መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ዓመት በኩዌት ሱላቢካት ከተማ ውስጥ የአሰሪዋን ልጅ የ19 ዓመቷን ወጣት ሲሃም ማህሙድ በስለት በመግደል ወንጀል ተከሳ የነበረችው የ22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ወጣት ራቢያ ማህሙድ ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ ውሳኔ መፅናቱን የአገሪቱ ፍርድ ቤት አስታውቋል። ግድያውን ለመፈጸም ያበቃት ሟቿ መኝታ ክፍልዋ በተደጋጋሚ ጊዜ በመምጣት በር በመዝጋት ጥቃት …

መስከረም ፯ (ሳባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮንጎ ብራዛቪል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በመላው የአፍሪካዊያን ጫወታ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል እየቀናቸው ነው። በ5 ሺ ሜትር የወንዶች የሩጫ ውድድር ጌትነት ሞላ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ፣ ርቀቱን በ 13 ደቂቃ 21 ሰከንድ 88 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ልዑልሲ ገብረስላሴ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። በ1 ሺ500 ሜትር …

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መስከረም 16፣ 2008 ዓም በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ወናጎ ከተማ ከንግድ ቤት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ውዝግብ አድጎ ወደ ብሄረሰቦች ግጭት በማምራቱ በርካታ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ የተለያዩ የንግድ ቤቶችም ተዘርፈዋል። የከተማው ባለስልጣኖች ሆን ብለው ቀስቅሰውታል በተባለው በዚህ ግጭት፣ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ነን የሚሉ ሰዎች፣ የሌላ አካባቢ ብሄረሰቦች …

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት፣ ሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ቶም ሮድስ፣ የዞን 9 ጸሃፊዎች የዚህን አመት የአለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሽልማት የሚገባቸው በርካታ ጋዜጠኞች አሉ ሲሉ ጋዜጠኞች ለፕሬስ ነጻነት እየከፈሉ ያለውን መስዋትነት አወድሰዋል። የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችን ለመሸለም የፈለግነው በኢትዮጵያ …

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፊታችን መስከረም 24 ቀን በኢህአዴግ መቶ በመቶ የተያዘው ፓርላማ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የጠ/ሚኒስትርነት ሹመት ካጸደቀ በሃላ በጠ/ሚኒስትሩ አቅራቢነት የሚካሄደው የካቢኔ ሹም ር አዲስ ነገር ይዞ አይመጣም ተብሎአል። ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን እንደተናገሩት ግንባሩ በሙስናና በመልካም አስተዳደር ችግሮች በተጨማለቁ የካቢኔ አባላት …

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ድርጅትን እንዲያስተዳደር ለሁለት አመታት 21 ሚሊዮን 700 ሺ ዶላር ወይም ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለው ፓወር ግሪድ ይህ ነው የሚባል ስራ ሳያከናውን ተሰናብቷል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የመብራት መጥፋት ሊሻሻል ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ፣ ቀድሞውንም ይህን ያክል ገንዘብ ማውጣት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ስራ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስጎደም ለ14 ዓመታት የነበሩበትን ድርጅት ከድተው ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እጃውን መስጠታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ እየሰራ ያለው የቅስቀሳ ስራ በህዝብ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ትህዴን የአርበኞች ግንቦት7 አንድ የጦር ክፍል እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው፣ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካካል ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ሳቢር ይርጉ፣ አቡበከር ዓለሙ እና ገጣሚው ሙኒር ሁሴን ከእስር መለቀቃቸውን አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ባወጣው መግለጫ፣ ሁሉም እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተፈቱ ድረስ ትግላቸው እንደሚቀጥሉ በአጽንኦት ገልጿል። ድምፃችን ይሰማ ፣ ” ተፈቺዎቹም ይሁኑ ታሳሪዎቹ ጀግኖቻችን ሃይማኖታችን በተደፈረበት፣ …

መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በለቡ መዝናኛ ውስጥ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በመዝናናት ላይ የነበረችው ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ”አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድ ነው?” በሚል ተልካሻ ምክንያት መሳሪያ የታጠቀው የፌደራል ፓሊስ አባል ተኩሶ ገድሏታል። ታጣቂው በወቅቱ እራሱንም ለማጥፋት ጭንቅላቱ አካባቢ ላይ ያቆሰለ ሲሆን፣ ሳይሞት በሕይወት መትረፉንና በሕክምና ላይ እንዳለ ለማወቅ …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን ሐብት ምዝገባ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እንደተሳነው የኮምሽኑ ምንጮች አጋለጡ፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑትን የኮምሽኑ ኮምሽነር ዓሊ ሱሌይማን ትዕዛዝ ተቀብለው ብቻ የሚያስሩና የሚፈቱ በመሆናቸው በአዋጁ መሰረት ለህዝብ ይፋ መደረግ የነበረበት የባለለስጣናት የሐብት ምዝገባ በወቅቱ ለማከናወን ድፍረት ማጣታቸው ታውቆአል፡፡ የሐብት ምዝገባ ሥራን በኢንፎርሜሽን …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው ባለፈው ታህሳስ ወር 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዳላር ከግል ባንኮች የተበደረው መንግስት፣ ተጨማሪ በድር ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምሯል። በሚቀጥለው ሳምንት የመንግስት ባለስልጣኖች ከአበዳሪ ተቋማት መሪዎች ጋር ለንደን ውስጥ ይገናኛሉ። ላዛርድ የተባለ የመንግስት የገንዘብ አማካሪ ድርጅት ባለስልጣኖቹን ከጀርመኑ ዶች ባንክና ከአሜሪካው ጄፒ ሞርጋን ሃላፊዎች ጋር እንደሚያገናኛው የዘገበው …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞው የህወሃት አባልና በሁዋላም የአፋር ፓርቲ መስርተው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው ለ20 አመታት በስልጣን ላይ የነበሩት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ ከስልጣናቸው ከተነሱ በሁዋላ፣ የአብዴፓ ሊቀመንበር ሆነው በተመረጡት በአቶ ጠሃ ሙሃመድ ቡድንና በአቶ አሊ ሴሮ ቡድን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል። የውዝግቡ መነሻ አቶ ጠፋ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንግድ ስራ የምትደዳረዋ ካሚል ሙሃመድ ታውኒ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላት በሚል በኬንያ ልዩ ፖሊስ ተይዛ ለሶማሊና ለኢትዮጵያ መንግስታት ተላልፋ መሰጠቷን ተከትሎ ሰቆቃ እንደተፈጸመባት ተናግራለች። ቃሏን ለፍርድ ቤት ስታሰማ እንባዋ ያቋርጣት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ወ/ት ትዌኒ የህክምናዋን ወጪ ለመሸፈን የኬንያ መንግስት የገንዘብ ካሳ እንዲሰጣት ፍርድ ቤትን ጠይቃለች። ፍርድ …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ግዛት ራሶ መንደር አቅራቢያ የ20 ና የ25 ዓመት ወጣት የሆኑት ወንድማማቾች ሶማልያዊያንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአልሸባብ ታጣቂዎች በግፍ ተገለው ተገኝተዋል። ሁለቱ ወንድማማቾች ባለፈው ሳምንት ነበር በቡቃበል ከተማ ውስጥ በድንገት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በአልሸባብ ሚሊሻዎች ታግተው የተያዙት። የአካባቢው …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል። የጋዜጠኞች መብት …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታዋቂዋ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በ ቅድስ ስላሴ ካቴደራል ወዳጅ ዘመዶቿና አድናቂዎቿ በተገኙበት ተፈጽሟል። አርቲስት ሰብለ ተፈራ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አይቤክስ ሆቴል አካባቢ በግንቦት ወር 1968 ዓም. የተወለደች ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በንፋስ ስልክ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በዛው …

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋይ መኮንን ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱ ከሚያዚያ እስከ ነሃሴ በነበሩት ወራት ከታች እስከ ላይ የ7 ዓመታት ግምገማ አድርጓል። የሞላ አመራር “ትህዴንን ወደ ድል አላበቃውም ይቀየር” የሚል ጥያቄ በመላ ሰራዊት አባላት መነሳቱን የተነገሩት ምክትል አዛዡ፣ ሞላ አስጎደም አገርህን አድን ከሚለው አዲስ ጥምረት መመስረት ጋር …

መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን፣ የቀድሞው የድርጅቱ መሪ ሞላ አስገዶም የተወሰኑ ተከታዮቹን በመያዝ በሱዳን በኩል አድርጎ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በሰጠው መግለጫ ” የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛናው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈና ስላጡ ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸስተዋል” ብሎአል። ንቅናቄው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ የትግል ስትራቴጂውን በአዲስ መንገድ እንደሚቀይስ ማስታወቁን ተከትሎ፣ የመጀመሪያውን ትግል አንድ ቁጥር በመያዝ ትግሉን ጀምሯል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ በቅርቡ ፍርድ ቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ የሰጠውን ፍርድ ” የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ አምባገነናዊ ፍርድ አንቀበልም” የሚል መፈክር በማሰማት ተቃውሞ አሰምቷል። አሃዱን አሃድ፣ ትግላችን ይቀጥላል፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሳይቷል በዘንድሮ የአዲስ አመት ገበያ፣ የዶሮ ዋጋ ከበፊቱ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን በአቃቂና በሳሪስ አካባቢ ዶሮ ከ200 ብር እስከ 400 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ በግ ከ1100 እስከ 3500 ብር፣ በሬ ከ4500 እስከ 25ሺ ብር፣ ፍየል ከ750 እስከ 4ሺ ብር እየተሸጡ ነው፡፡ በሾላ ገበያ በግ ከ900 ብር እስከ 4500 ብር፣ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ባጠናው ጥናት ከአዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚወጣው ኬሚካል ሃይቁንና ወንዙን በመበከሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል። ከፋብሪካው የሚወጣው ውሃ በቀጥታ ወደ ጥቁር ውሃ ወንዝ የሚፈስ ሲሆን፣ ወንዙም ወደ ሃይቁ የሚፈስ በመሆኑ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል። የኬሚካሉ ወደ ውሃው መግባት የአሳዎችን ስደት እንደሚያስከትል የሚገልጸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው መስከረም ወር 2008 መቶ በመቶ በኢህአዴግና አጋሮቹ በተያዘው ፓርላማ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ ለማድረግ በሚል በእነሠራዊት ፍቅሬ እና ሽዋፈራው ደሳለኝ አጋፋሪነት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጅምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚገኙበት ታላቅ የፌሽታ በዓል ተዘጋጅቷል፡፡ እነሠራዊት ፍቅሬ …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር እስረኞችን ጭኖ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ማእከላዊ እስር ቤት በመጓዝ ላይ ያለ ሚኒባስ ታክሲ ፣ ማለዳ 1 ሰአት ተኩል አካባቢ ሾላ ሰሜን ሆቴል ወይም መቀጠያ ሃበሻ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሲደርስ ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመቆሙ በውስጡ ከነበሩት 13 እስረኞች መካከል 6ቱ ከመኪናው በመውረድ አምልጠዋል። የተቀሩት ከሚኒባስ ባለመውረዳቸው …

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በተጠለሉባቸው የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረሽኝ በአጎራባች የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አካባቢ ስጋት እየፈጠረ ነው። ይህንን ተላላፊ ገዳይ በሽታ ለመግታት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅትና ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በጥምረት ክትባትና የንጹህ ውሃ አገልግሎት አቅርቦት መስጠት ጀምረዋል።በአስር የስደተኞች መጠለያ …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቫይስ ኒውስ የተባለው ድረገጽ የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወቅታዊ ሁኔታ ይዞ በወጣው ዘገባ እንደገለጸው፣ የእንግሊዝ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ታስረው ከነበሩበት ስውር ቦታ ወደ ቃሊቲ መዛወራቸው በጎ ነገር ቢሆንም፣ በቃሊቲ በጥሩ ሁኔታ ተይዘዋል ብለው አያምኑም። የእንግሊዝ የውጭና የጋራ ብልጽግና አገራት ቃል አቀባይ ” ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተለያዩ አገራት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2012 ለትምህርት የመደቡትን በጀትና ወደ ውጭ አገራት በህገወጥ መንገድ የወጣውን ገንዘብ በማነጻጸር ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው ፣ በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የወጣው ገንዘብ፣ ለትምህርት ከወጣው ገንዘብ በ245 በመቶ ይልቃል። ድርጅቱ ቀድም ሲል ባወጣው ሪፖርት ከ2008 እስከ 2012 ባሉት …

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢሮው በጣና ሐይቅ ላይ በቱሪስት ማስጎበኘት ስራ በተሰማሩ ማህበራት አሰራር ጣልቃ በመግባቱ በተከሰሰበት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡ ባለስልጣን ቢሮው የቱሪስት ጀልባዎችን በተራ ለማሰራት ያደረገው የተራ ማስከበር ስራ ህግና ደንቡን ያልተከተለ ነው በማለት የተቃወመውን የጥዋት ብርሃን አነስተኛና መለስተኛ የግል ጀልባ ባለንብረቶች ማህበር ፣ …