በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ “አይናለም” የተባለ ጣብያ (ንኡስ ወረዳ) አለ። በዛ አከባቢ ያለው ደን “የመለስ ፓርክ” ተብሎ ተከልሏል። ኗሪዎቹ “የመለስ ፓርክ” መባሉ አልተዋጠላቸውም፤ ተቃውመውታል። ባለፈው ወር ነው። “ከመለስ ፓርክ” የተወሰነ ዛፍ ይቆረጣል። በዚህ ጉዳይ የተቆጡ ካድሬዎች የአይናለም ኗሪዎችን ሰብስበው ዛፉ የቆረጠው ማን እንደሆነ ይጠይቃሉ። አውጫጭ መሆኑ ነው። ህዝቡ ላለመናገር አደመ። ህዝቡ ስላልተናገረ ለስምንት […]

በራያ ዓዘቦ ወረዳ ነው። ህዝብ ማዳበርያ አንገዛም፣ ገንዘብ የለንም በሚል አቋሙ ፀንቷል። የህወሓት ባለስልጣናትም የወረዳና የጣብያ (ቀበሌ) አስተዳዳሪዎችን ህዝብ ማዳበርያ እንዲገዛ እንዲስያገድዱ ያስፈራራሉ። አንዳንድ ካድሬዎች አለቆቻቸውን ለማስደሰት ህዝብን ያስፈራራሉ፣ ያስገድዳሉ። አብዛኞቹ ደግሞ የህዝብን ችግር፣ ጭቆናና በደል ተረድተው ከህዝብ ጎን ይሰለፋሉ። በራያ ዓዘቦ ወረዳ ህዝብ ለማሳመን (ለማስፈራራት) ማስፈራርያ የሚደርስባቸው አስተዳዳሪዎች ህዝብን ማስፈራራቱ ሰልችቷቸው ህዝብን አናስገድድም ብለው […]

አንድነት ለዴሞክራና ለፍትህ ፓርቲ የሀገራችን ውስብስብ ችግር በዘላቂነት እንዲፈታና ህዝቡ ለዘመናት ዋጋ ሲከፍልበት የኖረው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነ ይረዳል፡፡ የተቃውሞ ጎራው አንድ ጠንካራ ሃይል ለመፍጠር ከሚያስችለው ከግል ድርጅታዊ ጥንካሬና ስራ በተጨማሪ ልዩነትን አቻችሎና አጣጥሞ መሰባሰብ እንደሚገባም እንገነዘባለን፡፡ የህዝባችን ፍላጎትም የተበታተነ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳይሆን የተጠናከረና የተሰባሰበ አንድ ፓርቲ ማየት እንደሆነ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዘንድሮው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እንሆ ከአንድ ሰዓት ተኩል ገደማ በኋላ በሳዖ ፓውሎ ስታዲየም በደመቀ ሥነ ሥርዓት ይከፈታል ተብሎ በመጠበቅ ላይ ነው። ከዚያም ሥነ ሥርዓቱ ከተጠናቀቀ ከ 2 ሰዓት ገደማ በኋላ የመክፈቻው ግጥሚያ

የአሥራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን እ ጎ አ ከ 2009 ወዲህ እንደገና 5 የአፍሪቃን አገሮች ለ 10 ቀናት ለመጎብኘት በዚህ ሳምንት ተንቀሳቅሰዋል። የሚጎበኟቸው አገሮች፤ ሩዋንዳ ፤ አይቮሪኮስት፤ ጋና ፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው።

የኢራቅ ኩርዶች የሰሜናዊቷን የነዳጅ ዘይት አምራች ከተማ የኪርኩክን አንዳንድ አካባቢዎች በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ ዘግቧል ። ትናንት ሞሱልንና ቲክሪትን የተቆጣጠሩት የኢራቅ ሱኒ አማፅያን ደግሞ ይዞታቸውን በማጠናከር ወደ ኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ለመገስገስ መዛታቸው ተሰምቷል ።

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች በየቀኑ የውኃ አቅርቦት ችግር እንደሚያጋጥማቸው በመማረር ገልጸዋል። ችግሩ መኖሩን እንደተገነዘበው ያመለከተው የከተማይቱ አስተዳደር የሕዝቡን ችግር ለማቃለል የሚያስችል ርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።

ጦርነት እና ግጭት በሚካሄድባቸው ሀገራት እና አካባቢዎች ሴቶችን በማስገደድ ወሲባዊ ጥቃት በሚፈፅሙ የጦር አባላት እና ግለሰቦች በአካባቢው ሰላም ከወረደ በኋላ ለፈፀሙት ወሲባዊ ጥቃት ሕጋዊ ከለላ እንዳይኖራቸው፣


ሁለተኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሲከናወን ከተፈጸሙት ነገሮች አንዱ የተሸላሚዎችን ታሪክ የያዝ መጽሔት መታተሙ ነው፡፡ መጽሔቱን በፒዲኤፍ ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ የመጽሔቱን ጠንካራ ቅጅ የምትፈልጉ ካላችሁ ለም ሆቴል ማትያስ ሕንጻ በሚገኘው የአግስዮ መጻሕፍት መደብር በነጻ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ በተለይም አብያተ መጻሕፍት፣ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶችና የወጣት ማኅበራት መጽሔቱን እንዲወስዱ ይበረታታሉ፡፡

የመጽሔቱ ሽፋን(cover page)
የመጽሔቱ ይዘት(bego sew bulletin pdf)

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

አራት የኤርትራ ካቶሊካውያን ጳጳሳት “ወንድምሕ የት ነው?” የሚል ጥያቄ ርእሱን ያደረገ ባለ 33 ገጽ ጽሁፍ አቅርበዋል።ጳጳሳቱ ሐዋሪያዊ መልእክት ያሉት ጽሁፍ በኤርትራ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የሚገመግምና ለችግሮች መፍትሄዎች እንዲፈልጉ ጥሪ የሚያያቀርብ ጠለቅ ያለና ጥንቃቄ የተመላበት አቀራረብን ያዘለ ነው።

ብራዚል የምታስተናግደው ፤ የዘንድሮው የዓለም የአግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ነገ የሚጀመር ሲሆን፣ የ 5ቱም- ክፍላተ-ዓለም እግር ኳስ አፍቃሪዎች፤ ይህን ልብ አንጠልጥል የአስፖርት ውድድር አንድ ወር ሙሉ ለመከታተል ተዘጋጅተዋል። በዘንድሮው የዓለም

የኢጋድ አባል ሃገራት መሪዎች ትናንት በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ ማምሻውን ባወጡት መግለጫ መንግሥትና አማፅያን ከዚህ ቀደም የተፈራረሟቸውን ሁለት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ባለማክበራቸው ቅር መሰኘታቸውን ሳይገልጹ አላለፉም ።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃዋሚ-ይባሉ ገዢ፤ ያገር ዉስጥ ይሁኑ የዉጪ ለመተባባር፤ ግንባር ለመፍጠር፤ ለመዋሐድ ሲዋዋሉ፤ መዋዋላቸዉ በተነገረ ማግሥት መለየያየት፤ መጣላት መወቃቀሳቸዉ ከመደጋገም አልፎ-ተለምዷል።ያለፈዉ ላለመደገሙ ለጊዜዉ ማረጋገጫ የለም። ካለም አቶ ስዩም «ተምረናል» ያሉት ነዉ።

በታደሰ ብሩ

መንደርደሪያ

ፌስ ቡክ ላይ ህወሓትን (ወያኔን) የሚተች ጽሁፍ ሲወጣ ስድቦችን “በብርሃን ፍጥነት” የሚያዥጎደጉዱ ሃያ ያህል ሠራተኞች ሬድዋን ሁሴን ቢሮ ውስጥ መኖራቸውን ሰምቼ ነበር። ይህ ራሱ እየደነቀኝ እያለ ሰሞኑን ሌሎች ዜናዎች ተከታትለው መጡ። በፌስ ቡክና መሰል ማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሚቀርቡበት ትችቶች ፈጣን የስድብ ምላሽ የሚሰጡለት 235 “ባለሙያ ተሳዳቢዎችን” ኢህአዴግ አሠልጥኖ ማስመረቁ ከግንቦት 27 ቀን 2006 ዓም የኢሳት ዜና ሰማሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በቀረቡ ዘገባዎችና ጽሑፎች ላይ ተመሥርቶ በሚ/ር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው በተመራው የሚኒስቴሩ ግምገማ፣ የተላለፉት መረጃዎች ሐሰት እንደሌለባቸውና እነዶ/ር ሺፈራው በፀረ አክራሪነት ትግሉ አያያዝ ላይ ድክመት እንዳለባቸው ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡ የግንባሩ አመራሮችና አባላት ጭምር የተቃወሙት የእነዶ/ር ሺፈራው ማኅበሩን በማዳከም ቤተ ክርስቲያንን የማቀጨጭ የአክራሪነት ፍረጃና መፍቀረ ፕሮቴስታንታዊ ብሎግ መር ትንታኔ የግንባሩን ድርጅታዊ መዋቅር ለማይቀለበስ አደጋ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የስዊድን ጠቅላይ ሚንስትር ፍሬድሪክ ራይንፌልት ትናንት በሀርፕሱንድ ከተማ የጠሩት ሦስት የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት መራሕያነ መንግሥት የተካፈሉበት ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ። በዚሁ የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ የተጋበዙት የጀርመን መራሒተ

በኮሎኝ ከአሥር ዓመት በፊት የቀኝ አክራሪዎች በብዛት የውጭ ሀገር ዜጎች፣ በተለይም ፣ ቱርካውያን በሚኖሩበት ሠፈር አንድ የሚስማር ቦምብ አፈንድተው ከ22 የሚበልጡ ሰዎች ሲያቆስሉ አንድም የሀገሪቱ ፖለቲከኛ ጥቃቱ ወደተጣለበት ቦታ

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ፣ «ኢጋድ» አባል ሀገራት ሚንስትሮች የሱዳንን ውዝግብ ማብቃት ስለሚቻልበት ጉዳይ ዛሬ በአዲስ አበባ ምክክር አካሄዱ። የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች መሪዎች ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር

ከ120 ተጠቋሚ ኢትዮጵያውያን መካከል በበጎ ሰው ዳኞች የተመረጡት ሰባት ኢትዮጵያውያን ‹በጎ ሰዎች› ቅዳሜ ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓም በኢሊሊ ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ተሸለሙ፡፡


የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ከየትምህርት ቤቱ የተጋበዙ ወጣቶችና ሌሎችም በተገኙበት በተከናወነው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና ኢንተርፕርነርሺፕ ዘርፍ ወ/ሮ ቤተ ልሔም ጥላሁን፣ በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ብጹዕ አቡነ ዮናስ፣ በርዳታና ሰብአዊ ሥራ ዘርፍ ዶክተር በላይ አበጋዝ፣ መንግሥታዊ  የሥራ ኃላፊነትን በመወጣት ዘርፍ አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ፣ በጥናትና ምርምር ዘርፍ አምባሳደር ዘውዴ ረታ፣ በቅርስ፣ ባሕልና ቱሪዝም ዘርፍ አብዱላሂ ሸሪፍ፣ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ደግሞ አባባ ተስፋዬ ሣሕሉ ተሸልመዋል፡፡

ሽልማቶቹን የተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የሸለሙ ሲሆን ከተሸላሚዎቹ መካከል አምባሳደር ዘውዴ፣ አምባሳደር ቆንጂትና  ወ/ሮ ቤተ ልሔም ጥላሁን ለሥራ ከሀገር ውጭ በመሆናቸው በተወካዮቻቸው በኩል ተቀብለዋል፡፡


ለሀገር በጎ ሥራ መሥራትንና ያለውንም በጎ ተጽዕኖ በተመለከተ ዶክተር እሌኒ(የ2005 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ) እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ጸጋየ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ገጣሚ አበባው መላኩና ገጣሚ ምንተስኖት ደግሞ ግጥሞችን አቅርበዋል፡፡

የመዝጊያ ንግግሩን ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መሥራችና የ2006 የበጎ ሰው ሽልማት ዕጩ አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም የአምባሳደር ልብስ ስፌት ባለቤት አቶ ሰይድ ለአባባ ተስፋየ አሥር ሺ ብርና ሙሉ ልብስ ሲሸልሙ የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ለሜሪ ጆይ አሥር ሺ ብር ለግሰዋል፡፡


ዳሽን ቢራ መርሐ ግብሩን በክብር ስፖንሰር አድርጓል


ሸገር ሬዲዮ፣ ኢቢኤስ ቴሌቭዥን፣ ኢሊሊ ሆቴል፣ ምርፋቅ ካፌና ሬስቶራንት አጋሮቻችን ሆነው ለሰጡን አገልግሎት እናመሰግናለን

በሀገራችን ከድህነት እኩል የሚፈታተነን ችግር፤ ቢያንስ ግማሽ መንገድ እንኳ ሄዶ ለመደራደር ዕውቀቱን፣ ጥበቡን አሊያም ቀና ልቡናውን ማጣታችን ነው፡፡ ግማሽ መንገድና የመቻቻል፣ ልዩነትን የማስተናገድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመልመድ ትልቅ ፀጋ ነው፡፡ አገር በኔ ብቻ ተመርታ አገር አትሆንም ብሎ፤ ኃይለኛውና አሸናፊው ከወጣበት መሠላል ዝቅ ብሎ፤ ግማሽ መንገድ ወርዶ እንነጋገር፣ እንወያይ የማለት ባህል፤ ተሸናፊውም ከቁጭቱ፣ ከቂሙ፣ ለመጣል እንጂ አብሮ […]

ሰኔ ፪ 2006 ተሰናክለን ነበር፤ አሁን ግን ጸንተናል! «ዉጊያዉን ተሸነፍን እንጂ ጦርነቱን አልተሸነፍንም» ነበር ያሉት የፈረንሳዩ የ2ኛው ዓለም ጦርነት መሪ፤ ጀነራል ቻርለስ ደጎል፣ አገራቸው በናዚዎች ሥር በወደቀች ጊዜ። ልክ እንደ ዉትድርናዉም፣ በሰላማዊ ትግል ዉስጥ መሸነፍ፣ መዉደቅ፣ መሳሳት አለ። መነሳትም እንዲሁ፡፡ ታላቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እንዳሉትም፤ «በሕይወት ውስጥ ትልቁ ነገር ፈትሞ አለመውደቅ ሳይሆን፤ በወደቁ ቁጥር […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የ5 ቱ ክፍለ-ዓለማት እግር ኳስ አፍቃሪዎች አሁን ፊታቸውን ወደ ብራዚል መመለሳቸው እሙን ነው። ከሰኔ 5 እስከ ሐምሌ 6 , 2006 ዓ ም፣ አንድ ወር ሙሉ ፣ ኳስ አፍቃሪዎች የገንዘቡ አቅም ካላቸው መካከል ጥቂቶች

ጦር አዛዦች ወደ ፊልድ ማርሻል በርናርድ ሞንትጎመሪ እና ወደ ጄኔራል ኦመር ብራንድልያ ዞር አሉና «እንቀጥላለን» አሉ።ሰኔ ስድስት 1944—የኖርማንዲ ሰማይ ሰዉ እንደ ዶፍ-ይዘንብበት ገባ።ሐምሳ ሺሕ የሚገመተዉ የጀርመን ወታደር በመቶ-ሐምሳ ሺሕ የተባባሪዎቹ ሐገራት ወታደሮች ተጥለቀለቀ።ባሕሩም ምድሩም፤ ሰማዩም አስከሬን ይለብቀዉ ያዘ።

በፓኪስታን የካራቺ ከተማ በሚገኘው የጂና ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ላይ የታሊባን ሚሊሺያዎች ትናንት በጣሉት ጥቃት እና ጥቃቱን ለማብቃት የአየር ማረፊያው ፀጥታ ኃይላት በወሰዱት አፀፋ ርምጃ ቢያንስ 28 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።

በዩናይትድ ስቴትስ ተነሳሽነት የመካከለኛው ምሥራቅ የመጨረሻ ዙር ድርድር ከከሸፈ ከሳምንትታ ወዲህ ፤ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍርንሲስ፤ በቅርቡ መካከለኛውን ምሥራቅ ሲጎበኙ ያነጋገሯቸውና