ዛሬማ መንገድ ላይ ተንበርክኮ አንዲት የሃምሳ ብር አበባ ይዞ መለመን ነው አሉ፡፡ በኛ ዘመን በሬ ጎትተህ፣ መኪና አንጋግተህ፣ ጥሎሽ አግተልትለህም ከተሳካልህ ነው፡፡

ታድያ መጋባት አይቀርም ተጋባን፡፡ የእርሱ ወላጆች የሚያከራዩት ቤት ነበራቸው፡፡ አንዱን ቤት ሰጡንና ኑሮ ጀመርን፡፡ መቼም ፍቅርና ትዳር ለየቅል ነው፡፡ ታድያ እኛ ትዳር እንደጀመርን ባለቤቴ የልጅነት ነገር ሆነበትና ከጓደኞቹ እየተማረ ውኃ ቀጠነ ማለት ጀመረ፡፡ ባልነት ማለት መኮሳተር፣ መጎማለል፣ አንቺ እያሉ መጣራት፣ አምሽቶ መምጣት መሰለው፡፡ ይህን ጠባይ እርሱ እንዳላመጣው ዐውቅ ነበር፡፡ ጓደኞቹ ናቸው ያስተማሩት፡፡ በጊዜ ገብቶ አብረን ነበር ስንስቅና ስንጫወት የምናመሸው፡፡ እንዲያውም የኔ ባልኮ ዘመናይ ነው እያልኩ ነበር ለሰው የምናገረው፡፡ ወጥ ስሠራ እንኳን የሚያቀራርብልኝ እርሱ ነበር፡፡ በኋላ ጓደኞቹ ጠምደው ያዙት፡፡ ‹ለምን ቀሚስ አትለብስም› እያሉ መሳቂያ መሳለቂያ አደረጉት፡፡

የእነርሱን ወሬ መቋቋም ሲያቅተው እንደ እነርሱ ሆነ፡፡ ያገባሁትን ባል ወሰዱብኝና ሌላ ባል አጋቡኝ፡፡ አየህ ብዙ ሚስቶችኮ ባሎቻችንን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ስናገባ ያገኘናቸውን ባሎች ወይ ጓደኞቻቸው ወይ ወላጆቻቸው ወይም ደግሞ የሥራ ባልደረቦቻቸው ነጥቀውናል፡፡ ያላገባናቸውን ሌሎች ባሎችም አጋብተውናል፡፡ አንዳንዶቻችንኮ ከተፈራረምናቸው ባሎቻችን ውጭ ነው የምንኖረው፡፡ የኔም እንደዚያ ሆነልህ፡፡

ይህንን ሲተርኩልኝ ባልየው እያሳቁ ያዩናል፡፡ አማትዬው ደግሞ ‹‹መቼም አትረሽም አንቺ›› ይላሉ እርጅና እንኳን ብልቀነሰው ጆሯቸው እየሰሙን፡፡ እርሳቸውም ‹‹ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል›› ብለው በባላቸው ተረቱና ቀጠሉ፡፡

ነጋ ጠባ ጭቅጭቅ ሆነ፡፡ አምሽቶ መምጣት፣ ጠጥቶ መምጣት፣ የት እንደሄደ ሳይናገር ሶደሬና ላንጋኖ ጠፍቶ መክረም፤ የት ገባሽ የት ወጣሽ ማለት አመጣ፡፤ በእርሱ ቤት መቀናቱ ነው፡፡ ጓደኞቹ ሲያወሩ የሰማውን ሁሉ እውነት አደረገው፡፡ እኔም እየመረረኝም እየሰለቸኝም መጣ፡፡

የእርሱ እናት እንዴት ጥሩ ሰው መሰሉህ፡፡ ምናለ እንደርሳቸው ያለውን አማት እንደ ካሴት አባዝቶ በየቤቱ ቢያድሉት፡፡ በዚያ ዘመን እንደ አጤ ቴዎድሮስ ቀድመው የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ከቤታችን አይጠፉም፡፡ ምን ጎደለ? ምን ጠፋ? ነው ሐሳባቸው ሁሉ፡፡ በዚያ ዘመን አማት ልጅ ቤት የሚመጣው እንድም ሊያንጓጥጥ አንድም ሊያመናጭቅ ነው፡፡ አማት ሲባሉ ደርሰው መጥተው ሞያህን፣ ቤትህን ይገመግሙና ይዘረጥጡሃል፡፡ እርሳቸው እቴ፡፡ አንድ ቀን ክፉ ቃል ወጥቷቸው አያውቁም፡፡ ኧረ እንዲያውም ክፉ ቃል የሚባለውን ራሱን የሚያውቁት አይመስለኝም፡፡ የሚጨነቁት ለእኔ ነበር፡፡ ቁጭ ብለው ይመክሩኛል፣ ሞያ ያስተምሩኛል፣ ታሪክ ይተርኩልኛል፡፡ አቤት ቀልዳቸው፡፡ የባሌን ችግር የምረሳው በእርሳቸው ቀልድ ነበር፡፡ ከነገሩኝ በኋላ እንኳን ብዙ ጊዜ ብቻዬን እስቅ ነበር፡፡ ታድያ የቤቱን ችግር ነግሬያቸው አላወቅም፡፡ ለምን ይጨነቁ ብዬ፡፡

በኋላ ግን ባሰብኝ፡፡ ‹‹ቡችላው ሲጮህብሽ ዝም ካልሽው ውሻው ይነክስሻል›› ይባላል፡፡ ጭቅጭቁን ስታገሠው ጊዜ ዱላ ጀመረ፡፡ እርሱን ግን መቋቋም አቃተኝ፡፡ ሲብስብኝ ለእማማ ነገርኳቸው፡፡ አረሩ፣ ደበኑ፡፡ ምን አድርገሽው ነው እንኳን አላሉኝም፡፡ እስኪመጣ ድረስ አብረውኝ ቁጭ አሉ፡፡ አጅሬው አገር ሰላም ነው ብሎ ማታ ነበር የመጣው፡፡ እናቱን ይወዳቸዋልም ያከብራቸዋልም፡፡ ለእናት ለአባቱ አንድ ልጅ ነው፡፡ ከአባቱ ይልቅ እናቱን ነበር የሚፈራው፡፡ እርሳቸውን እንኳን ልጃቸው የሠፈር ሰው እንደ ንጉሥ ነው የሚያከብራቸው፡፡

ሲመጣ እሳት ጎርሰው እሳት ልሰው ጠበቁት፡፡ ‹‹አንተ ይህችን ትመስል ልጅ ያጋባንህኮ ተንከባክበህ፣ አክብረህ እንድትይዛት ነው፡፡ እንድትጫወትባት አይደለም፡፡ በእርሷ ላይ ነው ዱላ የምታነሳው፣ በእርሷ ላይ ነው አምሽተህ የምትመጣው፡፡ አየሁህኮ፣ በዓይኔ በብረቱ አየሁህ፡፡ ይህችን ትመስል ልጅ እንድታበላሽ አልፈቅድልህም፡፡ እኔ ጥሩ ሰው መስለህኝ ነበር የዳርኩልህ፡፡ ለካ እንደዚህ ሆነሃል፡፡ በይ ተነሽ፤ እኔ ምን የመሰለ ባል ፈልጌ እድርሻለሁ፡፡ ያዥ ልብስሽን›› አሉና ያን ጊዜ ሞባይል የለም በቤት ስልክ ለባላቸው ደወሉ፡፡ ባላቸው ፔጆ መኪናቸውን ይዘው መጡና ተነሥቼ ወደ አማቴ ቤት፡፡

እዚያ ስደርስ የእንግዳ ክፍል ተከፈተልኝ፤ ልብሴ ተጣጥፎ ተቀመጠልኝ፡፡ ‹‹አይዞሽ የኔ ልጅ፤ እርሱ የእኔ ልጅ አይደለም፡፡ ልጄ አንቺ ነሽ፡፡ እንኳን መምታት ዘወር ብሎ ሊያይሽ አይችልም›› ተባልኩ፡፡ መቼም የእርሳቸውን ነገር አውርቼ አልጠግበውምኮ፡፡ የእኔ እናት እንጂ የእርሱ እናት አይመስሉኝም፡፡ የእኔ እናትና አባትማ ናዝሬት ስለነበሩ እንዲህ በቶሎ መምጣት አይችሉም፡፡ እናቴም ‹‹ምን ከእኔ የበለጠ እናት አግኝተሻል፤ እኔ ምን አደርግልሻለሁ›› ነበር የምትለኝ፡፡

ባለቤቴ ጨነቀው፡፡ ምን ያድርግ፡፡ መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ነው የወረደበት፡፡ እናቱን ያውቃቸዋል፡፡ አይወስኑ እንጂ ከወሰኑ ማንም አይመልሳቸውም፡፡ እንደፎከሩት ለሌላ ቢድሯትስ ብሎ ፈራ፡፡ማን ተከራክሮ ይመልሳቸዋል፡፡ እንደ ዘንድሮ ባልና ሚስት ፍርድ ቤት መሄድ ያኔ አይታወቅ፡፡ ምን ያድርግ? ወስከንቢያው ነው የተደፋበት፡፡ ከአንድ ሳምንት በኋላ የእርሱ ሽማግሌዎች የነበሩት ታላላቅ ሰዎች መጡ፡፡ እማማ እሽ ሊሉ ነው፡፡ ‹‹ልጄን እንዲያበላሽ አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ ጓደኞቹ ካዋጡት ይዳሩት፡፡ እኔ የሚሳደብና የሚደባደብ ልጅ አልወለድኩም፤ አላሳደግኩም፡፡ ይቺን ትመስል ልጅ ብንድርለት በእርሱ ብሶ ሊማታ፡፡ የለም የለም፤ ልጄን እኔ ምን የመሰለ ጠባይ ከመልክ የተሰጠው ፈልጌ እድራታለሁ እንጂ እርሱማ አይጫወትባትም›› ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ የእኔ እናት እንጂ የእርሱ እናት አይመስሉም ነበር፡፡ ሽማግሌዎቹም ተጠራጠሩ፡፡ እኛ ቤት የመጡ ነበር የመሰላቸው፡፡ እማማኮ ስለ ምራታቸው የሚያወሩ አይመስሉም፡፡

በሁለተኛው ሳምንት አጅሬ ለካ እናቴ ጋር ደውሏል፡፡ ስትሰማ ደነገጠች፡፡ ለአባቴ ነግራው ሲበሩ መጡ፡፡ ከቤት መውጣቴን ሰሙ፡፡ ደግሞ ወጥቼ የገባሁት አማቶቼ ጋ፡፡ ጉድ ተባለ፡፡ አቤት እማማ የሠሩት ሥራ፡፡ የእርሱ እናት እኔን አልሰጥም ብለው የእኔ እናትና አባት ለእርሱ አማላጅ ሆነው መጡ፡፡ ተገላበጠ፡፡ እማማ እንደ ባሕሉ አስተናገዱና ምን ልታዘዝ? አሉ፡፡ ‹‹ልጃችሁ ሽምግልና ልኮን ነው›› አሉ፡፡ እማማ አልሰጥም ብለው እምቢ አሉ፡፡

‹‹ምንም ብትወልዷት አልፈቅድላችሁም›› አሏቸው፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲለምኑ ዋሉ፡፡ አባቴ ብልሃተኛ ነው፡፡ ‹‹እንጥራውና እዚሁ ዋስ ጠርቶ ቃል ይግባ›› አለ፡፡ እማማ ተስማሙ፡፡ ተጠርቶ መጣ፡፡ እየተንቀጠቀጠ ነበር የገባው፡፡ ወዳደገበት ቤት የሚገባ አይመስልም ነበር፡፡ ‹‹ሁለተኛ አንዳች ነገር አልናገራትም፣ እጄን አላነሣም፣ አላመሽም፣ አልጠጣም፣ ከቃሏ አልወጣም ብለህ ቃል ግባ›› አሉት እማማ፡፡ ቃል ገባ፡፡ ዋስ ጥራ ተባለ፡፡ ዋስ ማንን ቢጠራ ጥሩ ነው፤ የእኔን አባት፡፡ እዋሰዋለሁ አለ አባቴ፡፡ ‹‹በል ሁላችንምም ጉልበት ሳም›› አሉት እማማ፡፡ ሳመ፡፡ ‹‹አንድ ነገር ቢልሽ ደውይልኝ፤ ልጄን እወስዳታለሁ፡፡›› አሉ እማማ በማሠሪያው፡፡

እኔም ቤቴ ተመለስኩ፡፡ ኩሽ የለ፤ ዱሽ የለ፡፡ ሰላም፡፡ ጠባዩ ለወጥ ሲል ‹‹ለእማማ እደውላለሁ›› ነበር የምለው፡፡ እንዲህ ‹‹ለእማማ እደውላለሁ›› እያልኩ ይኼው ዐርባ ዓመት ኖርን፡፡ ስናስበው እንስቃለን፤ ለእኛ በሰላም መኖር ምክንያቱ እማማ ናቸው፡፡ ብዙ አማቶች ለልጃቸው አግዘው ከምራታቸው ጋር ነው የሚጣሉት፡፡ እንዲህ እንደርሳቸው ከዝምድና በላይ የሚያስብ አይገኝም፡፡ እናቴ ለእኔ በትረዳ ምን ይገርማል፡፡ አማቴ እናት ሲሆኑ ግን እንዲህ ትዳርን ያዘልቃል፡፡ እርሱማ ልጃቸው ነው፡፡ የት ይሄድባቸዋል፡፡ አሁን አሁን ነገሩ ሲነሣ ‹‹እማማ ግን እውነት ለሌላ ሊድሩኝ ነበር›› እላቸዋለሁ፡፡ ‹‹ባክሽ ላስፈራራው ብዬ ነው፡፡ ስቆርጥ ያውቀኝ የለ፡፡ ጉድ ትሠራኛለች ብሎ ነውኮ የፈራው፡፡ እናቱ ሚስቱን ወሰዱበት ቢባል እነዚህ ጓደኞቹ የሚለቁት ይመስልሻል?ጳውሎስ ኞኞ ነበር በጋዜጣ የሚያወጣው›› ይላሉ እየሳቁ፡፡

መከራየት እኒህን አማት ነበር፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡

ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”

በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ስዊድን በጉዲፈቻ ያደጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማህበር ባለፈው እሁድ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ባዘጋጀው ስብሰባ የማህበሩ አባላትና ሃገር ቤት የሚገኙ ወላጆቻቸው እርዳታና ምክር በሚያገኙበት መንገድ እንዲሁም በጉዲፈቻ ማዕከል ምሥረታ ላይ ተነጋግረዋል ።

የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን በአገሪቱ መሰል ጥቃቶችን የሚያደርሰው ቦኮሃራም በጥቃቱ ተጠርጣሪ መሆኑን ተናግረዋል ። አደጋው የደረሰበትን አካባቢ የጎበኙት ፕሬዝዳንቱ ሃገሪቱን ወደ ኋላ ለመጎተት የሚፈልጉ ባሏቸው ኃይሎች ተቀነባበረ ያሉትን ጥቃት አውግዘዋል ።

የመኢአድ አባላት ከእስር ሌላ በአንዳንድ አካባቢዎች ስብሰባ ማድረግ እንደሚከለከሉና በአጠቃላይ የመደራጀት መብታቸው እንደተነፈገ አመራሮቹ አስታውቋል ። የክልሉ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ሰሞኑን የቀረበ ቅሬታ መኖሩን እንደማያውቅ ከዚያ ቀደም ሲል ግን በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው እንደሌለ አስታውቋል ።

የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ሥልጣን ከያዙ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለሀገራቸው ሕዝብ ለማሟላት የገቡትን ቃል መጠበቅ ተስኗቸዋል። በሀገሪቱም የፀጥታው ስጋት እየጨመረ ሄዷል።

ጊኒ ቢሳው ውስጥ አጠቃላዩ ምርጫ እሁድ ሚያዝያ 5 ቀን፥ 2006 ዓም ሲካሄድ ዋለ። የሀገሪቱ ሕዝብ እአአ በ2012 ዓም መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ወዲህ አንድ ሕጋዊ መንግሥት እንዲመሠረት ሲጠብቅ ነው የቆየው። ለብዙ ጊዜ ሲተላለፍ በቆየው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ

ዩክሬይን፤ ዛሬም የዓለም ልዕለኃያላኑን እንዳፋጠጠች ነው። በክሬሚያ የነገሰው ውጥረት ልሣነ-ምድሪቱን በሕዝበ-ውሳኔ ለሩስያ ግብር ዳርጎ ወደ ምሥራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ተዛምቷል። መፍቀሬ-ሩስያውያን በምሥራቅ ዩክሬይን በርካታ የመንግሥት ተቋማትን እንደተቆጣጠሩ ነው።